Sunday, 14 October 2012

ALERT! URGENT CALL FOR ACTION


ALERT! AGENTS OF THE HUMAN RIGHTS ABUSERS SEEK ACCREDITATION
By Wondimu Mekonnen,

On 10th October 1991, few months after the TPLF/EPRDF led rebel (terror[i]) group took o ver the power in Addis Ababa, Prof. Mesfin Woldemariam, a retired Professor of Addis Ababa University saw how the new regime dealt with citizens in ferocity with iron fists. He foresaw the brutality they may unleash upon Ethiopians and spearheaded the establishment of Ethiopian Human Rights Council (EHRCO). EHRCO was created legally and obtained its certificate to openly advocate for human rights regardless of the harassment and persecution of its activists and members, including the life of its Executive Member, Assefa Maru. It started educating the people about the rights, published hundreds of accounts of atrocities committed by those in power and gained credibility both at home and internationally. For his action, Prof. Mesfin Woldemariam paid dearly to the extent of being jailed for speaking up for human rights and bear long term hunger strike for his rights. This took place following  his addressing of University students along with Dr Berhanu Nega on human rights. 
One of the tried and proved methods of destroying national institutions of the country by the current regime in Ethiopia is cloning organisations in its own image, to replace the genuine ones. In order to silence EHRCO, it had to create a surrogate fake human rights organisation to destroy the genuine one. At the time, Professor Mesfin Woldemariam saw it as a good step by the “government” because he thought that would give them a chance to learn how to respect human rights. Many of us who knew the true colour of TPLF from inception to maturity rejected the idea since we know that was just a new trick to undermine EHRCO. Our fear became a reality.

To know the nature of TPLF one does not need to be a rocket scientist. Cloning fake organisations is its best art of deception of the international community. It just did that with Confederation of Ethiopian Labour Union (CELU), Ethiopian Teachers Association (ETA) and many others. Therefore, when the regime in power realised that it could not carry on committing crime against humanity while EHRCO was around, it decided to clone its own “Human Rights Organisation” that would exactly sound like EHRCO in violation of patent and copy rights law. On 4th July 2000 (it looked like to deliberately match the Independence Day of The USA), the dictatorial tribalist regime created its own “human rights organisation” with fanfare - The Ethiopian Human Rights Commission by proclamation No 210/2000[ii]. At the time of preparation for the fanfare, the Ethiopian Diaspora received lists of invited guests from all over the world including Rt Hon Betty Boothroyd, the Speaker of the House of Commons in the UK. The exiled Ethiopian community activists prepared a dossier containing catalogues of atrocities committed by the regime in Addis Ababa and sent it together with a letter to each and every person on the list pleading to boycott the fanfare. We succeeded! We received letters from hundreds of invitees, including Ms Boothoryd confirming that they would not be setting their feet on the soil where such fake event was going to take place.
If there had been justice in the land, EHRCO would have legally challenged the creation of another “EHRCO” and forced it to change at least the name to something “appropriate”. Unfortunately, that did not happen. The true EHRCO’s money was confiscated and their legal existence restricted.

Among the five fascistic rules edited by the regime one can find “The Charities and Societies Proclamation law (CSO law)” a “repressive new law which could criminalise the human rights activities of both foreign and domestic non-governmental organizations (NGOs).”[iii] This law gave the right to hit EHRCO, forcing it to drop the word “Ethiopian” from its name to become hrco as it “would confuse the public” with the “legitimatised” extended arm of Human Rights abusers – The Ethiopian Human Rights Commission. Ever since its creation, the cloned “EHRC” (thanks for dropping the “o”) has not exposed a single crime committed by the regime apart from attempting to protect the dictatorial regime’s action which have been systematically exposed by Amnesty International, Human Rights Watch and other credible human rights organisations.

Now, EHRCO reduced to “hrco” penniless and powerless, the regime went on editing laws after laws that curtailed human rights. The Press law and Broadcast Proclamation No. 533[iv], the CSO law and new “anti-terrorism law”[v] have successfully gagged the press and silenced the opposition. As per Amnesty International’s report reveals, “Thousands of protesters, political party leaders, journalists and human rights defenders were arrested and detained following the disputed November 2005 elections in which the ruling Ethiopian People's Revolutionary Democratic Front (EPRDF) retained political power.” While we hear the domestic and international cries against the gross violation of human rights in Ethiopia by the EHRC’s creators, we have yet to see or hear a word against these crimes from EHRC but to the contrary defending the perpetrators.

Just reading pages of Committee to Protect journalists reveals horrific miscarriage of justice against journalists[vi]and opposition activists. Eleven journalists including Eskinder Nega, Reeyot Alemu and Woubshet Taye have been convicted under Anti-Terrorism Law and serving up to 18 years jail sentence. Andualem Arage, Nathnael Mekonnen, Mitiku Damte, Yeshiwas Yehunalem, Kinfemichael Debebe, Zerihun Gebre-Egziabher and many others opposition members are also sentenced up to death under the same laws but EHRC justifies that by silence.
EHRC is led by none but an official of the dictatorial regime appointee Ambassador Tiruneh Zena. He may be wrapped up in a designer clothes but one can read from his eyes there is nothing kindness in them that is crucial for one to stand with the victims. While EHRC is silently watching, hundreds of thousands have been evicted from their birth place and their farm land sold to global agro-conglomerate[vii]. The Human Rights Ombudsman Commissioner’s eyes cannot see injustices perpetrated against innocent people, he doesn’t want to know or hear cries of victims of those who hired him to sit at the helm of the cloned organisation as human rights commissioner. He wouldn’t want to know why thousands are rotting in jail, why millions are flooding into exile. He occupies the office and gets his salary for silence. Now he is seeking legitimacy from the United Nations for his excellent job of turning blind eyes on the atrocities committed right under his nose[viii]. 

The need to be accredited by the United Nations gives the Commissioner and his bosses two advantages. From one angle, he may seek funding to keep his inactive office alive and may even share the money with his bosses. On the other hand he would try to claim recognition for silence on human rights abuse in Ethiopia as legitimate. This would undermine Amnesty International’s and Human Rights Watches Reports. If he succeeds, Zena would be awarded with a medal of the highest honour in the country for his service in the violation of human rights.
This writer would like request all peace loving members of the international community, every Ethiopian in exile and all human rights organisations throughout the world, to take up the matter with the UN and demand justice for the victims by preventing the imposter from taking up a seat in the UN and succeeding in fooling that prestigious organisation. The AU had turned into dictators club, but there is time to the reputation of UN from becoming the next. Individual victims, who have left their loved ones behind and went into exile, may flood the United Nations with letters requesting to block the application of the fake human rights organisation. When you write the letter to the UN, make sure you copy Amnesty International and Human Rights Watch. Let these two credible organisations know what the sneaky dictators are about to achieve and also let them know that we do thank them for exposing crimes committed in Ethiopia against innocent people and continue discharging their duties as they are the only hope we count on to stand with the victims of dictatorship in Ethiopia.

Please send your protest letter to the following addresses:
Office of the United Nations High Commissioner for Human Rights (OHCHR)
Palais Wilson
52 rue des Pâquis
CH-1201 Geneva, Switzerland.

 

Friday, 5 October 2012

የለንደን ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን አባላትና ወዳጆች


ቀን 01/10/2012

የለንደን ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን አባላትና ወዳጆች

በስመ አብ፤ ወወልድ፤ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!

1.      እንደሚታወቀው ሁሉ ከሁለት ዓመት በፊት የቤተ ክርስቲያኗ ሕንጻ ግዢ ክፍያ ሳይጠናቀቅና በተለይም ከፍተኛ የሕግ ክፍተቶችን በመያዝ የቤተ ክርስቲያኗን ሰላም በማናጋት ብጥብጥን ለማስነሳት ምክንያት ሆኖ የነበረው፤ በሥራ ላይ ያለው የውስጥ መተዳደሪያ ደንብ ስለነበር፤ ይህ ቤተ ክርስቲያኗ የደረሰችበትን የእድገት ደረጃ የማያካትት እና ሌላ ሰበካ አስተዳደር ጉባኤ ማስመረጥ የማያስችል የውስጥ መተዳደሪያ ደንብ ሳይሻሻልና ሳይለወጥ የቤተ ክርስቲያኗ አስተዳዳሪ፤ የሰበካ አስተዳደር ጉባኤውና የልዩ ልዩ ኮሚቴዎች የአገልግሎት ዘመን መጠናቀቂያው ጊዜ ደረሰ።

ቀደም ሲል ግን የደንቡ መሻሻል ለቤተ ክርስቲያኗ ህልውና ፍጹም አስፈላጊነት ታምኖበት ከJanuary 22 2009 ጀምሮ አርቃቂ ኮሚቴ ተቋቁሞ የውስጥ መተዳደሪያ ደንቡን ማሻሻያ የማርቀቁን ተግባር በማከናወን ላይ ስለነበር የቤተ ክርስቲያኑ ህንጻ ግዢና በተለይም ምንም ዓይነት የአስተዳደር ለውጥ ለማድረግ የማያስችለው የውስጥ መተዳደሪያ ደንብ ተረቆ እስከሚጸድቅ ድረስ የቤተ ክርስቲያኑ አስተዳዳሪ፤ የሰበካ አስተዳደር ጉባኤውና ልዩ ልዩ ኮሚቴዎች የአገልግሎት ጊዜአቸው ላልተወሰነ ጊዜ እንዲራዘም በጥምር ጉባኤው የተነደፈ ሃሳብ ለጠቅላላ ጉባኤው ቀርቦ የቤተ ክርስቲያኗ አባላት የሆኑ የአባል መዝገባቸው ተጣርቶና ተረጋግጦ በጉዳዩ ላይ በመምከር የአገልግሎት ጊዜአቸው ያለቀው አስተደዳሪው፤ ሰበካ ጉባኤውና ልዩ ልዩ ኮሚቴዎች በሥራቸው ይቀጥሉ ወይም አይቀጥሉ የሚል ድምጽ እንዲሰጡ የምርጫ ካርድ ታድሏቸው በዛም መሠረት ከ99% በላይ የሚሆነው ሥራው እስኪጠናቀቅ ድረስ አገልግሎታቸውን እንዲቀጥሉ የሚለውን በመምረጥ የሁሉም የአገልግሎት ጊዜ ሊራዘም ችሏል።

2.     በተራዘመው የአስተዳዳሪው፤ የሰበካ አስተዳደ ጉባኤውና የልዩ፤ ኮሚቴዎች አባላት የአገልግሎት ዘመን መሠረትም የቤተ ክርስቲያኗ አባላትና ወዳጆች፤ ሥራ ያለው፤ ከደምወዙ፤ በመንግሥት ድጋፍ የሚኖረው ደግሞ ከዳረጎቱ፤ በጡረታ ላይ ያለው ደግሞ ከጡረታው በመቀነስ ትንሽና ትልቅ ሳይል፤ ከራሱና ከልጆቹ አፍ እየነጠቀ ገንዘቡን በማውጣት፤ ሃብትና ጉልበቱን በማፍሰስ የእግዚአብሔር በረከት ተጨምሮበት በአጭር ጊዜ ውስጥ የቤተ ክርስቲያኗ ገንዘብ 1.7 ሚሊዮን ፓውንድ እንዲደርስ በማድረግ በመጀመሪያ በApril 11 2010 የቤተ ክርስቲያኑን ህንፃ፤ ቀጥሎም በ May 2011  የቪካሬጅ ህንጻው የግዢ ክፍያ ተጠቃሎ ተከፍሎ ግዢው ሊጠናቀቅ ችሏል።

3.     በቀጣይነት መፈጸም የነበረበት የውስጥ መተዳደሪያ ደንብም ለ24 ወራት ከተደከመበት በኋላ የመጀመርያው ረቂቅ ተጠናቆ በJune 19 2011 ለሰበካ አስተዳደር ጉባኤው ቀረበ።

4.     የደንቡ ረቂቅ የቤተክርስቲያኗን ንብረት በአስተማማኝ የሕግ መሠረት ለመጠበቅ፤ ዘለቄታነት ያለው ሚዛናዊ አስተዳደር (Check & Balance) እና ተጠያቂነት የሰፈነበት ለማድረግ ታስቦ ከፍተኛ ሙያ፤ ልምድና ተሞክሮ ባላቸው አንጋፋ ካህናትና ምእናን የኮሚቴው አባላት የተዘጋጀ ሆኖ የኮሚቴው አባላትም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መተዳደሪያ ደንብ የሆነውን ቃለ ዓዋዲውን፤ የUK አጠቃላይ ሕግ፤ የቻሪቲ ደንብና መመሪያን በማገናዘብና በማቀናጀት በከፍተኛ ጥናትና ጥንቃቄ ያዘጋጁት ነው።

5.     ይህም የውስጥ መተዳደሪያ ደንብ ረቂቅ፤ የቤተ ክርስቲያኗ አባላት ተወያይተውበት አዳብረውት፤ አርመውና አስተካክለው በመጨረሻም ካጸደቁት በኋላ በሥራ ላይ ውሎ የቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ፤ የሰበካ መንፈሳዊ አስተዳደር ጉባኤና የልዩ ልዩ ኮሚቴዎች ምርጫ እንዲካሄድ መደረግ ሲገባው ከዚህ በታች በተዘረዘሩት የተለያዩ ማሰናከያዎችና ማዘግያዎች ምክንያት የደንቡ መጽደቅ ቀርቶ ለህዝብ ውይይት የመቅረቡ ህጋዊ አካሄድ እንኳ በተለያየ የተንኮል ሥራ እየተደናቀፈ ሂደቱ ለረጅም ጊዜ ለመጓተት ችሎ ነበር።

6.     June 19 2011 ረቂቁ ለሰበካ አስተዳደር ጉባኤው እንደቀረበ የሰበካ አስተዳደር ጉባኤው  የካህናቱም ሆነ የምእመናኑና የሰንበት ት/ቤት ተወካዮችና ተመራጮች የሚገኙበት የአስተዳደር ማዕከል እንደመሆኑ መጠን ከሥራ ልምዱና ተሞክሮ በመነሳት የካህናቱንም ሆነ የምእመናኑን ፍላጎት ባማከለ ሁኔታ በረቂቁ ላይ ሃሳብና አስተያየት በመስጠት ረቂቁን ማዳበርና ማስተካከል ይጠበቅበት ነበር።

ነገር ግን በዚህ ፋንታ የቤተ ክርስቲያኑ አስተዳዳሪ የሆኑት አባ ግርማ ከበደ 4 ካህናትና 4 ምእመናን ያሉበትን የሰበካ አስተዳደር ጉባኤ ለሁለት ከፍለው ከሳቸው ጋር 4 ካህናትን በመያዝ፤ ቀጥለውም በአርቃቂ ኮሚቴ ውስጥ ካሉት ካህናት ውስጥ አንድ ካህን ብቻ እንቢ ሲሏቸው ሌሎቹን ከምእማናኑ ለይተው በመውሰድ ካዋቀሩ በኋላ ካህናቱና እሳቸው በመሆን የደንቡን ረቂቅ ማሻሻል ጀመሩ።

በዚህ በተዋቀሩት የካህናት የረቂቅ አሻሻይ ክፍል አማካኝነት የተለያዩ ማረሚያና ማሻሻያ ሃሳቦችን በመጥቀስ በዛ ውስጥ ግን በተለይ እሳቸውን ብቻ የዕድሜ ልክ አስተዳደሪ፤ ብቸኛ ባለስልጣንና ፈላጭ ቆራጭ የሚያደርጉ አንቀጾች በረቂቁ ውስጥ እንዲካተቱላቸው በማሰብ ቀጥሎ የተመለከቱት ድንጋጌዎች በማሻሻያነት አቀረቡ።

1.      የቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ መመዘኛ መነኩሴ ብቻ እንዲሆን፤ (ይህ ማለት አንድ መነኩሴ ብቻ ባለበት ሌላ ተፎካካሪ እንዳይኖር ማለት ነው። በቃለ አዋዲው ላይ ግን ቄስም መነኩሴም የቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ መሆን እንደሚችል ይገልጻል።)

2.     ከቻሪቲ ሕግም ሆነ ከቤተ ክርስቲያን ቃለ ዓዋዲ ሕግ ውጪ አስተዳዳሪው በገንዘብ ማዘዣ ላይ እንዲፈርም፤

3.     አስተዳዳሪው ለካህናትና ለቅጥር ሰራተኞች ደምወዝ የመጨመር፤ ጉርሻ የመስጠት ስልጣን እንዲኖረው፤

4.     አስተዳዳሪው የጠቅላላ ጉባኤው፤ የሰበካ አስተዳደሩ፤ የካህናቱ ጉባኤ፤ የጥምር ጉባኤውና በአጠቃላይ የሁሉም የበላይ ስብሳቢና ፍጹማዊ ባለስልጣን እንዲሆን የሚሉት ከብዙ በጥቂቱ ናቸው። 

7.     ከዚህም ቀጥሎ አርቃቂ ኮሚቴው ለንዋይና ለስልጣን ሲባል የቀረበለትን አባ ግርማን ፈላጭ ቆራጭ ለማድረግ ታስቦ የተቀነባበረውን ድንጋጌ ከመርህ አኳያ በረቂቁ ውስጥ አላካትትም በማለቱ አባ ግርማ ከበደ ይህ ካልተካተተልኝ ሞቼ እገኛለሁ በማለት ከፍተኛ ሙግት አንስተው አልሳካ ሲላቸው ከአርቃቂ ኮሚቴው ጋር እልህ በመያያዝ ለየሰው ስልክ በመደወልና በአካል በማግኘት የአርቃቂ ኮሚቴ አባላት ቤተ ክርስቲያንን ለማጥፋት ሥውር ዓላማ ይዘው የተነሱ ናቸው በማለትና ሌላም ሌላም ነገር በማውራትና በማስወራት የተለያየና ተዘርዝሮ የማያልቅ ከአንድ መነኩሴ ቀርቶ ከማንም ሰው የማይጠበቅ ፍጹም፤ አስነዋሪ፤ አሳዛኝና ሕገው ወጥ ተግባር መፈጸማቸውን ተያያዙት።

8.     ከአባ ግርማ ድርጊቶች ውስጥም፤ እጅግ አስገራሚው ከሰበካ አስተዳደሩም ሆነ ከአርቃቂው ኮሚቴው ጋር ሲሰበሰቡና በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ውይይት ሲደረግ፤ ሁሌም የሚጠቀሙበት ዘዴና ተንኮል “ይህ ጉዳይ በዚህ አይነት ቢሄድ ወይም ቢወሰን ለኔ ግድ የለም ነገር ግን ካህናቱ አይቀበሉትም” በማለት የመስማማት አዝማሚያ ያሳዩና ከህናቱ ጋ ሄደው ደግሞ ይህ ጉዳይ እንዲህ ይሁን ስለተባለ እነዚህ ምእመናን እንዲህ ሲደፍሩን ምን ትጠብቃላችህ!! ተነሱ በማለት በእሳት ላይ ነዳጅ የማፍሰስ ያህል ካህናቱን ከምእመኑ የሚያጋጩበት ዘዴ ነው።

ሌላው አባ ግርማ ከበደ አንድ ካህን አንድ ሺህ ምእመን ያሳምናል የሚለውን መርሃቸው ነው፤ ይህንንም በየስብሰባው ላይ ለኮሚቴ አባላት በማስፈራሪያነት በማቅረብ እሳቸው ያለሙትንና ያቀዱትን ሁሉ ካህናቱን በማስፈራሪያነት እየተጠቀሙ በማቅረብ ተፈጻሚነት እንዲያገኝ የሚጠቀሙበት ዘዴ ነው።

ከዚህ በተጨማሪ አባ ግርማ ከበደ በሳቸውና ደጋፊዎቻቸው በሆኑ ካህናት አማካኝነት የሰንበት ት/ቤት ወጣቶችን በሰብሰብ፤ እኛ ካህናት ተሰደብን፤ ተዋረድን፤ ተናቅን፤ ቤተ ክርስቲያን ተደፈረች በማለት እሳቸው ከሚቀበሉት ውጪ ያለ ሃሰብ ሁሉ የሰይጣንና የዲያብሎስ ሥራ አድረገው እንዲያዩት ከሃይማኖትና ከቀኖና ቤተ ክርስቲያን ጋር በማወሳሰብ ለቤተ ክርስቲያናችሁ ስትሉ ህይወታችሁስ ብታልፍ በማለት ወጣቶቹ ለሃይማኖታቸው ያላቸውን ቀናዒነትና ለካህናት ያላቸውን ከበሬታ በመሣሪያነት በመጠቀም ወጣቶቹ በእልህና በቁጭት ተነሳስተው በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ለአንባጓሮ የሚጋበዙ፤ ታላቆቻቸውንና በዕድሜ ወልደው የሚያደርሷቸውን አዛውንቶች የሚሳደቡ፤ የሚያዋርዱ፤ የሚያንጓጥጡና የሚያስፈራሩ  እንዲሆኑ በማድረግ፤ ወጣቶቹ በዚህ ድርጊታቸው ከገፉበት ወንጀለኛ ተብለው የዘለዓለም ህይወታቸው እንደሚበላሽ እያወቁ በሕገ ወጥና ፍጹም ክርስቲያናዊና ኢትዮጵያዊ  ባልሆነ ባህሪአቸው እንዲገፉበት ማበረታታትና ማወደስ ነው።

በወጣቶቹ ዘንድ ይህን እያደረጉ በሌላ በኩል ደግሞ ለሰበካ አስተዳደር ጉባኤውና ለአርቃቂ ኮሚቴው አባላት  የሰንበት ት/ቤት ወጣቶቹን እሳቸው በደንብ እንደሚያውቋቸውና ምሥጢር ሊነገራቸው የማይገባ፤ የዚህና የዛ ተወካዮች በመሆናቸው እንዳታምኗቸው በማለት ስለነሱ መጥፎ በማውራት ወጣቶቹ በተለያየ ስብሰባ ላይ ተገኝተው እንኳ ከሌላው ጋር መቀራረብ እንዳይፈጥሩ ምሥጢር መስማት የለባቸውም እያሉ  ወጣቶቹን ማራቅ ነው።

ሌላው የአርቃቂ ኮሚቴ አባላትንም ሆነ አንዳንድ ለዓላማዬ እንቅፋት ይሆኑብኛል ብለው የሚያስቧቸእውን ምእመናን  ከካህናቱ ጋር ለማጋጨትና ለማራራቅ አባ ግርማ ከተጠቀሙበት ስልት አንዱና በምሳሌነት የሚጠቀሰው ቀጥሎ የተመለከተው ነው።

አባ ግርማ ከበደ ብዙ ምእመናንን ሥረ መሠረታቸውን የሚያውቁ አድርገው በማቅረብ ቤተ ክርስቲያንን ሊያፈርሱ፤ ሕገ ቤተክርስቲያንን ሊጥሱ ድብቅ ዓላማ  የያዙ አረመኔዎች አድርገው ለካህናቱ በማቅረብ አንዳንድ ካህናት የመነኩሴውን ቅስቀሳ በማመን በንዴት ገንፍለው በመነሳት የእግዚአብሔርን ቃል ማሰማት ትተው በስብከት ፋንታ በቀጥታና በተዘዋዋሪ መንገድ ምእመኑን በሃጢአት የተለወሰ እርኩስ አድርገው ሲያኮስሱት፤ ሲያዋርዱትና ሲሰድቡት ይደመጥና  ከምእመኑ አካባቢ እንዴት ካህኑ እንዲህ ሲል እርሶ ዝም ይላሉ ተብለው ስሞታ ይቀርብላቸዋል።

በዚህ ወቅት አባ ግርማን ሦስት ሰው በዚሁ ጉዳይ ላይ ያነጋገራቸው  ሲሆን ለአንዱ ሰው፤ “በወቅቱ እኔ ደክሞኝ እንቅልፍ ይዞኝ ስለነበር ስብከቱን አልሰማሁም” ሲሉ፤ ለሁለተኛው ሰው ደግሞ “እኔን አያገባኝም እሱ በተናገረው እራሱ ይወጣው” ካሉ በኋላ ቀጥሎ ያነጋገራቸው ሦስተኛው ሰው ምሥጢሬን ይጠብቅልኛል ወይም ይደግፈኛል የሚሉት ሰው ስለነበር ይህ ሰው ሲጠይቃቸው የሰጡት መልስ ደግሞ “አታስብ፤ ካላረፉ ገና ከዚህም በላይ እንላለን” የሚል ነበር። እነዚህ ባንድ አባ ግርማ ምላስ የተነገሩ ሦስት የተለያዩ ቃላትን የሰሙ ሦስት ሰዎች ዛሬ ድረስ ነገሩን በአግራሞት ያስታውሱታል።

ከዚህ ያለፈውንና ለሃይማኖታችንም ሆነ ለቤተ ክርስቲያናችን አጸያፊ የሚሆነውን የመነኩሴውን ተግባር በዚህ ላይ ከመግለጽ መቆጠቡን መርጠናል፡፤

ባጭሩ ግን እንዲህ በማድረግ ነው አባ ግርማ ካህኑን ከምእመኑ፤ የሰንበት ት/ቤተ ወጣቶቹን ከምእመኑ፤ እንዲሁም ምእመኑን ከምእመኑ  እርስ በርሱ እንዲከፋፈል፤ በጥርጣሬና በጠላትነት እንዲተያይና እንዲጣላ ወሬ አሉባልታና ሽብር በመንዛት ረቂቁ ለአንድ ዓመት ያህል ለጠቅላላ ጉባኤ ሳይቀርብ በጓዳ ውስጥ በሚደረግ ጭቅጭቅና ንትርክ ብቻ ተጠምዶ እንዲጓተት ያደርጉትና ረቂቁ ለውይይት ሲቀርብም ረቂቁ የያዘው ቁም ነገር ላይ መነጋገር ተትቶ በተንኮል መረብ የተተበተበው ሰው እርስ በርሱ መደማመጥ ተስኖት በጥሞና፤ በሰለጠነ መንገድና በጨዋነት ለመወያየትም አልቻለም ነበር።

9.     ዓመት በፈጀ ትግልና ክርከር በመጨረሻ ረቂቁ በJanuary 26 2012 እሁድ ዕለት ለህዝብ ቀርቦ ውይይት እንዲደረግበት የጠቅላላ ጉባኤ ስብሰባ ተጠርቶ እያለ፤ አባ ግርማ ከበደ ከሰበካ አስተዳደር ጉባኤውና ከአርቃቂ ኮሚቴው ጋር ሆነው በረቂቁ ላይ ህዝብ የሚያደርገው ውይይት እንዲደረግ ከተስማሙ በኋላ በጎን ሄደው ደግሞ ካህናቱን በማሳደም በአቢይ ጾም እንዴት ውይይቱ ይካሄዳል በማለት በረቂቁ ላይ ለመወያየት ለተጠራው ሕዝብ በአቢይ ጾም ውይይቱ መካሄድ የለበትም የሚለውን የካህናቱን ውሳኔ ደብዳቤ አንባቢ እሳቸው ራሳቸው በመሆን ሕዝቡ በጾሙ ውስጥ እንወያይ ቢል ሃጢአተኛና የክርስቶስን ስቃይ የማያስብ በሚያስመስል መልክ በማቅረባቸው የረቂቁ ቅጂ ለሕዝቡ እንዲታደልና ውይይቱ ከጾሙ መፈታት በኋላ እንዲጀመር ተወሰነ።

10.    ጾሙ ከተፈታ በኋላ ደግሞ አባ ግርማ ከበደ የተለያየ ሰበብ በመፍጠርና የተለያየ የተንኮል መረብ በመዘርጋት ረቂቁ ለጠቅላላ ጉባኤ ውይይት ሳይቀርብ በመጓተቱ ይህንን የተገነዘቡ የቤተ ክርስቲያኗ አባላት ከውስጥና ከውጪ ባደረጉት ግፊትና  ምንም ቢሆን በሰበካ አስተዳደሩ ውስጥ የምእመናኑ ተወካዮች በመኖራቸው ምክንያት በአባ ግርማ ላይ በደረሰባቸው ጫና የተነሳ ወደው ሳይሆን ተገደው ከJuly 7 2012 ጀምሮ ረቂቅ 3 ለጠቅላላ ጉባኤ ውይይት ቀረበ።

11.      አሁንም ረቂቁ ለጠቅላላ ጉባኤው ውይይት እንዲቀርብ የማይፈልጉትና ምእመን መርጦ እንደሾማቸውም ሆነ ደምወዝ እየከፈለ እንደሚያኖራቸው ጨርሶ የረሱት አባ ግርማ ከበደ ሁሌም እንደሚሉት “ምእመን ምን ያውቃል፤ ማነው ምእመንን በቤተ ክርስቲያን ጉዳይ ወሳኝ ያደረገው” በማለት የጠቅላላ ጉባኤው ስብሰባ በሰንበት ት/ቤት ወጣቶችና ሌሎች እሳቸው አዕሞሯቸውን በገዟቸው ሰዎች አማካኝነት ተረብሾ እንዲሰናከል የሚቻላቸውን ሁሉ አደረጉ፤

12.    በዚህ ወቅት ጉዳዩ ያሳሰባቸው ምእመናን በመሰባሰብ አስታራቂ ሽማግሌ ቡድን በማቋቋም ሁኔታው በእርቅና በሰላም እንዲፈታና ውይይቱ እንዲቀጥል በካህናቱ፤ በሰበካ አስተዳደር ጉባኤው አባላትና በአርርቃቂ ኮሚቴው አባላት መካከል ይቅር ለእግዚአብሔር እንዲካሄድ አደረጉ።

13.    ከዛ ቀጥሎም በሰበካ አስተዳደሩ፤ በአስታራቂ ሽማግሌዎችና በአርቃቂ ኮሚቴው ተመርጦ በጠቅላላ ጉባኤው የተሰየመው ገለልተኛ አወያይ ውይይቱን እንደገና ለማስጀመር በተደረገው የጠቅላላ ጉባኤው ስብሰባ እንደገና የተፈጠረውን ተመሳሳይ ረብሻ ያሳሰበውና ያሳዘነው አወያይ፤ ግለሰብ የሰበካ አስተዳደሩን ካህናቱን፤ አስታራቂ ሽማግሌዎችንና አርቃቂ ኮሚቴውን በመሰብሰብ ለምን የጠቅላላ ጉባኤው ውይይት በሰለጠነና በጨዋነት መንፈስ ከመካሄድ ይልቅ ይረበሻል? በማለት ጥያቄ ሲያቀርብ፤ አባ ግርማ ከበደ ካህናቱን አስቀድመው በማሳደም አዘጋጅተዋቸው ስለነበ፤ በአንድ ቃል “ረብሻው የተነሳው ካህናቱ በቂ ጊዜ ተሰጥቷቸው በረቂቁ ላይ ያላቸውን ሃሳብ ባለማቅረባቸው ነው” በማለት ገለጹ። አወያዩም ግራና ቀኝ የተነሳውን ሃሳብ በማዳመጥ፤ መፍትሔ ቢሆን በማለት በሚቀጥለው ስብሰባ ካህናቱ ያላቸውን ሃሳብ እንዲያቀርቡ ጊዜ እሰጣለሁ በማለት ማረጋገጫ ሰጠ።

እዚህ ላይ በተዘዋዋሪ ካህናቱ ስብሰባውን ሆነ ብለን ያስረበሽነው እኛ ነን፤ ብለው ማመናቸው እንደሆነ እንኳ ሳያገናዝቡ ይህን ማለታቸውና እነሱ ረቂቁን ለመቃወም ጊዜ ይሰጠን በሚለው ተመካክረው መጥተው ከዚህ ሌላ መፍትሔ የለም ብለው ጠንካራ ክርክር ማንሳታቸው በእጅጉ የሚያስገርምና ሃይማኖታችንም ሆነ ቤተ ክርስቲያናችን ከቶ ምን እየሆነች ነው ብሎ የሚያነጋግር ነበር።

14.    ካህናቱ ያላቸውን ሃሳብ እንዲያቀርቡ ጊዜ ይሰጣል የሚለው ቃል ከአወያዩ እንደወጣም አባ ግርማ ከበደ የተወሰኑ ካህናትን በማስተባበር በአጠቃላይ ረቂቁን የሚቃወምና የሚኮንን ሃሳብ በማቅረብ  “የሃይማኖተ ሕግ ሊፈርስ ነው፤ ቀኖና ቤተ ክርስቲያን ሊጣስ ነው፤ ቤተ ክርስቲያን ልትረክስ ነው” በማለት ምእመናኑን ካሸበርነውና ካስፈራራነው ረቂቁን ውድቅ ያደርገዋል የሚል ዕቅድ በመንደፍ ከሳቸው ጋር በድምሩ አራት ካህናት ለሁለት ተካታታይ ሳምንት ረቂቁን በመቃወም፤ በማራከስና በመኮነን አንዳችም በጎ ነገር የለሌው የእርኩስ ሥራ ነው በማለት ገለጻ አደረጉ።

ከቀረበው ገለጻ ውስጥ ግን 90% ፍጹም የለየለት ውሸትና ቅጥፈት ሲሆን የተቀረውም በዚህ ሃገር ከሚኖርና ከሚሰራ ሰው ቀርቶ እንግዳ ደራሽ ሰው እንኳ ለማወቅ በማያዳግተው ጉዳይ ላይ እንኳ ጨርሶ ግንዛቤና እውቀት በጎደለው ሁኔታ የቀረበ አስቂኝ ድራማ ነበር።

 ከሁሉም ውሸት የላቀውና የበሬ ወለደ ያህል የሆነው ግን ከራሳችን ቤተ ክርስቲያን አልፈው የኤርትራ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያንን መጥፎ ምሳሌ አድርገው በማቅረብ እኛም እንደ ኤርትራው ቤተ ክርስቲያን የጥፋት ሰለባ እንዳንሆን በማለት ያቀረቡት ማስፈራሪያ ነበር። ይህ ሁሉ ሃሰት፤ ይህ ሁሉ የፈጠራ ታሪክ ተወርቶ ህዝብን አታሎ በተሳሳተ መንገድ ለመምራት የተደረገው ሙከራ እዛው እግዚአብሔር ቤት ውስጥ ያውም ከጽላቱ አጠገብ፤ በተቀደሰውና በተባረከው ቦታ በመሆኑ እነዚህ ሃሰትን የሚሰብኩ ካህናት እግዚአብሔርን መፍራት ቀርቶ የእግዚአብሔርን መኖርንስ የሚያምኑ ይሆን? ብሎ ጥያቄ ውስጥ የሚያስገባ ነበር።

15.    በዚህ ወቅት አባ ግርማ ከበደ ካህናት የሃሰት መረጃ ለሕዝብ እንዲያቀርቡ አስተባባሪ ብቻ ሳይሆኑ ከሰበካው ጋር ሆነው የወሰኑትንና ያደረጉትን ሁሉ ያለምንም ፍርሃትና ሃፍረት በመካድ እንደውም የለየላቸው የሃሰት ተዋናኝ ሆነው ነበር የቀረቡት።

16.    ከካህናቱ የሃሰት መረጃ አቅርቦት በኋላ ደግሞ አባ ግርማ ሌላ ህዝብን የሚከፋፍልና የሚያበጣብጥ ተግባር በማውጠንጥን የአባ ጳውሎስን መሞት ምክንያት በማድረግ በዛም ሁሌም የሚመኙትን ሹመትና ሽልማት ለማግኘት እንዲያስችላቸው ለአባ ጳውሎስ ፍታት ይደረግ በሚል ፍትሐትን እንደምክንያት ለመጠቀም በማሰብ የእግዚአብሔር ቃል በሚነገርበት መድረክ አዋጅ መናገር ጀመሩ።

መቸም እግዚአብሔር በቤቱ ይህን የመሰለ ተንኮልና ደባ ሲፈጸም ዝም ብሎ አያይምና እሳቸው እንዳሰቡት ሳይሆን ህዝቡ ተባብሮ ከፍተኛ ተቃውሞ በማንሳቱ ፍትሐትን እንደ መከፋፈያ መሣሪያ አድርገው ለመጠቀም ያቀዱት ዕቅድ ሊሰረዝባቸው ችሏል።

17.    ከካህናቱ ገለጻ በኋላ የተፈራው አልቀረም አርቃቂ ኮሚቴው ለሁለት ተከታታይ እሑድ በማስረጃ የተደገፈ ገለጻ በማድረግ የካህናቱም ሆነ የአባ ግርማ በሬ ወለደ ውሸትን አጋለጠ።

18.    ከአርቃቂ ኮሚቴው ገለጻ በኋላ አወያዩ ቀደም ብሎ ባስያዘው የስብሰባው አካሄድ መሠረት በ16/09/2012 የሚደረገው ስብሰባ የጠቅላላ ጉባኤው አባላት ጥያቄ የሚያቀርቡበትና ተገቢውን መልስ የሚያገኙበት ወቅት ሆኖ ሳለ አሁንም አባ ግርማ ካህናቱንና የሰንበት ት/ቤት ወጣቶችን በማሳደም ካህናቱ በተጨማሪ የሚገልጹት ሳላለ (በሌላ አነጋገር ሌላ ውሸት አዘጋጅተናልና እንደገና ውሸታችንን ስሙን በሚል አይነት) ገለጻ ማድረግ አለባቸው የሚል ክርክር አነሱ።

በዚህ ወቅት ሰብሳቢው ይህ ከሆነ ሕዝቡ በድምጽ ብልጫ ይወስንበት እንጂ በዛሬው ዕለት ቃል የገባሁትና የያዝኩት የሕዝቡ ተራ ነው በማለት አሳሰበ።

በዚህ ወቅት አጨብጭብ ሲሉት እንዲያጨበጭብላቸው፤ እልል በል ሲሉት እልል እንዲልላቸው ካልሆነ በስተቀር ሕዝብን እንደ ሕዝብ ምንም ዓይነት ክብር የማይሰጡት አባ ግርማ ከበደም ሆኑ የሳቸው ደጋፊ ካህናትና የሰንበት ት/ቤተ ወጣቶች፤ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ በድምጽ ብልጫ አይወሰንም፤ ሕዝብም ሊወስን ስልጣን የለውም በማለት አይን ያወጣ ክርክር አነሱ።

ይህንንም በመቃወም አንዳንድ ምእመናን ሲናገሩ አባ ግርማ ከበደ ያዘጋጇቸው የሰንበት ት/ቤት ወጣቶች በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ሰውን ከመሳደብና ከማንጓጠጥ አልፈው ለዱላ በመጋበዝ ስብሰባው በተያዘለት አጀንዳ ላይ ሳይወያይ እንዲቋረጥ አደረጉ።

19.    ካህናቱን በማስዋሸትና እሳቸውም በመዋሸት የደንብ ረቂቁን ውድቅ ለማድረግ ያደረጉት ጥረት ያልተሳካላቸው የመሰላቸው አባ ግርማ ከበደ፤ ላለፉት ዓመታት በሥራ ጫናም ይሁን አባ ግርማ ከበደ በሚፈጥሩት ከፍተኛ የተንኮል መሰናክል ሥራቸውን ለመልቀቅ ሲያንገራግሩ የነበሩትን የሰበካ አስተዳደር ጉባኤ አባላትን ግፊቱ እንዲጠናከርባቸውና እርስ በርሳቸው ሆድና ጀርባ እንዲሆኑ በማድረግ በተለይ የሰበካ አስተዳደሩ ም/ሊቀመንበር የሆነው አቶ ታዬ ኃይሉ ላይ በቃልም ሆነ በጽሑፍ ከፍተኛ ማስፈራራትና ስድብ እንዲካሄድበት በማስደረግ ብስጭትና ተስፋ መቁረጥ ደርሶበት የሥራ መልቀቂያ ደብዳቤ እንዲያቀርብ አስደረጉ።

ከአሁን በፊት እንኳንስ ም/ሊቀመንበርና በቤተ ክርስቲያኑ አስተዳደር ከ10 ዓመት በላይ ያገለገለው አቶ ታዬ ቀርቶ አንድ የኮሚቴ አባል ከሥራ እለቃለሁ ሲል ከልመናና ከምልጃ በተጨማሪ የቤተ ክርስቲያኗ የውስጥ መተዳደሪያ ድንብ በሚያዘው መሠረት ጊዜ ሳያጠፉ የጥምር ጉባኤውን ስብሰባ በመጥራት እንዲመክርበትና የውሳኔም ሆነ የመፍትሔ ሃሳብ እንዲያፈልቅ የሚያስደርጉት አባ ግርማ ከበደ፤ በአሁኑ ጊዜ ግን የአቶ ታዬ መወገድ ያሰቡትን ለማከናወን ልክ አንድ መሰናክል እንደተወገደላቸው የሚመኙትና የሚፈልጉት በመሆኑ የጥምር ጉባኤውን ስብሰባ አልጠራም በማለት ውስጥ ውስጡን ነገሮችን ማመቻቸት ጀመሩ።

20.   የጥምር ጉባኤው አባል የሆኑና ከሰበካ አስተዳደሩ ቀጥሎ በሕዝብ ተመርጠው የተወከሉ በመሆናቸው ላለፉት 5 ዓመታት ማንኛቸውንም የቤተ ክርስቲያኗን ከፍተኛ ውሳኔዎችን ከሌሎች የጥምር ጉባኤው አባላት ጋር በመሆን በመወሰንና የውሳኔ ሃሳብ ነድፈው ለጠቅላላ ጉባኤው  ያቀርቡ የነበሩት የቁጥጥር ኮሚቴ እና የህንፃና ልማት ኮሚቴዎች የአቶ ታዬ ኃይሉ የሥራ መልቀቂያ ደብዳቤ በግልባጭ ደርሷቸው ሥለ ነበር በውስጥ መተዳደሪያ ደንቡ መሠረትና ሲሰራበት በነበረው ሕጋዊ አካሄድ መሠረት አባ ግርማ ከበደ በበላይነት የሚመሩት የሰበካ አስተዳደር ጉባኤ የጥምር ጉባኤውን ስብሰባ ይጠራል ብለው ሲጠብቁ ባለመጥራታቸው የአቶ ታዬን የሥራ መልቀቂያ ደብዳቤ ማቅረብ ከፍተኛ የቤተክርስቲያኗ አነጋጋሪ ጉዳይ በመሆኑ የጥምር ጉባኤው ስብሰባ በአስቸኳይ  ይጠራ ዘንድ በ14/09/2012 በተጻፈ ደብዳቤ የሰበካ አስተዳደር ጉባኤውን ጠየቁ።

21.    አባ ግርማ ከበደ ግን ሕዝብ የመረጣቸውን ኮሚቴዎችና ከጠቅላላ ጉባኤ በታች ከፍተኛ ውሳኔዎችንና የውሳኔ ሃሳብ የሚያቀርበውን የጥምር ጉባኤ ስብሰባ አልጠራም በማለት ነገሮች ሁሉ እሳቸው በሚፈልጉበት መንገድ ብቻ እንዲሄዱላቸው ለማድረግ መሰናክል ይሆንብኛል ያሉትን የሰበካ አስተዳደር ጉባኤ ለማፍረስና ከዛም ይህ በተለያየ መንገድ ጥረው አልቆም ያላቸውን የውስጥ መተዳደሪያ ደንብ ረቂቅ ከመድረክ ላይ ጨርሶ ለማጥፋት እንዲያስችላቸው የተንኮል ሥራቸውን ገፍተውበት ቀጥሎ የተመለከቱትን እርምጃዎች አስወሰዱ፡

1.      በውስጥ መተዳደሪያ ደንባችን በአንቀጽ 44 ቁጥር 2 (ለ) የተመለከተውን በጥምር ጉባኤው ሳይመክርበትና ሳይወሰን የሰበካ አስተዳደር ጉባኤው የሰበካ ጠቅላላ ጉባኤ ስብሰባ ጥሪ አያደርግም የሚለውን በመጣስ በ23/09/2012 በዕለት እሁድ የጠቅላላ ጉባኤውን ስብሰባ ጠሩ፡

2.      በ23/09/2012 በዕለተ እሑድ ከቅዳሴ አገልግሎት በኋላ የሰበካ ጠቅላላ መንፈሳዊ ጉባኤ ወይም የAGM ስብሰባ ሕግን በጣሰ ሁኔታ የቤተ ክርስቲያን አባላት የሆኑና ቤተ ክርስቲያኗን ላለፉት 20 ዓመታትና ከዛም በላይ በሃብታቸው፤ በገንዘባቸውና በጉልባታቸው በመርዳት አሁን የምትገኝበት ደረጃ ያደረሷትን ሳይሆን የቤተ ክርስቲያን አስተዳደር ፈረሰ ሲባል የሚያጨበጭቡና በቤተ ክርስቲያን ውድቀት እልል የሚሉ ሰዎችን የስብሰባው ተሳታፊ  በማድረግ የሰበካ መንፈሳዊ አስተዳደር ጉባኤ አባላት በሙሉ በገዛ ፍቃዳቸው ከሥራቸው መልቀቃቸው በጽሑፍ እንዲነበብ ካስደረጉ በኋላ የቤተ ክርስቲያኑ አስተዳደር በመውረዱ አጨብጭቡ በማለት አስጨብጭበው ሌሎች በሂደቱ ላይ ሕጋዊ ጥያቄ ሊያነሱ እጃቸውን ያወጡ ምእመናን እንዳይናገሩ እድል በመንፈግ ለመጨረሻው ጸሎት እንነሳ በማለት ህዝቡን እንደ ህጻን ልጅ በማሞኘት ስብሰባውን ዘግተዋል።

3.     በዚሁ ስብሰባ ላይም ስለ ሰበካ አስተዳደር ጉባኤው አባላት የሥራ መልቀቅ ሲገለጽ ከዛ ጋር ተያያዥነት ያላቸውና በጥምር ጉባኤውም ሆነ የቤተ ክርስቲያኗ አባላት ብቻ በተገኙበት የሰበካ ጠቅላላ ጉባኤ ፊት ቀርበው ውይይትና ውሳኔ የሚያስፈልጋቸው፡ 1)የቤተ ክርስቲያኑ አስተዳዳሪ ጉዳይ፤ 2)ሕዝብ መርጦ የሰየማቸው የንዑሳን ኮሚቴዎች ቀጣይ ዕድል ጉዳይ፤ 3)የቤተ ክርስቲያኗን ንብረት በአደራ የያዙ (Holding Trustee) የሰበካ አስተዳደር ጉባኤው አባላት ጉዳይ፤ 4)ጠቅላላ ጉባኤው እየተወያየበት ስላለው የውስጥ መተዳደሪያ ደንብ ረቂቅ ጉዳይ፤ አንዳችም ውይይት ሳይደረግባቸውና እልባት ሳይበጅላቸው ስለ አስመራጭ ኮሚቴ አመራረጥ ጊዜና ሁኔታ መወሰን ያለበት ራሱ ጠቅላላ ጉባኤው ሆኖ ሳለ ሕዝቡን ምን ያመጣል ብሎ በመናቅ ይመስላል ራሳቸው ሥራችንን ለቀናል የሚሉት የሰበካ አስተዳደር ጉባኤ አባላት የአስመራጭ ኮሚቴውን የምርጫ ጊዜና ሁኔታ ወስነው በማቅረብ በስብሰባው ላይ አስመራጭ ኮሚቴ ይቋቋማል የሚል መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

4.     በዚህ ዕለት ሌላው አስገራሚ ነገር የቤተ ክርስቲያኑ አስተዳዳሪ የተመረጡበት የአገልግሎት ዘመን ከሰበካ አስተዳደሩ አባላት የአገልግሎት ዘመን በፊት ያለቀ ቢሆንም ከሰበካ አስተዳደሩ አባላት ጋር እንዲራዘምላቸው በጠቅላላ ጉባኤው ውሳኔ የተወሰነ በመሆኑ የሰበካ አስተዳደሩ አባላት ከሥራቸው ሲለቁ የሳቸውም የአገልግሎት ዘመን እንደሚያልቅ በትክክል የሚረዱት አባ ግርማ በገዛ ፈቃዳቸው ከሥራ ለቀናል ያሉትን የሰበካ አስተዳደሩ አባላትን እባካችሁ አሰናብቷቸው እያሉ ሕዝቡን ይገፋፉና ይማጸኑ ነበር እንጂ እራሳቸውን ግን የቆጠሩት ዘላለማዊ የሥልጣን ባለቤት አድርገው ነበር።

22.   የቤተ ክርስቲያኑ አስተዳዳሪ አባ ግርማ ከበደ የሰበካ አስተዳደር ጉባኤውን በያዙት መንገድ በማፍረስ ቤተ ክርስቲያኗን ከፍተኛ ጉዳት ላይ ከመጣላቸው በፊት የጥምር ጉባኤው አባል የሆነው የሕንጻና ልማት ኮሚቴ አባላት ከላይ የተዘረዘረው ሕገ ወጥ አሰራር ተወግዶ የሰበካ አስተዳደር ጉባኤው አባላት የሥራ መልቀቅም ሆነ የወደፊት ቀጣይ ክንዋኔዎች በጥምር ጉባኤው ስብሰባ ታይተው ከውሳኔ ሃሳብ ጋር ለጠቅላላ ጉባኤው ውይይት ይቅረብ በማለት ለሁለተኛ ጊዜ 30/09/2012 በተጻፈ ደብዳቤ ቢያስገነዝቡም አባ ግርማ ከበደ ግን በያዙት ሕገ ወጥ ተግባር ቀጥለውበት፡

1.      የአስመራጭ ኮሚቴ ምርጫ እንደሚደረግና ቀጣዩም የሰበካ አስተዳደር ጉባኤ ምርጫ እንደሚደረግ መወሰኑን በ30/09/2012 ለአገልግሎት ለተሰበሰበው የሰበካ ጉባኤ በንባብ እንዲሰማ አድርገዋል

2.     ለተመረጡት ገለልተኛ አወያዮች እና ገለልተኛ ጸሐፊ በአድራሻ፤ እንዲሁም በግልባጭ ለአርቃቂ ኮሚቴው ደብዳቤ  በመጻፍ 30/09/2012 ጀምሮ በረቂቁ ላይ የሚደረገው ውይይት መቆሙን በመግለጽ ገለልተኛ አወያዮቹና ጸሐፊውን አመስግነው ከሥራቸው አሰናብተዋቸዋል።

ከቶ ይህ ሁሉ ደባ የተፈፀመበት ህዝበ ክርስቲያን አፉን ዘግቶና እግሩና እጁን አጣጥፎ አባ ግርማ በሚነዱትና በሚጎትቱ መንገድ እንደ እንሰሳ ይከተላቸው ይሆን? እሱ በተግባር የሚታይ ይሆናል።

23.   በግልጽ እንደተረጋገጠው የሰበካ አስተዳደር ጉባኤው አባላት ከሥራቸው መልቀቅ ዋናው ዓላማና ጥንስስ ለውይይት የቀረበውን የውስጥ መተዳደሪያ ደንብ ረቂቅ ለአንዴና ለመጨረሻ ለማስቆም የሚያስችል ተመራጭ ዘዴ ነው ተብሎ ስለታመነበት ነው።

አባ ግርማ ከበደ ይህንን የውስጥ መተዳደሪያ ደንብ ከምድረ ገጽ ለማጥፋት ይህንን ያህል ለረቂቁ ጠላት የሆኑበትና ይህንን ሁሉ ለማድረግ የተገደዱበት ምክንያቱ ምንድን ነው? ለሚለው ጥያቄ መልሱ ከብዙ በጥቂቱ ቀጥሎ የተመለከተው ነው።

1.      በረቂቁ ውስጥ ትልቁ ለውጥ ቤተ ክርስቲያኗን Incorporated የሚያደርገው አንቀጽ ሲሆን  በዚህም እስከ አሁን ድረስ ቤተ ክርስቲያኗ የምትተዳደረው በቻሪቴብል ትረስትነት (Charitable Trust) እና ንብረቷም የተያዘው በአደራ ጠባቂዎች በ(Holding Trustee) ሰዎች በመሆኑ ረቂቁ ከጸደቅ ግን የነበረው ተቀይሮ ቤተ ክርስቲያኗ ንብረቷን በራሷ ስም በመያዝ በትረስቲዎች ሳይሆን ራሷ ሕጋዊ ሰውነት Legal Entity ኖሯት ማንኛቸውንም ነገር በስሟ እንድታከናውን የሚያደርጋት በመሆኑ ነው።

ይህ ማለት ደግሞ በአሁኑ ወቅት አባ ግርማ ከበደ በገበያ ዋጋ ሲተመን (Market Value) ከ8 ሚሊዮን ፓውንድ ያላነሰ ዋጋ ሊያወጣ የሚችል ንብረት ሕጋዊ ባለቤት (Legal Owner) በመሆን አደራ ከያዙ 4 ሰዎች ውስጥ አንዱ በመሆናቸውና ይህም የንብረት ባለቤትነት ትልቅ Power እና ተሰሚነት የሚሰጣቸው በመሆኑ፤ ይህ ተሰሚነታቸው ደግሞ የሚመኙትን የጵጵስና ሹመት የሚያሰጣቸውና ምናልባትም በአውሮፓ የሃገር ስብከት ስልጣን አስጥቶ ተደላድለው ለመኖር የሚያስችላቸው መደራደሪያ አቅም እንደሚሆናቸው አስቀድመው ሂሳባቸውን አስልተው ያስቀመጡ በመሆኑ ነው።

አባ ግርማ ከዚህም ባለፈ አሁን በያዙት የተንኮል አካሄድ ገፍተውበት የተቀሩት ሦስቱ Holding Trustees ከሰበካ አስተዳደሩ በገዛ ፍቃዳቸው እንደለቀቁ ሁሉ ከHolding Trusteeው ከለቀቁ የቤተ ክርስቲያኗ ንብረት በአባ ግርማ እጅ ብቻ እንዲቀር ለማድረግ እንደሚያስቡ መገመት አዳጋች አይሆንም።

አባ ግርማ ከበደ የቤተ ክርስቲያንን ንብረት አጠባበቅ አስመልክቶ ውይይት ሲደረግ፡ “በቤተ ክርስቲያን ንብረት ላይ (ቤትና መሬት ማለት ነው) መፈረም የማይችል የቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ ምን የቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ ይባላል” በማለት ያላቸውን አቋም ግልጽ አድርገው በመናገር በቁጭትና በንዴት መሬት ሲደቁ፤ ራሳቸውን በቆባቸው ሲያኩ ማየት የተለመደ በመሆኑ ይህን ቢያቅዱ የሚያስገርም አይሆንም።

አስቡት እኚህ የዓለምን ነገር ትቻለሁ ብለው መንኩሰው ቆብ የደፉ አባት፤ ተርታው ምእመን እንኳ በማያስበው ደረጃ በንዋይና በስልጣን ጥም እዕምሮአቸው ተነክቶ፤ ልባቸው ተሰውሮ ቀን ተሌሊት የሚያስቡት የሕዝብን ሃብትና ንብረት እንዴት የግሌ አድርጌ ይዤ በመሣሪያነት እጠቀምበታለሁ የሚለውን ነው።

2.     ከዚህ ቀጥሎ ረቂቁ የያዘው የገንዘብ አስተዳደርን፤ ቁጥጥርን፤ የአስተዳደር check and balance; ተጠያቂነትን እና የስልጣንና የሥራ ክፍፍልን የሚተነትን በመሆኑ ይህ በሙሉ አባ ግርማ ከበደ የማይቀበሉትና የማይዋጥላቸው ሥለሆነ በዚህ ፋንታ የሁሉም ነገር አዛዥና ፈላጭ ቆራጭ እሳቸው የሚሆኑበት፤ ሌላው ቀርቶ በቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ ምርጫ እንኳ ሌላ ካህን በተወዳዳሪነት የማይቀርብበት እና ከሁሉም በላይ ደግሞ በገንዘብ ላይ የማዘዝ ሥልጣንን የሚሰጣቸውን ደንብ ወይም ደንብ አልባነትን ስለሚመርጡ ነው።

3.    ይህን በመሰለ ሰውን ከእግዚአብሔር እና ሰውን ከሰው በማስታረቅና በማቀራረብ ፋንታ፤ ሰውን ከእግዚአብሔር መንገድ አስቶ ካህኑን ከምእመኑና ምእመኑን ከምእመኑ በማናከስ፤ መንፈሳዊ ሥራን ትቶ ሥጋዊ  የሆነውን ንዋይና ስልጣንን በማሳደድ፤ ከደግነት ይልቅ በክፋት ሥራ መካን  መሾምና መሸለምን ቀርቶ ተደላድሎ መኖርን ካስገኘ፤ ያለው ትውልድ የአባቶቹ ሃይማኖት ቆሽሾና አድፎ ሞቶ እንዲቀበር ድንጋይ አቀባይና ጉድጓድ ማሽ ሆኗል ማለት ነው።

 

24.  ማጠቃለያ

የመጨረሻው መጀመሪያ የሆነው የሰበካ አስተዳደር ጉባኤው አባላት በገዛ ፍቃዳቸው ከሥራ የመልቀቅ ውሳኔ ሲሆን እነዚህ ሰዎች ይህንን የማለት መብታቸው የተጠበቀ በመሆኑ ማንም ሰው አስገድዶ ስሩ ወይም አገልግሉ ሊላቸው እንደማይችል የታወቀ ነው።

ይህ እንዳለ ሆኖ ግን የሰበካ አስተዳደር ጉባኤ አባላቱ የሥራ መልቀቂያቸውን ካቀረቡበት ጊዜ ጀምሮ በሥራ ላይ በቆዩበት ጊዜ ስላከናወኑት ተግባር የሥራ ሪፓርትና የኦዲት ሪፓርት ከማቅረብና ለርክክብ ከመዘጋጀት ያለፈ በተለይ ሥለ ቤተ ክርስቲያኑ ቀጣይ ሥራዎችና ክንዋኔዎች በጠቅላላ ጉባኤው ከማስወሰን በስተቀር እነሱ ራሳቸው እንደገና ተሰብስበው አንዳችም ውሳኔ የማስተላለፍ ሕጋዊ መብት ስለሌላቸው ውሳኔ እናስተላልፍ ካሉ ግን ሕግን በመጣስ በከፍተኛ ደረጃ የሚያስጠይቃቸውና የሰሩትን በጎ ሥራ ሁሉ ገደል በመጨመር በሰሩት ሥራ ላይ ጥርጣሬን ጭሮ ጥብቅ ምርመራ እንዲደረግባቸው የሚያስገድድ ሁኔታን የሚፈጥር ነው።

አባ ግርማ  ከበደ ግን ይህን ሁሉ ተላልፈው ጠቅላላ ጉባኤው በደንቡ ረቂቅ ላይ የሚያደርገውን ውይይት በተለያየ የተንኮል ድርጊት ማስቆም ሲያዳግታቸው በሌላ መንገድ ረቂቁን እስከመጨረሻው ድረስ ለማዳፈን ቀጥሎ የተመለከተውን የጥምር ጉባኤውና ጠቅላላ ጉባኤ ብቻ መወሰን ያለበትን ጉዳዮች ከስልጣኑ በወረደው ሰበካ አስተዳደር ጉባኤ ተወስኗል በማለት ሕገ ወጥ ውሳኔ አስተላልፈዋል።

1.      የአስመራጭ ኮሚቴ አመራረጥን ጊዜና ሁኔታ መወሰን፤

2.     የሰበካ አስተዳደር ጉባኤ ሊያስመርጥ የሚያስችል ደንብ በሌለበት ሰበካ አስተዳደር ጉባኤ ማስመረጥ ስለማይቻል ሌላ ሕጋዊ አማራጭ መውሰድን በተመለከተ፤

3.     የአስተዳዳሪውን ምርጫ በተመለከተ፤

4.     ከሁሉም በላይ ደግሞ የቤተ ክርስቲያኗን ንብረት በግል ንብረት ባለቤትነት Legal owners በመሆን በአደራ ይዘው የሚገኙት የHolding Trustees ጉዳይ።

በዚህ መሠረትም በአሁኑ ወቅት ሃብቱን፤ ገንዘቡንና ጉልበቱን መስዋዕት በማድረግ ቤተ ክርስቲያኑን የከፍተኛ ንብረት ባለቤት ያደረገው ሕዝብ የቤተ ክርስቲያኔ ንብረት በምን ሁኔታ ነው የተያዘው? በማን እጅ ነው ያለው? በማለት ጥያቄ እንዳያነሳና ተቃውሞ እንዳይቀሰቀስ አባ ግርማ ከበደ ዘለቄታዊ ጥቅምና ስልጣን ይሰጡኛል በሚሏቸው የወያኔ ጽ/ቤትና በወያኔ ኤምባሲ የቅርብ ደጋፍና ትብብር ፀጉረ ልዉጥ ሰዎችን ወደ ቤተ ክርስቲያን በማምጣት ማንኛቸውንም ነገር እንዲቆጣጠሩና ሌሎች ለአመታት ለቤተ ክርስቲያን ሲጥሩና ሲግሩ የኖሩ አገልጋዮች እንዲገለሉ በማድረግ ላይ ይገኛሉ።

ከላይ ባጭሩ ለመግለጽ በተሞከረው መሠረት ሕዝበ ርስቲያን ለዓመታት ጥሮና ግሮ ለዚህ ያበቃትን የለንደን ደብረጽዮን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን ትላንት በመንገድ ላይ በአጋዚ ጥይት ለተገደሉ ህጻን፤ ወጣትና አዛውንት ጸሎት ለምን ይደርግባታል ብለው ሲያወግዟት የነበሩና የቤተ ክርስቲያኗ ህንፃ እንዳይገዛ አትሽጡላቸው በማለት ለቤተ ክርስቲያኗ ባለቤቶች ማገጃ ያስተላልፉ የነበሩ የወያኔ ወኪሎች እኛው መርጠን የሾምናቸው የአባ ግርማ ከበደና የደጋፊዎቻቸው አጠናካሪ ኃይል በመሆን ቤተ ክርስቲያናችን ውስጥ ሰርገው በመግባት እኛ እርስ በርሳችን በመናቆር ስንዳከምላቸው ቤተ ክርስቲያናችንን እና ሃብትና ንብረቷን ለመረከብ ሲጣደፉ እያየን እኛ የቤተ ክርስቲያኗ አባላት ዝም ማለትም ሆነ በቸልተኝነት መቆም የሞት ሞት ያህል መሆኑን ተገንዝበናል፡፡

በዚህም መሠረት የቤተ ክርስቲያኗ አባላትና ወዳጆች ሁሉ ባንድ ላይ ተሰብስበን ሙሉ ነጻነት ባለውና በሰለጠነ መንገድ ስለ ቤተ ክርስቲያናችን ጉዳይ በመወያየት መሆን ያለበትንና የሌለበትን በሚገባ በመረዳት ከቤተ ክርስቲያናችን እና ከህዝባችን ጎን በመቆም በጋራና በተናጠል የሚጠበቅብንን በሚገባ አውቀን መፈጸም እንድንችል ሁሉንም ነገር በግልጽ መወያየት ስላለብን ምንም ዓይነት ምክንያት ሳያግደን ቀጥሎ በሚዘጋጀው የስብሰባ ቀንና ቦታ በመገኘት ክርስቲያናዊና ኢትዮጵያዊ ግዴታችንን እንወጣ ዘንድ በእመቤታችን በቅድስት ድንግል ማርያም ስም ጥሪአችንን እናቀርባለን።

የርዕሰ አድባራት ለንደን ደብረጽዮን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን ተቆርቋሪ አባላት።

 

ፍትሐት


ፍትሐት -