Monday, 4 August 2025

አቡነ ፋኑኤል የጎረጎሩት ዓሣ ዘንዶ ሆኖ ወጣ!

 አቡነ ፋኑኤል የጎረጎሩት ዓሣ ዘንዶ ሆኖ ወጣ! 

August 2, 2025 

ሐምሌ ፲፱፱ ፳፯፻፯ ዓ.ም. 

መግቢያ 

        አቡነ ፋኑኤል በቨርጂንያ ስቴት አሌክሳንደርያ ከተማ የምትገኘው የሐመረ ኖኅ ኪዳነ ምሕረት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ በነበረዉ በታደሰ ሲሳይ ላይ በሶስት ካህናት የተላለፈውን ዉግዘት ዉድቅ ለማድረግ ሲሉ አቡነ ፋኑኤል የሰጡት የዉሸት ምክንያት የሚቀጥለው ነው። ይህም የአቡነ ፋኑኤልን ዉሸት ዛሬ የትግራይ ቤተክርስቲያንን ገንጥለው በሚመሩት በአባ ሰረቀ ብርሀን “እውነትና ንጋት” በሚል ርዕስ የተጻፈዉን መጽሐፍ እምቅ የሆነውን ታሪካዊ ሂደት እንደገና ቀስቅሶታል። አቡነ ፋኑኤል ሐሰታቸውን በገለፁበት ደብዳቤው ላይ እንዲህ ብለው ጽፈው ነበር። “...ሦስተኛ አስተርአየ ጽጌ ቀድሞ ቄስ የነበሩ ሲሆን በአሁኑ ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት ቀደም ሲል የሰሜን አሜሪካ ሊቀ ጳጳስ በነበሩበት ጊዜ አስተርአየ ጽጌ በሃይማኖት ምክንያት ተወግዘው ክህነታቸው የተያዘ ሆኖ እያለ አሁንም በድፍረት የሚቀድሱ መሆናቸው ሀገር ያወቀው ጉዳይ ሆኖ እያለ አውግዣለው ሲሉ ኃፍረት የማይሰማቸው በመሆኑ ድርጊቱ አሳዛኝ ሀኖ አግኝተዋለን…” የደብዳቤውን ሙሉ ይዘት ለማግኘት የሚቀጥለውን ሰንሰለት ይጫኑ “አባ ፋኑኤል የታደሰ ሲሳይን ውግዘት ስለማንሳት የጻፉት ደብዳቤ"። 

        አቡነ ፋኑኤል ስለ ቀሲስ አስተርአየ ጽጌ ያቀርቡት የሐሰት ሽፋን ከነበረው ሁኔታ ጋር በፍፁም የራቀ ነው። በአጭሩ ጉዳይ እንዲህ ነው። የዉግዘቱ መነሻ በቪርጂኒያ፣ በዲሲና ሜሪላንድ የሚኖረውን ህዝበ ክርስቲያን ያመሰው የታደሰ ሲሳይ ዉድቀት ነበር። በስብሰባው ላይ ተገኝተው ህዝበ ክርስቲያኑ ያቀረበውን የታደሰ ሲሳይን ስህተት ቤተ ክርስቲያናችን በምትመራባቸው መጻህፍት መዝነው ህዝባዊውን ውግዘት ካጸደቁት ቀሳውስት አንዱ ቀሲስ አስተርአየ ናቸው። ቀደም ሲል ከዛሬ 20 ዓመት በፊት መስከረም 22 ቀን 1997 ዓ/ ም (October 2, 2004 CE) በወቅቱ የሰሜን አሜሪካ ሊቀ ጳጳስ በነበሩት በአሁኑ ፓትርያርክ አቡነ ማትያስና በካንሳስ ኪዳነ ምሕረት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ በነበሩት በቀሲስ አስተርአየ ጽጌ መካከል ውዝግብ ተነስቶ ነበር። ይህንን ተከትሎ አቡነ ማትያስ በቀሲስ አስተርአየ ጽጌ ላይ ጊዚያዊ እገዳ አስተላለፉ። የደብዳቤውን ሙሉ ይዘት ለማግኘት የሚቀጥለውን ሰንሰለት ይጫኑ አቡነ ማትያስ ደብዳቤ በቀሲስ አስተርአየ ላይ የጣሉት ጊዚያዊ እገዳ። 

        ያ ዉዝግብ በሊቀ ሊቃውንት ወርቅነህ ሰብሳቢነት ይመራ በነበረው ማህበረ ካህናት ጉባኤ ተመርምሮ የቀሲስ አስተርአየ ትምህርትና እምነት ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ እምነታና አስተምሮ እንዳልወጣ አረጋግጧል። ሙሉ ዉሳኔውንም በአቡነ ጳውሎስ ይመራ ለነበረው ሲኖዶስ ከመረጃዎች ጋር አያይዞ አዲስ አበባ ልኳል። የማህበረ ካህናቱ ጉባኤም ያንኑ ውሳኔ አያይዞ በስደት ለሚገኘውም ሲኖዶስም ልኳል። አቡነ ይስሐቅ ይህንን ተንተርሰው በቀሲስ አስተርአየ ላይ ተጥሎ የነበረውን የ6 ወር ጊዚያው እገዳውን አነሱት። የደብዳቤውን ሙሉ ይዘት ለማግኘት የሚቀጥለውን ሰንሰለት ይጫኑ አቡነ ይስሀቅ ለክንሳስ ህዝብ በላኩበት ወረቀት እግዳው መነሳቱንተረጋግጧል። 

        አቡነ ማትያስ በዘንዘርጡ ዳንኤል ክብረትና ከፈለኝ በሚባለው ቄስ ምክር እየተመሩ በሊቀ ሊቃውንት ወርቅነህ ሰብሳቢነት ይመራ ከነረው ማህበረ ካህናት ጉባኤ ጋር ተጋጩ። በአቡነ ማትያስና በማህበረ ካህናቱ መካከል ከፍተኛ ዉዝግብ ተነስቶ ማህበረ ካህናቱ አቡነ ማትያስን ገስጿቸዋል። በዚህም ምክንያት በአቡነ ማትያስና በማህበረ ካህናቱ መካከል በተነሳው ከፍተኛ ዉዝገብ ዉስጥ አባ ሰረቀ ብርሀን ዋና ተዋናይ ነበሩ። በዚህ ዉዝግብ ከተሳተፉት ዉስጥ በሞት ከተለዩት ከአቡነ ይስሐቅ፣ አቡነ ገብርኤል፣ አቡነ ጳውሎስና መጋቢ አእላፍ መክብብ በስተቀር ሁሉም በሕይወት ለምስክርነት አሉ። በአቡነ ጳውሎስ ይመራ የነበረው ሲኖዶስ በሊቀ ሊቃውንት ወርቅነህ ሲመራ በነረው የካህናት ጉባኤ ዉሳኔ በመስማማት፣ በዳንኤል ክብረትና በከፈለኝ ምክር የሚራመደውን የአቡነ ማትያስን ሃሳብ ዉድቅ አድርጎታል። አቡነ ጳውሎስ አቡነ ማትያስንና ዳንኤል ክብረትን በቃል ገስጿቸዋል። 

        አቡነ ማትያስ በዘንዘርጡ ዳንኤል ክብረትና በከፈለኝ እየተመከሩ የሚያራምዱትን ሀሳብ ባለማቆማቸው አቡነ ጳውሎስም ሊያስቆማቸው ባለመቻላቸው ጉዳዩ የተነሳበት የካንሳስ ኪዳነ ምሕረት የሚቀጥለውን አደረጉ። ይህ የተነሳው ጉዳይ ቤተክርስቲያናችን ጥንታዊት ኦሮዶክሳዊት መሆኗን ከምታረጋግጥባቸው አስተምሮዎች ዋናውና አንዱ ስለሆነ ለአቻዎቿ ለአሕት ባተክርስቲያንና ለባዛንታን ኦርቶዶክስ አብያተ ክርስቲያናት የካንሳስ ኪዳነ ምሕረት ቤተክርስትያን ምዕመናን ጉዳዩን አቀረቡት። አሐት አብያተ ክርስቲያናትም በሊቀ ሊቃውንት ወርቅነህ ሰብሳቢነት ይመራ በነረው ማህበረ ካህናት ጉባኤ ተመርምሮ የተወሰነውና የቀሲስ አስተርአየ ትምህርትና እምነት ከኦርቶዶክስ እምነታና አስተምሮ እንደሆነ አረጋገጡ። እስከዚህ ቅጽበት ድረስ ቀሲስ አስተርአየ ጽጌ በአቡነ ማትያስ የተላለፈባቸውን የ6 ወር ጊዚያዊ እገዳ የተሳሳቱ መሆኑን እየገለፁ እገዳውን በማክበር ወደ ቤተመቅደስ ገብተው ኪዳንም አልደርሱም ቅዳሴ አልቀደሱም። ይህንንም በማድረጋቸው ማህብረ ካህናቱ በጣም አድንቆአቸዋል። 

        አባ ፋኑኤል ግብረ አበራቸውን ታደሰ ሲሳይን ለመሸፈንና ቆሞስ ለማድረግ ሲሉ ይህንን ሁሉ በቅርብ ሆነው እያወቁ እንዳልነበረ አድርገው የተነሳውን ጊዜዊ እገዳ ወደ ዉግዝት ቀይሩት። አቡነ ፋኑኤል ግብረ አበራቸውን ለመሸፈን ብቻ ሲሉ የአቡነ ማትያስን ስም ለስህተታቸው መሸፈኛ ማድረጋቸው የመጨረሻ ሀጥያት ነው። 

        ይህ የአቡነ ፋኑኤል ተደጋጋሚ ሐሰት “እውነትና ንጋት” በሚል ርዕስ በአባ ሰረቀ ስም የታተመችው መጽሐፍ የያዘችውን እምቅ ጉዳይ እንደገና እንዲቀሰቀስ አድርጎታል። ከዚህ ቀደም አቡነ ፋኑኤል የሚያደርጉትን ስህተት እንዲያርሙ የተገሰጹበት አባ ፋኑኤል አዲስ ተክል ናቸው የሚለውን ያንብቡ። 

        ከዚህ ቀጥሎ በ“እውነትና ንጋት” የቀረበውን የመጻህፏን ሐተታ አጠር ባለ መልኩ የቀረበ አስተያየት ስለሆነና አቡነ ፋኑኤል የነኩትን በሚከተሉት ገጾች ላይ ቀርቧል።


እውነትና ንጋት 

        ቅዱስ ጳውሎስ “ወኩሎ ዘተጽህፈ ለተግሳጸ ዚአነ ተጽህፈ” ( ሮሜ ) እንዳለው የተጻፈ ሁሉ ትምህርት የተጠሙት እንዲማሩበት፤ ሰነፎችና የሚስቱ እንዲገሰጹበት ተጻፈ። በየዘመኑና ትውልዱ የተነሱ ችሎታ ያላቸውም ይሁን ችሎታ የሌላቸው ጸሀፊወች በነበሩበት ዘመን ለመጉዳትም ብለው ይሁን ለመጥቀም በብዙ መንገድና በተለያዩ ምክንያቶች ይጽፋሉ። በዚህ ነባራዊ ሂደት ኢትዮጵያ ያለፈችባቸውን ዘመንን የትውልዱን ውድቀትና ትንሳኤ ለማሳየት የተመዘገቡትን ሁሉ ሰብስባ ይዛለች። ሰብስባ የያዘቻቸው መዛግብቶች በተገቢው መንገድ እየተጠቀሱ ጎጅውን ተጎጅውን ለማሳየት ቅዱሳት መጻህፍትን እንደ ምሳሌ ተጠቅማለች። 

        ለምሳሌ፦ መጽሀፍ ቅዱስ የእግዚአብሄርን ከሀሊነትና መጋቢነት ለማድነቅ፤ የሰውን ደግነትና ክፋት ለማሳየት፤ የቃየልና ገዳይነትና የአቤልን ተገዳይነት፤ የሙሴንና የአሮንን ብርታትና ድካም፤ የዳዊትን በጎ ባህርይና ክፉ ባህርይ ጎን ለጎን አስቀምጧል። በሀዲስ ኪዳንም የነጴጥሮስና የነጳውሎስንም ድካምና ብርታት የዲያብሎስም ስእል ሳይቀር እናያለን። 

        ይሁን እንጅ ሳጥናዔል ቃዔል ይሁዳ በቅዱስ መጽሀፍ ተመዘገበው ስለተገኙ ማንም በሳጥናኤል ወይም በቃኤል የሚጠራ የለም። ይህ ሁሉ የተዘጋጀው ለውድቀትና ለውርደት ክፉ ምሳሌ የሆነውን እንድንሸሸው፤ የሚጠቅመውን እንድንከተለው እንድንማርበት ነው። አሳሳች ተግባራቸው የሚታፈርባቸውና የምንሸሻቸው እንጅ ተጽፎ ስለተገኙ እንደምሳሌ የምንኮራባቸው አይደሉም። 

        በታላቁ ቅዱስ መጽሀፍ እንደምናየው፤ በጥንታዊነት ዜግነት ጉዟችን ውስጥ የተፈጸሙትን ውድቀትን ትንሳዔ የሚያሳዩ መዛግብቶች በጥንታዊት ቤተ ክርስቲያናችን በመጽሐፍ በቅኔ በገድል በተአምር መልክ ተጽፈዋል። እነዚህ ሁሉ ከኛ በፊት ባለፈው ዘመን የነበሩት ተከታታይ ትውልዶች ያለፉባቸውን የተጎዳዱባቸውን የተደጋገፉባቸውን የወደቁባቸውንና የተነሱባቸውን እንድናይባቸውና የእግዚአብሄርን ዘላለማዊ ታዳጊነት እንድናደንቅባቸው ተጽፈዋል። 

        በኛ ዘመንም ወያኔዎች በዘረጉልን የጥፋት ጎዳና ያለፍንባቸው ውድቀታችንና ትንሳያችን ለማሳየትም ሆነ ለግል ጥቅም በቤተ ክርስቲያናችን ባብነቱ ትምህርት ያላለፉ ልቅ በሆነ መንገድ እያዘጋጁ ለግል ጥቅም ሸጠው ለመጠቀም ሲሉ በደህናው ዘመን ይደረግ እንደነበረው በሊቃውንት ጉባዔ ሳይጠና ሳይመረመር አቋማቸውን እየቀያየሩ የመዝሙርና የተለያዩ ድርሳናት በመድረስ ቤተ ክርስቲያናችንን አጥለቅልቀዋታል።

        ይህችም አባ ሰረቀ ያሳተሟት የዘገባ ስብስብ በዘመናችን የተከሰቱትን ነገሮች ውድቀታችንን ከምናይባቸው መዛግብቶች አንዷ ናት። 

        ከላይ እንዳልነው ቤተ ክርስቲያናችን ከምትደንቅባቸው ብዙ ነገሮች አንዱ ይህንን የመሳሰሉ ያለፈውን ውድቀት የሚያሳዩንን መዛግብት በግምጃ ቤቷ ሰብስባ በመያዟ ነው። ለተለያዩ ጥቅማ ጥቅም ሲሉ አውቀም ሆነ ሳያውቁ በጉባዔ አባቶች ያላስተማሩን ከውጭ እየለቃቀሙ አሳትመው ለገብያ ያቀረቧቸው በግምጃ ቤታችን በመገኘታቸው ፤ለነገረ መለኮትና ነገረ ማርያም ማስረጃ አድርገው በማቅረብ እራሳቸው ተሳስተው ምእመናንንም ከማሳሳታችን በቀር፤ የተጻፈውን ሁሉ ለትምህርት ለትግሳጽ በእቃ ግምጃ ቤታችን መጠበቃቸው መልካም ነው። 

        ይህች እውነትና ንጋት በሚል ስም የታተመችው መጽህፍ አሳታሚው ለምን ብለው እንዳሳተሙት መርምሮ እንዲደርስበት ለተመልካች እየተውን፤ ያለፍንባቸውን ብዙ ፈተናወች ከሚያሳዩን ብዙ መዛግብቶች አንዷ በመሆኗ እንድንገሰጽባት እንድንታዘብባትባና የገባውን ስህተት እንድናርምባት በውስጧ የያዘቻቸውን ዓበይት ቁም ነገሮች ገጽ በገጽ ለመመልከት እንሞክራለን። 

        ይህችን የመዛግብት ክምችት እውነትና ንጋት በሚል ስም አባ ሠረቀ ብርሃን ወ/ ሳሙኤል ታህሳስ 2004 በMega Printing P.L.C አሳተሟት። በአቡነ ጳውሎስ ዘመን በቤተ ክህነቱ አዳራሽ ተመርቃለች። መጽሀፏ በሶስት ክፍል ተደራጅታለች። ሰፊውንና የመጀመሪውን ውዝግብ የያዘችው ከገጽ 18 እስከ ገጽ 80 ያለው ክፍል ነው። ይህ ክፍል ወያኔ በጠቅላላ ቤተ ክርስቲያናችን ከፈጸማቸው ከብዙ አስተዛዛቢ ነገሮች አንዱን ክስተት ብቻ የያዘች የመዛግብት ክምችት ናት። ይህ የመዛግብት ክምችት ዋሸንግተን ዲስ ቅድስ ማርያም ደብር ቀሲስ ዶ/ ር አማረ በአስተዳዳሪነት ሊቀ ሊቃውንት ወርቅነህ የሃይማኖቱ የበላይ ጠባቂነት ይመሩ በነበሩበት ወቅት የተከሰተውን የመከፋፍያ ደባ የሚያሳይ ነው።

        ወቅቱንና በመዛግብቱ የተጠቀሱትን ሰዎች የእውቀት ችሎታ አቋምና የተልእኳቸውን መሰረት ማመልከት ተገደደ። 

ወቅቱ 

        ያ ወቅት በአቶ መለሰና በእሰየ (ወያኔ) መካከል የቤተ ሰብ መከፋፈል ተከስቶ እርስ በርሳቸው ሲናጎዱ የዋሁን የኢትዮጵያን ህዝብ የእርስ በርስ መታግያቸው የሚዳ ሳር ያደረጉበት ወቅት ነበር። አቡነ ጳውሎስ ከመለሰ ጋራ አቡነ ማትያስ ከእሰየ ጎራ ተሰለፉ። በዚህም ምክንያት“ገደሉን ሳያይ ሳር ብቻ እየተመለከተ ገደል እንደሚገባ በሬ አቡነ ማትያስም በወያኔ ደጋፊነታቸው ላይ የሚያስከትልባቸውን ሳይመለከቱ አቡነ ጳውሎስን “ከመከፋፈል ሌላ ማድረግ የመያውቁ ከፋፋይ” ብለው የዘለፉበት ወቅት ነበር። 

        በዚህ ወቅት በኢትዮጵያውያን መካከል በሰፊው ሲነገር እንደነበረው፦ በአቶ ስብሀት ነጋና በገብረ ኪዳን ደስታ ሰልጥነው ጎንደርን ጎጃምን ሸዋን እየሰለሉ ወያኔን ከምንይልክ ቤተ መንግስት ካስገቡት መነኮሳት መካከል አንዱ አባ ሰረቀ ነበሩ። በውስጥ ያልሆነ ነገር እያነሱ ህዝቡን ይከፋፍሉበት ወቅት ነበር። በአገር ውስጥ የነበራቸውን ተልእኮ ከፈጸሙ በኋለ ወደ አሜሪካ ተሻግረው የውጩን ህዝብ ለመሰለል እንደመጡ ይነገራል። ወደ አሜሪካ መጥተው ቅዱስ ጊዮርጊስ በሚል ስም ቤተ ክርስቲያን መስርተው በስደት ላይ ያለውን ህዝብ በመሰለል ላይ ነበሩ። በዚህ ወቅት የመከፋፈሉ መንፈስ በሰፊው ተሰራጭቶ ሁሉንም ከፈለው። 

        አባ ሰረቀ የመለሰ ደጋፊ ሲሆኑ ከአቡነ ማትያስ ጋራ የሚፋለጡበት ዘመን ነበር። በዚህ ወቅት የማይደግፉትን ጎራ ለማስያዝ ይጣደፉ ነበር። በዚህ ወቅት ህዝቡ የሚከፋፈልበት ትንሽ ነገር እየተከሰተ በአገር ቤት የሚደረገው ሁሉ ወደ ውጭም እየወጣ የተሰደደውን ይከፋፍሉ ነበር። በዚህ ወቅት አንዳንድ ሰወች የቤተ ክርስቲያን አገልጋይ እየመሰሉ ከአዲስ አበባ ወደ ውጭ ይጎርፉ ነበር። 

        ይህች መጽሀፍ ሰብስባ በያዘቻቸው መዛግብቶች የተከሰቱትን የመከፋፍያ ስህተቶች ይዘው ወደከንሳስ የዘለቁት በዲቁና በዘማሪ ስም ከዋናው ካዲስ አበባ የመጡ ነበሩ። “በእንተ ስማ ለማርያም” እያሉ እውቀቱንና ሙያውን እየተማሩ ካደጉት በላይ እናውቃለን የሚሉ ለህዝብ የሚመስል ነገር ፈጠው የማርያም ጠላት ናቸውና አደባድቡን የሚል የመከፋፍያ ሸፍጥ በከንሳስ ኪዳነ ምህረት ቤተ ክርስቲያን ችግር አፈነዳ ። 

        ቀሲስ አስተርአየን መናፍቅ ናቸው የሚል የሀሰት ክስ ማሰራጨት ጀመረ። በጥጉ ያሉትን ሴቶች ዘማሪ ብሎ አደራጀ። እነዚህ ሰዎች በከተማውና በመላ አሜሪካ አሰራጩት። ቀጠሉና ከአቡነ ማትያስ የበለጠ ስለ ቤተ ክርስቲያናችን የሚያውቅ የለምና ይመስክሩልን ብለው ጠሯቸው። አቡነ ማትያስም ከሰንበት ተማሪወች ጋራ በመስማማት፤ የሰንበት ተማሪዎች ትክክል ናቸው ቀሲስ አስተርአየ ክዷል ብለው በማገድ አገልግሎቱን ለለሰንበት ተማሪዎች አስረክበው ወደ መኖሪያ ቤታቸው ተመለሱ። 

        በዘገባው የተጠቀሱት ሰዎች ተልእኳቸው ምን ይመስላል? እነማን ነበሩ? በወያኔ ዘመን ብሄራው አቋማቸው ምንድነው? ። 

        መጽሀፏ አካታ ወደ ያዘቻቸው መዛግብት ዝርዝር ሀተታ ከመግባታችን በፊት በስማቸው ያሳተሟት አባ ሰረቀ ማናቸው? በወያኔ ዘመን ምን አደረጉ? ለምን ወደ አሜሪካ መጡ? ተሰደው ወይስ ተልከው? ወደ አሜሪካ የመጡበት ዘመን ምን ይመስል ነበር? በወያኔወች መካከል ማለት በአቶ እሰየና መለሰ በቤተ ሰብ መካከል ምን ተከሰተ? በአቡነ ማትያስና አቡነ ጳውሎስ መካከል 7 የተከሰተው ድራማ ምን ይመስል ነበር? በአባ ሰረቀና በአባ ማትያስ መካከልስ የነበረው ግንኙነት እንዴት ነበር? የጠቅላላዋ ቤተ ክርስቲያን ይዘት ምን ይመስል ነበር? በእውነትና ንጋት ስም ተሰብስበው በታተሙት መዛግብቶች ውስጥ በተደጋጋሚ የተጠቀሱት ሰዎች እነ ማናቸው? ምን አቋምና ችሎታ ነበራቸው? በቤተ ክርስቲያናችን ውስጥ ያላቸው እውቀትና ችሎታ ምን ያህል ነበር? የተከሰተው ስህተት የማን ነበር? አባ ሰረቀ ለምን ሰብስበው አሳተሙት? ምን አሳሰባቸው? ምን አስገደዳቸው? ለቤተ ክርስቲያን አስበው ነው? ወይስ በግላቸው የመጣባቸውን ችግር ማርገቢያ ለማድረግ? ጥያቄውን እራሳቸውና በወቅቱ የነበሩት የሚመልሱት ነው። 

በመዛግብቱ የተካተቱት 

        የወቅቱን ሁኔታ ከተገነዘብን ወደ ዘገባው ዝርዝር እንሻገራለን። የዘገባውን ዝርዝር ከተረዳን ቤተ ክርስቲያናችን በወያኔዎች የገባችበት አዘቅት እንገነዘባለን። ችግሩ ከገባን ከገባችበት አዘቅት አውጥተን ወደ ነበረችበት አቻወቿ (ኦሬንታል አብያተ ክርስቲያናት) ለመመለስ የሚያቅተን አይኖርም። 

        የመዝገቡ ስብስብ የሰዎችን ድካምና የስርአት የእምነትና የአላማ ጽናት እየገለጠ፤ ቤተ ክርስቲያናችን በምን አይነት ሰዎች አመራር እጅ ላይ እንደወደቀች ያሳያል። ማንም ሰው በቀላሉ ይገነዘብ ዘንድ መጽሀፏ በሰበሰበቻቸው መዛግብት የሚታዩትን በሀሰትን በእውነት መካከል የተካሄደውን ትንቅንቅ ይገልጣል ለጥንካሬና ለጥራት ለሚያዘጋጃት አድማስ ላይ ለመድረስ ለሚደረገው ጥናት ይጠቅማል። ሁለት ተቃራኒ ሀሳብና የእምነት አቋማ ያላቸው ባንድ ጎራ አቡነ ማትያስ በሌላው ጎራ ማህበረ ካህናቱ የተለዋወጧቸውን ሀሳቦች ከዚህ በታች እናቀርባለን። ከአቡነ ማትያስ እንጀምራለን። 

የአቡነ ማትያስና የሰንበት ተማሪወች እምነትና አቋም 

        በብጹእ አቡነ ማትያስና በማህበረ ካህናቱ መካከል የተከሰተው ውዝግብ 33 እስክ 80 ይቀጥላል። አቡነ ማትያስ “እመቤታችንን በተመለከተ የምንከተለው እምነትና ትምህርት እንደሮማ ካቶሊክ ከአዳምና ከሄዋን ውርስ የነጻችው ከመወለዷ በፊት ነው” ይላሉ። ገጽ 39 ይመልከቱ። ቀሲስ አስተርአየ ግን “ቅዳሴ ለመቀደስ ህብስት በጻህል ወይን በጽዋዕ መሰየም አለበት። እመቤታችንም በአዳም በኩል ከነበረው ቁርኝት የተቀደሰችው መጀመሪያ ወደ ህልውና መምጣት ነበረባት” ይላሉ። ገጽ 41 ላይ ይመልከቱ። አቡነ ማትያስ ደግሞ “ቅዳሴ ለመቀደስ ህብስት በጻህል ወይን በጽዋዕ መሰየም አለበት። እመቤታችንም በአዳም በኩል ከነበረው ቁርኝት የተቀደሰችው መጀመሪያ ወደ ህልውና መምጣት ነበረባት በማለታቸው ቀሲስ “ኑፋቄያቸውን በመግለጻቸውና በድፍረት በማስተማራቸው ክህነታቸው ተይዟል” ይላሉ። ገጽ 41 ላይ ይመልከቱ። የቀሲስ አስተርአየ ትምህርትና እምነት ሰምተውት እንደማያውቁ “ይህን ክህደት መቀበል አለብን ነው የቀሲስ አስተርአየ ትምህርት አይገርምም? እያሉ አቡነ ማትያስ ይገረማሉ ገጽ 40 ላይ ይመልከቱ። 

        ከቀሲስ አስተርአየ ደግሞ ምን ይገርመወታል “ይህንን ትምህርትና እምነት ካስተማሩኝ መምህራን የተረከብኩት ሲሆን የመላው ኦርቶዶክስ እምነትና ትምህርት ነው” ይላሉ ገጽ 39 ይመልከቱ። ቀሲስ አስተርአየ ይቀጥሉና፤ “ይህ የነ አቡነ ማትያስ እምነት በ20 አመት ውስጥ የተፈጠረ እምነት እንጅ የተዋህዶ እምነትና አይደለም” ይላሉ። ገጽ 41 ላይ ይመልከቱ። 

        ቀሲስ አስተርአየ በወያኔ ዘመን በሲኖዶሱ ዙሪያ በተሰበሰቡት ጳጳሳት ላይ የሚታየውን ድክመትና ሞራል የለሽነት ታዝበው የተናገሩትን አቡነ “ሲኖዶስ እርስ በርስ የሚደባደብ ነው። አገር የካደ ነው። እንኴን ዶክትሪን ሊያስጠብቅ ሀገርን ማስጠብቅ ያልቻለ ነው” ብለው ባደባባይ ፊት ሲኖዶሱን ተሳድበዋል” ቀሲስ ይህን በመናገር ብቻ አልተወሰኑም፤ “ሊቃውንቱ ሁሉ አፈር በልተዋል። እኔ ብቻ ባሜሪካ እገኛለሁ። ብለው የኢትዮጵያ ኦ ቤ ራሳቸውን ብቻ ሊቅ አድርገው አስቀምጠዋል” እያሉ ቀሲስን ይወቅሳሉ። ይህ ያቡነ ማትያስ ወቀሳ፤ ማህበረ ካህናቱ የቀረበለትን ጉዳይ ከመመልከቱ በፊት የቀሲስ አስተርአየን እድገትና የትምህርት ችሎታ በቤተ ክርስቲያን ያበረከቱትን መመልከት ነበረበትና ቀሲስን ጠየቀ። ቀሲስም ከልጅነታቸው ጀምረው በጉባዔ ትምህርት ብዙ የተማሩ መሆናቸውን በካህናት ማሰልጠኛ ትምህርተ አበ ንስሀና እና አዲሲ የወጣውን ቃለ ዓዋዲ እንዲያስተምሩ የተላኩበትን መረጃ በማቅረብ ያበረከቱትን አስተዋጽኦ፤ የሚያሳይ መረጃ አቀረቡ። ገጽ 32 ላይ ይመልከቱ ። 

        ማህበረ ካህናቱ የቀሲስን ሁኔታ ከተረዳ በኋላ “ቀሲስ አስተርአየ ተራ ሰው አይደሉም የተማሩ ብዙ ያወቁና የሚጽፉ ናቸው። ወደ እልክ የሚያስገባ ነገር ከመጣ ችግሩ ይብሳልና ያስቡበት በማለት አቡነ ማትያስ የሄዱበትን የተሳሳተ መንገድ እንዲያስተካክል ጥያቄ አቀረበላቸው” ገጽ 31 ይመልከቱ። የማህበረ ካህናቱ ጉባዔ “የቀሲስ አስተርአየ ትምህርት ከቅዱሳት መጻህፍት ያልወጣና እምነታቸውም ያልተለየ እንዳልሆነ ተረዳ።” ገጽ 32 ላይ ይመልከቱ። ቀሲስ እምነታቸውና ትምህርታቸው ከጥንታዊት ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያናችን ትምህርትና እምነት ላይ በጽኑዕ የተመሰረተ ንደሆነ እያመኑና 0ፕ[የሰንበት ተማሪወችና ያቡነ ማትያስ እምነትና ትምህርት የተሳሳተና በስህተት ያገዷቸው እንደሆነ እየመሰከሩ፤ ለአናርኪነት ምሳሌ ላለመሆን የአቡነ ማትያስን እገዳ አክብረው መቀበላቸው ጉባዔውን አስገርሞታል። ገጽ 41 ላይ ይመልከቱ። 

የማህበረ ካህናቱ እምነትና አቋም 

ከገጽ 56 እስከ 66 ባሉት ገጾች ላይ የሰፈሩት መዛግብቶች እንደሚያመለክቱት ማህበረ ካህናቱ አቡነ ማትያስን እንደተሳሳቱ ተገነዘበ። ማህበረ ካህናቱ አቡነ ማትያስን “የተሳሳቱት እርሰዎ እንጅ ቀሲስ አስተርአየ አይደሉም። ከንሳስ ላይ የፈጸሙትን የተሳሳተ እገዳ ያንሱ” አላቸው። አቡነ ማትያስ ስህተታቸውን ከመቀበል ይልቅ “ቀሲስ ተሳስቻለሁ ከአሁን በኋላም ይህንን የተሳሳተ ትምህርት አላስተምርም ብለው ይቅርታ እንዲጠይቁ ማድረጉ ይቀላል” ብለው የማህበረ ካህናቱን ጥያቄ አልተቀበሉትም ገጽ 42 ይመልከቱ።

        ማህበረ ካህናቱ የቀሲስ አስተርአየን እድገትና የትምህርት ችሎታ በቤተ ክርስቲያን ያበረከቱትን መመልከት ነበረበትና ቀሲስ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሊቃውንት ተቀርጸው ያደጉና፤ በካህናት ማሰልጠኛም አዲሲ የወጣውን ቃለ ዓዋዲ እና ትምህርተ አበ ንስሀ እንዲያስተምሩ የተላኩበትን መረጃ በማቅረብ የኦርቶዶክስ ጥንተ ትምህርት እንደነበረ ማህበረ ካህናቱ ተመለከተ” ገጽ 32 ላይ ይመልከቱ። ወደ ዝርዝር በመግባት ውዝግቡን ተመለከተ ። “ካህኑ ተራ ሰው አይደሉም የተማሩ ብዙያወቁ ያወቁና የሚጽፉ ናቸው። ወደ እልክ የሚያስገባ ነገር ከመጣ ችግሩ ይብሳልና ያስቡበት በማለት አቀረበላቸው” ገጽ 31 ላይ ይመልከቱ ። የቀሲስ አስተርአየ ትምህርት ከቅዱሳት መጻህፍት ያልወጣና እምነታ ቸውም ያልተለየ እንዳልሆነ ጉባዔው ተረዳ ገጽ 32 ላይ ይመልከቱ። 

        አቡነ ማትያስ ጉዳዩን በቀሲስ ላይ አክብደው ለማቅረብ “ይህ እምነት በ20 አመት ውስጥ የተፈጠረ እምነት እንጅ የተዋህዶ እምነትና አይደለም። ሲኖዶስ እርስ በርስ የሚደባደብ ነው። አገር የካደ ነው። ስንኴን ዶክትሪን ሊያስጠብቅ ሀገርን ማስጠብቅ ያልቻለ ነው ብለው ባደባባይ ፊት ተሳድበዋል” የሚል በቀሲስ ላይ ሌላ ተጨማሪ ክስ ፈጠሩ ገጽ 41 ላይ መልከቱ። አቡነ ማትያስ “በ20 አመት ውስጥ የተፈጠረ እምነት እንጅ የተዋህዶ እምነትና አይደለም“ ላሉት አቡነ ማትያስ የሰጡትን “በሞት የተለዩት ሊቃውንት በሊቃውንት ተተክተዋል። በህይወት ያሉት ሊቃውንት የቀድሞዎችን ጽኁፎች የሚተኩ ሌሎች መጻህፍት ጽፈው ያበረከቱ መሆናቸውን መረዳት እጅግ አስፈላጊ ይመስለናል” የሚል መልስ ሰጡ ገጽ 42 ይመልከቱ። 

        ከማህበረ ካህናቱ ለቀረበላቸው ጥያቄ በመመለስ ፋንታ አቡነ ማትያስ “ማህበረ ካህናቱ የይግባኝ ሰሚነቱን ስልጣን ከየት አገኘው? በየትኛው ስርአተ ቤተክር ስቲያን መሰረት ነው” የሚል መልስ ሰጡ ገጽ 37 ላይ ይመልከቱ። 

        በማለታቸው ማህበረ ካህናቱም “በዚህ አባባልዎ አንድ ጳጳስ እንደፈለገው ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን የጻፏቸውን መጻህትና ለረዥም ዘመናት ቤተ ክርስቲያን አምናበት የኖረችውን እምነት መሻር መለወጥ ይችላል ማንም ሊቃወመው አይገባም ማለተዎ ነውን? የነገረ ሃይማኖት ውሳኔ ባንድ ጳጳስ ብቻ እንዲወሰን የታዘዘው በየትኛው ህገ ቤተ ክርስቲያን ነው? እነዚህን ጥያቄዎች እንዲመልሱልን ተስፋ እናደርጋለን“ የሚልስ ሰጣቸው። ገጽ 50 ይመልከቱ። 

        የቀሲስ አስተርአየ አቋም ኦርቶዶክሳዊ በመሆኑና የአቡነ ማትያስን እምነትና አቋም ከኦርቶዶክስ ክልል የወጣ በመሆኑ ማህበረ ካህናቱ ከአቡነ ማትያስ ቱ ጋራ ተጋጩ ከገጽ 46 እስከ ገጽ 54 ያሉት ዘገባዎች ይመልከቱ። 

        በመጨረሻም አቡነ ገብርኤል “እንደ እውነቱ ከሆነ ስለ ድንግል ማርያም ያለን እምነት በተመለከተ ከእስክንድርያ ስርአተ ትምህርትና እምነት ባንለይ እጅግ መልካም ነው። ካልሆነ ከኦሬንታል አብያተ ክርስቲያናት መለየትን ያስከትላል።” ከመወለዷ በፊት ቅዱስ ገብርል ወይም ራሱ መንፈ ቅዱስ አነጻት ካልን እናትና አባቷን አንጽቷቸዋል ወደ ማለት ያደርሳል” ብለው በጽሁፍ ገለጹ ገጽ 67 ላይ ይመልከቱ ። 

        “ቤተ ክርስቲያንና አማራውን ሰበርኩት” እያለ ለ27 አመታት የመከፋፍያ ምክንያት እየፈጠረ ሲከፋፍል እንደኖረና የገቡ ስህተቶች እንዲታረሙ የሁሉም ሀላፊነት እንደሆነ ለማሳሰብ ይረዳል። 

        አባ ሰረቀ ማሳተማቸው መልካም ቢሆንም፤ ከማህበረ ቅዱሳን ጋራ በሌላ ነገር በተጋጩበት ወቅት ማሳተማቸው ሌላ ጫጫታ ለመፍጠር እንጅ የገባው ስህተት ባለመታረሙ አሳስቧቸው እንዳልነበረ ታዛቢወች ይናገራሉ። አቡነ ጳውሎስ ሞተው አባ ማትያስ በቦታው መተካታቸውን ቢያውቁ ኖሮ ማሳተም ቀርቶ መዛግብቱን ያጠፏቸው ነበር” ይላሉ። 

(ይኸ መጣጥፍ፣ የብሎገሩ ሀሳብ ሳይሆን፣ የደራሲዎቹ ሀሳብ ነው። በውስጡ ያሉትን ሀሳቦች፣ ለመጠየቅም ሆነ ለመሞገት ከተፈለገ፡Abunepetros1928@gmail.com ደራሲዎቹን መጠየቅ ይቻላል) 

        የወያኔ የጥፋት ዘመን በማለፍና በዮዲት፤ በግራኝ መሀመድና በጣሊያን ወደ ተሰበሰበው የታሪክ ቌት እየገባ ነው። “እውነትና ንጋት” በሚል ርእስ የታተመች ይህች የመዛግብት ስብስብም፤ የወያኔን ዘመነ ሙስና የሚቀጥለው ትውልድ የሚያስብባቸው ብዙ የታሪክ መዘክሮች አንዷ ወደ መሆን ትሻገራለች።

(መጣጥፉ የብሎገሩ ሳይሆን የደራሲዎቹ ነው። ደራሲዎቹን ማግኘት ለሚፈልግ፥ በኢሜል፥

Abunepetros1928@gmail.com

ማግኘት ይቻላል።)

Sunday, 3 August 2025

AN OPEN LETTER TO THE NAACP- written in 1998

WHY DO “ERITREANS” WANT TO BECOME MEMBERS OF THE NATIONAL ASSOCIATION FOR THE ADVANCEMENT OF COLORED PEOPLE (NAACP)? 
AN OPEN LETTER TO THE NAACP! 
 
By Wondimu Mekonnen London, UK 

Beware of the wolf in sheepskin! 




Almost the entire educated population of Africa knows of the sacrifices our brothers and sisters in America have made in their struggle to liberate themselves, first from the direct bondage of slavery, and then, after achieving that tremendous objective, from the ravages of inequality and injustice. Malcolm X, Martin Luther King, … and many others are household names of African youth. You, our brothers and sisters in America, have sacrificed so much to turn America from the graveyard of the blackman into a safe haven for the persecuted. We, in Ethiopia, are proud of you! 

 In the history of your struggle for freedom and equality, Ethiopia occupies a special place. Why is that? We all know the reason. When you were persecuted for being “black” in America, as “ the Negro”, your brothers and sisters in Africa were also taken hostage by the same kinds of people. The mighty European force, which came first with a Bible preaching Christ, a White Christ, and after stealing the people’s hearts and minds, later, with a gun to steal their land and pride, failed when it reached Ethiopia. When they attempted to come in with their perverted Gospel, a living, true Bible awaited them, humbling them with the knowledge that we Ethiopians had first known Christ while Europeans were still dwelling in Caves. They could not bring us, the Ethiopian people, their new God, for the God they sought to preach was alive in Ethiopia and by then had dwelt there for one and a half millennia. The gun could only come through the road torn open by their perverted Gospel. Ethiopia had kept holy the original Bible and its message of loving kindness, and she fought back steadfastly, refusing to accept their tainted Gospel, for the Living Word of God is a two-edged sword in the hands of the faithful. Therefore, they went about wreaking havoc until they had subjugated all of our Black brothers and sisters, all except our small corner of Africa, where we, the original Ethiopians, survived unconquered. 

From that part of Africa, the Horn of Africa, the light of freedom for all Africans continued to flicker, no matter how weak and dim it might have become. All the conquerors, who tried to subdue Ethiopia, one by one, failed and failed utterly to subjugate these last defiant black people. First, the Ottoman Turks attempted to conquer Ethiopia. Ethiopia lost a great deal of land and people to the Turks, but she stood her ground on the very soil that is still her home today, including the land recently rechristened "Eritrea". Then the Portuguese came. They too badly failed. The English were the last but one to nearly occupy her. Yet the invaders soon realised that administering Ethiopia was an impossibility, unleashing a disaster of unprecedented magnitude. They left in peace. All learned their lessons bitterly and in the end left her alone. Finally, one more macho gangster by the proud name of Italy cast its eyes on these freedom-loving people and this beautiful, holy black land. 

The first bitter pill the black man forced Italians to drink took place in 1887 at Dogali, not very far from the present Port of Massawa. At this spot, the invincibility of the adventurist European race was proven as vulnerable as that of any mortal human being, at the hands of an Ethiopian Ras, Alula Aba Nega. An entire contingent of the Italian army, armed to the teeth, was wiped out, leaving only eight people to escape and tell the tale. This event was not considered by the Italians as the victory of courageous Ethiopians, but as the horror of their soldiers being devoured by wild animals. There were cries of outrage, mourning, and gnashing of teeth in Rome, where everyone demanded vengeance. Yet vengeance was not that easy against Ethiopians – The Africans! 

The death of Emperor Yohannes IV gave rise to a period of confusion among Ethiopians. The Europeans were giving arms to each rival group of contenders to the throne and waiting for the right time to strike. It was during this period, in August 1889, that for the first time, Asmara was sacrificed to the occupant white race from Europe. There was no one to guard the city, for everyone was busy holding onto the reins of leadership. It was too late to save Asmara. The Italians quickly settled into dismantling every trace of “Ethiopianness” from the hearts and minds of our people of the Red Sea Coast. Immediately, they changed the name of the newly acquired territory from Behir Medri to "Eritrea." They then launched their psychological warfare against the rest of the Ethiopians. They ruled over the people with a heavy hand and bred among them ignorance and forgetfulness. No Ethiopian in “Eritrea” was allowed to learn beyond the Fourth Grade. Many escaped to the Southern free land and obtained their educations there. The rest were subdued and dehumanized into mindless animals. 

After settling well in Asmara, the Italians used Eritrea as a stepping stone for launching their heavy assault on the remaining territory of Ethiopia to finalize their dream of uniting their ill-gotten Italian territories from Eritrea to Somalia. Menelik, the Warrior King, arose with his people and devastated the power of the “Mighty Whiteman from Europe” once again, in March 1896. This victory opened the eyes and minds of our brothers and sisters under subjugation in Africa. From horizon to horizon, the Victory of Adwa was engraved in the minds of our brothers and sisters. 

From this moment onward, resistance against colonialism mushroomed throughout Africa. Our brothers and sisters in America rejoiced more than anyone else. That was why Ethiopian Orthodox Churches, Abyssinian Baptist Churches, and Ethiopian Methodist Churches everywhere became established and remain well-known to all members of the National Association for the Advancement of Colored Peoples (NAACP.) I come before you now only to invoke your memories. The mischief of the colonialists did not stop there. Although Italy was deterred from penetrating into the deeper heart of the Blackman’s Holy Land, Menelik and his men were unable to push the wretched oppressors into the Red Sea. The reasons reside in the historic fact that the Italians had earlier introduced new human and cattle diseases into Ethiopia, including rinderpest, which had badly hurt our nation. Forcing the Italians to sign capitulation papers and exacting from them a vow never again to try, Menelik left them in "Eritrea." 

However, from that moment on, the Italians began their strategy of avenging Dogali and seeking revenge for their humiliation in Adwa. For the next 40 years, they varied their tactics. They began by working with the local people. They recruited the ignorant and rejected of our subjugated people, those degenerated and humiliated in our lost territories, and refashioned them into Askaris, "local soldiers." This includes kids, which were called "Belilas"


When they grew up, they were called "Askaris". 
They trained these Askaris, both physically and psychologically brainwashing them, to hate their blood brothers in the South. These Askaris thought the blue-eyed Romans that administered them were angels who fed them when happy, and destroyed them when angry. 

The Italians stockpiled weapons of mass destruction, tanks, planes and all modern weaponry to launch their assault against Ethiopia once more in 1935. Our Ethiopian brothers forgot their roots and fought for the colonialist Whiteman against their own people, like mad dogs in service to their Italian masters. The Italians rained down nerve gas by planes from the sky and assaulted us with rocket propellers and grenades from the land. Temporarily, the Italians gained the upper hand with war tactics cowardly planned and inhumanly executed. The last, defiant black nation stood at risk of falling. This moment marked a significant solidarity of “coloured people” across the globe in support of the heroic Ethiopians. Especially our African American brothers and sisters in the US and the Caribbean islands identified themselves with Ethiopians. This was a time many African Americans volunteered to fight for Ethiopia and to die an honourable death alongside their brothers and sisters.
They did so gloriously! They contributed money and fought the Ethiopian war in their own way. Ironically, the majority of the Italian forces who were massacring our people were the newly created Eritrean Askaris. That was the worst pain Ethiopia had to endure. What can you do when your brother becomes your enemy's servant and shoots to kill you? With the help of God and the invincible spirit of Ethiopia, together with the British army and African American support, within five years that ordeal was over. This time, despite their nerve gas and barbaric cruelty, crimes not yet accounted for, despite their sycophant Askaris, the Italians were driven out for good, not only from Ethiopia, but also from the territory they had occupied for 70 years, from “Eritrea.” 

After bitter diplomatic battles with the British, the land and the people were reunited with joy, hoping to become one happy family once more in 1952. 

Alas, the Whiteman left the territory only after burying a time bomb. After the last and decisive victory over the occupying Italians, a question remained: What was to be done with the Askaris. Emperor Haile Sellassie I and his men, ardent Christians, chose the path of reconciliation and forgiveness, in understanding of the conditions under which these people were used by the forces of the occupying enemy. Therefore, no punishment was brought upon a single Askari for the crimes committed against their blood brothers and sisters, forgiving crimes against humanity that involved even mass genocide. The “Eritreans” became once more Ethiopians, without even converting their place names back to their original African forms. They lived everywhere within Ethiopia. They prospered. 

To keep the lost and regained territory, at least economically, at the same level as the Italians left it - although the economic benefit was always for the Italians and never for the local people under occupation - the Emperor pumped every meagre resource into Eritrea. The best schools were opened and Eritreans got the best educations, while the rest of Ethiopia was still illiterate. The best hospitals were built in Eritrea, while millions died of malaria and other curable disease elsewhere in Ethiopia. 

All these benefits failed to win the appreciation and loyalty of the Askaris. They developed a perverted nostalgia for serving their white masters. They continued to rebel against Ethiopia for no reason. They secretly entered into alliances with the enemies of Ethiopia. They stealthily worked at it day and night, forging again the old, Italian grand plans of destruction for Ethiopia. To this very day, they are working towards that goal, and will not rest until they have achieved that final, wicked goal. 

One of the main aims of the children and grand children of the Askaris is the defamation of the struggle Ethiopia waged against colonialism. They desecrated our Ethiopian history and heritage wherever they went. But, what is to be expected from such "Uncle Tom" servants? They are hypnotized and controlled. We often cannot but feel sorry for them. They found sympathisers within Ethiopia and managed to overthrow the military regime following Emperor Haile Sellassie I. They found a regime that would accept carrying out Mussolini’s plans for Ethiopia. They executed these plans to every detail through their chosen puppet regime in Ethiopia. As for themselves, they declared independence and started building their “Piccola Roma.” 

Then on 06 May 1998, however, they have fallen out with their puppet regime in Ethiopia, who refused to accept their orders any longer. With a very lame excuse for conflict, a mythical “Colonial Border”, they opened war over our remaining people, killing tens of thousands and displacing hundreds of thousands of Ethiopians. They are still at it when this open letter is written. To begin with, their question of “respect for colonial borders” is a disgrace to the black race. Ethiopia had never signed into existence any such colonial border with the European invaders. Why should she now be bogged down with their Askari arguments today? 

Recently, I was horrified to learn that the same children of the Askaris who had migrated to America have decided to join one of the sacred communities of the African Diaspora, The National Association for the Advancement of Colored Peoples (NAACP). One wonders, why they might have wanted to do that? The very people who had rejected their own African heritage, the very people who had fought so vigorously to become members of the Arab League, are now pretending to be honourable Blackmen in order to qualify for membership in the NAACP! It might have been acceptable to affiliate with this distinguished and sacred society on an individual basis, but why as a group? Given their idolatrous worship of a Whiteman, what is the purpose of their interest in becoming members of an organisation sworn to fight the injustice of domination by one race over another? 

For many Ethiopians and other Africans, who know the so-called “Eritreans,” it is an open secret. They seek to become part of you just as they became part of Ethiopia, and to work from within you, to eat you like a cancer from the inside out, and destroy your historic solidarity with Ethiopia. I personally protest as a free and proud African against their admission into your sacred society, for I know the underling motivation of this group purportedly seeking your friendship. They are in fact your deadly enemies. 

 I urge you to exercise caution. I implore you to safeguard this wonderful society of and for our African American brothers and sisters. Launch your own research. Find out the validity of my claims for yourselves before admitting this group, who target you for evil motives. Discover and reveal the true motivation behind this sinister move by these so-called “Eritreans”. When you face the truth, you too will be horrified just as I am in this moment forced to write this open letter to warn you. Demand answers to the question: If becoming members of the NAACP is so important to them, why only now, when their leadership is engaged in a life and death struggle to destroy the remaining part of Ethiopia? If their intentions are genuine and pure, you have nothing to lose in patiently awaiting an end to this war. And, in truth, you will yet see who they really are.

Beware of the wolf in the sheep-skin! 
ETHIOPIA REACHES HER HANDS UNTO GOD! 

PS: Dear Web readers, Please forward this open letter of mine to whom it may concern in the NAACP. Thank you very much for your co-operation 

CC: NAACCP National Headquarters 
       4805 Mt. Hope Drive 
       Baltimore, MD 21215Mbr 
       Tel. (410) 358-8900 NAACP 

       Branch Office in Los Angles area
      3910 Martin Luther King Jr. Blvd. 
      Suite 202 Los Angeles, 
      Calif. 90008 
      Phone: (323) 296-2630

Thursday, 16 January 2025

ከተዘራ ያልታረመ አንደበት

 ከተዘራ ያልታረመ አንደበት

የጠቅላይ ሚኒስትሩ አነጋጋሪ ንግግሮች

“በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ፤ ኃጢአተኛ በፊቴ በተቃወመኝ ጊዜ በአፌ ላይ ጠባቂ አኖራለሁ።”

መዝሙረ ዳዊት 39:1

 

ኢል ዱቼ ዐቢይ አህመደ አሊኢ

ወንድሙ መኰንን ኢንግላንድ 15 January 2025

 መግቢያ

የአገር መሪ፣ በስሜታዊነት እንዳመጣለት አይዘረግፍም። እያንዳንዷ ንግግሩ እየተሰነጠቀች ትታይበታለች። ንግግሩ ቁጥብ መሆን አለበት። ጥሩ ከተናገረ፣ እንደ ኦባማ፣ ታሪካዊ ንግግር ሆኖ ሲወሳለት ይኖራል። ከዘበዘበ መዘባበቻ ይሆናል። አንድ የአገር መሪ ብቃቱ የሚለካው፣ በተግባሩ ብቻ ሳይሆን፣ በምግባሩ፣ በኑሮው፣ በሥነ-ሥርዓቱ፣ በዕውቀቱና በአነጋገሩ ጭምር ነው። እነዚህ ክህሎቶች የሚዳብሩት ደግሞ ከተፈጥሮ ችሎታ ባሻገር፣ በትምህርት፣ በልምድ፣ በዕድሜና፣ እንዲሁም በዙሪያው በከበቡት ችሎታ፣ ዕውቀትና ብስለት ባዳበሩ ባለሙያ አማካሪዎቹ ነው። የበሰለ መሪ፣ የበሰሉትንና አስተዋይ አማካሪዎችን ይሰበስባል። ያልበሰለ መሪ ግን፣ እንደሱ እንጭጮችንና እበላ ባይ አማካሪዎችን ይሰበስባል። ለምሳሌ በመጽሐፍ ቅዱስ፣ ሮብዓም የተባለ እንጭጭ በነገሠ ጊዜ በአባቱ በንጉሥ ሰሎሞን ፊት ይቆሙ የነበሩትን አስተዋይ አዛውንቶችን ትቶ እንደሱ ባሉ ባልበሰሉ ወጠጤ ጎረምሳዎች በመከበቡ እስራኤል ለሁለት የመከፈል አደጋ ደረሰባት (መጽሐፍ-ቅዱስ)። ኢትዮጵያስ ለስንት ትከፈል ይሆን?

በአብዛኛው በአደጉት ታላላቅ አገሮች፣ በሆነ ተአምር ካልሆነ በስተቀር፣ ሁልጊዜም ለአገር መሪነት የሚመረጠው፣ ምራቁን ዋጥ ያደረገ፣ ከጀርባው ብዙ አዎንታዊ ተግባራትን የፈጸመ፣ ለአገሩ በተሰለፈበት መስክ ተጨባጭ ሥራ የሠራ መሆን ይጠበቅበታል። ለምሳሌ፣ አሜሪካን ብንወስድ በዕድሜ የመጨረሻ ትንሹ ፕረዝደንት፣ ሩዝቨልት (Theodore Roosevelt 1909-1913) ሲሆን ፕረደዝንት የሆነው፣ 42 ዓመቱ በአጋጣሚ ነበር። የጦር አመራር ጀግናም ነበር። ለዚህ ከፍተኛ ሹመት የበቃው፣ ፕረዝደንት ዊሊያም ማኪንሌይ (William McKinley 1897-1901) በነፍሰ-ገዳይ ጥይት ሕይወቱ ስላለፈ ምክትሉ መተካት ነበረበት። ታስቦ የነበረው ይኽ የጦር ጀግና ጎልማሳ በምክትልነት ቆይቶ የፕሬዝደንቱ የሥራ ጊዜ ሲያልቅ፣ ሰክኖ፣ ልምድ አካብቶ፣ በራሱ ተወዳድሮ ካሸነፈ ፕረዝደንት ይሆናል ተብሎ ሲጠበቅ ዕድል የራሷን መንገድ ቀይሰችለትና በአቋራጭ ሩዝቨልት ፕረዝደንት ሆነ። ቢሆንም የከበቡት አማካሪዎች ምራቅ የዋጡና አንቱ የሚባሉ ስለነበሩ፣ አንዳችም ከነሱ ምክር ወጥቶየፈጸመው ተግባር አልነበረም። የመጨረሻው ከፍተኛ ዕድሜ የነበረው አሁን ሥልጣን ላይ የሚገኘው ፕርዝደንት ጆ ባይደን ነው (Joe Biden 2021 - incumbent)። ሥልጣን ላይ የወጣው በ78 ዓመቱ ነው። በሚመጣው 20 January 2025 ለሁለተኛ ጊዜ ሥልጣን ላይ ሊቀመጥ የተመረጠው ትራምፕ (Donald Trump) በዓለ ሲመቱ ሲጀምር 78 ዓመት ከ6 ወር ይሞላውና ከባይደን ሊበልጥ ይችላል። በእኛና አፍሪካ አገሮች ግን ያልበሰሉ ጎረምሶች፣ በየጊዜውሥልጣን ላይ እየወጡ፣ አገራቸውን ያምቦጫርቃሉ። ልጅ ያቦካው ለእራት አይበቃም ይባል የለ? ለዚህ ነው የማያልፍልን።

ጠቅላይ ሚኒስትራችን ዳግማዊ ጠቅላይ ሥቃይ ሁኖ ቁጭ ብሏል። ያኔ በወረት መስማት የምንፈልገውን እያወራ ሲመጣ፣ ወያኔ የጫነችብንን የዘረኝነት ቀንበር ይሰብርልናል ብለን ስንጠብቅ፣ የባሰውኑ የኦሮሙማ የጭቆና የገዳ ሥርዓት ቀንበር ደረበብን። ወያኔ በዘር ከፋፈለችን፣ እሱ ደግሞ በ16ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ጭንቅላት የሚያስቡትን የኦሮሙማን የበላይነት ቀንበር በህዝቡ ላይ ጫነ። በመግደል፣ በማፈናቀል፣ በማሳደድ፣ በማሠር፣ በማንገላታት ብቻ ሳይሆን፣ አንድ ሰው ጥሮ ግሮ፣ ላቡን አንጠፍጥፎ ሠርቶ ወይም ገዝቶ የኖረበትን ቤት ሳይቀር በላዩ ላይ በማፍረስ፣ ቦታውን ለሚወደው የኦሮሙማ አቀንቃኝ  ሸልሞ፣ ህዝቡን ጎዳና ተዳዳሪ አደረገው። እንደመጣ ኢትዮጵያዊ ሊመስል ሞክሮ ነበር። እየዋለ ሲያድር ግን፣ ከኦነጎችም የከፋ በራሱ ፍቅር የወደቀ ናርሲስት (narcissist) ሁኖት አረፈው።

ከአያያዝ ይቀደዳል፣ ከአነጋገር ይፈረዳል።

አንድ ብልህ መሪ አብዛኛውን ጊዜ የሚናገረውን፣ መጥነው፣ መዝነው የሚጽፉለት ሊኖሩት ይገባል። ከአያያዝ ይቀደዳል፣ ከአነጋገር ይፈረዳል ይባል የለ? በእንግሊዝኛው “Speech Writers” ይኖሩታል። ትልቅ ሹመት ነው። የአገር መሪ  ሲናገር ፈጽሞ መዘባረቅ የለበትም። ስለዚህ ባለሙያዎች (professionals) ሊቀጠሩለት ይገባል። የራሱን እንኳን ንግግር ማድረግ ሲፈልግ፣ ሊያቀርብ ያሰበውን አሳይቷቸው፣ አስተካክለው ይሰጡታል።  የሌሎችን ሀሳብ እንዴት መጠቀም እንዳለበት ያስተካክሉለታል። አለበለዚያ “ኮራጅ” እየተባለ ጣት ይቀሰርበታል። ለዚህ አልታልደንም። ሰውዬው አመዛዝኖ መናገር አይችልም። አሁን የተናገረውን፣ ከ10 ደቂቃ በኋላ አይደግመውም። በዚህ ምክንያት የሚከተሉትን ለናሙና 10 የተመረጡ ዝብርቅርቅ ንግግሮቹ እንዴት መዘባበቻ እንዳደረጉት እንመልከት። ኩረጃውን ለጊዜው እንርሳ! ማዋረዴ አይደለም። ድንገት ቢታረም ተግሳጽ ነው። ለሚፈልግ፣ የአሥሩም ቪዲዮዎች አሉኝና ጠይቁኝ ላጋራ እችላለሁ።

1) የሕልም እንጀራ!

በሕልም ዓለም ቅዠት፣ እየተጋገረ

ወፋፍራም እንጀራን፣ እንልፈው ጀመር።

ወፍራም የዐቢይ የሕልም እንጀራ


ድሀ በህልሙ ቅቤ ባይጠጣ እከክ በወረሰው ነበር። ይላል ያገራችን ሰው። ነዳጅ ድፍድፍ ተገኘ ጨፍሩ አሉን። እንኳን ነዳጅ ድፍድፍ ሽታውም አልነበረም። ኢትዮጵያ በስንዴ ምርት እራሷን ቻለች፣ ደንሱ አሉን። ከተመረተ በኋላ፣ ስንዴው ለውጭ አገር ሺያጭ የሚቀርብ ሁኖ ተገኘ። ከተመጽዋችነት ሳንወጣ ቀረን። አንድ ሰሞን ደግሞ፣ አሰብ የኛ ሆነች ተባለና፣ እስክስታ ውረዱ ተባልን። እንደተወራ ቀረ። ከሶማሌ ላንድ ወደብ ተሰጠን ተባልን ኧረ እሱ ነገር ህጋዊ አይደለም፣ ጣጣ ውስጥ አገሪቱን ይከታል አልን።”የመከላከያ ተሸላሚ የክብር አባላት” ዩ-ትዩበሮች እና ደንገጡሮቻቸው፣ ያዙን ልቀቁን፣ ወደብ አገኘን፣ ደስ ሲላችሁ ሲገባ እንዴት በአገራችሁ ላይ ትመቀኛላችሁ?” ብለው ድረ-ገጾችን አጣበቧቸው። ትንሽም ሳንቆይ ያልነው ደረሰ። ወፍ የለ፣ ወደብ የለ። በዓለም አቀፍ መድረክ መዘባበቻ ሆን። ጦርነት አንዣበበ፣ ቀኝ ኋላ መዞር መጣ። ይኸ አሳፋሪ ተግባር እንዴት ይሸፈን? የማያፍረው ጠቅላይ ሚኒስትር ታዲያ አሰበበትና በማይመስል ትርክት መጣ። ፊቱን በጨው አጥቦ ያለምንም ማፈር፣ ለአሻንጉሊቶቹ የፓርላማ ኣባላት ጥፋቱን ወደኛ አዙሮ ቁጭ አለ።

ህልም የሌላቸው የሚቃዡ ሰዎች ምን ይላሉ? ይኸውና ቀይ ባህር እናሳካለን ብለው ዓመት ሞላ ሳይሳካ ይላሉ! እኛ እኮ እንኳን በዓመት፣ በሀያ ዓመት ባይሳካም ልጆቻችን ያሳኩታል ነው ያልናቸው። አይሰሙም! ለምን? ህልም አያውቁማ!”

“ቀጣፊ!” ልለው አሰብኩና የአገሬ መሪ መባሉ ትዝ ሲለኝ፣ አፌ ላይ አድርሼ መለስኩት። ምክንያቱም፣ “በኢትዮጵያ እንደኔ የተሰደበ መሪ የለም” ብሎ ስሞታ ሲናገር ሰምቼ አዝኘለት ነዋ! ዝም ባለ አፍ እኮ፣ ዝምብ አይገባበትም!ይባላል። በቃ አልተሳካም ብሎ ዝም ቢልስ! ሆነልኝ ብሎ ታምቡር ካስመታ በኋላ፣ “ከሀያ ዓመት በኋላ ነው ያልኩት”፣ ከሚለን አፉን ዘግቶ፣ እንደልማዱ ወደ ችግኝ ወደ መትከሉ ቢሄድ ያዘናጋን ነበር። ባህር በር ተገኘ አይደል እንዴ የተባልነው። ሾርት ሚሞሪ ነበር ያለን?

ስለጠቅላይ ምንስትሩ ህልም ሳስብ፣ አንድ ሰው የተገጠመው ግጥም ትዝ አለኝ።

ስስምሽ ስላደርኩ፥ ትላንት በህልሜ፣

ዛሬ ቶሎ ተኛሁ፥ ልሰምሽ ደግሜ።

ታዲያ ምን ያደርጋል!

የህልሜ ደራሲ፥ አትታደል ቢለኝ፣

ህልሜን ገለባብጦ፥ ሲስሙሽ አሳየኝ።

 

አንድ ሰው ለማለም መጀመሪያ መተኛት አለበት። አገራችን አደጋ ውስጥ ሁና መች ልንተኛ! ሰው በቁሙ ህልም አያይም። ይኸ ዕውነታ ሊታመን ይገባል። በሕልሙ ሲደሰት አድሮ፥ ሲነቃ በገሀዱ ዓለም አስደሳች ነገር ሳይኖር ይከፋዋል። ለምን ነቃሁ ይላል። ባዶነት ይሰማዋል! እየተበሳ መዋል ነው። የአዕምሮ በሽታም ሊያመጣ ይችላል። ይኸ የአገሪቱ መሪ ህዝቡን የህልም እንጀራ ሊመግበው ያምረዋል። የህልም እንጀራ ደሞ አያጠግብም። ክውሸቱ ጭካኔው፣ ከጭካኔው ውሸቱ!

 

አንዲት ዓይታው ዓይታው ስልችት ያላት ወጣት እንዲህ ስትል አሾፈችበት።

 

ማመስገን የምፈልገው እኔ፣ አባታችን ብላቸው ቅር አይለኝም። አባታችን ዶክተር ዐቢይን ... አመሰግናለሁኝ። በተለይ በቃ ሳንጠይቅ የሚያደርጉትን ነገር። አሁን እኛ ስለዳቦ፣ ... ዳቦ ራበን ብለን ብንጠይቅ፣ እሳቸው ደሞ፣ የዳቦን አመጣጥ፣ ዳቦ ለምን እንደሚያስፈልግ፣ የአሜሪካው ዳቦ ከኡጋንዳው ዳቦ በምን እንደሚለይ፣ ባንበላ እራሱ፣ ችግር እንደሌለው እያስረዱ ስለሚያጠግቡን እግዚአብሔር ይስጦት እላለሁኝ። እንደአባት ደሞ፣ ... እኔ እንደአባት የምለው ደሞ ይቆጣል አይደል? ቤተሰብ ይቆጣናል። እንደአባት ደሞ እናነተ ሾርት ሚሞሪ ያላችሁ  ልጆች እያሉን፣ እየተቆጡን፣ ደንገጥ እንድንል ስለሚያደርጉን፣ እንዲያው ቤተሰብ እንዳለን ስለሚሰማን አመሰግናለሁኝ።

 

የፒተር ፓንን (Peter Pan) ፊልም አይታችኋል? እነዚያ ህጻናት ተሰባስበው የምናብ (imaginary) ምግብ ሲያነክቱ?! በልጆች የዕቃ-ዕቃ ጨዋታ ሊያታልለን ሲሞክር ያናድዳል! ህልም የሚታመን ነገር ሊሆን አይችልም። ህልም ተግባራዊ አይሆንም። ራዕይ ነው ታስቦበት ተግባራዊ የሚሆነው።

2ኛ) ዶሮ አርቢዋ የጤና ባለሙያ

ግራ የሚይጋባ ጉድ እዩ፡

አንድ የጤና ... ሙያተኛ የሆነች ሴት፣ ከሥራዋ በተጓዳኝ፣ 40 ዶሮ፣ 50 ዶሮ፣ በቤቷ ውስጥ በዚያች ትንሽ ቦክስ ቢኖራት፣ በቀን 20 30 40 ዕንቁላል ብታመርት፣ ማሩ ሲጨመር፣ ዓሣው ሲጨመር፣ ወተቱ ሲጨመር፣ በቤት በቂ ምግብ ስላለ፣ በሥራ ከሚገኘው ገንዘብ፣ ተጨማሪ ማጣፈጫ ይሆናል ማለት ነው።

“ጉድ በል ጎንደር!” አለ ያገሬ ሰው! ይኸን ሰው ሳስበው አንድ ነገር ትዝ ይለኛል። “ቡና የለም እንጂ፣ ከሰል ቢኖር የዶሮ ዓይን የመሰለች ቡና አፈላልህ ነበር” አለች ድኃይቱ! ይኸንን አባባል፣ ሌላ ጊዜ እጠቀምበታለሁ፣ ደግሜ! የጤና ባለሙያዋ፣ የዶሮ ዕርባታ ባለሙያ ስትሆን ይታያችሁ። ትምህርቱንም መውሰድ ነበረባት ማለት ነው? እሷ ዶሮ አርቢ ስትሆን፣ ህክምናውን ማን ሊሸፍንላት ነው? ኧረ እየተስተዋለ! በዚያ ትንሽ ቤት ውስጥ ከዶሮዎቹ ጋር በደባልነት ስትኖር፣ የ40 ዶሮ ኩስ ስትጠርግ ታየችኝ እኮ! ቆዩኝማ! እሺ ዶሮዋንስ አቅፋ በኪራይ ቤት ትደር እንበልማሩ፣ ዓሣው እና ወተቱ ከሰማይ ቤት እንደመና እየተግተለተለ ሊወርድላት ነው ወይስ ከሥራው በተጓዳኝነት፣ ንብም ታርባ፣ ዓሣም ታስግር፣ ላምም ታርባ ሊለን ፈልጎ ነው? ምነው የሚመስል ወሬ ቢያወራ! አንድ ጊዜ ማን እንዳናደደው አላውቅምምን ዓይነቱ ጀዝባ ነው!” ሲል ሰማሁት መሰለኝ።ጀዝባምን እንደሆነ ባላውቅም፣ በዚህ ላይ ሽንኩርት በየመሥሪያ ቤቱ መመረት እንዳለበት የሰጠውን መመሪያ ስናክልበት፣ማነው ጀዝባ?” ያሰኘናል። መሪያችንን ደፈረ እያሉ ደንገጦሮቹ ሲጨፍሩ ታየኝ። እኔ ላይ ከማላዘናችሁ በፊት እሱ ክብሩን ይጠብቅ!

3ኝ) አንድ ዓመት ብትዋጉን አታሸንፉንም!

ሳያስበው በጀብደኝነት ጦሩን ልኮ፣ በአስራ አምስት ቀን ትጥቁን ብቻ ሳይሆን ሱሪውንም አስወልቀዋለሁ ብሎ ዘሎ የገባበት ጦርነት እንዳሰበው፣ እንዳሳመረው ፓርክ ውስጥ መንሸርሸር ያህል ሳይቀለው ሲቀር ዓይኑን በጨው አጥቦ፣ እንዲህ አለን።

ደጋግሜ እንዳነሳሁት፣ በኦሮሚያ ክልል፣ በአማራ ክልል ያሉ፣ ወንድሞቻችን፣ አንድ ዓመት ቢታገሉ ስለማያሸንፉ፣ አንድ ዓመት ቢወድቁ ቢነሱ ለውጥ ስለማያመጡ፣ ያኛውን መንገድ ጥለው ወደ ሰላም እንዲመጡ፣ በዚህ በተከበረ ጉባዔ በድጋሚ ጥሪ አቀርብላቸዋለሁ።

አንድ ቀልድ ትዝ አለኝ። እስቲ እንዝናናበት። አንድ ጠና ያሉ ሀብታም ሰው፣ ቆንጂዬ ኮረዳ አግብተው ይኖሩ ነበር። ብዙ ጊዜ ለሥራ ወጣ ብለው ይመለሳሉ። አንድ ቀን ታማኝነቷን ለማረጋገጥ ሩቅ ቦታ እንደሚኼዱና አድረው እንደሚመለሱ ነግረዋት ተሰናብተዋት ወጡ። ለትንሽ ሰዓታት ከኼዱ በኋላ፣ ተመለሱ። ድምጻቸውን አጥፍተው በጓሮ በር ገቡ። ቤቱ ጸጥ ብሎ ነበርና በቀጥታ ወደ መኝታ ቤታቸው ዘው አሉ። አንድ ጎረምሳና ሚስታቸው ተቃቅፈው እንደተኙ እጅ ከፍንጅ ያዟቸው። ሁለቱ ወንዶች ትግል ገጥመው ተናነቁ። እንግዳው ጎረምሳ ወደማሸነፉ ተቃረበ። አዛውንቱ ዞር ብለው ሲያዩ ከፍቅር ጨዋታቸው በፊት ለምግብና ለመጠጥ ወጥተው የተደረደሩትን በጣም ውድ ውድ የሆኑ ሰሀኖች፣ ሲኒዎች፣ ክርስታል ብርጭቆዎችን አስተዋሉ። ታዲያ፣ሰሀኑን አንሺው! ብርጭቆውን አንሺው፣ ሲኒውን አንሺው!” ይሏት ገቡ። ሚስትየዋ ግራ ተጋብታውይ! በሞቴ! ሊወድቁ ነው?” አለቻቸው። ሰውዬው ንድድ ብሏቸው፣የለም! የለም! አንቺ ባመጣሽው ጣጣ ተገትሬልሽ ላድር ኑሯል!” አሏት ይባላል።

“ይሞታል እንዴ?!” አለች አንዲት የምወዳት እህቴ! ትላንትና ወደ አማራው ሲዘምት እኮ፣ በ15 ቀን ውስጥ ትጥቁን ብቻ ሳይሆን፣ ሱሪውን እናስፈታለን ብሎ ፎክሮ አልነበር የኦህዴድን መከላከያ ያዘመተው? ካልተሳካስ? ምን ችግር አለው እንደ ወደቡ ፍጥጥ ብሎ ማራዘም ነዋ! ምነው አሥራ አምስቱን ቀን ወደ ሺ ዓመት አራዘመው?! ለምን ይሆን Not in a million yearsአለ የተባለው እዚህ ላይ ትዝ ያለኝ? በ15 ቀን ባንጨርሰው፣ ልጆቻችን በሺ ዓመት ያሸንፋሉ ማለት ይችላል። ምን ችግር አለው፣ ሁሉ በእጁ ሁሉ በደጁ! ግን፣ የሱሪዋ ነገር እንዳላየ ታለፈች አይደል? ነገ ረጋፊ መሆኑን ተረሳው።

ይኸ ሰው፣ ህዝቡን ሲገድሉት፣ ሲያስሩት፣ ሲያሳድዱት ቁጭ ብሎ እስኪጨርሱት መጠበቅ አለበት ብሎ ያምናል መሰለኝ።  ግድግዳን ገፍተኸው ገፍተኸው ማለፍ አትችልም ሰውዬ! መልሶ ይገፋሀል! ይኸ የፊዚክስ ሕግ ነው። ጦርነቱም ሆነ ማንኛው በኢትዮጵያ ላይ የሚደርሰው ግፍ እሱ ባመጣው ጣጣ መሆኑን ግን ማን በነገረው?

ድንቄም ጠቅላይ  ሚኒስትር! ለመሆኑ፣ የትኛው ፕላኔት ላይ ነው የሚኖረው? እኛንShort memory” አለን እንጂ፣ ከቀን በፊት ያለውን የማያስታውስ ፍጡር ነው። አሳዳጊው ሕወህት/ወያኔ እኮ 17 ዓመት ተዋግቶ ነበር፣ ዝሆን የማያገፋውን ጦር ገዝግዞ ደርግን የጣለው! ህዝብን አታሸንፍም በሉት!! የኢትዮጵያ ህዝብ 27 ዓመታት ታግሎ ነው ወያኔን የተገላገለው። የሦሪያው ፕረዝደንት ባሻር አል-አሳድ ዲሰምበር 8 ቀን 2024 በኃይል መገርሰሱን ጆሮውን በጥጥ ደፍኖ አልሰማ ካላለ እንጂ ሁኗል፣ ተፈጽሟል።

የአማራ ጥላቻው ግርም ይለኛል። ልጆቹ እኮ ግማሽ አማራ ናቸው። ወያኔ ሲያሳድደው በቤቱ ደብቆ ያተረፈው እኮ አማራ የሆነ ሰው ነው። ከአሳዳጊው ወያኔ ጋር የገጠመውን ማን ነበር ያሸነፈለት? ከመከላከያ ቀድሞ ምሽግ እየደረመሰ፣ እራሱን እየሰዋ፣ ወያኔን ወደመጣችበት የሰደደለት ማን ነበር? ሾርት ሜሞሪ ማለት ይኸ ነው ወዳጄ! አሁንስ ቆሌው ርቆታል።

በጣም ከገረመኝ ንግግሩ፣ በሰላም መታገሉ ነው የሚያዋጣቸው” ማለቱ ነው። በሰላም የታገሉትማ አዋሽ አርባና ቅሊንጦ እሥር ቤት እየማቀቁ ናቸው። እነ ክርስቲያን ታደለ፣ ዮሐንስ ያለው፣ መስክረም አበራ፣ ታዲዮስ ታንቱ፣ ገነት አስማማው፣ በሰላም ታግለው ምን እንዳጋጠማቸው እያየን እኮ ነው። ታየ ዳንዳአን ክፉ ተናገረኝ ብሎ፣ ምን እንደ ገጠመው አይተናል። በጠብመንጃ የተፋለሙትማ፣ እነስብሀት ነጋ በክብር ተሸኝተው በአሜሪካ በኩራት ይንቀባረራሉ። ከፍ ዝቅ እያደረጉ ሲያዋርዱት የነበሩት፣ እኔ ጌታቸው ረዳ ተሹመው ተሸልመው አገር ውስጥ ይንፈላሰሳሉ። ሰሞኑን እንኳን፣ ህዝብን ሲፈጁ የነበሩት እነ ጃል ሰኚና ጓደኞቹ ለሹመት በቅተዋል። በሰላም ኢትዮጵያ ውስጥ መታገል፣ ለአሳር ነው።

4ኛ) ሳናጣራ አናስርም

ለሥልጣን በበቃ ማግስት፣ በስሜት ቃል የገባውን ሁሉ አንድ በአንድ ክዷል። በኢትዮጵያ ባህል፣ ቃል ማፍረስ ነውር ነው። ሎሪየት ጸጋዬ ገብረመድኅን ስለ ቃል እንዲህ ብለው ነበር። “ቃል የዕምነት ዕዳ ነው እንጂ፣ ያባት እናት እኮ አይደለም።”[1] ይኸኛው ደሞ ቃል ኪዳን ገብቶልን ካፈረሳቸው አንዱ አብረን እንይ።

እንደ ከዚህ በፊቱ፣ አስረን ከምናጣራ፣ አጣርተን ብናስር ብለን ነው። አንድ ንጹህ ሰው ከሚታሰር ለፍትህ ሲባል መቶ ወንጀልኛ መፍታት ይሻላል ይባላል።

ጽድቁ ቀርቶብኝ በቅጡ በኰነነኝ ይባላል። ነገር ማሳመር ሲችልበት! ለመሆኑ በጅምላ እየታፈሱ፣ አዋሽ አርባና ቅሊንጦ እንዲሁም ድብቅ እስር ቤቶች አዲስ አበባ ውስጥ የሚማቅቁ ጋዜጠኞችና ንፁሀን የአማራ ተወላጆች አጣርተን ነው ያሠርነውሊለን እንዳይሆን የበሻሻው አራዳ? ጅምላ እሥሩ እኮ፣ ከኛ ከባለጉዳዮች አልፎ፣ የዓለም አቀፍ ሚዲያዎችንና፣ የዓለም አቀፍ ሰባዓዊ መብት ተሟጎቾችን ሁሉ ያሳሰበ ጉዳይ ሁኗል። November 6, 2024 የአምነስቲ ኢንተርናሽናል ዘገባ ብቻ ማንበብ ይበቃል (Amnesty, 06 November 2024)። በተግባ የሚሠራውን እያየን “ዓይናችሁን ጨፍኑ ላሞኛችሁ ነው” ማለቱ ነው። ከሰሞኑ፣ እነ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባኤን (ኢሰመጉ)፣ የሕግ ባለሙያዎች ሰብዓዊ መብቶች፣ የመብቶችና ዲሞክራሲ ዕድገት ማዕከል፣ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ተሟጋቾች ማዕክል መሣሪያ አንስተው ተዋግተው ነው የታገዱት? ሰው ምን ይለኛል አይልም እንዴ!

5ኛ) “አዲስ አበባ ውስጥ ኦሮሞ ጠል አስተሳሰብ አለ”

ሕዝብን አክብሮ እንጂ፣ አዋርዶ ሰድቦ ለማስተዳደር የደፈረ፣ አንድም መሪ አይቼ አላውቅም። የንጉሡንም አስተዳደር ደርሼበታለሁ አላደረጉትም። ጄኔራል አማን አንዶምም አላደረጉትም። መንግስቱ ኃይለማሪያምም አላደረገውም። ኧረ መለስም፣ ኃይለማርያም ደሳለኝም አላደረጉትም።

የጉራጌን ህዝብ በጅምላ ሲሰድብ ያየነው፣ ዐቢይ አህመድ አሊ ነው። “የጉራጌ ህዝብ፣ ማንም የሚጭነው፣ የኅዳር አህያ ነው” አለ። ስለእሱ እኛ ተሸማቀቅን። “የኢትዮጵያን ህዝብ ከማስተዳደር ሺ ጉንዳን በጫንቃ ተሸክሞ መሄድ ይቀላል” አለ። አሁን ደግሞ፣ የአዲስ አበባን ህዝብ ሙልጭ አድርጎ እንዲህ ሲል ሰደበው።

“አዲስ አበባ ላይ ከፍተኛ ኦሮሞ ጠል ኃይሎች፣ ኦሮሞን የሚጠሉ፣ ግን ኢትዮጵያ ውስጥ መኖር የሚያስቡ ሰዎች፣ “ኦሮምኛ ተዘመረ አሉ። የግሪክ ትምህርት ቤት አለ አዲስ አበባ ውስጥ፣ ሊሴ አለ፣ ፈረንሳይ ትምህርት ቤት፣ ጣሊያን ትምህርት ቤት አለ፣ ጀርመን አለ፣ ማሪፍ አለ፣ ኢንተርናሽናል ኮሙዩኒቲ ስኵል አለ። ይኸ ሁሉ በቋንቋው ነው የሚዘምረው። ሊሴ ሲዘምር ያላመመው ኢትዮጵያዊ በኦሮኛ ሲዘመር የሚያመው ኢትዮጵያዊ ምን ኢትዮጵያዊ ይባላል? ኢትዮጵያዊ ነው ይኸ? በዚያ ደረጃ ጥላቻ ጥሩ አይደለም። ኦሮሚያን ለአዲስ አበባ ውሀ አላመጣህም ብለን የምጮህበት፣ ቆሻሻ ሲደፋበት እያየን የተቀበልን፣ ኦሮምኛ ሲሰማ የሚጎረብጠን ከሆነ እንዴት በጋራ እንኖራለን።”

አይባልም! ድንቄም! አስረድቶ ልቡ ውልቅ ብሏል። አንድ በአንድ ቃላቶቹን እንሰንጥቅለት። በመጀመሪያ ደረጃ፣ አንድ የአገር መሪ እንዲህ የወረደ ንግግር ከአፉ ይወጣል ተብሎ አይጠበቅበትም። ነውር ነው! ቀጥሎ የአዲስ አበባ ሕዝብ፣ ዘር ብሎ ነገር አያውቅም። ኦህዴዶች ዘረኝነታቸውን በግድ ልትጭኑበት ሲትነሱ “እምቢዮ” ማለቱ በኦሮሞ ጠቅላይ ሚኒስትር “ከኦሮሞ ጠልነት” ሊያስፈርጀው አይችልም። የአዲስ አበባ ህዝብ ዘረኛን ይጠላል። አይፈረድበትም። ዘረኝነት ውዳቂ አስተሳሰብ ነው። ጥንብ ነው።

ዐቢይ አህመድ አሊ ኦሮሞ መሆኑን ከመጀመሪያው ጀምሮ የአዲስ አበባ ህዝብ ግጥም አድርጎ ያውቃል። ኦሮሞ መሆኑን ስላላወቀ ነበር ያንን ሁሉ ፍቅር ያለ ገደብ የቸረው? የአዲስ አበባ ህዝብ እነዚህ ዘረኞች በጉልበት የአንድ ጎሳ የዘረኝነት መርዝ አትግቱኝም ነው ያለው። አዲስ አበባ ወለጋ አይደለም። ሰውን እንደሰውነት ተቀብሎ ወንድሜ፣ እህቴ እያለ የሚኖር የሜትሮፖሊታን ህዝብ ዘረኝነትን ይጸየፋል።  

እስቲ ሰኔ 10 ቀን 2010 (23 June 2018) እናስታውሰው። ያችን መስቀል አደባባይ በህይወቱ ላይ በራሱ ሰዎች የቦምብ ጥቃቷን ረስቷት ይሆን? የአዲስ አበባ ህዝብ ኦሮሞ ጠሊታ በመሆኑ ነበር እንዴ፣ ሁለት ኗሪዎቿ ህይወታቸው የሰዉለትና 44 ሰዎች ቆስለው ህይወቱን ያተረፉለት?! ምስጋና ቢስ!!! 10/10/10 መሆኑን ልብ በሉ። እሱ ቢረሳው እኛ አንረሳም፡፡ የሚረሳ ቁጥር አይደለም።

የግሪክም ሆነ፣ ሊሴም ሆነ፣ ጣሊያንም ሆነ፣ ጀርመንም ሆነ፣ ማሪፍም ሆነ፣ ኢንተርናሽናል ኮሙዩኒቲ ስኵልም ሆነ በቋንቋቸው በግል ትምርት ቤታቸው ይዘምራሉ። የግል ትምህርት ቤት ነዋ! ወላጆች ፈቅደው ፈልገው፣ ገንዘባቸው ከፍለው ነው እዚያ ትምህርት ቤት ልጆቻቸውን የሚያስተምሩት። የኛዎቹ ባለጊዜዎች ኦሮሞዎቹ እኮ፣ የጋራ በሆነው በየመንግሥት ትምህርት መዝሙራችን ካልተዘመረ፣ ባንዲራችን ካልተሰቀለ ነበር ያሉት። የማንኛውም ብሔረሰብ ህዝባዊ መዝሙር ነው በፌዴራሉ መቀመጫ ከተማ ሲዘመር ያዩት? የአማራ ነው? የአፋሩ ነው? የሱማሌው ነው፣ የሐረሬው ነው፣  የሲዳማው ነው?  የቤኒ ሻንጉል ግሙዙ ነው ወይስ የደቡቡ? እደግመዋለሁ! በፈቃደኝነት ሳይሆን ሊያስገደዱት እኮ ነው የሞከሩት። በኦሮምኛ ብቻ የሚያስተምሩ ትምህርት ቤቶች ካሉ፣ እዚያ ኦሮሙማቸው ያድርጉ። መስመር አትለፉ፣ ዘረኛ አታድርጉን ማለቱ “ኦሮሞ ጠል” ያሰኘዋል? አዲስ አበባን ለመንጠቅ ከታቀደው አንዱ ስግብግብነት፣ የተጠነሰሰች ሴራ መሆኗን የአራዳ ልጅ ያውቀዋል። የአዲስ አበባ ህዝብ ነቅቶበታል። አዲስ አበባ በግድም በወድም ተነጥቃ “ፊንፊኔ ኦሮሚያ” እስካልሆነች ድረስ፣ የማይታሰብ ሙክራ ነው። እስከ መጨረሻው ይፋለማቸዋል። የዐቢይ ድንፋታ የሚያስከትለው፣ እመኑኝ የሥልጣኑ ማብቂያ ደወል ነው። አዲስ አበባ ክሥሩ ተንሸራተተች ማለት፣ የመንበሩ መፈንገል ትንቢታዊ ምልክት ነው።

16ኛው መቶ ክፍለ ዘመን፣ አንድን ሕብረተሰብ ወረው ካንበረከኩት በኋላ፣ ኦሮሞዎች ያደርጉ የነበሩት ግፍ አለ። እሱም የተሸነፈውን ወገን በኦሮምኛ እንዲዘፍን ያስገድዱት  ነበር። በቋንቋቸው “ሲርባ ጊዲ!” ይሉታል። “የግድ ዘፈን!” ማለት ነው። አሁንም የአዲስ አበባን ህዝብ አስገድደው የዘረኛ መዝሙራቸውን ሊያስዘምሩት ነዋ ህልማቸው! አዲስ አበቤው ታክስ እየከፈለ በሚያስተምርበት የመንግሥት ትምህርት ቤት ውስጥ የሚፈልገውን ይበል፣ በጋራ የመንግሥት ትምህርት ቤት ውስጥ አይታሰብም። ይኸ ዓይነቱ ግፍ በአዲስ አበባ ህዝብ ላይ ሊፈጸም እንዴት ተሞከረ? ደግሞ መዝሙራቸው የጥላቻ መዝሙር እኮ ነው። ሲተረጎም እንዲህ ነው የሚለው!

ኦሮሚያ፣ ኦሮሚያ፣ የትልቅ ታሪክ ባለቤት

የኦሮሞዎች ማዕከል፣ የገዳ ሥርዓት ማህደር

የሕግና ሥርዓት ምድር፣ የጨፌ ኦዳ እናት

የታደለች ለምለሚቷ፣ ሁሉን አብቃይ

የመቶ ዓመት ግፍን፣ በደም አጠብንልሽ

በውድ መስዋዕትነት፣ ሰንደቅሽን ከፍ አደረግን

ደስ ብሎናል ደስ ይበልሽ፣ ገዳችንን አስመልሰን

ሰላምና ዲሞክራሲ፣ ሰብዓዊ መብት

አስተማማኝ ልማት፣ ፈጣን ዕድገት

ከሌሎች ህዝቦች ጋርም፣ በፍቅርና በአንድነት

ለመኖር ዋስትና፣ ጽኑ ዓላማ አድርገን

በኃይላችን አንድ አድርገን፣ ተነስተናል ተመኚልን

ኦሮሚያ ልምላሜ፣ ብልጽግና ኑሪ!

 

ቁም ነገሩ በኦሮምኛ ዘፈን ስንጨፍር ነው የኖርነው። በውድ እንጂ በግድ ሲጫንማ ወዲያልኝ ወዲያ! በውስጡ ያሉትን መርዝ ማየት ያስፈልጋል። “የመቶ ዓመት ግፍን በደማችን አጠብንልሽ” የሚል ጉድ! የምን ግፍ ነው የሚያወሩት። ባለፉት መቶ ዓመታት ውስጥ ምን ግፍ ተፈጸመባቸው? የምን ደም ነው ዘምሩልን የሚሉት? ላለፉት 50 ዓመታት አንዴ መኢሶን ውስጥ ተሰግስገው፣ አንዴ ደርግ ውስጥ ተሰግሰገው፣ ሌላ ጊዜ ወያኔ በፈጠረላቸው ኦህዴዳቸው፣ አሁን ደግሞ በብልጽግና ያአማራውን፣ የጋሞውን፣ የወላይታውን ደም ሲያፈሱ የነበሩት እነሱ ሁነው፣ የአዞ እምባ ሊረጩብን ተነሱ! “በኃይላችን አንድ አድርገን” የሚልም ቃል ይገኝበታል። በፍቅርማ መኖር ከፈለጉ፣ የዘር ማጽዳት በወለጋና በመሳሰሉት ማጽዳት ዘማቻቸውን ባልፈጸሙ ነበር። ያንን አዲስ አበባ ላይ ሊደግሙት?! ቡና በኦሮሚያ ተገኘ የሚሉትን ትርክት እየሰማን ነው። ክትፎ የኦሮሞ ባህላዊ ምግብ ነው ሲሉም ሰማናቸው። ባዲስ አበባ በፍቅር መኖር ህዝቡን ምን ገዶት! የ16ኛውን የጭካኔ እጃቸውን መልሰው ሊያነሱበት ሲነሱ “ክላ” ቢላቸው ይፈረድበታል? ክፋታቸው መልሶ ባርቆባቸው ነው። የአዲስ አበባ ህዝብ እኮ በየቀኑ የሽመልስ አብዲሳን ንግግር ይከታተላል። ለአዲስ አበባ የደገሰውን እልቂት በተጠንቀቅ እየተጠባበቀ ነው። ሸገር ተብሎ ተቀርፎ የከበበውንም የእሳት ግንብ ይረዳል። “ፊንፊኔ ኬኛ” እየተባለ የሚፎከርበትንም በትዕግስት ያስተውላል። ትላንት ቡራዩ ላይ ጋሞዎችን የጨፈጨፉትንም አልረሳም። ወለጋ ውስጥ የተጨፈጨፉትንም አልረሳም። በገዛ እጃቸው ሀጫሉን ገድለው፣ በሻሸማኔ፣ በዝዋይ፣ ያረዷቸውን ሁሉ የአዲስ አበባ ህዝብ ያውቃል። አሁንም በአዲስ አበባ ቤቱን ሁሉ በላዩ ላይ የሚያፈሱትን የኦህዴድ ባለሥልጣኖች እያየና እየሰማ የግድ አፍቅሩኝ ነው? ክፉን ከወደደ የጠላ ነገደ!

 

አንድ የኦህዴድ ባልሥልጣን ኢቲቪ  ላይ ቀርቦ ስለሚፈርሱት ቤቶች እንዲህ አለ፡

 

“አሁን፣ የሚገርመው እኮ፣ ከትግበራው በፊት መለየት ሁሉ አለ ስንለይ እራሱ ያውቃሉ። እንወያያለን፣ ከተወያየን በኋላ ማኅበረሰቡ እያለ ያምናል። ሕገወጥ ነው በቃ ብለው ያምናሉ። ከዚያ ካመኑ በኋላ ወደ መለየቱ ይኬዳል። አሁን ቅድም አልፎ አልፎ የሚባለው፣ ይታለፋል ምናምን ነገር አንዳንዴ ጊዜ፣ ኢንዲጂነስ የሆነውን ማኅበርሰብ አናፈርስበትም።”

https://www.facebook.com/watch/?v=2022652128175165&rdid=nls47Vg4voWrB5d3

 

እንዲህ ነው እንጂ! ኢንዲጂነስ የሚባለው ምርጡ ዘር ኦሮሞ መሆኑ ነው? የሚሉሽን በሰማሽ ገበያ ባልወጣሽ ይባላል። አረብ ፋቂ (Arab-Faqih, 2003) የተባለው የመኒ፣ አህመድ ኢብን ኢብራሂም አል ጋዚ (Ahmad ibn Ibrahim al-Ghazi)፣ በተለምዶ ግራኝ አህመድን ጦር እየተከተለ በዘገበው ዜና መዋዕል መጽሐፉ ላይ፣ በረራ (ያሁኗ አዲስ አበባ) ትግራይ እስኪደረስ፣ አንድም ቦታ “ኦሮሞ” ወይም “ጋላ” የሚል ቃል አታገኙበትም። ኦሮሞ ከኋላው እየተከተለው ስለነበረ አላጋጠሙትማ! የያኔው በረራ የአሁኑ አዲስ አበባ የአጼ ልብነድንግል መናገሻ ከተማ እንደነበረች ማንኛውም የታሪክ ምሑር የሚያውቀው ሐቅ ነው። አጼ ምንሊክና እቴጌ ጣይቱ ናቸው ዳግም አዲስ አበባን ከመቃበር ያነሷት። ምርቱን ለገበያ ለማቅረብ ወደ ንጉሡ ከተማ ዙሪያ የሠፈረው ኋላ-መጥ ኦሮሞ እንዲጂነስ ሁኖ፣ የአያት ቅደመ አያቱ አጽመ ርስት ላይ የሚኖረው “መጤ” ከተባለ በገዛ ዳቦዬ ልብ ልቡን አጣሁት የሚባለው ዓይነት ግፍ ያንገፈፋል። “ሲርባ ጊዲ” ማለት ይኸ እኮ ነው። አስገድዶ ከመድፈር ምን ለየው? ባሰ እንጂ!

6ኛ) የአካም ኦልቴ ነገር

አሁንም፣ ስለ ኦሮምኛ! ይኸ ሰውዬ፣ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር መሆን አልነበረበትም። ምክንያቱም፣ ኢትዮጵያ ሳትሆን አልፋውና ኦሜጋው፣ ኦሮሚያ ናታ! የኦሮሚያ ነገር ብቻ ነው የሚጨንቀው። እንዲህ አለን። 

“አማሮች ደፈር ብላችሁ ‘አካም ኦልቴ’ ማለት መጀመር አለባችሁ።”

ጉድ ፈላ! ልክ ቀደም ብዬ የነገርኳችሁ “ሲርባ ጊዲ” ተመልሶ መጣ። የአሥራ ስድስተኛው መቶ ክፍለ ዘመን ግፍ ዓይኑን አፍጥጦ መጣባችሁ አማሮች! እንደዚያ ኦሮሞነቱ ካልበለጠበት ምነው፣ “ዲጎ ቤቴ? በሉ አላለን? “ኬሮ ሆሲቶ” በሉ አላለን? ለምን_”ፈያዲያይ” በሉ አልተባልንም? ለምን “ፈያ ወክሙ” በሉ አልተባልንም? ኬሬ ሆሲኒም እኮ ከቋንቋችን አንዱ ነው። 86 የኢትዮጵያ ቋንቋዎች እኮ አሉን። አማሮች በሄዱበት የአካባቢውን ቋንቋ በፈቃዳቸው በደስታ ነው ተምረው የሚናገሩት። አስገድዶ አንድም ነገር የሚፈጽም የለም። በግድ? እንዲህ የሚል ህግ በቅርቡ እንጠብቅ። “በብልጽግና ዘመን፣ ሁሉም ብሔረሰቦች እኩል ናቸው። አንዳንድ ብሔረሰቦች ግን ከሁሉም በበለጠ እኩል ናቸው”።

ይኸ ሰው ሊመከር የሚገባው አንድ ነገር ቢኖር፣ ሁሉም ኢትዮጵያዊ፣ አማራው ብቻ ሳይሆን ሌሎች ብሔረሰቦች (ብሔር አላልኩም፣ ልብ በሉ። ብሔር አገር ነው) እንዲህ የሚንገበገብበትን ኦሮምኛን የሚማሩለት የሱን ፍላጎት ለማሟላት ሳይሆን፣ ፈቅደው፣ ፈልገው፣ ወደው ነው መሆን ያለበት። ይኸ ሰውዬ፣ በዚህ ቢያበቃስ! ቀጠለ።

 7ኛ) “አማሮች ኦሮምኛ መማር አለባቸው”

አሁንም ኦሮምኛ ለሦስተኛ ጊዜ። ብሶበታል! እንዴት ነው፣ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ነኝ የሚል ግለሰብ የኦሮሞ ነገር ከምንም በላይ የሚቆጠቁጠው? በኦሮምኛ “አካም ኦልቴ በሉ”፣ ኦሮሚኛ ተማሩ፣ በኦሮሚኛ ዝምሩ ...። ካልሆነ ኦሮሞ ጠል ናችሁ ይለናል። ግን ሌሎች ብሔርሰቦች በኦሮምያ ሲጨፈጨፉ፣ ሲፈናቀሉ፣ ሲሰደዱ፣ ቅንጣት ያህል አይሰማውም። አቅጣጫ ለማስቀየር ችግኝ ተከላ ይወጣና፣ ካድሬዎቹን ያንን አስጩሁ የሚል ትዕዛዝ ይሰጠቸዋል። እንዲህ ተባልን፡

“በአማራ ክልል የኦሮኛ ትምህርት መጀመር አለበት። አማራ ክልል ኦሮኛ ለማስተማር፣ በፍጥነት ካልወሰነ የሆነ ጊዜ ላይ አንድ መሆን አስቸጋሪ ጉዳይ ነው። ከኦሮሚያ ክልል ቀጥሎ፣ ሰፊ የኦሮሞ ህዝብ ያለው አማራ ክልል ውስጥ ነው። በዞን የተደረጀ አለ፣ ከዚያም በላይ ቅድም እንዳነሳሁት ጎንደር ውስጥ ጎራድ (?) አለ፣ ጎጃም በጣም በርካታ ኦሮሞ አለ፣ ወሎ በርካታ ኦሮሞ አለ፣ ሸዋም እንደዚሁ የተቀላቀለ ነው። ብዙ ኦሮሞው ያለዉም እዚሁ ክልል ነው። አማራ ክልል ኦሮኛ ለማስተማር በፍጥነት ካልወሰነ እዚህም እዚያም  የተለያየ ቋንቋ እየተናገርን፣ የተለያየ ባህል እየገነባን፣ የተለያየ ማንነት እየገነባን የሆነ ግዜ ላይ አንድ ላይ መሆን አስቸጋሪ ነው፣ ጉዳይ ነው።”

 

ለዘመናት ከነበሩት መንግሥታት መሪዎች ተለይቶ፣ ይኽ ድንቅ ምስጢር እንዴት ተገለጠለት ጃል?! በመርዝ የተለውሰ ማር ዓይነት ንግግር ነው። ሁለት እኵይ ዓላማ አለው። አንዱ ልክ ኦሮሚያ ውስጥ ኦሮሞዎች በዘር ፖሊቲካ ተነስተው ከክልላቸው አማራውን ከቤት ንብረቱ  ሲያፈናቅሉት፣ አማራ ክልል የሚኖሩት ኦሮሞዎች በሰላም መኖራቸው ያበሳጨው ይመስላል። ለዚህ ሰው፣ አማራውና ኦሮሞው በሰላምና በፍቅር 400 አመታት በላይ የኖረ መሆኑን ማን በነገረው! በአማራው ክልል እንደዚያ ያለ የዱር አውሬ ጭካኔ ባለመተግበሩ አንጀቱ አሯል። አማራ የሞራል የበላይነት ማግኘቱ አንገብግቦታል። የኦሮሞ ደም ደሜ ነው ብሎ ወንድምነቱን ሲገልጽ፣ ለለበጣ አልነበረም። ሸዋን ብትወስዱ የቱ ኦሮሞ፣ የቱ አማራ እንደሆነ አይታውቅም። ወሎም እንደዚያው። ኦሮሚያ ውስጥ ዘረኞች ሲያብዱና አማራውን ሲያሳድዱ፣ አማራ ውስጥ የሚኖሩ ኦሮሞዎች አጸፋው ስላልተወሰደ፣ ያለሥጋት በሰላም መብታቸው ተጠብቆላቸው መኖራቸው፣ የዘረኞችን ትርክት አከሸፈባቸው። አማራ ጨዋ ህዝብ ነው።

 

ሌላው ግን፣ ቋንቋቸውን ከዚያ የማይመች የላቲን ሾርባ ከነቁቤያቸው፣ ልክ አሁን አዲስ አበባ ላይ ለማድረግ እንደሚሞክሩት፣ አማርኛን ለማዳከም የታቀደ ከንቱ መርዝ ነው። ሺመልስ አብዲሳ እኮ በግልጽ የአማርኛን ቋንቋ በ50 ዓመት ውስጥ እናጠፋለን ብሏል። ጠቅላይ ሚኒስትሩን እንዲህ ግብግብ አድርጎ የሚያስለፈልፈው፣ ያንን ዕቅድ አለማሳካቱ ነው። አማርኛ ኦሮሚያ ክልል በደንብ ማስተማር አለበት ብሎ እኮ መመሪያ ቢሰጥ መርዙ ይሸፈንለት ነበር። ለምን ጉራጊኛ፣ ሲዳምኛ፣ ጋሞኛ፣ ወላይትኛ፣ አፋርኛ ካፊኛ፣ አርጎብኛ፣ ሐረሪኛ፣ ሶማሊኛ ... አላለም? የሱ መነሻና መድረሻ፣ አልፋና ኦሜጋ ኦሮሞና ኦሮሞ በመሆኑ ነው! ሲያምረው ይቅር። አማራ ኦሮምኛ ፈቅዶ ቢያስተምር፣ በላቲን ቁቤ አይሆንም! 

በአንድ አገር ውስጥ አንድ ብሔራዊ የሁሉም መግባቢያ ቋንቋ፣ የተለመደ አሠራር ነው። እስካሁን አማርኛ በደንብ አገልግሏል። ሁሉም ብሔረሰብ የሚባል ተሰብስቦ እንደገና ተወያይቶበት አማርኛ አስጠላኝ ብሎ፣ ሌላ ተመራጭ ብሔራዊ ቋንቋ ላይ በድምጽ ብልጫ እስካለወጠው ድረስ፣ ቢመረው ይጋተው፣ አማርኛ ብሔራዊ ቋንቋ ነው። የሚመረጠው ኦሮምኛ ከሆነ፣ ሁሉም ኦሮምኛ ይማራል። ያኔ አማሮችም የግዳቸውን ይማሩታል። አሁን ግን በፈቃደኝነት ካልሆነ ንክችም አያደርጋትም። 

ሕንድ ውስጥ ከ2,000 በላይ ብሔርሰቦችና ቋንቋዎች አሉ። ሁሉም የተስማሙበት አንድ ብሔራዊ ቋንቋ ከ1950 ጀምሮ ሒንዲ ነው። ዛሬም በዚያው እየተሠራ ነው። ቻይና ውስጥ 56 ትላልቅና ስፍር ቁጥር የሌላቸው ትናንሽ ድሀጣን ህብረተሰቦች አሉ። ከ1930 ዓ.ም. ጀምሮ ማንደሪን ብሔራዊ ቋንቋቸው ነው። አሜሬካም፣ ቱርኪያም ሌሎችም እንደዚሁ። ኢትዮጵያ የተለየች አገር አይደለችም! ዋጠው! 

8ኛ) “ደሞዝ የማንከፍላቸው ከቁጥጥራችን ውጪ ሊሆኑ” ነው። 

በሰላም ታገሉ ይለናል። ጋዜጠኞችን እያደነ ያስራል። ሰብዓዊ መብት ተሟጋቾችን፣ ያግዳል። ተመልከቱ! 

“አሁን የተከበረው ምክር ቤት፣ ብዙ ነገረ ሳላበዛ፣ የሰብዓዊ መብት የሚባል፣ አዋጅ ተቋም አሠራር መፈተሽ ያስፈልጋል። እኛ ደሞዝ የማንከፍለው፣ ሌሎች ኃይሎች የቀጠሩት፣ ለሌሎች ኃይሎች ሪፖርት የሚያቀርብ ተቋም ኢትዮጵያ ውስጥ ከፈቀድን፣ ምን ሌፈጸም እንደሚችል፣ ለእናንተ መተው ነው።” 

“በነጻ” እንዲንቀሳቀሱ ህጋዊ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች ነበሩ። “ሳስበው ታከተኝ፣ አለች ሴትዮዋ! “ከቁጥጥራችን ውጪ በመሆናቸው ጉዳችንን ሊያጋልጡብን ነው” ብሎ ሰጋ። ስለዚህ በተዘዋዋሪ መንገድ እንደፈለገው ደሞዝ እየከፈለ የሚዘውረውን “የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን” የሚባለውን “ጨርግደህ ጨርግደህ ጣልልኝ” እያለ የሥራ አቅጣጫ አሳየ። ይኸን ተከትሎ፣ በትዕዛዙ መሠረት እነ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባኤን (ኢሰመጉ)፣ የሕግ ባለሙያዎች ሰብዓዊ መብቶችን፣ የመብቶችና ዲሞክራሲ ዕድገት ማዕከል፣ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ተሟጋቾች ማዕክልን፣ እንዳይንቀሳቀሱ አግዷቸዋል።  

ይኸ ማለት፣ ዋና ኮሚሽነር ዳንኤል በቀለ ወርዶ (Editor, 2024)፣ በአሁኑ ሰዓት በተጠባባቂ ኮምሽነር ራኬብ መሰለ፣ የሲቪል ፖሊቲካ ሶሻል-ኢኮኖሚ ኮምሽነር አብዲ ጂብሪል እና የሴቶች፣ ሕጻናት፣ አረጋውያን እና የአካል ጉዳተኞች መብት ኮምሽነር ርግበ ገብረሐዋሪያ የሚመራውን የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽንን፣ “ደሞዛችሁን የምንከፍለው እኛ ነን፣  ቁጥጥራችን ውስጥ ናችሁ፣ የመንግሥትን ገጽታ የሚያበላሽ ሪፖርት ካቀረባችሁ፣ ወየውላችሁ”፣ እያላቸው ነው። ይኸን ጽሑፍ ላኩላቸው። 

ድመት መንኩሳ፣ አመሏን አትረሳ ይባላል። ወያኔ የፈለፈላቸው ዘረኞች ምንጊዜም መርዘኞች ናቸው። በአንድ አፍ ሁለት ምላስ ይሉታል ይኸ ነው እንግዲህ። ካጠፋን ንገሩን እያለ ሲያማልል የነበረው ጠቅላይ ሚኒስትር፣ ነጻ የሰብዓዊ መብት ድርጅቶችን ደሞዝ እኛ አንከፍላቸውምና ከቁጥጥራችን ውጪ ስለሆኑ ገመናችንን እንዳያዝረከርኩብን፣ ይታገዱ ብሎ ፓርላማ ላይ አወጀ። ይኸ ዓይን ያወጣ አምባገነን መሆኑን፣ ቁልጭ አድርጎ ያሳያል። የኢሕአዴግ ልጅ፣ ብልጽግና! 

9ኛ) “ኢትዮጵያዊ ሸንኩርት እይበላ ዶሮ በላሁ ይላል። 

የኢትዮጵያን ባህልና እሴት የሚጠላ፣ የሚንቅ፣  ምን ሲባል ነው፣ እየኢትዮጵያ መሪ የሚሆነው? ኤዲያ! 

"ኢትዮጵያ ውስጥ ዶሮ እንላለን? ከዚህ ቀደም፣ ዶሮ ሳይሆን  ሽንኩርት ነው ምንበላው። ሽንኩርቱን ውስጥ ትንሽ ዶሮ ጨምረን፣ ከዚያ ዶሮ በላን እንላለን እንጂ ፕራይመርሊ የሚበላው ሽንኩርቱ ነው። ሽንኩርቱን መብላት ሳይሆን፣ ወደ ዶሮ መብላት መሸጋገር ነው የሚያስፈልገው። ተጠብሶ፣ በጣም ብዙ ዘይት፣ ብዙ ሽንኩርት ሳይኖርበት፣ ዶሮውን ከዳቦ ጋር እያደረግን መብላት እንድንችል ነው፣ ዋናው ፍላጎት።” 

“አይ አለማወቅሽ አገርሽ መራቁ!” ይባላል። በመጀመሪያ የዶሮ አሠራራችን ከኢትዮጵያ አልፎ በዓለም ደረጃ የተደነቀ፣ የተወደደ ምግብ ነው። ውጭ አገር፣ ሒልተን ውስጥ ዶሮ ወጥ በአገራችን አሠራር ተቀምሞ ተሠርቶ ፈረንጆቹ ሲወርዱበት ሳይ፣ የተሰማኝን ኩራት ለመግለጽ አልችልም። የዶሮ አሠራር ሁሉም ኢትዮጵያዊ የተራቀቀበት ተወዳጅ የአገሪቱ ምግብ ነው። “ከዘፈን እንደ ትዝታ፣ ከዘፋኝ እንደ ጥላሁን፣ ከምግብ እንደ ዶሮ ወጥ” ተብሎ በአንደኝነት ደረጃ የተቀመጠ ባህላዊ እሴታችን ወይም ፋይዳችን ነው። ይኸ የኦህዴድ ጠቅላይ ሚኒስትር፣ ከኢትይጵያ ባህል ጋር፣ ምን በጠላትነት አቆመው? ባህሏን ከጠላ፣ ማንነቷን ከጠላ፣ ለምን አገሪቱን ለቆልን አይገላግለንም?! 

ለመሆኑ፣ ዶሮ እኮ ዋጋዋ በአሁኑ ጊዜ የበሬ ዋጋ መሆኑን ማን በነገረው! ይኸ የደላው ሰውዬ፣ “ለምን ኬክ አይበሉም” ("Qu'ils mangent de la brioche") አለች የተባለችውን የፈረንሳይ ልዕልት ሜሪ አንቷነትን (Marie Antoinette) ያስታውሰናል። እንኳን በዚህ ውድ ዋጋ የተገዛች ዶሮ ይቅርና፣ ድሮም ዶሮ በሀምሳ ሳንቲም ስትገዛ፣ የምትበላው ቢያንስ ቢያንስ እስከ ሰባት የቤተሰብ አባላት ድረስ እንድታዳርስ ተደርጎ ነው። ዶሮ ታርዳ፣ አሥራ ሁለት ቦታ ተቆርጣ፣ ሙልጭ ተደርጎ ልፋጯ ተጠርጎላት፣ በሎሚና ሞቅ ባለ ወሀ ተደጋግሞ ታጥባ ትዘጋጃለች። ንጹህ  ቆዳዋም ቢሆን፣ በነበልባል እሳት ተለብልቦ፣ ፀጉሮቿ ተወግደው፣ በንፅህና ተዘጋጅታ ቁሌቱ ውስጥ ትጨመራለች። ዋናዎቹ ብልቶቹ ሰባት ናቸው፤ እነሱም ሁለት ረዥም እግር፣ ሁለት መላላጫ፣ ፈረሰኛ፣ ሁለት አጭር እግር ሲሆኑ፣ ሁለት ክንፎች፣ መቋደሻ፣ ማቀፊያ፣ አንገት ግን እንደተጨማሪ የሚቆጠሩ ናቸው። ሰውዬው የታየው ሽንኩርቱ እና ዘይቱ ብቻ ነው። “በ12 ቅመም የተሰራች ዶሮ፣ እኔ እሷን ቀምሼ አልተርፍም ዘንድሮ” ተብሎ ቅኔ የተቀኘው እኮ ባህላዊ አሠራሯ ልቅም ብላ፣ ሽንኩርቱም፣ ነጭ ሽንኩርቱም፣ ዝንጅብሉም፣ ኮረሪማውም፣ በሶ ብላውም፣ ድምብላሉም፣ ሌሎቹም ቅመማ ቅመሞች በምጥን በምጥን በባለሙያይቱ በጥንቃቄ ተዘጋጅቶ 12ቱ ብልቶች ተቆራርጠው ተጨምረውባት፣ በልዩ ዘዴ የተነጠረ ቅቤ ተጨምሮባት፣ እንቁላልም ተቀቅሎ ገብቶበት፣ መጨረሻ ላይ መከለሻ ተጨምሮበት ይወጣል። ታዲያ ያ በሞንሟና የጤፍ እንጀራ ከነአይቡ ሲቀርብ “እጅ አያስቆረጥማል” እንላለን፣ ሲጣፍጠን። በዳቦ? የምን ዳቦ አመጣብን? በእንጀራ ነው የሚበላው! የዶሮ ዝግጅት ለየት ያለ በመሆኑና ጥንቃቄ የሚፈልግ በመሆኑ፡ እንዲህም እየተባለ ተዘፍኗል፡

ሀ)ዓሣ አበላሻለሁ፣ ዓባይ ዳር ነው ቤቴ፤

ዶሮ መረቅማ፣ ከወዴት አባቴ

ለ) ተስማሚዬ ሁነህ፣ እንድትዋብልኝ፤

እንደ ዶሮ መረቅ፣ ፍቅርህ ይጣፍጥልኝ። 

የኢትዮጵያ ዶሮ፣ ከሥጋዋ ሳይሆን ከመረቋ ነው ቁምነገሩ ያለው። ማማሩስ? ማስጎምጀቱስ? እስቲ የሚከተሉትን ፎቶዎች አወዳድሩ። ከዐቢይ ዶሮና ከኢትዮጵያ ዶሮ፣ የትኛው ነው ምራቅ የሚያስውጣችሁ? 

የዐቢይ አህመድ አሊ ዶሮ ጥብስ

የኢትጵያ ባህላዊ ዶሮ ወጥ
 

ሰሞኑን ዝነኛዋ የባህል ዘፈን አቀንቃኝ አርቲስት አምሳል ምትኬ፣ ሰይፉ ፋንታሁን በኢቢኤስ ላይ ቀርባ፣ ከዘፈኗ ባሻገር እሷ የሠራችውን ዶሮ የቀመሰ እንግዳ፣ ዕድሜ ልኩን ጣዕሟን አይረሳትም ብላ ስትፎክር ሰምቼ ፈገግ አሰኘችኝ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ የዶሮ አሠራር ባህላዊ መሆኑን ረስቶ፣ ለኮለስትሮ የሚዳርገውን ልፋጯ ሳይወጣ፣ በሎሜ ሳትታጠብ፣ የተጠበሰችውን ዶሮ በዳቦ ብሉ እያለ ሲመክረን፣ ገረመኝ። ዳቦውስ ሲገኝ አይደል? ዳቦ በሙዝም ብሉ ብሎ እኮ መክሮን ነበር። ዳቦዋ ተደጋገመችሳ! ለዚህ ነው ምስኪኗ፣ “ቡና የለም እንጂ፣ ከሰል ቢኖር የዶሮ ዓይን የመሰለች ቡና አፈላልህ ነበር!” ያለችው። እኛ በስደት አገራችን፣ ዶሮ እንደልብ የምትመረትበት ምዕራብያውያን አገር የምንኖርው ኢትዮጵያውን፣ ባይገርመው፣ አሁንም በባህላዊ ዘዴ የተሠራችውን ዶሮ ነው በእንጀራ ጠቅልለን ቅርጥፍ አድርገን የምንበላት፣ በዳቦማ አንነካትም። ዳቦ የፋራ ነው! ኢትዮጵያዊ ዶሮዋን ጠብሰን አንበላም፣ እንጀራችንንም በዳቦ አንቀይርም። ተስፋ ይቁረጥ! አሁን ገና በዓይናችን መጣ። 

10ኛ) የሆያ ሆዬና የአበባ አየሽ ወይ ግጥሞች መቀየር አለባቸው 

ሆሆ! ይኸ ሰውዬ አበላላችንን ብቻ ሳይሆን፣ በሌሎች ኢትዮጵያዊ ባህሎችን እና እሴቶች ላይ ነው ዘመቻውን ያጧጧፈው! እስቲ የሚከተለውን አባባሉን እዩልኝማ! 

“ተረትና ምሳሌዎቻችን፣ ሆያ ሆዬና አበባ አየሽ ወይ ሳይቀሩ፣ ግጥም መቀየር አለበት። እንጨት ለቅሜ፣ እንጀራ እናቴ፣ ምናምን መቆም አለበት። እሱ መጥፎ መርዝ ነው ግጭት ውስጥ የሚገባው። ያ ግጥም ካልተቀየረ ውስጥ ውስጡን እየገባ እየገባ ሂዶ ጥፋት ያመጣል። እና ትርክት ፣ ስንጠይቅም፣ ስንመልስም፣ ስንሠራም፣ ስንኖርም የሚገነባ ነገር ነው። እኛ አንጨርሰው። ተባብረን ግን ልጆቻችን እንደዚህ በሠፈር ሳይባሉ፣ እንዲኖሩ ማድረግ፣ የሚያስችል ነው።” 

“ለዛው ሙጥጥ” አሉ አባት እናቶቻችን! ሲጀመር በሆያ ሆዬና በአበባ አየሽ ወይ ውስጥ ያሉትን ባህላዊ ግጥሞች ጥልቀት ለመረዳት፣ የዳበረ ጭንቅላት የለውም። በነዚህ ባህላዊ ጭፈራዎች ምክንያት የሠፈር ልጆች ተባሉ ሲባል፣ ገና ከዚህ ሰውዬ ለመጀመሪያ ጊዜ መስማቴ ነው። ከኢትዮጵያ ባህልና ቅርስ ጋር ሰውዬው ሆን ብሎ ሲጣላ ሊኖር ነው? ምን ይሻለዋል? ማስተዋል የሚችል በአካባቢው፣ የሚያምርበትንና የማያምርበትን የሚነግረው አንድ ምራቅ የዋጠ ደፋር ሰው ይጥፋ! መሳቂያ ሆነ እኮ። 

ከዚህ ቀደም አንበሳ የኢትዮጵያ አርማ መሆን የለበትም በማለት፣ ካለበት ሁሉ እንዲጠፋ ሀሳብ አቅርቦ ነበር። ከሱ ይልቅ ከኢትዮጵያ ጋር በምንም ዓይነት የማትቆራኘውን የበርማ ወፍ ምልክታችን ለማድረግ ሐውልት ሁሉ እንደ አኖሌ ሳይቀር አቆመላት። በመጀመሪያ ደረጃ የፒኮክና (peacock) ፒኸን (peahen) ልዩነቱንም የሚያውቅ አይመስለኝም። ፒኮክ አውራው ነው። ላባው አምሮ በተለያየ ቀለም የሚምነሰነሰው ፒኮክ ፒኸኗን (ሴቷን) ለማማለል የፍቅር ግብዣ ነው። ይኸ ሰውዬ ያልተረዳው፣ ኢትዮጵያውያን ከሰሜን እስከደቡብ አንበሳን የሚያዩት በልዩ አድናቆት ነው። እሱ ወጣሁበት የሚለው የኦሮሞ ሕብረተሰብ አንበሳን ከመወደዱ የተነሳ፣ ወንድ ልጆቹ ሲጎብዙለት፣ “ያ ሌንጫ ኮ!” እያሉ ያንቆለጳጵሳሉ። ለዚህ ነው ለልጆቻቸው ሌንጮ እያሉ ስም የሚያወጡት። ለምሳሌ፣ ሌንጮ ባቲ አለ፣ ሌንጮ ለታም ከጎኑ አሉለት አይደል? 

የአንበሳ ጥላቻው በጣም የጠለቀ በመሆኑ፣ በገደምዳሜ፣ በአንበሳ የሚጠሩ ድርጅቶች በሙሉ እንዲጠፉ እየጣረ ነው። አንበሳ ፋርማሲ ማፍረሱን ልብ ብላችኋል? አንበሳ አውቶቡስንም፣ ስሙንና መልኩን ሊቀይሩለት ነው። ሲቲ ባስ ሊባልም ነው። “ሞጋሳ” መሆኑ ነው። ምን አግብቶት ነው አባቶቻችን የሰየሙትን ለመቀየር የዳዳው? 

“አያገባው ገብቶ፣ ሰው ይዘባርቃል፤

እኔ ስሜን እንጂ፣ ምኞቴን ማን ያውቃል።” 

ነበር ያለቺው፣ ብዙነሽ በቀለ! ሲጀመር አንደኛ ቅኔ ምን እንደሆነ ምንም የሚያውቀው ነገር የለም። የሚያውቃት አማርኛ፣ ጥራዝ ነጠቅ፣ የጎዳና አማርኛ ናት። ወዳጄ! አማርኛ ከምታስበው በላይ ጥልቅ ነው። አንድ ባለ ቅኔ ያደነቀህ መስሎ ሙልጭ አድርጎ ሰድቦህ ይኼዳል። አንዳንዴ ቶሎ የሚገባ አይደለም። በዚህ የታወቁት፣ አለቃ ገብረሀና የሚባሉ ሊቅ ነበሩ። ታዲያ አንድ ጎረምሳ፣ ከሰድቡት ሊደበድባቸው ዝቶ፣ አህያውን ጭኖ፣ ዱላውን ጨብጦ ከቤቱ ወጣ። መንገድ ላይ ተገናኙ፣ የእግዚአብሔር ሰላምታ ተሰጣጥተው ተላለፉ። ወደ መንደር ገባና፣ “ያ ደብተራ ጸባዩን አሳምሮ አለፈኝ” አለ። ሌላው “ምን ነበር ያሉህ?” ቢለው፣ “ኧረ ምንም! በትህትና እጅ ነስቶ ‘ደህና አደራችሁ” ብሎኝ አለፈ” አለ። “ከማን ጋር ነበርክ?” አለው። “እንድምታየው ብቻየን ነበርኩ። አህያዬን ጭኜ፣ ወደዚህ እየመጣሁ ነበር” አለው። “አዪዪ! በል ተወው! አንተና አህያዋ አንድ ናችሁ ብለውህ ሰድበውህ አለፉ” አለውና አበገነው። 

ጠቅላይ ምንስትሩ ጨርሶ የግጥሞቹ ጥልቀት ስላልገባው፣ በማያውቀው ገብቶ ዘላበደ። የሆያ ሆዬም ሆነ የአበባ አየሽ ወይ ግጥሞች እሱ ካሰበው በላይ ጥልቅ ትርጉም አላቸው። አማርኛን ጠልቆ ለማወቅ አማራ መሆን ብቻ አይበቃም። መማር፣ መመራመርን ይጠይቃል። አማራ ሳይሆኑ፣ በአማርኛ የረቀቁ ሞልተዋልና! የግጥሞቹን ጥልቀት፣ እኔ እዚህ ከማሰለቻችሁ፣ እንደሱ ከምዘበዝብ፣ አንድ አዋቂ ሰው በአርትስ ቲቪ ላይ፣ በሚከተለው ቪዲዩ በሚገባ መልክ አስረድቶ ነበር። ተጋበዝልኝ አደራ! 

https://youtu.be/cIW57vXoVEk?si=D5aXNNfqLG0h8dke 

ስለዚህ፣ የሚሰማችሁ ከሆነ፣ ይኸ ሰው ከመዘባረቁ በፊት የሚናገረውን ብታስተካክሉለት እንደዚህ አዋርዳለሁ ብሎ ከመዋረድ ይተርፋል። ይኸ ወጣቶች በታላቁ ሩጫ ላይ ሲዘፍኑ “ጠቅላይ ሚኒስትራችን ላይ አሾፋችሁ” እየተባለ የሚታፈሱበት ምክንያት ባልኖረ ነበር። እረፍ በሉት። “በአፍ ይጠፉ፣ በለፈለፉ።“አፍ ሲከፈት፣ ጭንቅላት ይታያል” ይባላል። ተረትና ምሳሌ ይጠላ የለ? ቅመስ በሉት! 

ማጠቃለያ! 

በአገር ደረጃ የገጠመን፣ ቀላል የሚባል ችግር አይደለም። ከዮዲት ጉዲት ጊዜም የከፋ ነው። ከግራኝ ጀሀዳዊ ጦርነትም ጊዜ የከፋ ነው። ከዘመነ መሳፍንትም ጊዜ የጨቀየ ነው። ከአድዋ ጦርነትም ሆነ፣ ከማይጨው ጦርነትም ጊዜ በበለጠ የሚያሰጋ ነው። እርስ በርስ የመባላት ጊዜ ነው። ሕገ-መንግሥት ቀርጸው፣ ዘረኝነትን ያስተዋወቁንም ህወሀቶች ዙሮባቸው እሳቱ ፈጃቸው። የትግራይንም ህዝብ ለእልቂት ዳርጓል። የ16ኛውን ክፍለ ዘመን ነፍሰ-በላ ኦሮሙማ ሥርዓት ቀንበር ተጭኖብናል። አማራው በአሁኑ ሰዓት በጦርነት ቁም ስቅሉን እያየ  ነው። የኦህዴድ መከላከያ ሠራዊት አማራ ክልል ዘሎ ገብቶ፣ ሕጻናትን፣ ሽማግሌዎችን፣ ሴቶችን ከውጪ ከወረሩን ጠላቶች በበለጠ እየጨፈጨፈን ነው። እንኳን ለአማራውና ሌሎች ብሔረሰቦች ቀርቶ፣ ለራሳቸው ለኦሮሞዎችም የስቃይና የሰቆቃ ዘመን ሆኖባቸዋል። የባሰውን፣ ጠቅላይ ሚኒስትራቸው፣ ከአንድ የአገር መሪ የማይጠበቅ አነጋጋሪ ግግሮች ከአንደበቱ እያፈለቀ፣ ህብረተሰቡን እያሸማቀቀ ነው። አትኵሬ ፎቶውን ሳስተውል ኢል ዱቼ (IL Duce) እየመሰለኝ መጣ።ሆድ ለባሰው ማጭድ አታውሰውይባላል። አንድ ቀን የከፋው ቆራጥ እርምጃ ይወስድበትና፣ ይገላግለናል። በቅርቡ ነገሮች እንደሚገለባበጡ ነው። ሰከን ቢል ይሻለዋል። 

የጆርጅ ኦርዌል (George Orwell) “እንስሳት ግብርና (Animal Farm) የሚባል መጽሐፍ አንብባችኋል? ካላነበባችሁ አንብቡት። ዐቢይ አህመድ አሊ ማለት ናፖሊዮን (Napoleon) ነው። ለማ መገርሳ ማለት ስኖውቦል (Snowball) ነው። ሙአዘ ኅምዝ ዘልዘሊቱ ዳኒኤል ክብረት ማለት ስኵለር (Squealer) ነው። ኮሬ ነጌኛ ማለት፣ እነዚያ ስኖቦልን ሊዘነጣጥሉት በድበቅ የሰለጠኑ አደገኞቹ ውሾች፣ ናፖሊዮን ገና በቡችልነታቸው ክብሉቤል (Bluebell) እና ጄሲ (Jessie) እንደተወለዱ፣ ዓይናቸውን ሳይከፍቱ ነጥቆ፣ በሰዋራ ቦታ ለአደገኛ ገዳይነት 9 ወራት የደበቃቸው ነፍሰ በላ ናቸው።። ሺመልስ አብዲሳ፣ ኦሮሚያን የሚያስተዳደራት ከሌሎቹ ባለሥልጣናት፣ በአራተኛ ደረጃ ተቀምጦ ነበር። ከስኖቦል መባረር በኋላ፣ ወደ 3 ደረጃ ከፍ ብሏል። ሌሎቹ አሳሞች በየክልሉና ዞኖች ላይ ተሹመው ብልጽግናን የሚያገለግሉ፣ የእንስሳት ግብርና” ሹሞችን ይመስላሉ። ደመቀ መኰንን ፈረሱ ቦክሰር (Boxer) ነው። የዐቢይን ብልጣብልጥነት ነቅተውበት፣ ግን መኼጃ አጥተው ዝም ብለው የሚያገለግሉት፣ ፈረሷ ክሎቨር (Clover) እና አህያው ቤንጃሚን (Benjamin) ናቸው። የኦህዴድ መከላከያ ያለምንም ጥያቄ ትዕዛዝን ተቀብለው ንጹሓንን የሚጨፈጭፉ፣ ከኤታ ማጆር ሹሙ፣ እስከ አየሩ ኃይሉ፣ ከሎጂስቲክ ጠቅላይ መመሪያ ኃላፊው እስክ እዞቹ አመራር ቁልፍ ቁልፍ ቦታ የያዙ የኦህዴድ ጀኔራሎችና ከፍተኛ መኰንኖች፣ የሰለጠኑ ምርጥ ዘር አሳሞች ናቸው። ዐቢይ ይምራን እያሉ፣ የሚያስተጋቡት ደንገጡሮቹ፣ ናፖሊዮንን የሚያመልኩት ምስኪን በጎች ናቸው። አገር ውስጥ የህዝብ ደህንነት ውስጥ፣ እንዲሁም በአፋቸው ጥሬ የቆሉ ካድሬዎች፣ እንዲሁም በዓለም የተናኙት ልዩ የመከላከያ የክብር አባል ተሸላሚ ሆድ አደር ጋዜጠኞች፣ የእንስሳት ግብርና” ውስጥ በየዘርፉ የተሰማሩ፣ ማንበብና መጻፍ የተማሩ፣ ሌሎች ምርጥ ዘር አሳሞችና ሙሴ (Moses) የተባለው ለስለላ የሰለጠነ ቁራ ናቸው። 

አገራችን ኢትዮጵያ፣ በአሁኑ ሰዓት፣ ቅጣአምባሯ የጠፋ ሆናለች። ዜጎቹ፣ እየተራቡ፣ “ጠግበናል በሉ”፣ የሚበላ የሚቀምስ ጠፍቶ “ሞልቶናል ብሉ”፣ እየተራቆቱ “ለብሰናል በሉ”፣ እየከሱ “ወፍረናል በሉ”፤ እየተረበሹ “ሰላም ነን በሉ”፣ እየደኸዩ “በልፅገናል በሉ”፣ እየታመሙ “ጤናማ ነን” በሉ፣ ተብለው በኦሮሙማ መረብ ተተብትበው፣ በእግዚአብሔር ተአምር ኑሮ ይገፋል። አገራችን፣ በአሳሞቹ መሪዎቿ የምትዘወር፣ ጆርጅ ኦርዌል የደረሳትን መጽሐፍ፣ “የእንስሣት ግብርናን” ትመስላለች። 

ከአያያዝ ይቀደዳል፣ ከአነጋገር ይፈረዳል ይባላል። ፖለቲካ የውሸት ጥበብ ቢሆንም፣ መሪዎቻችን እየመረጡ ቢዋሹ ይመረጣል። በተላይ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተናገሮ የሚያሳምናቸው ቢኖሩ፣ ደንገጡሮቹን ብቻ ነው። እኛስ እሺ ቀደዳውን ለምደናል፣ እንደ ብርክስ (BRICS), አፍሪካ ሕብረት (African Union), ዩኤንዲፒ (UNDP) ፊት እየወከለን ቀርቦ፣ ስለልማት፣ ስለ ዕድገት፣ ሰለሰላም ባያወራ ሀቁን ግጥም አድርገው ያውቃሉና፣ ባያሳፍረን ይመረጣል። 

ከተዘራ ያልታረመ አንደበቱን፣ ማን ያስተካክልለት? ከባድ ነው!

References

Amnesty, I. (06 November 2024). Ethiopia: End the month-long arbitrary detention of thousands in Amhara Region. Retrieved December 04, 2024, from https://www.amnesty.org/en/latest/news/2024/11/ethiopia-end-the-month-long-arbitrary-detention-of-thousands-in-amhara-region/

Arab-Faqih. (2003). “Futuh AL-Habasha, The Conquest of Abyssinia (16th Century), 2003, .

Editor. (2024, July 5). Daniel Bekele Steps Down From His Position As Chief Commissioner Of The Ethiopia Rights Commission. The Habesha. Retrieved January 11, 2025, from https://zehabesha.com/daniel-bekele-steps-down-from-his-position-as-chief-commissioner-of-the-ethiopia-rights-commission/

መጽሐፍ-ቅዱስ. (n.d.). መጽሐፈ ነገሥት ቀዳማዊ ቁጥር ምዕራፍ 12 ቁጥር 4-15.

 

 

 

 

 

የግርጌ  ማስታወሻ

[1] ጸጋዬ ገብረ መድኅን፣ “ቴዎድሮስ”፣ ታሪካዊ ተውኒቶች፣ 2093፣ ገጽ 119፣ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ