Thursday, 13 November 2014

RESPONSE TO ABA ZEKARIAS FROM BOSTON ST MICHAEL CHURCH

አባ ዘካርያስ የተባሉ፣ ወያኔ የሚቆጣጠረው የአዲስ አበባው ሲኖዶስ፣ በአሜሪካ ጉዳይ አስፈሳሚ፣ "ማንኛውም 'የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስትያን፣ የተባለ ሁሉ ከነ-ንብረቱ፣ ማንም አቋቋመው ማንም፣ አዲስ አበባ የሚገኘው የኢትዮጵያ ተዋሕዶ ኦርቶዶክስ ሲኖዶስ ንብረት ነው" ብለው አውጀው በዩ-ትዩብ እንደለቀቁ የሰማና ያነበበ ሁሉ ይገነዘበዋል። የቦስቶክ ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያንን ገለልተኛ በመሆኗ አውግዘው አስተዳዳሪዋንም መልአከ ስላም አባ ሐጎስ ብርሀኔን ከህነታቸውን እንደያዙባቸው በሚከተለው አያያዥ በመጠቆም ማየትና መስማት ይቻላል።


መላከ ሰላም አባ ሐጎስ ብርሀኔና የቦስተን ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን የሰበካ አስተዳደር ጉባዔ የሚከተለውን ደብዳቤ ጽፈውላቸዋል።

https://drive.google.com/file/d/0B7KetREHX_CgRTIyYmFEcVVtUWM/view?pli=1

ይኸ ነገር፣ ቤተክርስቲያኗን ቀምተው አባላቱን ሜዳ ላይ ለመጣል አልተቻላቸውም እንጂ፣ ነገሩ ልክ እንደ ለንደኗ ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን የወያኔ ዕቅድና አፈጻጸም ይመስላል።

እግዚአብሔር ከነዚህ መሠርይ ተንኮለኞች የሰውራችሁ

No comments:

Post a Comment