Tuesday, 22 November 2016

መካሪ ልቦናስ አለ ! ተመካሪ ሰዉ ግን ከወዴት አለ?


መካሪ ልቦናስ አለ ! ተመካሪ ሰዉ ግን ከወዴት አለ?
ሸንቁጥ አየለ
-------------------------------------
ሸዋ ዉስጥ ደብር ዜና ማርቆስ የሚባል ገዳም አለ::በ1986 ዓም የ12ኛ ክፍል ፈተኛ ስጨርስ ወደ አንድ መለኩሴ አጎቴ ካንድ ጓደኛዬ ጋር ወደ እዚህ ገዳም ሄድን::ይሄን ጓደኛዬን ለማስመከር መሆኑ ነዉ::በወቅቱ ይሄ ጓደኛዬ ነገር ክርስቶስ ላይ ጥርጣሬ ቢያበዛ እስኪ ከኝህ አጎቴ ምክር ስማ ብዬ ነበር ይዤዉ የሄድኩት::እናም መለኩሴዉ አጎቴ ልንጠይቃቸዉ እንደመጣን ሲያዉቁ ደስ አላቸዉ:: ፈገግ ብለዉም ተቀበሉን::

ሆኖም በቤታቸዉ ያለዉንም የሚበላ ነገር አቀራርበዉልን በትንሿ ቤታቸዉ ትተዉን "በሉ ተጨዋቱ:: እኔ ወደ ጸሎት መሄዴ ነዉ" ብለዉን ሄዱ::ቢጠበቁ አልመጡም::እኛም ስለደከመን ቁጭ ባልንበት መደብ ላይ እንቅፍል ይዞን ሄዶ ኗሯል::እሳቸዉ ግን በጣም ከመሸ መጡ::ጥቂት አርፈዉ እንደገና ተነስተዉ ሌሊትም ለጸሎት ብለዉ ሄዱ::ጠዋት ቅዳሴ ቆይተዉ መጡ::አሁንም ያላቸዉን ነገር አዘገጃጅተዉ አቀራርበዉልን የተሰዓት ጸሎት ደርሷል ብለዉ ሊሄዱ ተነሱ::

ነገር ክርስቶስ ላይ ጥርጣሬ የገባዉ ጓደኛዬም የመለኩሴዉ ለጸሎት እያሉ ጥፍት ማለት ገርሞታል እና አንድ ጥያቄ ጠዬቃቸዉ:: "ለመሆኑ ጸሎት የሚበቃዎት መቼ ነዉ? የሚጸልዩትስ ምን እያሉ ነዉ?" ሲል ጠዬቀ::እርሳቸዉም ፈገግ እያሉ " የምድር ጸሎቱ ስሞት ነዉ የሚበቃኝ::ሆኖም በሰማይም ክርስቶስን ማወደሱና እና ማመስገኑ ይቀጥላል::የምጸልዬዉም "አምላኬ : ጌታዬ : ፈጣሪዬ: ንጉሴ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ምስጋና ይገባሃል" እያልኩ ነዉ" ሲሉ መለሱለት::

ልቡ በክርስቶስ ነገር ላይ የሸፈተዉ ወጣትም "ክርስቶስ እኮ ፈጣሪ አይደለም::ለምንድን ነዉ ፈጣሪ የሚሉት?" ሲል ሳያፍር መለኩሴዉ አጎቴን ጠዬቃቸዉ::እኔም አመዴ ቡን አለ::በፍርሃትም ተሸማቀቅሁ:;እንዴት አንድን መለኩሴ እንዲህ በብልግና ይጠይቃል ብዬ መሆኑ ነዉ::እርሳቸዉም ፈገግ አሉ::"ክርስቶስን ፈጣሪ አይደለም ብለህ ታስባለህ? ማለት ነዉ?" ሲሉ::

"አዎን!" አለ ምንም ቅር ሳይለዉ::

"እዴት?" በድጋሚ ጠዬቁ::

"ምክንያቱም መጽሀፍ ቅዱስ እንደሚያብራራዉ..." ብሎ የሚያዉቃትን ጥቂት ጥቅስ ጠቃቀሰ::ድንገትም የዮሀንስ ወንጌል ምዕራፍ አንድን መናገር ጀመረ::ድምጹን ከፍ አድርጎም እየተናገር የነበረዉ መለኩሴዉን ክርስቶስ ኢየሱስ አምላክ አይደለም ብሎ ለማሳመን ነበር::ድንገት ግን ቀጥ ብሎ ቆመና መናገር አቆመ::"እንዴ ቆይ ? " ብሎ መንጎራደድ ጀመረ::"እንዴ ...ቆይ ይሄ ምዕራፍ እኮ ስለክርስቶስ አምላክነት እና ፈጣሪነት የሚያስረዳ ነዉ::እንዴ?..." እንደገና እራሱን አርሞ ምዕራፉን ደግሞ በቃሉ ለበለበዉ:: እራሱ እየተናገረ እራሱ ደግሞ እያብራራ "እንዴ ? እንዴ? ! ..." ማለቱን ቀጠለ::

መለኩሴዉ አጎቴ በዚህ ሁሉ የጓደኛዬ ንግግር መሃከል ጣልቃ አልገቡም::እራሱ ክርስቶስ ፈጣሪ አይደለም ብሎ ጥቅስ ማብራራት ጀምሮ እራሱ ደግሞ መዞ ባመጣዉ ጥቅስ ክርስቶስ ፈጣሪ ነዉ ብሎ እራሱን ማስረዳት ጀመረ:: መለኩሴዉ አጎቴም በመጨረሻ ጓደኛዬን እያስተዋሉ እንዲህ አሉ:: "አንተ ጎበዝ ልጅ ነህ::መካሪ ልብ ያለህ::ተመካሪ ልብም ያለህ:: አሳስተዉ ያስተማሩህን ነገር በየዋህነት ሰምተህ በልብህ ብታስቀምጠዉም ልቦናህ ግን እዉነትን የማድመጥ ጸጋን የተሰጠህ ሰዉ ነህና እዉነት እና ሀሰትን አብላልተህ በራስህ መለዬት ቻልክ::"

መለኩሴዉ አጎቴ ይሄችን ብቻ ከተናገሩ ብኋላ "በሉ እርስ በርሳችሁ ተማማሩ" ብለዉን ጥለዉን ወደ ጸሎታቸዉ ሄዱ:: የልጁ ክህደትም ሆነ እራሱን አርሞ ወደ ትክክለኛ ሀሳብ መምጣቱ ድንቅም አላላቸዉ::ሲጀምር እኝህ መለኩሴ ምንም ነገር የሚደንቃቸዉ ነገር ያለ አልመሰለኝም::ከመመልኮሳቸዉ በፊት አላቃቸዉም:: እንዲህ ምንም ነገር የማይደንቀዉ ያደረጋቸዉ ምልኩስናዉ ይሁን ወይም አይሁን ግን አላቅም::

በሶስተኛዉ ቀን ከትንሿ ቤታቸዉ ተሰናብተን እዬሄድን ሳለ ድንገት አንድ ሀሳብ መጣልኝ::ለዘለአለም ስንቅ የሚሆን ምክር ከኝህ ሰዉ ማግኘት:: እናም ዞር ብዬ እያስተዋልኳቸዉ "አባ ! በህይወታችን ሙሉ የምንመራበት ምክር ቢለግሱንስ?" ስል ጠዬቅኋቸዉ::እንደለመዱት ፈገግ አሉ::ከስዉ ልጅ ባህሪ ዉስጥ ፈግግ ማለት ጥልቅ የሰዉነት ህሳቤ ሚስጥር ይመስለኛል::ገና ህጻን ሆኜ::እናም እኝህ አባት ዉስጥ ይሄን ጥልቅ የሰዉነት ሚስጥረ ሀሳብ ያነበብኩት መስለኝ::እናም የሚናገሩትን ለማድመጥ በጥንቃቄ አቆበቆብን:: ሌላዉ ቀርቶ በነገር ክርስቶስ ላይ ልቡ ሲዋዥቅ የነበረዉ ጓደኛዬም በሶስት ቀን ዉስጥ የሆነ የማይታመን የአስተሳሰብ ለዉጥ አምጥቶ አባ የሚናገሩትን በአክብሮት እያደመጠ ነዉ::

አባ ምክር ስጠይቃቸዉ ፈገግ ብለዉ ሲያበቁ እንዳልሰማ ሆነዉ ግን "በሉ ሰላም ግቡ::ቆላማዉን ሀገር እስክትወጡ ቀስ እያላችሁ::" ብለዉን እንድንሄድ ገፋፉን:: እኔም "ምክሩን እኮ አልነገሩንም !" ስል በድጋሜ ጠዬቅሁ::አባ እንደገና ፈገግ አሉ:: እናም "እዉነተኛዉ ምክር እያንዳንዱ ሰዉ ልብ ዉስጥ አለ::ሰዉ የልቡን እዉነተኛ ምክር ለመስማት ከፈቀደ ከልቡ ዉጭ መካሪ አያስፈልገዉም::ለዚህ አባባሌም ምስክር የሚሆነዉ ይሄ ወጣት ነዉ" ብለዉ ወደ ጓደኛዬ በአገጫቸዉ አመለከቱ:: "ተመካሪ ሰዉ ካለ መካሪ ልቦናንስ እግዚአብሄር በየሰዉ ዉስጥ አኑሯል:: ሰዉ ከልቦናዉ ዉጭ መካሪ አያስፈልገዉም" በማለት አባ አብራሩ:: አጭር ግን ቆፍጠን ያለ ማብራሪያ ነበር::

እናም ሰሞኑን የመለኩሴዉ አጎቴ ጥልቅ ምክር ታስቦኝ እንደ እርሳቸዉ ብቻዬን ፈገግ አልኩ:: በኢትዮጵያዉያን ፖለቲከኞች መሃከል እየተከናወነ ያለዉን የእርስ በርስ መጠፋፋት ጉዳይ ሊያስቀር የሚችል አንድ ግሩም ምክር አዘል ጽሁፍ ማዘጋጀት አለብኝ ብዬ ሰሞኑን አስቤ ተነስቼ ነበር::የኢትዮጵያ ነገር ለልቤ ጭንቅ : ለመንፈሴ ህመም: ለህሳቤዬ እሩቅ ሲሆን በኢትዮጵያ ፖለቲከኞች መሃከል እኮ አብሮነት ቢፈጠር "አንዲት ዲሞክራሲያዊት ኢትዮጵያን" በፍጥነት እዉን ማድረግ ይቻል ነበር ብዬ እንደ ሞኝ እፈላሰፋለሁ::

እንደ ሞኝ ያልኩት ያለምክንያት አይደለም:: በጥልቅ ምክንያት ነዉ::እንኳን የማይተዋወቁ : በነገድ የሚለያዩ: በፖለቲካ ህሳቤ እና ርዕዮት አለም የተነጣጠሉ ሀይሎች አንድ ሊሆኑ ይቅር እና በእዉቀት ኮትኩተን እና አጀግነን ለጋራ ትግል ይሆናሉ ብለን የምናዘጋጃቸዉ ሰዎች በጣም በፍጥነት ሲገለባበጡ እና ሲከረባበቱ ብሎም ወደ ሌላ ጎራ ሲሰለፉ በተደጋጋሚ ላስተዋለ ሰዉ የኢትዮጵያ ፖለቲከኞች ለምን አንድ አልሆኑም ብሎ ማሰቡ በራሱ ሞኝነት ነዉ::አንድ ባይሆኑ ግን ለምን ተከባብረዉ አይታገሉም? ብሎ መጠዬቅ ግን ጤናማ ጥያቄ ይመስላል:: ግን ይሄም የኢትዮጵያን ፖለቲካ ቀርቦ በደንብ ለሚያጠናዉ ሰዉ የሞኝ ጥያቄ ነዉ::

እናም ማዘጋጀት የጀመርኩትን የምክር ጽሁፍ አጥፍቼ ስለ መለኩሴዉ አጎቴ ምክር ማንሰላሰል ጀመርኩ:: "ተመካሪ ሰዉ ካለ መካሪ ልቦናንስ እግዚአብሄር በየሰዉ ዉስጥ አኑሯል:: ሰዉ ከልቦናዉ ዉጭ መካሪ አያስፈልገዉም" የሚገርም እና የተራቀቀ አባባል ነዉ::ኢትዮጵያዉያን ይሄን ያህል ጥልቅ ህዝብ ሆነዉ ሳለ ለምን ጥልቅ መሰረት ላይ የቆመ ሀገር መመስረት አቃታቸዉ?
"መካሪ ልቦናስ አለ ! ተመካሪ ፖለቲከኛ ግን ከወዴት አለ?" የሚል ጥያቄ ሲቀርብም ይሰማኛል::እናም በክፉ መንፈስ የተጠለፈዉን: ዘረኛ እና አንባገነን ስርዓት ለማስወገድ በተጋድሎ ላይ ያለዉ ህዝባችን የተባበረ እርዳታ የሚፈልግበት ወቅት አሁን ነበር::ፖለቲከኞች ግን በመርዛማ የመጠላላት እና የመጠላለፍ ሀሳብ ዉስጥ ወድቀዋል:: ይሄ ዛሬ አልተጀመረም:: ቅንጅት የተበታተነዉ የተንኮል ፖለቲካ ማጥ ዉስጥ ተቀርቅሮ ጭምር ነዉ:: ከቅንጅት በፊት የነበሩትን አቢዮታዊ እንቅስቃሴዎች ሁሉ ወደ መርዛማ አዘቅት ዉስጥ የጣላቸዉም ይሄዉ በሸፍጥ እና በአሉታዊ እንቅስቃሴ የተሞላዉ የፖለቲካ ህሳቤ ነዉ:: የፖለቲከኞቻችን ልቦና እዉነትን ሳይሆን ሸፍጥን ለማፍልቅ ፈጣን ነዉ::

እናም ምክር ፖለቲካን አቅጣጫ አያሲዘዉም::በተለይም እንደ ኢትዮጵያ አይነት ፖለቲካዊ ምህዳር ዉስጥ የሚተራመስ የፖለቲከኛ ህዝነ ልቦናም እራሱን ለመምከር የሚያስችለዉን እዉነተኛ ምክር ለማፍለቅ ልቦናዉን ጸጥ የሚያደርግበት ሁኔታ ዉስጥ አይደለም::በኢትዮጵያ የፖለቲካ ተጨባጭ ሁኔታ መሰረት ፖለቲከኛነት በልብ ዉስጥ ትርምስ እና በዉጭም ትርምስ የሰፈነበት ከባቢ ህይወት ዉስጥ መመላለስ ይመስላላል::

እናም "እዉነተኛዉን እና ትክክለኛዉን ሁኔታ ለመለዬት እና ለማወቅ የሚያስችል መካሪ ልቦና በያንዳንዱ ዉስጥ አለ:: ተመካሪ ፖለቲከኛ ግን ከወዴት አለ?" ብሎ ዝም ማለት የቀለለዉ መፍተሄ ባይሆንም አንዱ አማራጭ ግን ይመስላል:: "መካሪ ልቦናስ አለ ! ተመካሪ ሰዉ ግን ከወዴት አለ?"

Thursday, 15 September 2016

ምነዋ አቦይ ዓባይ!

አቦይ ዓባይ!
ወንድሙ መኰንን፣ ብሪታኒያ፣ 14 September 2016 (ቀኖቹ በሙሉ፣ በአውሮፓውያን አቆጣጠር ነው)

ምነዋ አቦይ ዓባይ ጸሐ! በደም ሰከረውን ድፍርስ ዓይንዎን እያጉረጠረጡ ከስሙኒ ቀለሉሳ! ደኅናም ብቅል አልጠጡም? አቦይ በሚባሉበት ዕድሜዎ እንዲህ መዘላበድ?! ሽማግሌ አልነበሩም እንዴ?! ብቻአይ የኔ ነገር! ተሳስቼ! የናንተ ሽማግሌ የለውም ለካ! መዘላበድና መዛት ልማድዎ ነው። በዚያን ሰሞን፣ “ለጭቁን ብሔር ብሔርሰብ” ደረስንለት ባሉት አንደበትዎ፣ ኦሮሞ ወንድሞቻችንን “ልክ እናስገባዋለን” ብለው አልነበር። አቦይ ዓባይ! እግዚአብሔር እንኳን ከዛተ ከወረወርም ያድናል። ኦሮሞው አንዲት ብረት ሳያነሳ በባዶ እጁ ልክ አስገባችሁ አይደል? ሲዋሹ መቼም ዕድሜዎን እንኳን ግምት ውስጥ አያስገቡም። ሲዝቱ በጆሮአችን እየሰማንዎት፣ በነጋታው፣ “አላልኩም! አልወጣኝም”፣ ተቆርጦ የተቀጠለ ድምጼ ነው እንጂ እኔ እንደዚያ አላልኩም እያሉ ሲዘላብዱ ያኔ ሰምተን፣ ታዝበንዎት። 

እንደገና ደግመው ወጥ ረገጡ። ወያኔዎች ከሌላችሁ የኢትዮጵያ ሕዝብ ልክ እንደሩዋንዳ ይጨራረሳል[i] ብለውን እርፍ! ኤዲያ! ሕልምዎን ነው የሚነግሩን። “እኔ ይኸ ቤት ዛሬ ይቃጠላል ብዬ ነግሬአችሁ ነበር” አለች አሉ ያች ዕብድ? የኢትዮጵያን ሕዝብ አታውቁትም ማለት ነው። በዲኤንኤ የወረሳችሁት የኢትዮጵያ ጠላትነት ውርዴ አዕምሮአችሁን ስላደነዘዘው እናንተ ከምታስቡት ውጪ ማሰብ ስላቃታችሁ ከታሪክ ምንም መማር አትችሉምና አይፈረድባችሁም። አክሱምን ካፈራረሳችኋት፣ ከ፱፻፶ ዓመት ምሕረት ጀምሮ መልሳችሁ መላልሳችሁ ኢትዮጵያን ልታወድሟት የሞክራችኋቸውን ዕቅዶች በሙሉ፣ ሕዝቡ አክሽፎባችሁ፣ ዛሬ ደርሰናልና፣ ከዚህ በፊት ልትበታትኑን ሞክራችሁ እንዳልተሳካላችሁ ሁሉ ዛሬ አይሳካላችሁምና፣ ዕርማችሁን አውጡ። ለመሆኑ፣ እናንተ እነማናችሁ? የትግራይም፣ የኢትዮጵያም ሕዝብ እንዲያውቃችሁ፣ ያበጠው ይፈንዳ፣ የትውልድ ዘረ-ሐረጋችሁን፣ ይተንተን።

 ዘረኛው ጭንቅላታችሁ ነገሮችን በጥሞና ባይቀበልም፣ የተረገማችሁ መሆናችሁ ሊነገራችሁ ይገባል። ኢትዮጵያ ነበረች፣ አለች፣ ትኖራለች። የግሪኩ ጸሐፊና ፍላስፋ፣ ሆሜር፣ በኤሊያድና በኦዲሴ እያሽሞነሞነ ያነሳታል። እናንተ ወያኔዎች በእናታችሁ ሆድ ውስጥ ገና ሳትጠነሰሱ (ምነው እዚያቺው ውሀ ሆናችሁ በቀራችሁ!) ኢትዮጵያ ተጽፎ የተቀመጠ ከሶስት ሺህ ዓመት በላይ ዕድሜና አኵሪ የአንድ ሕዝብ ታሪክ ነበራት። እናንተ ከነተንኮላችሁ እዚህች ምድር ላይ ሳትኖሩ፣ ላም በፍቅር ሕዝቧ አብሮ ተባብሮ ከውጭ የመጣበትን ወራሪ መክቶ፣ ደሙን አፍሦ፣ አጥንቱን ከስክሶ ከመወሀዱ ባሻገር፣ በፍቅር ተጋብቶ ወልዶ ተዋልዶ ተከባብሮ አብሮ ኑሯል። የማን ርዝራዦች ናችሁ? ከወዴት መጣችሁ? ሊነገራችሁ ይገባል! በተለይ አቦይ ዓባይ፣ ልብ ብለው ያንብቡኝ - አብዛኛው የትግራይ ሕዝብ ሳይሆን እናንተ ዛሬ በስ ቀንቷችሁ ኢትዮጵያን የምትመዘብሯት ከየት እንደመነጫችሁ ከነማስረጃው እንንገራችሁ። የትግራይ ሕዝብ እኮ ልጆቹን አይድርላችሁም ነበር። ወይ ቀን! እናንተ የዮዲት ጉዲት ወታድሮች ውላጆች ናችሁ! አከተመ። እንዴት? ያውላችሁ!

ተይ ብሏት፣ ተይ ብሏት፣ ተይ ሏት አትሰማ
እንደበጎች ቀንድ፣ ዐመሏ ጠማማ  አለ ገጣሚው!

አቦይ ዓባይ! ቢያምኑም ባያምኑም፣ ከዮዲት በፊት ኢትዮጵያ ነበረች

“ዝም ባለ አፍ ዝምብ አይገባበትም” አሉ አበው! ተው እንጂ፣ አቦይ ዓባይ! ሁለት ዓይነት ትግሬዎች ትግራይ ውስጥ አላችሁ። አርበኞችና ከሀዲዎች። እናንተ የከሀዲዎቹ ዝርያ ናችሁ። ዕውነቷን አውጥተን ስናፈርጣት፣ ሬት-ሬት ብትላችሁም መድሃኒት ናትና ፉት በሏት! የናን ቅመ-አያቶችና ምንጅላቶች እንደዛሬው ሱዳን ተደራጅተው፣ ዮዲት ጉዲትን 960ዎቹ ዓ.ም ገደማ ተከትለው ወርረውን በለስ ቀንቷአቸው እክሱምን ሳያወድሟት ኢትዮጵያ ረች። ለዚህ አይደል፣ የሱዳን መንግሥት እስከዛሬ የሚያፈቅራችሁ? ዛሬ ዛሬማ፣ ሶማሌም ተጨምራለች። ሰሞኑን ስንት ሚሊዮን ዶላር ነበር የሶማሊያው ፕረዘደንት ሊሰጣችሁ ቃል የገባው? ለማንኛውም እነዚያ ወራሪ ቅመ-አይቶቻችሁ ሐውልቶቿን ሳያፈራርሱባ ኢትዮጵያ ነበረች። ክርስቲያኖቿን ሳያቃጥሉ ኢትዮጵያ ነበረች። ፈርሳ የማትፈርስ ተአምረኛ አገር! ትግራይ ውስጥ እንዴት እንደተዘራችሁ፣ እያያችሁ ነው? “እኛ ከሌለን ኢትዮጵያ እንደ ሩዋንዳ ትሆናለች” አሉን? ጉድ ነው ሲዳሩ ማልቀስ አሉ! ኤድያ! የሞኝ ለቅሶ መልሶ-መልሶ! በመጀሪያ ደረጃ፣ እናንተ ማን ሆናችሁና ነው ኢትዮጵያ የምትበታተነው?! በታኞችስ እናንተ አይደላችሁም?! እናንተ ከጠፋችሁ ሰላም ይኖረናል! የኢትዮጵያ ሕዝብ ፩ ቁጥር ጠላቶች፣ እናንተ ናችሁ። ከናንተ በኋላ፣ አንዲት ደም በከንቱ መሬት ላይ ጠብ አትልም
አቦይ ዓባይ! ቁልጭ ብሎ ይታይዎታል፣ ይኸ ጽሑፍ ወዴት እንደሚያዘግም? በ፲ኛው መቶ ክፍለ ዘመን፣ ዕውነተኛቹ አክሱማውያን ቅመአያቶቻችን፣ ሴቶችና አቅመ-ደካም ሕጻናት ወንዶች ሲቀሩ፣ ወደ ሸዋ፣ ወላይታ: ጎጃም፣ ጎንደር፣ ወሎ ከመሰደዳቸው በፊት፣ ታቦተ ጽዮንም ዝዋይ ሐይቅ ውስጥ ካሉት ደሴቶች በአንዷ ከመደብቋ በፊት፣ ለዮዲትና ለቅመ-አየቶቻችሁ፣ ቅጥር ነፍሰ ገዳዮችዋ  (mercineries) አክሱምን ጥለውላቸው፣ ሳይሰደዱ ኢትጵያ ነበረች። የናንተ ቅመ አያቶች ባል-አልባ ሴቶቻችንን ወርሰው ባልሠሩት ቤት ገብተው ሳይከረቸሙና የእርጉም ልጅ ዲቃሎች ሳይወልዱ፣ ኢትዮጵያ ነበረች።

ከላስታው ዛግዌ ሥረወ-መንግሥት በፊት ኢትዮጵያ ነበረች

ዓቦይ! ኢትዮጵያ የተፈጠረችው ከናንተ ጋር አይደለም! ተናግረው አያናግሩኝ! የመጨረሻው የአይሑዳዊቷ ንግስት የልጅ ልጅ በማራ ተክለ ሀይማኖት በሚመራው ጦር ተገደለ። ዘራችሁ ቂም ቋጥሮ ቀረ። የአገዎቹ የላስታው ላሊበላ የዛጔ ዳይናስቲ በ1137 ዓ.ም፣ ዮዲትና የናንተ ቅጥር ነፍሰ-ገዳዮቹ ቅመ-አያቶችሁ ያፈረሷትን አገር እንድገና መልሰው ከመገንባታቸው በፊት ኢትዮጵያ ለብዙ ሺህ ዓመታት ነበረች - ሕዝቧም አብረው አንድ ላይ ተፋቅረው ይኖሩ ነበር የተረፉት፣ የመርዘኞቹ የዮዲት ወታደሮች ዘር ለጊዜው አንገት ደፍተው፣ ክርስትናን ተቀብለው፣ የዛሬዩት ትግራይ አካባቢ ሲኖ፣ አንድም ቀን ለኢትዮጵያ ተኝተው አያውም። እንደገና ሊያፈራርሲያልሙ ኖሩ። ኢትዮጵያን እግዚአብሔር ጠብቋት ነበር ነው እንጂ ትግራይ ሕዝብ መሀል የተሸሸጉት የእርጉም ዘሮችማ ጊዜ እየጠበቁ፣ ከመመረዝ ቦዝነው አያውቁም

ይኵኖ አምላክ ከመንገሳቸው በፊት ኢትዮጵያ ነበረች

አቦይ ዓባይ! “እኛ ከሌለን ኢትዮጵያ የምትባል አገር አትኖርም” ብለው ነበር የቀባጠሩት?! እንዴት ተገለጠል? ሰንደቅ ዓላማችን ላይ የጨረቁት የአሽታሮት ኮከባችሁን ቆጥረው መሆን አለበት! አሁንም ታሪክ ላምጣልዎት! ሥረወ-መንግሥቱ በሰላም ከዛጔ ተወስዶ፣ ሸዋ ላይ ተደብቀው ከሚኖሩት የአክሱም ነገሥታት ዘር፣ በ1270 ዓ.ም ተመልሶ፣ ለይኩኖ አምላክ ከመሰጠቱ በፊት ኢትዮጵያ ከነሕዝቦቿ ነበረች። ለምን አንኮበርን እንደምትጠሏት ሕዝቡ ይወቅ። ከአክሱም ነገሥታት አንድ ሕጻን ብቻ ከዮዲት ሴይፍ አምልጦ ስለተሸሸገባት ነው። የአክሱም ዝርያን አጠፋን ስትሉ፣ የልጅ-ልጅ-ልቸውሐቀኛው አክሱማዊ ይኵኖ አምላክ ሊነግስ በመቻሉ ሸዋንና አንኮበር ጠምዳችሁ ቀራችሁ። ይመራል አይደል? ጋቱት! ዕውነቱ እሱ ነው። ኧረ አክሱም ለናንተ ምናችሁ ነው?? ከማፍረስ ውጪ፣ አንዲት ሰባራ ድንጋይ አንስታችሁ አልገነባችሁም! ይኸ ይታወቅ!|

ደብረ ብርሀን የኢትዮጵያ ዋና ከተማ ከመሆኗ በፊት ኢትዮጵያ ነበረች

የናንተ ቅደመ አያቶች እንደልማዳቸው ሸዋ ላይ የመሸጉትን የአክሱምን ነገሥታት ለማጥፋት እንዳይዘምቱ፤ የሰሩትን ከተማ እንዳያፈራርሱባቸው፣ ሲባል ነው መሰል፣ የኢትዮጵያ ነገሥታት በድንኳን ከአገር አገር እየተዘዋወሩ፣ ከላሊበላ በኋላ፣ ቋሚ ከተማ ሳይመሠርቱ፣ ኖሩ። ዳሩ ግን ሕልም ተፈርቶ ሳይተኛ አይታደርም  በ1434 ዓ.ም የነገሡት ንጉሠ ነገሥት ዘርዓያዕቆ፣ 42 ኪሎ ሜትር ከአንኮበር ርቃ በምትገኘው ደብረብርሀን ከመመሥረታቸው በፊት፣ ኢትዮጵያና ኢትዮጵያውያን ክፉውንም ደገኑም አብረው እያሳለፉ፣ ንጉሶቻቸው ከቦታ ቦታ እየተዘዋወሩ እንደ አብርሀም በድንኳን ቢኖሩም፣ ኢትዮጵያ ነበረች። እሶን ማስተማር አይቻለም። ወጣቱን ለማስተማር ነው እነዚህን የታሪክ ነጥቦችን አለፍ-አለፍ አድርጌ የምገርፈው!

የፋሲሏ ጎንደር ከመፈጠርዋ በፊት ኢትዮጵያ ነበረች!

አቦይ ዓባይ! ጎንደርን ለምንድነው የምትጠሏት፧ ኢትዮጵያ የመቶ ዓመት ታሪክ ነው ያላት ነበር ያላችሁን? ከየት መዘዛች? ከብብታችሁ?  “ትንሽ ዕውቀት በጣም አደገኛ ናት” ይላሉ፣ ፈረንጆች! በዚያ ላይ ዘረኝነት ተጨምሮበትማ፣ የቋያ እሳት ነው። የጥፋቱ መጠን አይነሳ! በ16ኛው ክፍለ ዘመን በፊት ኢትዮጵያ ነበረች። በ1636 አጼ ፋሲለደስ ጎንደርን ሳይመሠርቷት ሁሉ፣ ኢትዮጵያ ነበረች! ፋሲለደ ስ ደግሞ፣ የጠሩ የነጠሩ የጠላቶቻችሁ፣ የአክሱም ነገሥታት ዝርያ ናቸው። ሕዝቦችዋም አብረው ነበሩ። የጎንደሬ ጥላቻ ከየት እንደመነ ኮለል ብሎ ይታይዎታል? ጎንደርን ማን አፍራረሰው? ሁልተኛዋን አክሱም፣ የቀደሞዋ አክሱማውያን ሊነሱ ስለሆነ በዘዴ፣ በብልሀት፣ በሸር የናንተው ሚካኤል ስዑል ነበር። ኦሮሞ አይደለም! መርዛሞች!

ዘመነ-መሳፍንት

አቦይ ዓባይ! ኢትዮጵያን ለመበታተን ምን ያልሸረባችሁት ሤራ ቀረ? ምን ያልቧጠጣችሁ ቋጥኝ አለ? ብቻ አገሪቱ የቃል-ኪዳን አገር ናትና ተንኮላችሁ ከ900 ዓመት ጀምሮ እስከዛሬ እየከሸፈባችሁ መሆኑን እንዴት እናስረዳችሁ? እስቲ ማን ዘመነ-መሳፍንት ውስጥ ዶለን? ቀስ በቀስ የዮዲት ጉዲት ዲቃሎች ዝርያ ጎንደር ቤተመንግስት ዘልቀው ገብተው፣ ሿሚና ሻሪ ሆኑ። በ1769, ከዮዲት ጉዲት ርዝራዦች አንዱ የሆነው ሚካኤል ስዑል የተባለው ቅደመ አያታችሁ የ29 ዓመቱን አጼ ኢዮአስን ገድሎ፣ ሕጻን ልጁን አንግሶ፣ አሻንጉሊቱ አድርጎ፣ ኢትዮጵያን ዛሬ እናንተ እንዳደረጋችኋት፣ ዘመነ-መሳፍንት ውስጥ ሞጀራት። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይግባውና፣ እሱ እንዳሰበው፣ ኢትዮጵያ አልጠፋችም! ተረፈች! ሕዝቧም፣ ኦሮሞ፣ አማራ፣ ወላይታ፣ ከምባታ፣ ጎራጌ ... ሳይል፣ ሁሉም አብ በአንድነት በፍቅር እየኖረ፣ ዘመነ-ሳፍንትን አሳለፈ። ደም-መላሹ መይሳው ካሳ ተነሳ! እንደገና አንድ ሆን!

አጼ ቴዎድሮስ


የናንተን የመርዘኞቹን መርዝ የሚያበርስ፣ እግዚአብሔር ለኢትዮጵያ፣ አጼ ቴዎድርሶን በ1855 አነገሠ። ጎንደር ዕቅዳችሁን አፈረሰችባችሁ። ዘመነ መሳፍንት አከተመ። ጎንደርን ጥምድ አድርጋችሁ እንደዚህ የያዛችሁብት ምክንያት፣ ትላንት ሴራችሁን እንዳከሸፈባችሁ ዛሬም እንደትላንትና ሊያፈርስባችሁ ስለተነሳ ነውአጼ ቴዎድርስ የጎሳን ኬላ ሰባበሩ። ቅድመ አያቶቻችሁ ያመቻቸው ዘንድ የፈጠሯቸውን መሳፍንት አንድ በአንድ አንበርክከው አስገብሩ። ኢትዮጵያን እንደገና መልሰው ጠገኗት። እናንተም ወድ ትግራይ ተመልሳቸው የዋኹ ሕዝብ መሀል ተሸጉጣችሁ ቀናችሁን ትጠባበቁ ገባችሁ። ኢትዮጵያ ተረፈች። ሕዝቧም እንደተበታተነ አልቀረም። እንደገና ተሰባሰበ። እናንተ ግን ቂማችሁን እንደቋጠራችሁ ቀራችሁ። ዛሬም የሩዋንዳን ጦስ ትመኙልናላችሁ! ምነዋ አቦይ ዓባይ!






አጼ ዮሐንስ

ከጉዲት ዝርያ ነጻ የሆኑ፣ የተባረኩ፣ እናንተ ሳታስቡት፣ ከአፍንጫችሁ ሥር የፈለቁ፣ አጼ ዮሐንስ በ1871 ዓ.ም ነገሡ። አጼ ዮሐንስ፣ አጼ ቴዎድሮስ የጀመሩትን የኢትዮጵያን አንድነት ለማጠናከር፣ በጀግናው የጦር መሪያቸው፣ በአሉላ አባ ነጋ አማካይነት፣ ዛሬ ኤርትራ ተብላ የምትጠራውን አገር ሳይቀር በማስተዳደር፣ አስመራን መሥርተው የባሕር በራችንን ከጠላት እጅ ለመንጠቅ፣ የመረረ ውጊያ አካሄዱ። የውጪ ጠላትንም አሳፈሩ። ዶጋሊ ትመስክር። እናንተ መርዘኞች ግን፣ በወቅቱ የሠራችሁትን ወንጀል፣ ወደፊት ታሪክ ጎርጉሮ ያወጣታል። የዮዲት ጉዲት ወታደሮች የፈለሱባት አገር፣ ሱዳን፣ የኢትዮጵያን ድንበር ዘልቃ ገባች። ማን መራት? ጀግናው ዮሐንስ በመተማ ላይ ተሰው። አንገታቸው ተቆርጦ፣ ካርቱም ተውሰደ። ዛሬ የእናንተ እርጉሞቹ ልጆች የመሆናችሁ ዋናው ምስክር የሚሆነው፣ በጀግናው ዮሐንስ ጭንቅላት ተቆርጦ በተቀመጠባት፣ ካርቱም ላይ ሂዳችሁ ከገዳዮቹ ጋር አሸሻ ገዳሜ መደለቃችሁ ነው። ወያኔ ድል ቀንቶ አዲስ አበባ ሲገባ፣ ማን ነበር ድሉን ያከበረለት? ኢትዮጵያውያን ሳይሆኑ፣ ድግስ ደግሰው የጨፈሩት፣ ካርቱም ላይ ሱዳኖች ነበሩ። እናንተም ለውለታቸው፣ ከሰሜን እስከደቡብ ድረስ ያለውን ለም መሬታችንን ወስዳችሁ ለመሸላም ታጥቃችሁ ተነሳችሁ። የዮዲት ጉዲት ርዝራዦችማ ባትሆኑማ፣ ተቆርጦ በተቀመጠው በዮሐነስ ሬሳ ላይ ባልጨፈራችሁ ነበር።


አጼ ምኒልክ

ምኒልክ ተወልዶ፣ ባያነሳ ጋሻ
ግብሩ ዕንቁላል ነበር፣ ይኸን ጊዜ አበሻ!

አጼ ይሐንስ በመሞታቸው፣ አይቶቻችሁ እንደተመኛችሁት፣ ኢትዮጵያ አልተበታተነችም። አልጠፋችም! አጼ ምኒልክ በ1889 ነግሰው፣ የዮሐንስን ጋሻ አነሱ! ጣሊያን ዘመተባቸው። ኤርትራና ትግራይ ውስጥ ከቀሩት የዮዲት ርዝራዦች፣ ብዙ ሹምባሾችና ሹልቅባሾችን አሰልጥና፣ ጣሊያን አስወጋችን። ኢትዮጵያን ልታጠፋ ከናንተ በተደራጀ ጦር አገሪቱን ወረረች። ምኒልክና ቆራጥ፣ የአማራ፣ የኦሮሞ፣ የወላይታ፣ የጉራጌ፣ የካምባታ (በናታቸው ምኒልክ ከምባቴ ነበሩ) እና ከእርጉማን ነጻ የሆኑ የትግራይ ልጆች በአንድ ላይ ተነስተው ጣሊያንን አድዋ ላይ ድል ነሱ! ኢትዮጵያ ተረፈች! ኢትዮጵያ ተፈራች! ኢትዮጵያ ታፈረች! ነጮች ሴቶች እንኳን እርስ በርስ ሲተራረቡ፣ “አንቺ ምንደነሽ? ንግስት ጣይቱ ነሽ፣ የምትጀባነኒው?” እስኪባባሉ ደረሱ። ንጉሷ ብቻ ሳይሆኑ፣ እቴጌይቱ ጭምር በዓለም ክቡራት (celebrity) ሆኑ። የናንተም አያቶች አፈሩ። ራስ ሥዩም መንገሻም፣ ከመናደዳቸው የተነሳ፣ ለጠላት ካደሩት አያቶቻችሁ የብዞዎችን እጅ ቆረጡ። ትግራይን  ከናንተ የዮዲት ርዝራሾች ጠብቀዋት ኢትዮጵያም ለተወሰነ አጭር ጊዜ “እፎይታን” አገኘች። አገር አማን ሆነች። እባብ ሙቶ አይሞትምና፣ አያቶቻችሁ ግን፣ እንደእፉኝት ልጆች አፈሯን እየቃሙ አንሰራሩ። ጊዜ ጠበቁ። ጊዜ ተለዋዋጭ ናትና እንደገና ዕድል አገኙ።

አጼ ኃይለሥላሴ

አቦይ ዓባይ፣ እንደምንም በታሪክ ፈረስ እያጋለብን እርስዎ ጋ ልንደርስ ነው። እንዴት ነው፣ ልብዎ ድው-ድው! ማለት አልጀመረም? አይዞዎት፣ የእርስዎን ቤተሰብ ታሪክ በድንብ ስለማላውቅ፣ ለትግራይ ወንድሞቼና እህቶቼ ትቼዋለሁ። ስለሌሎቹ ጓደኞችዎ አባቶች ግን በግልጽ እነግርዎታለሁ። ብቻ እርስዎ በትዕግስት ያንብቡ።ኢትዮጵያና ሕዝቧ፣ ከእናንተ የውስጥ ቦርቧሪ ከሆናችሁት ከዮዲት ዘር ርዝራዦችና ከውጪ ወራሪ ኃይሎች ተርፋ፣ አጼ ኃይለሥላሴ ዘመን ደርሳ በ1930 ዓ.ም ነገሡ። ብዙም ሳይቆዩ፣ ታድላችሁ ጣሊያኖች በ1936 ዓ.ም ወረሩን። ከጣሊያን ጋር ማን ተሰልፈ መሰለዎት። አሁንም የዮዲት ዘር ርዝራዦች። ኃይለሥላሴ ጉግሳን፣ የንጉሡ አማች መሆን ባንዳ ከመሆን አላገደውም። ኢትዮጵያን ሊያጠፋ ጦሩን ይዞ ከጣሊያን ጋር ተሰለፈ። ጉድ ሳይታይ መስከረም አይጠባ። ሌላ ማን ነበር? አስረስ ናቸዋ! አስረስ ማ? ባሻ አስረስ ተሰማ! የመለስ ዜናዊ አያት! እስቲ ይኽቺን ጠቆም አድርገው ጉድዎን ይመልከቱ። http://wondimumekonnen.blogspot.co.uk/2012/02/basha-asres-tessema-meles-zenawis-banda.html። እንዲያም ሆኖ ታዲያ ኢትዮጵያ፣ አማሮችን፣ ኦሮሞዎችን፣ ጉራጌዎችን፣ ያልተረገሙ ትግሬዎችን፣ ወላይታዎችን ደም ገብራ፣ ተረፈች። ሕዝቧም አብሮ እንደናት ልጅ ተፋቅሮ፣ተቃቅፎ መኖሩን ቀጠለ። እኔና እርስዎ በዚህ ዘመን ነበር የተወለድነው።



ደርግ

በዕውነቱ የደርግ ወደ ሥልጣን መምጣት የናንተ ሠርግና ምላሽ ነበረ። ኢትዮጵያ ሌላ ትልቅ ፈተና የተደቀነባት፣ የወታደራዊው ደርግ፣ የንጉሠ ነገስቱን መንግሥት ገልብጦ ሥልጣን ላይ በ1974 ሲወጣ ነበር። ወታደር የአገርን ድንበር ጠብቅ ተብሎ መሣሪያ ሲሰጠው፣ አንዳንዴ ጥሩ ነገር አደርጋለሁ ብሎ ወደ አስተዳደር ይመጣና፣ በወታደራዊ ሥርዓት ሲቪሉን ሰጥ-ለጥ አድርጎ ሊገዛ ሲነሳ ብዙ ነገር ያጠፋል። ደርግም ደግ የሠራ መስሎት ሕዝባችንን ለሥቃይ ዳረገ። በዚህን ጊዜ ነው እናንተ የዮዲት ጉዲት ዘር ርዝራዦች አንዳንድ የዋሆችን በዘረኛነት አማልላችሁ፣ የሌለ ታሪክ ፈጥራችሁ ራሳችሁን ብቅ ያደረጋችሁት። በተንኰል፣ በሸፍጥ፣ በማታለል፣ “ከጭቁን ብሔር ብሔረሰቦች” የተውጣጡ ተዋጊዎች አደራጃችሁ። ሕዝቡ በበለጠ ደርግን እንዲጠላ፣ የሐዋዜንን የመሰለ የእልቂት ትርዒት አዘጋጃችሁለት። የኢትዮጵያ ውድቀት ወለል ብሎ ታያችሁ። ኢትዮጵያን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ልትበታትኗት ዕቅድ አውጥታችሁ፣ እርስዎና የስጋ ዘመድዎ መለስ ተነሳችሁ። መጀመሪያ ማርክሲስት ሌኒኒስትን ካባ አጠለቃችሁ። አላዋጣ ሲል አውልቃችሁ ጣላችሁ። ድሞክራቶች ነን አላችሁ። የትግራይ ሕዝብ ተራበብን ብላችሁ ስታለቅሱ፣ በቦብ ጊልዶፍ የተሰበሰበው ገንዘብ እንዳለ ተሰጣችሁ። በዚያ ገንዘብ እህል ገዝታችሁ ሕዝብ የቀለባችሁ ሳይሆን መሣሪያ እንደገዛችሁበት በዚያን ጊዜ የጦር መሪዎቻችሁ የነበሩት ሳይቀሩ በቢቢሲ መሰከሩባችሁ። የአዛኝ ቅቤ አንጓቾች! ያስታውሷታል አይደል ይህቺን? http://news.bbc.co.uk/1/hi/8535189.stm ጨካኝ አረመኔዎች። ኢትዮጵያ እጃችሁ ላይ ወደቀች። ለመውጣት ትፍጨረጭራለች! እናንተም ታስፈራሩናላችሁ!

አቦይ ዓባይ! ከ1991 ዓ.ም እስከዛሬው 2016  ደረስ፤ የኖርናት፣ የሞት፣ የእሥራት፣ የስቃይ፣ የስደት ዘመን፤ ዘመነ-ወያኔ ዘመነ ጨላማ ተብሎ ይጠራል። በታሪካችን በምሬት ወደፊት ተመዝግቦ ሲታወስ ይኖራልላለፉት 25 ዓመታት፣ ኢትዮጵያ ላይ የአደጋ ድባብ ተዘርግቷል። ታጥቃችሁ የተነሳችሁት ኢትዮጵያን ለመበታተን ነው። የዘረኝነትን አፓርታይድ ሕገ-መንግስት እንዳለ ገልብጣችሁ፣ ሥራ ላይ አዋላችሁ። ኢትዮጵያውያንን በክልል (Bantustand Homeland) ገለላችሁ። ከፋፍላችሁ የዘረፋ መረባችሁን ዘረጋችሁ። የወራሪ ጣሊያን ጌቶቻችሁን ዕቅድ በተግባር ተረጎማችሁ። አብረን ስንኖር ልትበዘብዙን፣ ካልሆነ ልትበታትኑን የእኵይ ተግባራችሁን ተያያዛችሁ። ይኸ ተንኰላችሁ፣ ቀኙ ክንፋችሁ ሻዕቢያ እርትራን ከመንገንጠሉ ባሻገር፣ ሌላው ሕዝብ “አንለይም!” በማለቱ እንዳሰባችሁት፣ አልተላለቅም፣ አልተበታተንም። እንደናንተ እንደናንተማ፣ አንዱን ዘር ከአንዱ በማጋጨት ለማጫረስ ነበር። እስከአሁን ኢትዮጵያውያን ሳይበታተኑ የሚኖሩበት ምክንያት በናንተ ሰብሳቢነት ሳይሆን፣ ሕዝቡ በኢትዮጵያዊነት ፍቅር ሐረግ ስለተሳሰረ ብቻ ነው። ይኸን ሐቅ እናንተም ታውቃላችሁ፣ እኛም እናውቃለን።

እስቲ ስላንዷ እህት፣ ለኢትዮጵያዊነት መስክራ በጨለማ ስላዋረዳችኋት ኦሮሞ፣ የደረሰባትን ጉድ ላስታውስዎ፣ አቦይ ዓባይ። በ2005 ዓ.ም ምርጫ የልብ ልብ ተሰማችሁና ከተቃዋሚው ጋር በቴሌቪዢን ክርክር ገጠማችሁ። የኦሮሞ ብሔራዊ ኮንግሬስ አባል የነበረቸው እህት ለበለበቻችሁ። የዮዲት ጉዲት ዝርያ ልጆች ከሆኑት አንዱ ጓዳችሁ፣ “ተመልከቷት! ለኦሮም ሕዝብ እስከመገንጠል ድረስ ያመጣነውን ዕድል የሚሰጠውን አንቀጽ 36ን ልትቀለብስብን ነው” አለ። አጂሪት፣ “አንቀስ 36 ለኛ ለኦሮሞዎቹ ምናችንም አይደለም። ያ ለእንደእናንተ ዓይነቶቹ አናሳዎች ይጠቅም እንደሆነ እንጂ፣ እኛን አብላጫዎቹ የኦሮሞ ልጆች የኢትዮጵያ ግድግዳና ማገር ነንና ለመገንጠል እሱ አያስፈልገንም” ብላ ዕውነተኛውን በውስጧ የሚንበለበልውን ኢትዮጵያዊነትን ነገረቻችሁ። ሕዝብ ሳቀባችሁ። አንጀታችን ራሰ። ጨለማን ተገን አድርጋችሁ ያደረሳችሁባትን ኢሰብአዊ ውርደት እናንተው ታውቁታላችሁ።  

አቦይ ዓባይ! ግድ የላችሁም! እናንተ ጥፉ እንጂ፣ ኢትዮጵያ እንደሩዋንዳ ትሆናለች ብላችሁ አትስጉ። በታታኙ ዞር ካለልንማ እኛ እንሰባሰባለን። እናንተ ዘረኞቹ የዮዲት እፉኝት ልጆች እስካላችሁ ሰላም አይኖርም። እኛም አንተኛላችሁም፣ እናንተም አትቦዝኑም።

እስቲ ትንሽ ስለዚህ ስለሩዋንዳ ማስፈራሪያ ዘፈናችሁ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ እንሂድበትና እናሳርፋችሁ። ለመሆኑ፣ ያንን የዘር ማጥፋት አዋጅ ያወጀው ማን ነበር? ሑቱዎች። በአገራችን፣ ስለዘር ማጥፋት የሚያቀነቅነው፣ “ልክ እናስገባዋለን”፣ እያለ የሚዝተው፣ አማራን እንጨፈልቀዋለን ብሎ የሚደነፋው ማነው? የዮዲት የልጅ ልጅ ወያኔ! ታዲያ በአገራችን ማን ነው የኛ ሑቱ? ወያኔዎች! ያ የዘር ማጥፋት ወንጀል ሲታወጅ፣ ማን ነበር ሥልጣን ላይ የነበረው? ሑቶዎች! ዛሬስ ማነው ኢትዮጵያው ውስጥ ሥልጣን ላይ ያለው? ወያኔ! ታዲያ ማነው የኛ ሑቱ? ወያኔዎች! በሩዋንዳ ውስጥ እስከአፍጢሙ የታጠቀው ኃይል ያኔ ማን ነበር? ሑቶዎች፣ ዛሬ ኢትዮጵያ ውስጥ እስከአፍ-ገደቡ የታጠቀው ማነው። ወያኔዎች! ታዲያ የኛ ሑቱዎች ማን ናቸው? ወያኔዎች! ቱትሲዎች ጠላታችሁ ናቸው ብሎ ልጆቹን ያስተምር የነበረው ማን ነበር? ሑቶዎች!  “አማራ የትግራይ አንድ ቁጥር ጠላት ነው” እያለ የሚያስተምር ማነው? ወያኔ! ታዲያ የኢትዮጵያ ሑቶዎች ማናቸው? ወያኔዎች! እኛ ከሌለን ትጠፋላችሁ እያለ ትግሬዎችን የሚያስፈራራው ማነው? ወያኔ! እኔ ወላጆቼ ሲያሳድጉኝ፣ አንድም ቀን ትግሬ ጠላትህ ነው ብለውኝ አያውቁም። ሌሎቻችንም እንደዚሁ ነው ያደግነው። እኔ ያደግኩት፣ “ጣሊያን ጠላትህ ነው” እየተባልኩ ነው። እኔ በወንድሜ ትግሬ ላይ ትንሿ ጣቴን አላነሳም። 

አንድ ነገር ሰምቼ በጣም አዘንኩ። “ገረብ ገረብ ትግራይ፣ መቃብር አምሀራይ”። በስመ አብ ወወልድ መንፈስ ቅዱስ። ከዚህ በፊት የትግራይ ተራሮች የአማራ መቃብር የሆኑት፣ ጣሊያን በትግራይ በኵል ስትወረን አድዋ ላይ፣ ሌላ ጊዜ ደግሞ፣ ወያኔዎች ባመጡብን ጣጣ፣ ሻዕቢያ ትግራይን አጠቃች፣ ትምሕርት ቤት አቃጠለች ሲባል፣ ከወንደሞቹ ከትግሬዎች ጎን ለመቆም ተሰልፎ ሕይወቱን ሲሰዋ የትግራይ ተራሮች መቃብሩ ሆነው ነበር። ከዚያ ባሻገር አይታሰብም። ዳግማዊ ሑቱዎች ዞር በሉልን። እኛ አንጨራረስም።

ወያኔና የትግራይ ሕዝብ

አቦይ ዓባይ! ሌላ ደግሞ አንድ አንጀት የሚያሳርር ነገር፣ ወያኔዎች ስትቀባበሉት እንሰማለን። ክፉዎች ናችሁ! ሕወሐት ማለት ትግራይ ነው፣ ትግራይ ማለት ሕወሐት ነው ብላችሁ ታቀነቅናላችሁ። አዪዪዩዩ! ትግሬ ሁሉ እኮ የዮዲት ጎዲት ወታደሮች ዲቃላ ዝርያ አይደለም። አንድ ወንድሜ ንግግርዎን ሰምቶ ምርር ብሎት፤ ምን አለ መሰለዎት? “እርግጥ ወያኔ ከትግራይ ነው የተገኘው። ነገር ግን ትግሬ ሁሉ ወያኔ ነው ማለት፣ ቅማል ከጸጉር ነው የሚገኘውና፣ ጸጉር ሁሉ ቅማል ነው እንደማለት አይሆንም” ብሎ አሳቀኝ። ንጹሕ ኢትዮጵያውያን እኮ ዛሬም ትግራይ ውስጥ ሞልተዋል። ዕውሮች ናችሁ ልበል? ብዙው እኮ የትግራይ ሕዝብ “አትወክሉኝም” እያላችሁ ነው። አታስተውሉም? አትሰሙሙ? የድንቁርና ኩካችሁን ከጆሮአችሁ በአንገት በላይ ሐኪም አስጠርጋችሁ ስሙ እንጂ! ወያኔና ትግሬ አንድ ቢሆን ኑሮ፣ አፈር ዲሜ ሊያስግጣችሁ ከትግራይ ልጆች በተገነባ፣ ከትግራይ ላንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ነቅሎ ሊጥላችሁ፣ በዚያውም ኢትዮጵያን ለመታደግ ቆርጠው በተነሱ የትግራይ ታጋዮች ኤርትራ ውስጥ በመዘጋጀት ላይ ያለው ዴምህት ባልተፈጠረ ነበር። በዘፈናቸው ላዛናናዎት? https://www.youtube.com/watch?v=ANLgxokrJW8::

ትግራ ሕወሐት ቢሆንና ሐወሐት ትግራይ ቢሆን፣ አረና ትግራይ በክልላችሁ ተፈጥሮ እንደ አብርሀ ደስታ ያሉ ትንታግ ኢትዮጵያውያን ባልተጋፈጧችሁ ነበር። አስገደ ገብረ ሥላሴ፣ ገብሩ አሥራት፣ ስዬ አብርሀ፣ ተስፋዬ አጽብሀ፣ ገብረመድኅን አራአያ፣ አረጋዊ ብርሀ፣ ጊዴይ ዘርዐጽዮን ... የመሳሰሉት አረጋዊያንና ምሑራን “አትወክሉንም” እያሉ ባልተጋፈጧችሁ ነበር። ለመሆኑ፣ ታዳምጣላችሁ? “አትወክሉንም” ያሏችሁን የሁለት የትግራይ ልጆችን ቃለ ምልልስ ሰምታችኋቸውል? ካመለጣችሁ ኧረ እንደገና ስሟቸው! https://youtu.be/_TFyKXb3WuE   

ማጠቃለያ!

አቦይ ዓባይ! መቼም እኔ ሲፈጥረኝ ደግ ነኝ። የምያዋጣውን ሳልነግርዎት ባልፍ ይቆጨኛል። ያ “አማራና የኢትዮጵያን ኦርቶዶክስ ሁለተኛ እንዳይነሳ አከርካሪውን ሠብረናል” ስትሉ ያወጃችሁበት ዕምነትና ሕዝብ፣ መጥያፋችሁ ነው። ለነገሩስ፣ እስላሙንም ሆነ፣ ኦሮሞውን መቼ ማራችሁት! ለመሆኑ፣ የትግራይ ሕዝብ፣ የኦርቶዶክስ ዕምነትን አጥብቆ እንደሚከተል አልተገነዘባችሁም፣ ወይስ እነዚያን ካባ አልብሳችሁ በየገዳማቱ በሰገሰጋችኋችሁ የበግ ለምድ የለበሱ ተኵላዎቻችሁን ተማምናችሁ ነው እንደዚያ የተጨማለቃችሁት? አማራን ተውት። ስለዚያ አከርካሪውን ሰብረነዋል ስለምትሉት ዕምነት፣ ትንሽ ልንርዎት። በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ቅዳሴ ውስጥ አንድ ስንኝ አለ። ምን ይላል መሰለዎት? አግርር ጸራ ታህተ እገሪሀ፤ እቀብ ሕዝባ ወሠራዊታ ለሀገሪትነ ኢትዮጵያ:: ያንን አብረው የሚዘመሩት፣ ካባ ያስጠለቃችሁ ተጋደልቲና ፓትርያርክ አድረጋችሁ የሾማችኋቸው ሳይቀሩ ነው። እንደነናተ ያሉትን ጠላቶቿን እየረገሙ ነው። እርግማኑ ደግሞ መሬት ላይ ጠብ አይለም። ቅስፍ ነው የሚያደርገው። ሹመኛ ፓትርያርካችሁንና፣ የምታመልኩትን መልስ የቀሰፈው ያ ዕምነት ነው። እናንተ ከውስጥ የበቀላችሁባት የእፍኝት ልጆች ይቅርና፣ ለፋሽስቱ ሙሶሊኒም አልበጀ። ኢትዮጵያን በመርዝ ጋዝ ያጋየው ሙሶሊኒ፣ ነግሮች ሁሉ ሲደበላለቁበት፣ እናንተ ዛሬ፣ ጦራችንን ይዘን ወደሕዝባችን፣ ወደ ትግራይ እንገባለን እንደምትሉት፣ ሸሽቶ ወገኔ ነው ወደሚለውን የጣሊያንን ሕዝብ ሸሽጉኝ ሲል ምን ያድረጉት መሰላችሁ? የራሴ ሕዝብ በሚለው ነው ሙሶሊኒ ከነፍቅረኛው ተዘቅዝቆ የተሰቀለው። አዩአቸውማ በደም የተለውሱትን የሙሶሊኒና የፍቅረኛውን ሬሳ? የናንተም ዕጣ ፈንታ ያ ነው። የዋልድባ ገዳማት መነኰሳት ሬሳ ይጮኻል!


በስሙ እየነገዳችሁ አትኖሩም። የትግራይ ሕዝብ፣ ከኦሮሞው፣ ከአማራው፣ ከጉራጌው፣ ከወላይታው፣ ከሀዲያው፣ ከሶማሌው፣ ከኮንሶው ለናንተ ሲል አይጣላም። ቀፈታችሁን ለመሙላት በስሙ ብትምሉ ከወንድሞቹና ከእህቶቹ ጋር አቃቅራችሁ ይሸሽጉናል ብላችሁ ማሰባችሁ በራሳችሁ ላይ የሞት ፍርድ እንደመፈረዳችሁ ቁጠሩት። እያንዳንዳችሁን፥ የዮዲት ጉዲትን ውልዶች የሚያጋጥማችሁ፣ ሙሶሊኒንና ፍቅረኛውን ያጋጠመው ዕድል ነው። ያንን በዕርግጠኝነት ነው የምነግራችሁ። ለምን ሲባል? ባዶ ስድስት በሚባለው እስር ቢታችሁ ውስጥ በብዙ ሺ የሚቆጠር የጨፈጨፋችሁት የትግራይ ቤተሰብ፣ ጊዜ እየጠበቀ ይገኛል። በወያኔ የታረዱት የትግራይ ልጆች ደም ይጮኻል! ትግሬ ነህ ብላችሁ አታላችሁ ባዶ ስድስት ውስጥ የጨፈጨፋችሁት የወልቃይት ጠገዴ ወጣቶች ደም ይጮኻል! ምናልባት ታላቅ ወንድሙን የገደላችሁብት፣ በረከት ስምዖን (መብራቱ ገብረሕይወት) የወንድሙ ደም ሳይከረፋው፣ ወይ ሆዱ አድሮወይም ዘረኝነት በልጦበት አጋልጋያችሁ ቢሆን፣ የትግራይ ሕዝብ የልጆቹ ደም እየከረፋው የሚሸሽጋችሁ ዋሻ አይሆንላችሁም። የመጀመሪያው የስቃይ ገፈታችሁን የቀመሰው እኮ የትግራይ ልጅ ነው! ትግራይ ውስጥ ሞት ይጠብቃችኋል። አትሞኙ። ወደዚያ እንሄዳለን ብላችሁ አታስቡ፣ አቦይ ዓባይ!


የመፍትሔ ሀሳብ አለኝ። ዕርቀሰላም አውርዱ ቢዬም ትንፋሼን አላረክስም። ግን እመክራችኋለሁ። ገንዘባችሁን በጊዜ አሸሽታችኋል። ጎበዞች! ልጆቻችሁንም በጊዜ ዞር አድርጋችኋል። ብልጦች! ደም ጠግባ መንቀሳቀስ እንዳቃታት ትኋን ተይዛችሁ ከመፍረጣችሁ በፊት፣ ጓዛችሁንና ጉዝጉዛችሁን ሰብስባችሁ፣ በጊዜ ውልቅ ችሁ ጥፉ። ኢትዮጵያ ሩዋንዳ አትሆንም። አበቃ!

ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዚአብሔር ስትዘረጋ እግዚአብሔርና ዕውነት ከሕዝቧ ጋር ይሆናል።