Friday 9 December 2011


የጐንቻው !

ወዮላቹህ፤የቀን ጅቦች ሳታስቡት፤መሸባቹህ፤             

ሕዝብ መሽጓል በዋሻቹህ፤መሸሸጊያም የላቹህ፤

አጥንት ነካሽ ‘የቄራ ውሾች’፤ተራብታቹህ፤

ስትጮሁ ለከርሳቹህ፤የሕዝብ እሮሮ ነቅፋቹህ፤

ምንደኞቹ፤ሕዝብ-አገር በቅርጫ ያረዳቹህ፤                       

ምረነኛ፤ጉጅሌዎች ‘ስጋ-በስጋ’ የደለባቹህ፤

እርም እምነት የበላቹህ፤በዘር በደም ተሳክራቹህ፤

የወየናቹህ፤በእብሪት በጥጋብ ተወጥራቹህ፤

ጎኁ ቀዷል፤ሊያባራ ነው ምጣችን፤ምጣታቹህ፤

በዓለም መስትዋት የበቀል ቁና ፍዳቹህ፤

ተቆልሏል፤አበሳቹህ፤ልክ ያለፈ ስንክሳራቹህ            

እንዳይነቱ ግብራቹሁ፤የአደባባይ ፍጻሜያቹህ፤

እንደ ቱኒዙ፤ግብጽ፤ሊብያ፤ ነው እጣ ፋንታቹህ።



በቁስላችን እሾህ የምትሰዱ፤የወያኔ፤ቁንጮዎች፤

እሾሁ ሲነጣጠር ወደ አይናቹህ በሚሊዎኖች፤

በሞተ ሰዓት የሟርት ሽብር ከበሮ ደላቂዎች፤

ስንቱን ክቡር ዜጋ ጭቃ ቀቢ፤የአገር ጉድፎች፤

የምታስሩ፤የምትገርፉ፤ወንድም፤ እህት፤ወላጆች፤

ቴሬሪስት፤ድራጊስት፤አልካኢዳ፤አልሸባብ ’ ክሶች፤

የወንበዴ ታርጋ ለጣፊዎች፤ምህረት የማትሹ፤ቂሎች፤

‘ዝና-ስሙ’ ለናንተ እንጂ እድራችሁ አጥፍቶ-አጥፊዎች፤

በፓርላማ፤በ‘አረንጓዴው አደባባይ’፤ባዶ አኬልዳማዎች፤

አይሰሩምና የ‘ጋዳፊ’ መፈክሮች፤የቅጥፈት ስልቶች፤

ወዮላቹህ! ፍጻሜያቹህ፤ለምህረትም-ለተረትም አይመች።



በግንባራችን የደቀናቹህ የወያኔ ‘ጠብ-አንጋቾች’፤

ቃታ ከሳበ ጣታቹህ ዛሬም ልትገድሉ የሕዝብ ልጆች፤

ቅጽፈት ናቹህ፤የሰማይ የምድር ዘላለም ሙቶች፤ 

በህግና በፍትህ ስም የምትቀልዱ ዳኛ ጠበቆች፤

የምታንገላቷቸው፤የትውልድ የሰላም አንኳሮች፤

የአገር-ሕዝብ አውራ፤ንግሥት ናቸውና እስረኞች፤

ዛሬ አስተውሉ፤እንዳይነድፏቹህ ኋላ ‘ሆ!ብለው ንቦች።                  

የኔሰው ገብሬ፤ የዳውሮ ዋርካው፤ ምሁሩ ሻማ፤በራሱ ለቆ፤

የጋረደንን የፍርሃት ድባብ በኃይዎቱ፤ውጋገን ለኛ፤ፈንጥቆ፤

አይሆንምና ደመ-ከልብ ቃል በምድር፤ቃል በሰማይ፤ተሰንቆ፤

እንዲጧጧፍ ትግላችን በየጉልቻው፤አናዳጆችን ማግዶ፤አስጨንቆ።



ወዮላቹህ! ወያኔዎች፤‘ሙባረክን’፤‘ጋዳፌን’ ያዬ፤

እዝነ-ልቦናቹህ፤ካልፈራ፤ዓይነ-ህሊናቹህ፤ካላዬ፤

እንደ ደመራ ልትሞቁን ከዳዳቹህ፤ሕዝብ ሲቃጠል እየታዬ፤

ኢትዪጵያዊ በግፋቹሁ እየጋዬ፤ንስሃቹህ፤ከዘገዬ፤

ወዮላቹህ፤ወገን ጥዶ ያብስላቹህ መስቀል ከቦ እያጋዬ።





እነሆ፤የተዳፈነው እሳት፤ተቀጣጥሏል፤ሰደዱ፤

የተቆጡት፤የቆረጡት፤በየማዕዘኑ፤ሊነጉዱ፤

‘የፎጡን’፤ግንብ፤ሊንዱ፤ቅቦችን ሊያስርዱ፤

ወዩላቹህ!፤ሕዝብ ሃያል ነውና የቁጣ ክንዱ፤

መውረጃቹህ ይኸኔ ነው፤ብትሰሙ፤ብትዱ፤

በግብጽ ‘ሙባረክ’፤ሕዝብ የናቁት፤ ‘አንበሳ’፤

እንደ ጨርቅ አልቀው ሲጓጓዙ በሳንሳ፤

አልጋ ወራሾች፤ተሳስረው ከንጉሱ፤የቁም እሬሳ፤

የሊቢያው ‘ጋዳፊ’፤ሕዝብን በስድብ አርክሰው፤

ተያዙ፤አይጥ ጉድጉድ ተወትፈው፤በቆሻሻ ማኩሰው፤

የሞት-ሞት፤ ሞቱ፤ያልማሩትን ሕዝብ ምህረት ለምነው፤

ወዮላቹህ! ወያኔዎች፤በደመ ነፍስ፤ያላቹህ፤

ቅንጣት እምነት ካላቹህ፤በደል ጥፋታቹሁን፤አምናቹህ፤ 

ግቡ ንስሃ ፤ባለቀ ሰዓት ሽብር አሳሩን ትታቹሁ።


 





ለኢትዮጵያ ሕዝብ ነፃነት መስዋዕቱ፤ ሰማዕታቱ የኔሰው ገብሬ!  ዳውሮ-ዋርካ
በወያኔ በደልና ግፍ ተንገብግቦ ሕይዎቱን በአደባባይ ለወገኑና ለሐገሩ መስዋዕትነት በቁሙ እሳት አጋይቶ የመጨርሻውን የሕይዎት ዋጋ ለከፈለው ጀግናው ወጣት ምሁር የኔሰው ገብሬ መታሰቢያ ትሁንልኝ።

እነሆ አምላካችን ነፍሱን ይማርልን፤ ለወላጅ ቤተሰቦችም ጽናትን ለመላው ኢትዮጵያ ሕዝብ በሙሉ ቆራጥነትን፤ እሻለሁ፡ ወንድማችን ደመ-ከልብ ሆኖ እንዳይቀር መልዕክቱን፤ተቀብለን መስዋዕትነቱን ግብ እናድርስ፡ የትግሉን ሰደድ አቀጣጥለን፤ለድል እንብቃ፤የሰማዕታቶቻችንን ነፍስ ይማር።

የወጣቱ ምሁር የኔሰው ገብሬ እንደ ቱኒዚያው መሐመድ ቡዋዚዚ ለዓረብ ሕዝብ ተምሳሌ ሆኖ በርካታ ህሕዝቦንችንና አገራትን ከዘመናት ከባርነት ያልተለየ አገዛዝ ነፃነት እንዳቀዳጀና እያቀዳጀም እንዳለው ሁሉ፤ የቆራጡ ወንድማችን ገድልም ለኛ ለኢትዮጵያዊያን ብቻ ሳይሆን እንደኛ በጨካኝ፤ገዥዎቻቸው ስር ለሚማቅቁ፤ ጥቁር አፍሪቃዊያን ወገኖቻችን ሁሉ፤የነጻነት ቀንዲል ይሆናል።

የጐንቻው!      yegonchaw@yahoo.co.uk










Thursday 8 December 2011

የብሶት ምጥ!


የጐንቻው!

ሃያ ዘመን ሕዝብ ያረገዘው፤ውል እድሩ፤ የብሶት-ምጥ፤

የተጣባ ከውስጣችን፤ሕመማችን ሥር የሰደደ አለቅጥ፤

ሲያስጨንቅ ሲያስጠብበን፤የኖረ፤ሲያንቆራጥጥ፤

ስንድህ በእንብርክክሽል’ በውስጣችን  ሲገላበጥ፤

የሁለንተናችን ግልግል ውስጠ-ደማሚት እበጥ፤

አልፈነዳ፤ አልወለድ፤ ብሎ፤ወገን በሕቡ፤ሲናጥ፤

በቁርኝት አሳስሮን፤እጅ መዳፉችን፤ሲላጥ፤

ግፍ፤ቆሰቆሰው፤ሊያቀጣጥሉን፤‘የቀኑ ሰዎች’ በፈሊጥ፤

ስም እያዋሱን ‘ሞግሸነት’ መዘባበቻ፤ሽብር ስላጥ፤             

ባጐረስን እየተነከስን፤ሲገፉን፤ኖረው፤ከድጥ ወደ ማጥ፤

‘ብሶት ወለደን’ ብለው፤ያነገሱት፤የእንግዴ-ልጅ ምጥማጥ፤

የትውልድ ተስፋ የምያመክኑ፤ለእሳት ዳረገውን ለረመጥ፤

በስለን አረናል፤በየጐጇችን፤እየተቃጠለን፤ሳንገላበጥ።

Wednesday 7 December 2011

አሻቅበው ቢተፉ፣ ተመልሶ ባፉ!

ወንድሙ መኰንን

አኬልዳማ (חקל דמא)ጥሬ ቃሉ የተገኘው ከአርማያክ ቋንቋ ነው። አርማያክ ጌታ እየሱስ ክርስቶስ በዚህች ግፍ በሞላባት ምድር ላይ ሲኖር ይናገርበት የነበረ ቋንቋ ነው። ዓለም ይኸን ቃል የወሰደው ከመጽሐፍ ቅዱስ ነው። የሐዋሪያት ሥራ ም. ፩ ቁ. ፲፱ እና የማቴዎስ ወንጌል ም፡ 27 ቁ፡ 8 ላይ ቃሉ ተጽፎ እናገኘዋለን። ነገሩ እንዲህ ነበር። ያኔ ይሑዳ የተባለ ከሀዲ ጌታን በ30 ብር (30 pieces of silver) አሳልፎ ሽጦት ነበር። ልክ የኢትይጵያን መሬት፣ ዛሬ ለባዕዳን እንደሚቸበችበው፣ ከሀዲ የወያኔ መንጋ እንደማለት ነው። ጌታ በግፍ ከተሰቀለ በኋላ፣ ታዲያ ይሑዳ ተጸጽቶ 30 ብሯን መልሶ “ተቀበሉኝ” አለ። ቀጣፊ! ከፋዮቹ፣ የደሙ ዋጋ ወደ እነሱ እንዳይመጣ ሰግተው፣ በዚያ ገንዘብ የአንድ ሸክላ ሠሪ መሬት ለእንግዶች መቃብር ይሆን ዘንድ ገዙበት። መሬቱንም አኬልዳማ ተባለ። ትርጉሙም፡ “የደም ምሬት” ማለት ነው። ጸረ እግዚአብሔር የሆነ ሌባ ወያኔ ቃሉን ከማያምንበት መጽሐፍ ቅዱስ እንደልማዱ ዘርፎ፣ ተጨማለቀበት! ለነገሩስ፣ “ሰይጣን ሀጃውን ለሟሟላት ሲከጅል፣ አንዳንድ የሚበጁትን ቃላት ከመጽሐፍ ቅዱስ ይጠቃቅሳል” ማለት ይኸው አይደል!

ወንጀል ፈጻሚው፣ ሰላማዊውን ሰው መልሶ ወንጀለኛ አድርጎ ድራማ ወይም ትርዒት መሥራትን ወያኔ የተካነበት ዘዴ ነው። አሳሪው ዕብሪተኛ የወያኔ መንጋ፣ ሕዛባችንና ወገናችን ላይ የሚያደርሰው ሰቆቃ አንሶት፣ አሁን ደግሞ የግፍ ግፉን፣ ሰው አስሮ እያሰቃየ፣ በስቃይ ብዛት ተገደው መሣሪያ በግንባራቸው ላይ ተደግኖ ሰለባዎቹ ስቃዩ እንዲቀልላቸው በሚለፈልፉት ላይ እየተመሠረተ እራሱ ሊዝናናበት (ተሳስቶ ዕውነትም ቢናገር የሚያምነው መቸም የለምና) ትርዒት መሥራት ከጀመረ ውሎ አድሯል። አሁን ደግሞ ይባስ ብሎ “አኬልዳማ ” የሚል ሶስት ክፍል ድራማ ሠርቶ ቅስማችንን ሊሰብር፣ በኢትዮጵያ ተሌቪዥን ለቀቀው። “እንደልማደህ ቅደድ” በሉት እንግዲህ! ትንሹን ውሸት ወያኔ እንዲሸፍነው፣ ሌላ ያንን የሚያሳንስ ትልቅ ውሸት መዋሸት ነበረበት። ትንሹን ወንጀሉን ወያኔ የሚያቀለው ሌላ ግዙፍ ወንጀል ፍጽሞ የበፊተኛውን ወንጅሉን በማደንከይ ነው።



ክፍል ፩፡ የእምዬን ወደ አብዬ

በክፍል ፩ ድራማ ወያኔ ከዚህ በፊት እራሱ በደኖ ላይ በፈጸመው የወገናችንን ጭፍጨፋ ወንጀል ያላንዳች እፍረት በሚያመቸው መንገድ እንደገና ከልሶ (ኤዲት አድርጎ) አቀረበ። አንድ ጥሩ ማስጠንቀቂያ ግን በአንድ ቆንጆ ድምጽ ባላት ሴት ንባብ ይጀምራል። እሱም፤ “ይኸ ፕሮግራም ከ13 ዓመት በታች ያሉ ሕጻናት እንዲያዩት አይመከርም” የሚል ነው። ደግ ብላለች። ይኽች ብቻ ናት ከዚያ ሁሉ ቆሻሻ የምትለቀም ደግ ነገር። ለዚያውም ቆሻሻ ውስጥ ለቅመው በልተው ሊሚያድሩ ሕጻናት ከታሰበ ባለት ነው። ለታሪክ ተመዝግቦ መቀመጥ አለበት። http://www.diretube.com/ethiopian-documentary/akeldama-part-1-video_25cf45af1.html ጉድ በሉ ጃል! ገደል ውስጥ እጃቸው ከኋላ ታስሮ ከነነፍሳቸው ተወርውሮ የተፈጠፈጡት ሕጻናት፣ ሴቶች፣ ወንዶች ሬሳ በገመድ እየተንጠለጠለ ሲወጣ ይታያል። ከተንቀሳቃሽ ስዕሉ በታች የተጻፈው “ኦነግ የፈጸመው ወንጀል” የሚል ነው። እ?? አይ አንተ አምላክ! አይ አንተ ፈጣሪ! ኦነግ በዚያን ጊዜ ከወያኔ ጋር የጊዜያዊ መንግሥት አካል አልነበር? ታዲያ ወያኔ ያኔ ምነው ሕግ አላስከበረ? የያኔው የወያኔ ጠቅላይ ሚኒስቴር፣ የአሁኑ ጴንጤ፣ ታምራት ላይኔ አልነበር፣ “ሽርጣም እያለ ይሰድብህ የነበርዉን አሁን በለው” እያለ ሕዝብን በሕዝብ ላይ ሲያነሳሳ የነበረው? የአዛኝ ቅቤ አንጓች! የነዚያን ንጹሀን ሰዎች ደም ደመ-ከልብ ሁኖ እንዲቀር ማን ነበር አድበስብሶት ያስቀረበት!? ያኔ አንዲት ቃል ያልተነፈሰው ይኸ የገዳዮች መንጋ፣ ዛሬ ያንን እራሱ የፈጸመውን ወንጀል ሌላ አካል እንደፈጸመው አቀነባብሮ ሲያቀርብ፣ ማንን ለማታለል ነው? ለነገሩ፣ አቶ ዲማ ነገዎ የተባሉ የኦነግ የአመራር አካል በኢሳት ቀርበው እንዳስረዱን ከሆነ፣ በጊዜው ነገሩ በነጻ አካል እንዲጣራ ኦነጎች ጠይቀው፣ ወያኔ እንዳዳፈነው ነው።ታዲያ ዛሬ ወያኔ እራሱ የፈጸመውን የአረመኔነት ወንጀል፣ እንደመሣሪያ መልሶ ሲጠቀም ማንን ለማታለል ፈልጎ ነው። ምነው እኛን ቤተሰብ አልቆባቸው የሚያለቅሱትን ንግግር ሙሉ በሙል አላውጣም ይኸ ጋጠ-ወጥ ቀጣፊ! “ቤተሰቤን ያስጨረሰው መለስ ዜናዊ ነው” አልነበር ያሉት? ያንን ቆርጦ ማውጣትን ምን አመጣው? ይኽ ሁል ሸንካላ ዝባዝንኬ፣ እነ ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋን፣ ርዕዮት ዓለሙን፣ የአንድነቱን ወጣት መሪ አንዱዓለም አራጌን ... ወዘተ በግፍ ማሠሩን ለመሸፈን መሆኑ ነው? ትልቅ ውሸት ተብሎ ካልተተረጎመ፣ ምን ፋይዳ ሊፈይድለት ነው? ይኸን ጉዳይ፣ አርቲስት ታማኝ በየነ በጥሩ ሁኔታ በኢሳት ቴለቢሽን ላይ ሂዶበታልና፣ እዚህ ላይ ገታ አድርጌ እንድታዳምጡ አንባቢን እጋብዛለሁ። አምላካችን ይባርክኽ፣ ታማኝ!

http://www.youtube.com/watch?v=PUMRnjrKL0c

የመለስ ዜናዊ አገዛዝ የፋሽስት አገዛዝ መሆኑ ጸሞቀው ሀቅ እኮ ነው። መለስ ዜናዊ እኮ በዘር ማጥፋት ተወንጅሏል። በጋምቤላ፣ በዚሁ አሁን ሊያታለለን በሚሞክረው በበደኖ እልቂት፣ የአርባ ጉጉ ጭፍጭፋ፣ የወተር፣ የእንዳየሱስ፣ የኦጋደን የአንድ መንደር መንደደድ በመሳሰሉት ዓለም-አቀፍ ፍርድ ቤት፣ ፋይል እንዲከፍት የጀኖሳይድ ዎትች ፕረዝደንት ዶክተር ግሪጎሪ ስታንተን አመልክተው ውጤቱን እየተጠበቀ እኮ ነው። ያውላችኋ! http://redsea1.websitetoolbox.com/post/Tigray-The-Looming-Genocide-By-Dr.Gregory-Stanton-5558857

አሁን ወያኔ የእምዬን ወደ አብዬ ማዞሩ፣ ያ እንዲደመሰስለት ይኾን? መለስ ዜናዊን የሚጠብቀው የሊቢያው ጋዳፊ ዕጣ ፈንታ እንደሆነ ማወቅ አለበት። አንድ “ውኒጥ-ዝኒጥ” የለም! “በነጻ ገቢያ ተሽጦ ገንዘብ የሚያወጣ” የተባለለት ጭንቅላት፣ እንደጋዳፊ የተፋትን መልሶ በአፉ እስኪውጣት ድረስ አያስቀርለትም።

ክፍል ፪፡ የሌባ ዓይነ-ደረቅ መልሶ ልብ ያደርቅ

የወያኔን ቅጥፈት ባየሁ ቁጥር፣ ሁሌ ትዝ የሚለኝ፣ አንድ ፒያሳ ያጋጠመኝ፣ ከዚህ በፊት የተረኩላችሁ የሌባ ገጠመኝ ነው። ልድገምላችሁ። ከጓደኛዬ ጋር ወደ አራት ኪሎ ለመሄድ ታክሲ አቁሜ ልሳፈር ስል፣ አንዱ ጎረምሳ ገፍትሮኝ፣ “ታክሲ፣ መርካቶ!” ብሎ ጮኸ። መገፍተሬ ሳያንሰኝ፣ አንደኛው እጁ እኪሴ ውስጥ ግብቶ ሲበረብኝ አገኘሁት። በደመ-ነፍስ፣ ባለኝ በሌለኝ ኃይሌ ተጠቅሜ የሞት ሞቴን እጁን ከኪሴ አውጥቼ ሳይታወቀኝ ጠመዘዝኩት። ታዲያ የወያኔው ብጤ፣ ዓይን-አውጣ ሌቦ ትኩር ብሎ ዓይኔን እያየ በንቀት ፌዝ፣ “በቃህ ነቅተሀል! ልቀቀኝ! የማነው ገገማ!” ብሎኝ አረፈው። ትልቅ ጥፋት ያጠፋሁ መስሎኝ ተደናብሬ ለቅቅኩት። እየሰደበኝ ሄደ። ወያኔ ማለት ከዚያ ሌባ የባሰ ዓይን አውጣ ነው። አያድርስባችሁ! እስቲ ይኸኛው የውሸት ቋጠሮውን በሁልተኛው ክፍል አብረን እናፍተልትለው። http://www.diretube.com/ethiopian-documentary/akeldama-part-2-video_30d42597c.html

ኤዲያ! “ዕድሜ ዘልዛላው” አሉ እኚያ አሮጊት! “የሞኝ ለቅሶ መልሶ መልሶ” ይባላል። ይኸ ሁለተኛው ክፍል፣ ከዚህ በፊት “ሲሉ ሰምታ ...” በሚል ርዕስ የተቸሁበትን ትርዒት ነው የተደገመብን። የያኔው ትችቴ ኢትዮሜዲያ፣ በአዲስ ቮይስ፣ በኢኤመኤፍ እና በዓባይ ሜዲያ ቁጥሩን የማላውቀው ሕዝብ ሲያነበው በራሴ ብሎግ ብቻ ከ10 ሺ ሰው በላይ አንብቦታል

 (http://wondimumekonnen.blogspot.com/2011/09/blog-post.html)።

ብዙ ስድብም ከወያኔ ቡችሎች ቀምሼአለሁ። እዚያ ላይ መጨመር የምፈልገው አለኝ። ወያኔ በሻዕቢያ ተጠፍጥፎ ተሠርቶ፣ ተዘርቶ፤ ተኮትኵቶ አድጎ፣ ለሥልጣን የበቃ ድረጅት ነው። ሻዕቢያ አባቱም እናቱም ነው። ዛሬ ከሻዕቢያ ጋር ተነጋገራችሁ ብሎ ሌሎችን መኰነኑ፣ የሌብነት ሌብነት ነው። እነዚህ፣ በአንድ አልጋ ካልተኛን፣ ባንድ ማዕድ ካልበላን፣ በአንድ ጉድጓድ ካልሸናን ብለው ሥቃያችንን ያበሉን የኢትዮጵያ ጥንድ ጠላቶች አልነበሩምን? ለመሆኑ፣ ከዚህ በፊት ማን ነበር፣ ከሻዕቢያ ጋር ኢትዮጵያን የወጋት! ያደማት! ያለባሕር በር ያስቀራት! ማን አባቱ ነበር፣ ኢትዮጵያን አኬልዳማ ያደረጋት! ከሀዲ የወያኔ መንጋ አልነበረም ወይ! የማን እናት ናት ለምሆኑ አሥመራ ድረስ ሂዳ ለኤርትራ ነጻነት ድምጽ የሰጠችው? ሰሞንን ከዳዊት ከበደ መጣጥፍ አንድ ነገር ተማርኩ። ምን ይላል መሰላችሁ?

“ሆኖም በኣዲ ቛላ፣ ኤርትራ ውስጥ ተወልደው ያደጉት የመለስ ዜናዊ እናት ወ/ሮ አለማሽ ገብረልዑል፤ በምኒልክ ቤተ መንግስት ውስጥ ሲደበቁ፤ ሌሎች ኤርትራዊያን ግን “የአይናቸው ቀለም አላማረንም” ተብለው ተባረሩ። ከነዚህ ተባራሪዎችም መካከል አድዋ ውስጥ የነመለስ ዜናዊ ጎረቤት የነበሩት ሴትዮ፤ “እኔ ለኤርትራ ድምፅ የሰጠሁት ከአለማሽ ጋር አብረን ሄደን ነው። እሷ ኢትዮጵያ ውስጥ እየኖረች እኔ መባረር የለብኝም።” ብለው እያለቀሱ ቢለምኑም የአይናቸው ቀለም አላማረምና እያለቀሱ የአድዋ ከተማን ተሰናበቱ።”

ለመሆኑ ከወያኔ የበለጠ፣ የሻዕቢያ ደንገጡር በዚህ ምድር ላይ አለ? ከመለስ ዜናዊ የበለጠ፣ የሻዕቢያ ጠበቃ ከየት ሊመጣ ነው? እኛም እናውቃለን። እነሱም ያውቁታል። እኛ እንደምንውቅባቸሁ እነሱም ያውቁታል። ለመሆኑ ማንን ለማደናገር ነው? ለምንኛውም፣ የሚከተሉትን ከህደቶች ለታሪክ መዝግባችሁ አኑሩት! አቦይ ሰበሀት የተባለው ወያኔ፣ “የኤርትራ ነጻነት አደጋ ላይ የሚወድቅ ከሆነ፣ ኢትዮጵያን ብትንትኗን አውጥተን ለኤርትራ ነጻነት እንደገና በረሀ እንግባለን” ያለበት ከነድምጹ ያውላችሁ! http://www.aigaforum.com/audiovideo.html። የካሀዲ የልጅ-ልጅ ከሀዲ መለስ ዜናዊ በኤርትራ የ“ናጽነት” ቀን ተግኝቶ፣ “የጠላቶቻችሁን አከርካሪ ላንዴና ለመሸረሻ ጊዜ ሰብረነዋል” ብሎ ሲቃ እየተናነቀው የተናገረው ከነድምጹ ያውላችሁ። http://www.fettan.com/Documents/Harvesting_of_Planted_Ethnic_Discord.pdf.

ትግርኛ ከሆነ የሚቀናችሁ ትግርኛውም ይኸውላችሁ!

http://www.fettan.com/Documents/Harvesting_of_Planted_Ethnic_Discord.pdf

እና የሻዕቢያ የጓዳ ገረድ ማን ሁኖ ነው እኛኑ መልሶ ልብ የሚያደርቀው? በየትኛው ሞራሉ ነው ማንንም በሻዕቢያ አሸክርነት ሊኮንን የሚችለው? ከወያኔ የበለጠ የሻዕቢያ ተላላኪ ነበረ ወይ?! አይኖርም! አለቀ! ደቀቀ! ዕውነቷ ይኽቺ ናት! በነገራችን ላይ ወያኔ፣ እኔ ከተጣላሁት ሰው ጋር ለምን ተነጋገራችሁ ብሎ የሚኮርፍ አባ ጉልቤ ታዳጊ ሞልቃቃ (bully boy) አይመስላችሁም? ስለአሸባሪነት ከተነሳም፣ ከወያኔ የበለጠ አሸባሪ ከቶ ከየት ሊመጣ ነው?። ዛሬ የሽብርተኝነትን ሕግ የቀዳሁት ከአሜሪኖቹ ነው የሚለን አሸባሪ፣ ስለሱ አሸባሪነትስ፣ በአሜሪካኖቹ የሚሉትን ያውቅ ይሆን? ይኸውላችሁ ሀቁ!

http://www.start.umd.edu/start/data/tops/terrorist_organization_profile.asp?id=4287

ወያኔ ጭርሶ ተጨማልቋል። ጭምልቅ ብሏል! አንድ ወራዳ ሥራ ይሠራና ሰው “ግድ! ጉድ!” ሲል ከዚያ የባሰ ወራዳ ሥራ ሠርቶ ነው ነው የመጀመሪያውን ግዙፍ ውራዳውን ሥራ በቀጣዩ ሱፐር ግዙፍ የቀድሞውን ውርደት የሚያደንከው። “ኢህአዴግ መስማትና ማየት የተሳነው መንግሥት አይደለም!” እያለ መልስ ሲቀባዥር ሰምተነዋል ትርዒቱ እዚህም ይደግማል። አንደኛ መስማትና ማየት የተሳናቸው እዚህ ላይ “እሪ” ማለት አለባቸው። ሰብአዊ መብታቸው በአንድ አባ ጉልቤ ጠቅላይ ስቃይ ተደፍሮባቸዋል። ሁለተኛ፣ እነ እስክንድርናና የአንደነትን መሪዎች ለማሰር ሲነሳሳ ያደረገው የፓራላም ድንፋታው ገና ለግና ሕግን ያለቦታው እንደሚጠቀም (abuse of power) እየነገረን ነበር። የሕግ ያለህ! መቼም የጊዜ ጉዳይ ነው። “የሽሮ ድንፋታ እንጀራ እስኪቀርብ” ነበር የተባለው? ይኸቺ ጊዜ ታልፋለች! እያንዳንዱ ምድረ-ወያኔ መንጋ ኢትዮጵያና ሕዝቧ ላይ ለፈጸመው የክህደትና የወንጀል ሥራ እንደ አጎቱ፣ እንደ ኃይለሥላሴ ጉግሳ ይጠይቅባታል። ወያኔዎቹ ብቻ ሳይሆኑ፣ ጀሌዎቹም ጭምር የሚጠይቁበት ጉዳይ ነው። ግፍ በዝቷል። ጽዋው ሞልቶ ፈሷል! ይቅርታ የሚባልበት ጊዘ አልፏል። አንገሽግሾናል!

እንዲያው በሞቴ፣ እነአንዳርጋቸውና ብርሀኑ ነጋ ምንኛ የወያኔን ካምፕ እንቅልፍ ነስተውታል ጃል! እኛ እኮ እዚህ እንሱን የምናያቸው እንደማንኛውም ተራ ዜጎች ነው። ጉድ እኮ ነው! እኔ እንዳርጋቸውን በመጠኑም ቢሆን አውቀዋለሁ። የምንገናኝበትም ሁኔታ አለ። በወያኔ የሽብርተኝነት ሕግ፣ እኔም እንደ እነስክንድር ሽብርተኛ ነኝ ማለት ነዋ! ቆይ እንጂ! በአንድ ወቅት አንዳርጋቸው፣ የወያኔ ማዘጋጃ ቤት ሹም አልነበር እንዴ! ታዲያ ከአንዳርጋቸው ጋር የተነካካ ሁሉ ሽብርተኛ ከሆነ፣ ከዚህ በፊት ቀጥሮት ሲያሰራው የነበረ ወያኔስ ምን ሊባል ነው? አንዳርጋቸው ሳያውቅ ምናልባት ከሽብርትኞች ጎራ በገባበት ዘመን ሳይከሰስ፣ ዛሬ ከሕዝብ ወገን ሲሆን ነው “አሸባሪ” ሲሆን ነጉር ሁሉ የተገለቢጦሽ ነው። ለመሆኑ አንዳርጋቸው ማንን ነው የሚያሸብረው! ወያኔን ከሆነ እያሸበረ ዕንቅልፍ የሚነሳው፣ ነገሩ ሌላ ነው። እንደኔ ያለው ተራው የኢትዮጵያ ሕዝብ ግን፣ አንዳርጋቸው የወያኔ ስለባ ከመሆኑና የሕዝብን ብሶት ከማጋባቱ በስተቀር ሽብርተኛ አድርጎ አያየውም። ለመሆኑ ለ17 ዓመታት ሙሉ ሕዝቡን በጠብመንጃ፣ በቦምብ ሲያጋዩት በርሀ ከርመው፣ ላለፉት 20 ዓመታት ደግሞ ስልጣን ላይ ፊጥ ብለው ሕዝቡን የሚያሸብሩት፣ አሸባሪዎች ምን ሊባሉ ነው? አሸባሪዎቹስ የምኒልክን ቤተመንግሥት በጉልበት የያዙ የኢትዮጵያ ጠላቶች፤ የተገንጣይዋ ኤርትራ ጠበቃዎች፣ እነመለስና ግብረአበሮቹ ናቸው። ይኸንን የምንለው እኛ የወያኔ ስለባዎች ብቻ አይደለንም። የዓለም ታዛቢዎችም ብለው ጨርሰውታል። ከፈለጋቸውሁ ይኸውላችሁ! http://www.youtube.com/watch?v=4WsV6fJJ51Q።

ክፍል ፫፡ ወያኔያዊ እኵይ ከፋፋይ ድርጊት በትርዒት

ወያኔ እስካሁን ከሠራው የወራዶች ትርዒት ሁሉ ሶስተኛው ከፍል የሚግለማ ነው።

http://www.ethiotube.net/video/16614/Must-Watch-ETV-Documentary--Akeldama--Part-3--The-case-for-Ginbot-7

ኤጭ! የፊተኞቹን ሁለቱን ርሷችው! ይኸን ትርዒት ነው ልብን ብግን የሚያደርገው። ሰው ሁሉ ልብ ብሎ አድምጦት ወስኖ ከነዚህ መዥገሮች ለመላቀቅ ቆርጦ መነሳት ያለበት።

ያን ዓይኑ እንደጉርጥ የተጎረጠረጠ ሞጋጋ ዝግጀት አቅራቢን፣ ከየት አገኙት? አስጠሊታ! ጻረ-ሞት (gohst) የመስላል። የካድሬነት እንጂ የጋዜጠኝነት ሙያ የማይታይበት የወያኔ ዕቃ! እዚህም ክፍል ውስጥ አንዳርጋቸው ጽጌና፣ እነዶክተር ብርሀኑ ነጋን በመኮነን በማላዘኑ ይቀጥላል። በዚህ አቀራርብ፣ የግንቦት ሰባትን አባላት የሆኑትንም ያልሆኑትንም እየጨፈለቀ ይዘባርቃል። ጽሑፉ፣ ወይም ስክሪፕቱ፣ በመለስ ዜናዊ የተደረሰ የዘረኞች ድርሰት መሆን አለበት። ለዛው ሙጥጥ! ትልቁ ኢሰብዓዊ የሆነው ድርጊቱ፣ በእስር ቤት ይዞ የሚያሰቃያቸውን ሰለባዎቹን (victims) በዱላና በመሣሪያ እያስፈራራ እያቀርበ ማናዘዝ ነው። በነገራችን ላይ በደርግ ዘመን እንደዚህ ስቃይ የበዛበት ወጣት፣ ዱላው እንዲቆምለት “ታንክ ከወላጆቼ ቤት ጓሮ ቀብሬአለሁ” ብሎ መርቶአቸው ጉድጓድ እንዳስቅፈረ ይተረካል። ቀለደብን ብለው እዚያው ገድለዉት በቆፈሩት ጉድጓድ ቀብረውት ሄዱ። “Under duress” ወይም “በሥቃይ ተይዞ” የሚባል ሕጋዊ አንቀጽ በዓለም ሕግ እንዳለ የወያኔ ቦዘኔ መንጋ ያውቅ ይሆን? መንግሥቴን ሊገለብጡብኝ ነው ብሎ አስሮ ደብድቦ እነ አቶ አሳምነው ጽጌና ብርጋዴር ጀኔራል ተፈራ ማሞ፣ ሌተና ኮሎሌል የሺዋስ አጥናፈ፣ ሌተና ኮሎኔል አስቻለው አምባቸው ላይ የፈበረከባቸውን ሸር እዚህም ደገመው። እነ ደበበ እሸቱ ላይ ተጠቀመ። እነዚያ ላይ የተጠቀመው ዘዴ፣ ከሥቃይ ብዛት አንደኛው በሌላው ላይ መስካሪ አንድርጎ ማስለፍልፍ ነበር። አሁንም ያንኑ አደረገው። ኤሊያስ ክፍሌ የግንቦት ሰባት አባሉ ሁኖ ቀርቧል። የውሸት ውሸት! ሀፍረተ ቢሶች! ኤሊያስ የወያኔን እርኩስ ሥራ ከማጋለጥ በስተቀር የማንም ፓርት አባል ሁኖ አያውቅም። ሲያስፈልገውም፣ ግንቦት ሰባትን ሲያብጠለጠለው እናነበዋለን። እሺ የኤሊያስስ ይሑን፣ አበበ ገላውን መክሰሳቸው፣ በደኅና ሕሊናቸው ነው? “የአራት ኪሎው ማም ቂሎ” ብሎት አልፈው ጓደኛዬ!

ከሁሉ ከሁሉ የሚገርመኝ፣ ወያኔ በደል በፈጸመ ቁጥር ዓይኑን ብልጥጥ አድርጎ “ይቅርታ ጠይቁኝ” ማለቱ ነው። ዓይኑ ይጥፋና! አንድ “ታዲዮስ አንተነህ” በሚል ስም የሚጽፍ የወያኔ ቡችላ ሰሞኑን ምን ያለኝ መሰላችሁ። የስድብ ጋጋታዉን ካዥጎደጎደው በኋላ፡ “ይልቅ ይቅርታ ጠይቀህ፣ ከሕዝብ ወግን ተቀላቀል” ነበር ያለኝ። በጣም ስለገረመኝ፣ ለብዙ ደቂቃዎች እዚያ ዐረፍተ-ነገር ላይ ፍዝዝ ብዬ ቀረሁ! ይገርማል! ይኸ የባንዳ ልጅ ባንዳ አገር ሻጮችን “ይቅርታ ጠይቅ” ይበለኝ!!! እኔን ነጻውን ስደተኛ ዜጋ ከማይደርሱበት የስደት ቤቴ “ይቅርታ ጠይቅ” ሊሉኝ የደፈሩ ወራዶች፣ እነዚያ በቁጥጥሩ ሥር ያሉትንማ እንዴት ያሰቃዩአቸው? መለስ ዜናዊ አንዴ ሲጨማለቅ የሰማሁት ትዝ አለኝ። “ከኦነግ የበለጠ የጎዳን የለም። ዳሩ ግን መሪዎቹ ይቅርታ ስለጠይቁን በሰላም በቦሌ በኵል አገር ለቀው እንዲሄዱ ፈቅደንላቸዋል ሸኘናቸው። ፕሮፌሰር አሥራት፣ ከሆነግ የበለጠ በደል እኮ መንግሥታችን ላይ አላደረሱም። ይቅርታ ቢጠይቁን ልንለቃችሁ እንችላለን ነበር ያለው ለጥያቄ አቅራቢው የውጭ ጋዜጠኛ! ወይኔ የሰውዬው ልጅ! በኋላስ! የቅንቅጅት መሪዎችን አፍሶ በአሰረ ማግስት፣ ተላላኪዎችን “ሽማግሌ” ተባዮቹን ጉዶች ልኮ ምን ነበር ለማግኘት የተሟሟተው? “ይቅርታ ይጠይቁኝ” ነበር ያለው። ከብዙ ውትወታ በኋላ “ይቅርታዋን” እንደፈለጋት አገኛት። ለመሆኑ “ይቅርታዪቱ” ከልባቸው መስሎት ይኾን? ዳሩ ግን፣ ከፋፍሎአቸው የሚፍልገውን አግኝቷል። ከተለቁቁም በኋላ፣ ብትንትናቸውን አውጥቶ እንዳይነሱ አደረጓቸዋል። “አከርካሪአቸውን መታን!” ብሎም ፎከሯል!

በእስር እንግልትም ቅስም መስበር ልማዱ ነው። ቅስም ለመስበር ደግሞ የማይጠቀመው ወራዳ ሥራ የለም። ለምሳሌ አንዷ የኦሮሞ ብሔራዊ ጎንግሬስ አባል ላይ ያደረሰውን በደል የቀድሞ ባለሥልጣናቸው የነበረ ሰው ሲነግረኝ፣ ሰውነቴን ሰቀጠጠኝ። አንድ የነሱ፣ ሰላይ አድናቂዋ መስሎ ቀረባት። እሥሯም ጉዳይ አስፈጻሚ መስሎ ጉድ-ጉድ እያለ አመኔታዋን አገኘ። በኋላ፣ እንዴት አድርጎ እንደመረዛት፣ እራሷን እንድሰት እንዳደረጋት፣ ከዚያ በኋላ እሷ ሳታውቅ ወራዳ ፎቶዎች እንዳነሳት፣ ወደ ልቧ ስትመለስ የወያኔ መንጋ ያንን ፎቶግራፍ አሳይቷት በወገኖቿ ላይ እንደትዘምት እንዳስገደዳት (blackmail)፣ ቅስሟን እንደሰበረና ከትግል ውጪ እንዳደረጋት አጫወተኝ። ከዚያ በኋላ ያች ጀግና ልጅ ሰው አልሆነችም። “አንቀጽ 39 ለነሱ ለአናሳዎቹ ይረዳቸው እንደሆነ እንጂ ለኛ ለብዙኃኑ ኢትዮጵያውያን ኦሮሞዎች ምናችንም አይደለም” ያለችው ጀግና ስነ-ልቦናዋ ተሰልቦ ከጨዋታ ውጭ ሆነች። አገር ጥላም በረረች። ያለችበትም አይታወቅም። ጭጭ ምጭጭ አደርጋት!

እህታችንን ብርቱካን ሚዴቅሳን እሥር ቤት ምን እንዳደረሰባት እስካሁን በግልጽ የተነገረ ነገር የለም። ብቻ ያደረገውን አድርጎ ያችን የአንበሳ ግልገል፣ “አጥፍቸአለሁ! ይቅርታ!” አሰኝቷት ለቀቃት! ይቅርታውን አግኝቷል። ብርትኳን ከስነ-ልቦናዋ ቁስል እያገገምች ነው። ብርቱካን! እንወድሻለን! አይዞሽ! በርቺ! ባለሽበት፣ አምላካችን ካንቺ ጋር ይኹን። እልባችን ቀርጸነሽ ይዘንሻል! የኛዋ ኦንግ ሳን ሱኪ!

ወያኔ ምን ጊዜም ቢሆን አስገደዶ ይቅርታ ቢያስብል፣ ልባዊ ይቅርታ ከማንም ኢትዮጵያዊ አያገኛትም! ሰው በድሎ ይቅርታ ጠይቁኝ የሚል አምባገነን ምናልባት ወያኔ ብቻ መሆን አለበት። ይኸ እንከፍ ቡድን ሰው አሰቃይቶ ይቅርታ ቢያሰኝ ዕውነት ያስገበረ ይመስለው ይኾን? እንዚህ መንጋዎች ከጫካ ከወጡ ሀያ ዓመት ቢደፍኑም፣ አሁንም እንደ ዱር አውሬ ነው የሚቅበዘበዙት። ከሁሉ ከሁሉ የሚያሳዝነው፣ በጁ ይዞ ካስለፈለፋቸው ሰዎች ሁሉ፣ የደበበ እሸቱ ቅስም መሰበር ነው። ጀግናው ደበበ፣ ተሰበረላቸው! ጀግናው ደበበ ግንቦት ሰባትን አወገዘላቸው። ብርሀኑ ነጋን ሰደበላቸው! ሲናገር የሰከረ እንጂ በብሩህ ልቦናው እንዳለ አይመስልም። ጸጉሩ ተንጨባሯል። ያበደ ነው የሚመስለው። “መንግሥት እኮ በግልጽ አስቅምጧል” ይላል ደበበ ዕንባ እየተናነቀው። “ግንቦት ሰባት አሸባሪ ድርጅት ነው ብሎ አስቀምጧል። እዚህ አገር ሁኜ፣ በየዕለቱ የሚሰጠውን መረጃ እያየሁ፣ አሸባሪ ነው ተብሎ ከተፈረጀ ድርጅት ጋር ለምንድነው፣ በምንም መልኩ ይኹን ግንኙነት ያደረግኩት! ይኸ ነው የሚያስጸጽተኝ” እያለ በራሱ ላይ የፈርዳል! በቤታቸው አዋርደውታል! ቅስሙን ሰበረውታል! ወንድሜን!!! የሚፈልጉትን ብሎላቸው ከእስር ቤት ወጣ። በነሱ ቤት አብቅቶለታል! ከዚህ በኋላ ሰው የሚሆን አይመስላቸውም። እኛ ግን እነሱ እንደፈለጉት አናወግዘውም። ማንም ሰው በጠላት እጅ ሲወድቅ፣ ጠላት የሚፈልገውን ተናግሮ ስቃዩ እንዲቀርለት የሚያደርገውን መለፍለፍ የሥነ-ልቦና ሊቃዉንት በግልጽ አብራርተውታል። ፒ ኤ ዲ (ዶክተሬት ድግሪ) ተሠርቶበታል። ነጻ ሲወጣ ዕውነቱን ይናገራል።

ስለእስክንድር ማለት የምፈልገው ነገር አለ። ወያኔ ያን ሁሉ ማስፈራራት ካደረሰበት በኋላ፣ መጽሐፉን እንዳይታትም ከለከለው። ያንን መጽሐፍ ጓደኞቼና እኔ ልናሳትምለት ታጥቀን ተነስተን። አንድ እስክንድር ያስጠነቀቀኝ ጉዳይ ቢኖር፣ ያንን መጽሐፍ ለማሳተም ከተሰብሰብን ቡድን መሀል አንድም የፖሊቲካ ድርጅት አባል እንዳይኖር ነበር ያለኝ። የትኛው ፍርድ ቤት ቀርቤ ዕውነቱን ልመስክር! ወይኔ የአቶ ሰውዬው ልጅ! በዚህ የተነሳ፣ ሌሎች ፈቃደኛ የሆኑቱን ሶዎች ሁሉ ነበር አይሆንም ብዬ ያስቀርሁት። መጨረሻ ላይ አንዳንድ ነገሮች ስላሳሰቡኝ፣ “እኔ የወያኔ ነቃፊ ስለሆንኩኝ፣ ምናልባት በኔ ምክንያት እንዳያጠቁህ፣ ሌላ ሰው ልወክልና ጀርባ ልሰለፍ” አልኩት! “የለም! አንተማ ወደ ጀርባ መሰለፍ አያስፈልገህም! ጓደኞቼን ሁሉ ወያኔ ሊመርጥልኝ አይችለም። የፖሊቲካ ድርጅቶችን ብቻ አስወግድ። ወያኔ ሊያጠፋኝ ሲነሳ ምንም ዓይነት ተጨባጭ ምክኒያት ሊኖረው አያገባም። ሳያመካኝ ይብላኝ!” ነበር ያለኝ። ይኸ ሰው ነው እንግዲህ፣ ከሻዕቢያና ከግንቦት ሰባት ጋር ግኑኝነት አለህ ተብሎ ለእስር የተዳረገው። ቢኖረውሳ! የአሜሪካን፣ የእንግሊዝ፣ የፈረንሳይ ጋዜጠኞች አፍጋኒስታን ተራራ ድረስ ሂደው ታሊባንን ያነጋግሩ የለም እንዴ! የሕሊና ደንቆሮ!

ወያኔ የመሀይም ጥርቅም ነው። ከጫካ እንደውጧት አንድም ያልተለውጡ የወንበዴ መንጋ የተጠራቀሙበት ዋሻ ነው። የሰላጠነ አገርማ፣ የሕግንና የሚዲያን ልዩነት ጠንቅቆ ያውቃል። ለፍዳዳው የወያኔ አፈ-ቀላጤ “ይኸ አገር እኮ በሕግና ሥነ-ስርዓት የሚመራ ነው ብሎ ሲመጻደቅ” ስሰማ ሊያመኝ ተናነቀኝ። በሕግና በሥነ-ሥርዓት የሚመራ አገርማ ውስጥ፣ በመጀመሪያ ደረጃ፣ በፍርድ ቤት የተያዘውን ጉዳይ በሜድያ ላይ፣ ያዉም በከሳሹ በመንግሥት ቴሌቪዥን ወጥቶ አይዝረከረክም። ነጻ ፍርድ ቤት ቢኖርማ እንዲህ ዓይነት ብልግና መንግሥት ሲፈጽም ሲያይ ጉዳዩን ወርውሮት ተከሳሾችን በነጻ ይልቅ ነበር።

በዚህ ፊልም፣ በጣም አስቂኝና አሰልቺ የግንባታ መንግስሥት ተረት-ተረት ሲተላለፍ እንሰማለን። ይገርማል! የጥፋቱ ገዥ የልማት መንግስት ነኝ ለማለት ይጣጣራል! ሰው ጦሙን ማደሩን ማን በነገረው! በልማት አመካኝቶ ገንዘብ ለመሰብሰብ እንዳበደ ውሻ ይሯሯጣል። ያ ቀላባጅ ፕሮግራም አቅራቢ እንዲ ሲል ፕሮግራሙን ይደመድማል።

“ለአሸባሪዎቹና ለዕኵይ ተግባራቸው ቀዳዳ ከፍተን ዕድል ከፈጠርንላቸው አንድ ቀን ከዚህ ቀደም እንዳደረጉት ሁሉ፣ አባት፣ እናት፣ እህት፣ ወንድም ወይንም እጅግ የምንወዳትን ሕይወታችንን ሊነጥቁን እንድሚችሉ መርሳት የለብንም። አሁንም፣ ሽብርተኝነት የመኖራችን ሕልውና ሥጋት እየሆነ መጥቶብናል። በመሆኑም እያንዳንዱ ዜጋ አካባቢውን በንቃት መጠበቅ ይኖርበታል። ለሀገሩ ሰልምና ልማትም ዘብ መቆም ይጠበቅበታል። እኛ ኢትዮጵያውያን ከሰላማንና ከልማታችን በላይ የሚበልጥብን ምንም ነገር የለም። አሸባሪዎቹ፣ በጥፋት መንገዳችው ሲዳክሩ፣ እኛ በሕዳሴ መንገዳችን እንቀጥላለን።”

ውይ! ተባለ እንዴ! ይኸን ሁሉ ሲለፈልፍ ታዲያ፣ አሜሪካ ውስጥ፣ በመንታ ሕንጻዎች ላይ የደረሰውን አደጋ ፊልም እያሳየ ነው። እሱ ስለሌለው ልማቱ ሲደሰኩር፣ የኢትዮጵያ ሕዝብ እንደነቃበት ከዚህ በታች ባለው የጸሎት መርዶ እናርዳውና እኛም በበኩላችን ቅስሙን እንስበረው። አሁንም ከሩቁ ወዳጄ ከጋዜጠኛ ከዳዊት ከበደ ያገኘሁት፣ ወያኔን “ሕዳሴ” እያለ “የአባይ መገደቤ ነው፣ ገንዘብ አምጡ” እያለ ሲይስጨንቅቸው፣ የአዲስ አበባ አራዳ ወጣቶች የደረሱት ጸሎት ነው።

የአባይ ህዳሴ ፀሎት

አባያችን ሆይ፣
በበርሃ የምትኖር፤
ስምህ ይመዝገብ፣ ግብርህም ይምጣ።
ማረፊያህ በግብፅ እንደሆነ፤ እንዲሁም በህዳሴው ላይ ይሁን።
የእለት ውሃችንን ስጠን ዛሬ፤
ደሞዛችንን ይቅር በለን፤
እኛም የጠየቁንን እንደምንሰጥ።
አቤቱ ወደ ቦንብ ግዢ አታግባን፤
ከብድር አድነን እንጂ።
ቦንድ ያንተ ነውና፤
አይ መብራት ኃይል፤
ለዘለአለሙ፤
አሜን።

ወያኔን ለማስወገድ ሁላችንም ከመተባብር ሌላ ምርጫ የለንም። ታስረው የሚንገላቱትን ወንድሞቻችንና እህቶቻችንን ከጎናቸው ከመቆም ሌላ አማራጭ የለንም። ወያኔ ሺህ ጊዜ ትርዒት ቢያቀነባብር፣ ለራሱ ይዝናናበት እንደሆን እንጂ ሀቋን አይቀይራትም። እስከዘልዓለም ልባችንን አያገኛትም! ውጭ ያለነው፤ ወያኔ ላይ ማመጽ አለብን! እያንዳንድህ! እያንዳድሽ ወግኔ ታጥቀህ ተነስ! ታጥቀሽ ተነሺ! ወያኔ ላይ፣ ጥርስህን ንከስ! ጥርስሽን ንከሺ! ልብህን ዝጋበት! ልብሽን ዝጊበት! አበቃ!|