ሕዳሴ ግድብ፣ ዓባይ፣ ኦርቶዶክሳዊት
(October 16, 2025)
This blog is about Ethiopian current affairs, literature, poetry, political, social and cultural issues.
ሕዳሴ ግድብ፣ ዓባይ፣ ኦርቶዶክሳዊት
(October 16, 2025)
አቡነ ፋኑኤል የጎረጎሩት ዓሣ ዘንዶ ሆኖ ወጣ!
August 2, 2025
ሐምሌ ፲፱፱ ፳፯፻፯ ዓ.ም.
መግቢያ
አቡነ ፋኑኤል በቨርጂንያ ስቴት አሌክሳንደርያ ከተማ የምትገኘው የሐመረ ኖኅ ኪዳነ ምሕረት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ በነበረዉ በታደሰ ሲሳይ ላይ በሶስት ካህናት የተላለፈውን ዉግዘት ዉድቅ ለማድረግ ሲሉ አቡነ ፋኑኤል የሰጡት የዉሸት ምክንያት የሚቀጥለው ነው። ይህም የአቡነ ፋኑኤልን ዉሸት ዛሬ የትግራይ ቤተክርስቲያንን ገንጥለው በሚመሩት በአባ ሰረቀ ብርሀን “እውነትና ንጋት” በሚል ርዕስ የተጻፈዉን መጽሐፍ እምቅ የሆነውን ታሪካዊ ሂደት እንደገና ቀስቅሶታል። አቡነ ፋኑኤል ሐሰታቸውን በገለፁበት ደብዳቤው ላይ እንዲህ ብለው ጽፈው ነበር። “...ሦስተኛ አስተርአየ ጽጌ ቀድሞ ቄስ የነበሩ ሲሆን በአሁኑ ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት ቀደም ሲል የሰሜን አሜሪካ ሊቀ ጳጳስ በነበሩበት ጊዜ አስተርአየ ጽጌ በሃይማኖት ምክንያት ተወግዘው ክህነታቸው የተያዘ ሆኖ እያለ አሁንም በድፍረት የሚቀድሱ መሆናቸው ሀገር ያወቀው ጉዳይ ሆኖ እያለ አውግዣለው ሲሉ ኃፍረት የማይሰማቸው በመሆኑ ድርጊቱ አሳዛኝ ሀኖ አግኝተዋለን…” የደብዳቤውን ሙሉ ይዘት ለማግኘት የሚቀጥለውን ሰንሰለት ይጫኑ “አባ ፋኑኤል የታደሰ ሲሳይን ውግዘት ስለማንሳት የጻፉት ደብዳቤ"።
አቡነ ፋኑኤል ስለ ቀሲስ አስተርአየ ጽጌ ያቀርቡት የሐሰት ሽፋን ከነበረው ሁኔታ ጋር በፍፁም የራቀ ነው። በአጭሩ ጉዳይ እንዲህ ነው። የዉግዘቱ መነሻ በቪርጂኒያ፣ በዲሲና ሜሪላንድ የሚኖረውን ህዝበ ክርስቲያን ያመሰው የታደሰ ሲሳይ ዉድቀት ነበር። በስብሰባው ላይ ተገኝተው ህዝበ ክርስቲያኑ ያቀረበውን የታደሰ ሲሳይን ስህተት ቤተ ክርስቲያናችን በምትመራባቸው መጻህፍት መዝነው ህዝባዊውን ውግዘት ካጸደቁት ቀሳውስት አንዱ ቀሲስ አስተርአየ ናቸው። ቀደም ሲል ከዛሬ 20 ዓመት በፊት መስከረም 22 ቀን 1997 ዓ/ ም (October 2, 2004 CE) በወቅቱ የሰሜን አሜሪካ ሊቀ ጳጳስ በነበሩት በአሁኑ ፓትርያርክ አቡነ ማትያስና በካንሳስ ኪዳነ ምሕረት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ በነበሩት በቀሲስ አስተርአየ ጽጌ መካከል ውዝግብ ተነስቶ ነበር። ይህንን ተከትሎ አቡነ ማትያስ በቀሲስ አስተርአየ ጽጌ ላይ ጊዚያዊ እገዳ አስተላለፉ። የደብዳቤውን ሙሉ ይዘት ለማግኘት የሚቀጥለውን ሰንሰለት ይጫኑ አቡነ ማትያስ ደብዳቤ በቀሲስ አስተርአየ ላይ የጣሉት ጊዚያዊ እገዳ።
ያ ዉዝግብ በሊቀ ሊቃውንት ወርቅነህ ሰብሳቢነት ይመራ በነበረው ማህበረ ካህናት ጉባኤ ተመርምሮ የቀሲስ አስተርአየ ትምህርትና እምነት ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ እምነታና አስተምሮ እንዳልወጣ አረጋግጧል። ሙሉ ዉሳኔውንም በአቡነ ጳውሎስ ይመራ ለነበረው ሲኖዶስ ከመረጃዎች ጋር አያይዞ አዲስ አበባ ልኳል። የማህበረ ካህናቱ ጉባኤም ያንኑ ውሳኔ አያይዞ በስደት ለሚገኘውም ሲኖዶስም ልኳል። አቡነ ይስሐቅ ይህንን ተንተርሰው በቀሲስ አስተርአየ ላይ ተጥሎ የነበረውን የ6 ወር ጊዚያው እገዳውን አነሱት። የደብዳቤውን ሙሉ ይዘት ለማግኘት የሚቀጥለውን ሰንሰለት ይጫኑ አቡነ ይስሀቅ ለክንሳስ ህዝብ በላኩበት ወረቀት እግዳው መነሳቱንተረጋግጧል።
አቡነ ማትያስ በዘንዘርጡ ዳንኤል ክብረትና ከፈለኝ በሚባለው ቄስ ምክር እየተመሩ በሊቀ ሊቃውንት ወርቅነህ ሰብሳቢነት ይመራ ከነረው ማህበረ ካህናት ጉባኤ ጋር ተጋጩ። በአቡነ ማትያስና በማህበረ ካህናቱ መካከል ከፍተኛ ዉዝግብ ተነስቶ ማህበረ ካህናቱ አቡነ ማትያስን ገስጿቸዋል። በዚህም ምክንያት በአቡነ ማትያስና በማህበረ ካህናቱ መካከል በተነሳው ከፍተኛ ዉዝገብ ዉስጥ አባ ሰረቀ ብርሀን ዋና ተዋናይ ነበሩ። በዚህ ዉዝግብ ከተሳተፉት ዉስጥ በሞት ከተለዩት ከአቡነ ይስሐቅ፣ አቡነ ገብርኤል፣ አቡነ ጳውሎስና መጋቢ አእላፍ መክብብ በስተቀር ሁሉም በሕይወት ለምስክርነት አሉ። በአቡነ ጳውሎስ ይመራ የነበረው ሲኖዶስ በሊቀ ሊቃውንት ወርቅነህ ሲመራ በነረው የካህናት ጉባኤ ዉሳኔ በመስማማት፣ በዳንኤል ክብረትና በከፈለኝ ምክር የሚራመደውን የአቡነ ማትያስን ሃሳብ ዉድቅ አድርጎታል። አቡነ ጳውሎስ አቡነ ማትያስንና ዳንኤል ክብረትን በቃል ገስጿቸዋል።
አቡነ ማትያስ በዘንዘርጡ ዳንኤል ክብረትና በከፈለኝ እየተመከሩ የሚያራምዱትን ሀሳብ ባለማቆማቸው አቡነ ጳውሎስም ሊያስቆማቸው ባለመቻላቸው ጉዳዩ የተነሳበት የካንሳስ ኪዳነ ምሕረት የሚቀጥለውን አደረጉ። ይህ የተነሳው ጉዳይ ቤተክርስቲያናችን ጥንታዊት ኦሮዶክሳዊት መሆኗን ከምታረጋግጥባቸው አስተምሮዎች ዋናውና አንዱ ስለሆነ ለአቻዎቿ ለአሕት ባተክርስቲያንና ለባዛንታን ኦርቶዶክስ አብያተ ክርስቲያናት የካንሳስ ኪዳነ ምሕረት ቤተክርስትያን ምዕመናን ጉዳዩን አቀረቡት። አሐት አብያተ ክርስቲያናትም በሊቀ ሊቃውንት ወርቅነህ ሰብሳቢነት ይመራ በነረው ማህበረ ካህናት ጉባኤ ተመርምሮ የተወሰነውና የቀሲስ አስተርአየ ትምህርትና እምነት ከኦርቶዶክስ እምነታና አስተምሮ እንደሆነ አረጋገጡ። እስከዚህ ቅጽበት ድረስ ቀሲስ አስተርአየ ጽጌ በአቡነ ማትያስ የተላለፈባቸውን የ6 ወር ጊዚያዊ እገዳ የተሳሳቱ መሆኑን እየገለፁ እገዳውን በማክበር ወደ ቤተመቅደስ ገብተው ኪዳንም አልደርሱም ቅዳሴ አልቀደሱም። ይህንንም በማድረጋቸው ማህብረ ካህናቱ በጣም አድንቆአቸዋል።
አባ ፋኑኤል ግብረ አበራቸውን ታደሰ ሲሳይን ለመሸፈንና ቆሞስ ለማድረግ ሲሉ ይህንን ሁሉ በቅርብ ሆነው እያወቁ እንዳልነበረ አድርገው የተነሳውን ጊዜዊ እገዳ ወደ ዉግዝት ቀይሩት። አቡነ ፋኑኤል ግብረ አበራቸውን ለመሸፈን ብቻ ሲሉ የአቡነ ማትያስን ስም ለስህተታቸው መሸፈኛ ማድረጋቸው የመጨረሻ ሀጥያት ነው።
ይህ የአቡነ ፋኑኤል ተደጋጋሚ ሐሰት “እውነትና ንጋት” በሚል ርዕስ በአባ ሰረቀ ስም የታተመችው መጽሐፍ የያዘችውን እምቅ ጉዳይ እንደገና እንዲቀሰቀስ አድርጎታል። ከዚህ ቀደም አቡነ ፋኑኤል የሚያደርጉትን ስህተት እንዲያርሙ የተገሰጹበት አባ ፋኑኤል አዲስ ተክል ናቸው የሚለውን ያንብቡ።
ከዚህ ቀጥሎ በ“እውነትና ንጋት” የቀረበውን የመጻህፏን ሐተታ አጠር ባለ መልኩ የቀረበ አስተያየት ስለሆነና አቡነ ፋኑኤል የነኩትን በሚከተሉት ገጾች ላይ ቀርቧል።
ቅዱስ ጳውሎስ “ወኩሎ ዘተጽህፈ ለተግሳጸ ዚአነ ተጽህፈ” ( ሮሜ ) እንዳለው የተጻፈ ሁሉ ትምህርት የተጠሙት እንዲማሩበት፤ ሰነፎችና የሚስቱ እንዲገሰጹበት ተጻፈ። በየዘመኑና ትውልዱ የተነሱ ችሎታ ያላቸውም ይሁን ችሎታ የሌላቸው ጸሀፊወች በነበሩበት ዘመን ለመጉዳትም ብለው ይሁን ለመጥቀም በብዙ መንገድና በተለያዩ ምክንያቶች ይጽፋሉ። በዚህ ነባራዊ ሂደት ኢትዮጵያ ያለፈችባቸውን ዘመንን የትውልዱን ውድቀትና ትንሳኤ ለማሳየት የተመዘገቡትን ሁሉ ሰብስባ ይዛለች። ሰብስባ የያዘቻቸው መዛግብቶች በተገቢው መንገድ እየተጠቀሱ ጎጅውን ተጎጅውን ለማሳየት ቅዱሳት መጻህፍትን እንደ ምሳሌ ተጠቅማለች።
ለምሳሌ፦ መጽሀፍ ቅዱስ የእግዚአብሄርን ከሀሊነትና መጋቢነት ለማድነቅ፤ የሰውን ደግነትና ክፋት ለማሳየት፤ የቃየልና ገዳይነትና የአቤልን ተገዳይነት፤ የሙሴንና የአሮንን ብርታትና ድካም፤ የዳዊትን በጎ ባህርይና ክፉ ባህርይ ጎን ለጎን አስቀምጧል። በሀዲስ ኪዳንም የነጴጥሮስና የነጳውሎስንም ድካምና ብርታት የዲያብሎስም ስእል ሳይቀር እናያለን።
ይሁን እንጅ ሳጥናዔል ቃዔል ይሁዳ በቅዱስ መጽሀፍ ተመዘገበው ስለተገኙ ማንም በሳጥናኤል ወይም በቃኤል የሚጠራ የለም። ይህ ሁሉ የተዘጋጀው ለውድቀትና ለውርደት ክፉ ምሳሌ የሆነውን እንድንሸሸው፤ የሚጠቅመውን እንድንከተለው እንድንማርበት ነው። አሳሳች ተግባራቸው የሚታፈርባቸውና የምንሸሻቸው እንጅ ተጽፎ ስለተገኙ እንደምሳሌ የምንኮራባቸው አይደሉም።
በታላቁ ቅዱስ መጽሀፍ እንደምናየው፤ በጥንታዊነት ዜግነት ጉዟችን ውስጥ የተፈጸሙትን ውድቀትን ትንሳዔ የሚያሳዩ መዛግብቶች በጥንታዊት ቤተ ክርስቲያናችን በመጽሐፍ በቅኔ በገድል በተአምር መልክ ተጽፈዋል። እነዚህ ሁሉ ከኛ በፊት ባለፈው ዘመን የነበሩት ተከታታይ ትውልዶች ያለፉባቸውን የተጎዳዱባቸውን የተደጋገፉባቸውን የወደቁባቸውንና የተነሱባቸውን እንድናይባቸውና የእግዚአብሄርን ዘላለማዊ ታዳጊነት እንድናደንቅባቸው ተጽፈዋል።
በኛ ዘመንም ወያኔዎች በዘረጉልን የጥፋት ጎዳና ያለፍንባቸው ውድቀታችንና ትንሳያችን ለማሳየትም ሆነ ለግል ጥቅም በቤተ ክርስቲያናችን ባብነቱ ትምህርት ያላለፉ ልቅ በሆነ መንገድ እያዘጋጁ ለግል ጥቅም ሸጠው ለመጠቀም ሲሉ በደህናው ዘመን ይደረግ እንደነበረው በሊቃውንት ጉባዔ ሳይጠና ሳይመረመር አቋማቸውን እየቀያየሩ የመዝሙርና የተለያዩ ድርሳናት በመድረስ ቤተ ክርስቲያናችንን አጥለቅልቀዋታል።
ይህችም አባ ሰረቀ ያሳተሟት የዘገባ ስብስብ በዘመናችን የተከሰቱትን ነገሮች ውድቀታችንን ከምናይባቸው መዛግብቶች አንዷ ናት።
ከላይ እንዳልነው ቤተ ክርስቲያናችን ከምትደንቅባቸው ብዙ ነገሮች አንዱ ይህንን የመሳሰሉ ያለፈውን ውድቀት የሚያሳዩንን መዛግብት በግምጃ ቤቷ ሰብስባ በመያዟ ነው። ለተለያዩ ጥቅማ ጥቅም ሲሉ አውቀም ሆነ ሳያውቁ በጉባዔ አባቶች ያላስተማሩን ከውጭ እየለቃቀሙ አሳትመው ለገብያ ያቀረቧቸው በግምጃ ቤታችን በመገኘታቸው ፤ለነገረ መለኮትና ነገረ ማርያም ማስረጃ አድርገው በማቅረብ እራሳቸው ተሳስተው ምእመናንንም ከማሳሳታችን በቀር፤ የተጻፈውን ሁሉ ለትምህርት ለትግሳጽ በእቃ ግምጃ ቤታችን መጠበቃቸው መልካም ነው።
ይህች እውነትና ንጋት በሚል ስም የታተመችው መጽህፍ አሳታሚው ለምን ብለው እንዳሳተሙት መርምሮ እንዲደርስበት ለተመልካች እየተውን፤ ያለፍንባቸውን ብዙ ፈተናወች ከሚያሳዩን ብዙ መዛግብቶች አንዷ በመሆኗ እንድንገሰጽባት እንድንታዘብባትባና የገባውን ስህተት እንድናርምባት በውስጧ የያዘቻቸውን ዓበይት ቁም ነገሮች ገጽ በገጽ ለመመልከት እንሞክራለን።
ይህችን የመዛግብት ክምችት እውነትና ንጋት በሚል ስም አባ ሠረቀ ብርሃን ወ/ ሳሙኤል ታህሳስ 2004 በMega Printing P.L.C አሳተሟት። በአቡነ ጳውሎስ ዘመን በቤተ ክህነቱ አዳራሽ ተመርቃለች። መጽሀፏ በሶስት ክፍል ተደራጅታለች። ሰፊውንና የመጀመሪውን ውዝግብ የያዘችው ከገጽ 18 እስከ ገጽ 80 ያለው ክፍል ነው። ይህ ክፍል ወያኔ በጠቅላላ ቤተ ክርስቲያናችን ከፈጸማቸው ከብዙ አስተዛዛቢ ነገሮች አንዱን ክስተት ብቻ የያዘች የመዛግብት ክምችት ናት። ይህ የመዛግብት ክምችት ዋሸንግተን ዲስ ቅድስ ማርያም ደብር ቀሲስ ዶ/ ር አማረ በአስተዳዳሪነት ሊቀ ሊቃውንት ወርቅነህ የሃይማኖቱ የበላይ ጠባቂነት ይመሩ በነበሩበት ወቅት የተከሰተውን የመከፋፍያ ደባ የሚያሳይ ነው።
ወቅቱንና በመዛግብቱ የተጠቀሱትን ሰዎች የእውቀት ችሎታ አቋምና የተልእኳቸውን መሰረት ማመልከት ተገደደ።
ወቅቱ
ያ ወቅት በአቶ መለሰና በእሰየ (ወያኔ) መካከል የቤተ ሰብ መከፋፈል ተከስቶ እርስ በርሳቸው ሲናጎዱ የዋሁን የኢትዮጵያን ህዝብ የእርስ በርስ መታግያቸው የሚዳ ሳር ያደረጉበት ወቅት ነበር። አቡነ ጳውሎስ ከመለሰ ጋራ አቡነ ማትያስ ከእሰየ ጎራ ተሰለፉ። በዚህም ምክንያት“ገደሉን ሳያይ ሳር ብቻ እየተመለከተ ገደል እንደሚገባ በሬ አቡነ ማትያስም በወያኔ ደጋፊነታቸው ላይ የሚያስከትልባቸውን ሳይመለከቱ አቡነ ጳውሎስን “ከመከፋፈል ሌላ ማድረግ የመያውቁ ከፋፋይ” ብለው የዘለፉበት ወቅት ነበር።
በዚህ ወቅት በኢትዮጵያውያን መካከል በሰፊው ሲነገር እንደነበረው፦ በአቶ ስብሀት ነጋና በገብረ ኪዳን ደስታ ሰልጥነው ጎንደርን ጎጃምን ሸዋን እየሰለሉ ወያኔን ከምንይልክ ቤተ መንግስት ካስገቡት መነኮሳት መካከል አንዱ አባ ሰረቀ ነበሩ። በውስጥ ያልሆነ ነገር እያነሱ ህዝቡን ይከፋፍሉበት ወቅት ነበር። በአገር ውስጥ የነበራቸውን ተልእኮ ከፈጸሙ በኋለ ወደ አሜሪካ ተሻግረው የውጩን ህዝብ ለመሰለል እንደመጡ ይነገራል። ወደ አሜሪካ መጥተው ቅዱስ ጊዮርጊስ በሚል ስም ቤተ ክርስቲያን መስርተው በስደት ላይ ያለውን ህዝብ በመሰለል ላይ ነበሩ። በዚህ ወቅት የመከፋፈሉ መንፈስ በሰፊው ተሰራጭቶ ሁሉንም ከፈለው።
አባ ሰረቀ የመለሰ ደጋፊ ሲሆኑ ከአቡነ ማትያስ ጋራ የሚፋለጡበት ዘመን ነበር። በዚህ ወቅት የማይደግፉትን ጎራ ለማስያዝ ይጣደፉ ነበር። በዚህ ወቅት ህዝቡ የሚከፋፈልበት ትንሽ ነገር እየተከሰተ በአገር ቤት የሚደረገው ሁሉ ወደ ውጭም እየወጣ የተሰደደውን ይከፋፍሉ ነበር። በዚህ ወቅት አንዳንድ ሰወች የቤተ ክርስቲያን አገልጋይ እየመሰሉ ከአዲስ አበባ ወደ ውጭ ይጎርፉ ነበር።
ይህች መጽሀፍ ሰብስባ በያዘቻቸው መዛግብቶች የተከሰቱትን የመከፋፍያ ስህተቶች ይዘው ወደከንሳስ የዘለቁት በዲቁና በዘማሪ ስም ከዋናው ካዲስ አበባ የመጡ ነበሩ። “በእንተ ስማ ለማርያም” እያሉ እውቀቱንና ሙያውን እየተማሩ ካደጉት በላይ እናውቃለን የሚሉ ለህዝብ የሚመስል ነገር ፈጠው የማርያም ጠላት ናቸውና አደባድቡን የሚል የመከፋፍያ ሸፍጥ በከንሳስ ኪዳነ ምህረት ቤተ ክርስቲያን ችግር አፈነዳ ።
ቀሲስ አስተርአየን መናፍቅ ናቸው የሚል የሀሰት ክስ ማሰራጨት ጀመረ። በጥጉ ያሉትን ሴቶች ዘማሪ ብሎ አደራጀ። እነዚህ ሰዎች በከተማውና በመላ አሜሪካ አሰራጩት። ቀጠሉና ከአቡነ ማትያስ የበለጠ ስለ ቤተ ክርስቲያናችን የሚያውቅ የለምና ይመስክሩልን ብለው ጠሯቸው። አቡነ ማትያስም ከሰንበት ተማሪወች ጋራ በመስማማት፤ የሰንበት ተማሪዎች ትክክል ናቸው ቀሲስ አስተርአየ ክዷል ብለው በማገድ አገልግሎቱን ለለሰንበት ተማሪዎች አስረክበው ወደ መኖሪያ ቤታቸው ተመለሱ።
በዘገባው የተጠቀሱት ሰዎች ተልእኳቸው ምን ይመስላል? እነማን ነበሩ? በወያኔ ዘመን ብሄራው አቋማቸው ምንድነው? ።
መጽሀፏ አካታ ወደ ያዘቻቸው መዛግብት ዝርዝር ሀተታ ከመግባታችን በፊት በስማቸው ያሳተሟት አባ ሰረቀ ማናቸው? በወያኔ ዘመን ምን አደረጉ? ለምን ወደ አሜሪካ መጡ? ተሰደው ወይስ ተልከው? ወደ አሜሪካ የመጡበት ዘመን ምን ይመስል ነበር? በወያኔወች መካከል ማለት በአቶ እሰየና መለሰ በቤተ ሰብ መካከል ምን ተከሰተ? በአቡነ ማትያስና አቡነ ጳውሎስ መካከል 7 የተከሰተው ድራማ ምን ይመስል ነበር? በአባ ሰረቀና በአባ ማትያስ መካከልስ የነበረው ግንኙነት እንዴት ነበር? የጠቅላላዋ ቤተ ክርስቲያን ይዘት ምን ይመስል ነበር? በእውነትና ንጋት ስም ተሰብስበው በታተሙት መዛግብቶች ውስጥ በተደጋጋሚ የተጠቀሱት ሰዎች እነ ማናቸው? ምን አቋምና ችሎታ ነበራቸው? በቤተ ክርስቲያናችን ውስጥ ያላቸው እውቀትና ችሎታ ምን ያህል ነበር? የተከሰተው ስህተት የማን ነበር? አባ ሰረቀ ለምን ሰብስበው አሳተሙት? ምን አሳሰባቸው? ምን አስገደዳቸው? ለቤተ ክርስቲያን አስበው ነው? ወይስ በግላቸው የመጣባቸውን ችግር ማርገቢያ ለማድረግ? ጥያቄውን እራሳቸውና በወቅቱ የነበሩት የሚመልሱት ነው።
በመዛግብቱ የተካተቱት
የወቅቱን ሁኔታ ከተገነዘብን ወደ ዘገባው ዝርዝር እንሻገራለን። የዘገባውን ዝርዝር ከተረዳን ቤተ ክርስቲያናችን በወያኔዎች የገባችበት አዘቅት እንገነዘባለን። ችግሩ ከገባን ከገባችበት አዘቅት አውጥተን ወደ ነበረችበት አቻወቿ (ኦሬንታል አብያተ ክርስቲያናት) ለመመለስ የሚያቅተን አይኖርም።
የመዝገቡ ስብስብ የሰዎችን ድካምና የስርአት የእምነትና የአላማ ጽናት እየገለጠ፤ ቤተ ክርስቲያናችን በምን አይነት ሰዎች አመራር እጅ ላይ እንደወደቀች ያሳያል። ማንም ሰው በቀላሉ ይገነዘብ ዘንድ መጽሀፏ በሰበሰበቻቸው መዛግብት የሚታዩትን በሀሰትን በእውነት መካከል የተካሄደውን ትንቅንቅ ይገልጣል ለጥንካሬና ለጥራት ለሚያዘጋጃት አድማስ ላይ ለመድረስ ለሚደረገው ጥናት ይጠቅማል። ሁለት ተቃራኒ ሀሳብና የእምነት አቋማ ያላቸው ባንድ ጎራ አቡነ ማትያስ በሌላው ጎራ ማህበረ ካህናቱ የተለዋወጧቸውን ሀሳቦች ከዚህ በታች እናቀርባለን። ከአቡነ ማትያስ እንጀምራለን።
የአቡነ ማትያስና የሰንበት ተማሪወች እምነትና አቋም
በብጹእ አቡነ ማትያስና በማህበረ ካህናቱ መካከል የተከሰተው ውዝግብ 33 እስክ 80 ይቀጥላል። አቡነ ማትያስ “እመቤታችንን በተመለከተ የምንከተለው እምነትና ትምህርት እንደሮማ ካቶሊክ ከአዳምና ከሄዋን ውርስ የነጻችው ከመወለዷ በፊት ነው” ይላሉ። ገጽ 39 ይመልከቱ። ቀሲስ አስተርአየ ግን “ቅዳሴ ለመቀደስ ህብስት በጻህል ወይን በጽዋዕ መሰየም አለበት። እመቤታችንም በአዳም በኩል ከነበረው ቁርኝት የተቀደሰችው መጀመሪያ ወደ ህልውና መምጣት ነበረባት” ይላሉ። ገጽ 41 ላይ ይመልከቱ። አቡነ ማትያስ ደግሞ “ቅዳሴ ለመቀደስ ህብስት በጻህል ወይን በጽዋዕ መሰየም አለበት። እመቤታችንም በአዳም በኩል ከነበረው ቁርኝት የተቀደሰችው መጀመሪያ ወደ ህልውና መምጣት ነበረባት በማለታቸው ቀሲስ “ኑፋቄያቸውን በመግለጻቸውና በድፍረት በማስተማራቸው ክህነታቸው ተይዟል” ይላሉ። ገጽ 41 ላይ ይመልከቱ። የቀሲስ አስተርአየ ትምህርትና እምነት ሰምተውት እንደማያውቁ “ይህን ክህደት መቀበል አለብን ነው የቀሲስ አስተርአየ ትምህርት አይገርምም? እያሉ አቡነ ማትያስ ይገረማሉ ገጽ 40 ላይ ይመልከቱ።
ከቀሲስ አስተርአየ ደግሞ ምን ይገርመወታል “ይህንን ትምህርትና እምነት ካስተማሩኝ መምህራን የተረከብኩት ሲሆን የመላው ኦርቶዶክስ እምነትና ትምህርት ነው” ይላሉ ገጽ 39 ይመልከቱ። ቀሲስ አስተርአየ ይቀጥሉና፤ “ይህ የነ አቡነ ማትያስ እምነት በ20 አመት ውስጥ የተፈጠረ እምነት እንጅ የተዋህዶ እምነትና አይደለም” ይላሉ። ገጽ 41 ላይ ይመልከቱ።
ቀሲስ አስተርአየ በወያኔ ዘመን በሲኖዶሱ ዙሪያ በተሰበሰቡት ጳጳሳት ላይ የሚታየውን ድክመትና ሞራል የለሽነት ታዝበው የተናገሩትን አቡነ “ሲኖዶስ እርስ በርስ የሚደባደብ ነው። አገር የካደ ነው። እንኴን ዶክትሪን ሊያስጠብቅ ሀገርን ማስጠብቅ ያልቻለ ነው” ብለው ባደባባይ ፊት ሲኖዶሱን ተሳድበዋል” ቀሲስ ይህን በመናገር ብቻ አልተወሰኑም፤ “ሊቃውንቱ ሁሉ አፈር በልተዋል። እኔ ብቻ ባሜሪካ እገኛለሁ። ብለው የኢትዮጵያ ኦ ቤ ራሳቸውን ብቻ ሊቅ አድርገው አስቀምጠዋል” እያሉ ቀሲስን ይወቅሳሉ። ይህ ያቡነ ማትያስ ወቀሳ፤ ማህበረ ካህናቱ የቀረበለትን ጉዳይ ከመመልከቱ በፊት የቀሲስ አስተርአየን እድገትና የትምህርት ችሎታ በቤተ ክርስቲያን ያበረከቱትን መመልከት ነበረበትና ቀሲስን ጠየቀ። ቀሲስም ከልጅነታቸው ጀምረው በጉባዔ ትምህርት ብዙ የተማሩ መሆናቸውን በካህናት ማሰልጠኛ ትምህርተ አበ ንስሀና እና አዲሲ የወጣውን ቃለ ዓዋዲ እንዲያስተምሩ የተላኩበትን መረጃ በማቅረብ ያበረከቱትን አስተዋጽኦ፤ የሚያሳይ መረጃ አቀረቡ። ገጽ 32 ላይ ይመልከቱ ።
ማህበረ ካህናቱ የቀሲስን ሁኔታ ከተረዳ በኋላ “ቀሲስ አስተርአየ ተራ ሰው አይደሉም የተማሩ ብዙ ያወቁና የሚጽፉ ናቸው። ወደ እልክ የሚያስገባ ነገር ከመጣ ችግሩ ይብሳልና ያስቡበት በማለት አቡነ ማትያስ የሄዱበትን የተሳሳተ መንገድ እንዲያስተካክል ጥያቄ አቀረበላቸው” ገጽ 31 ይመልከቱ። የማህበረ ካህናቱ ጉባዔ “የቀሲስ አስተርአየ ትምህርት ከቅዱሳት መጻህፍት ያልወጣና እምነታቸውም ያልተለየ እንዳልሆነ ተረዳ።” ገጽ 32 ላይ ይመልከቱ። ቀሲስ እምነታቸውና ትምህርታቸው ከጥንታዊት ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያናችን ትምህርትና እምነት ላይ በጽኑዕ የተመሰረተ ንደሆነ እያመኑና 0ፕ[የሰንበት ተማሪወችና ያቡነ ማትያስ እምነትና ትምህርት የተሳሳተና በስህተት ያገዷቸው እንደሆነ እየመሰከሩ፤ ለአናርኪነት ምሳሌ ላለመሆን የአቡነ ማትያስን እገዳ አክብረው መቀበላቸው ጉባዔውን አስገርሞታል። ገጽ 41 ላይ ይመልከቱ።
የማህበረ ካህናቱ እምነትና አቋም
ከገጽ 56 እስከ 66 ባሉት ገጾች ላይ የሰፈሩት መዛግብቶች እንደሚያመለክቱት ማህበረ ካህናቱ አቡነ ማትያስን እንደተሳሳቱ ተገነዘበ። ማህበረ ካህናቱ አቡነ ማትያስን “የተሳሳቱት እርሰዎ እንጅ ቀሲስ አስተርአየ አይደሉም። ከንሳስ ላይ የፈጸሙትን የተሳሳተ እገዳ ያንሱ” አላቸው። አቡነ ማትያስ ስህተታቸውን ከመቀበል ይልቅ “ቀሲስ ተሳስቻለሁ ከአሁን በኋላም ይህንን የተሳሳተ ትምህርት አላስተምርም ብለው ይቅርታ እንዲጠይቁ ማድረጉ ይቀላል” ብለው የማህበረ ካህናቱን ጥያቄ አልተቀበሉትም ገጽ 42 ይመልከቱ።
ማህበረ ካህናቱ የቀሲስ አስተርአየን እድገትና የትምህርት ችሎታ በቤተ ክርስቲያን ያበረከቱትን መመልከት ነበረበትና ቀሲስ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሊቃውንት ተቀርጸው ያደጉና፤ በካህናት ማሰልጠኛም አዲሲ የወጣውን ቃለ ዓዋዲ እና ትምህርተ አበ ንስሀ እንዲያስተምሩ የተላኩበትን መረጃ በማቅረብ የኦርቶዶክስ ጥንተ ትምህርት እንደነበረ ማህበረ ካህናቱ ተመለከተ” ገጽ 32 ላይ ይመልከቱ። ወደ ዝርዝር በመግባት ውዝግቡን ተመለከተ ። “ካህኑ ተራ ሰው አይደሉም የተማሩ ብዙያወቁ ያወቁና የሚጽፉ ናቸው። ወደ እልክ የሚያስገባ ነገር ከመጣ ችግሩ ይብሳልና ያስቡበት በማለት አቀረበላቸው” ገጽ 31 ላይ ይመልከቱ ። የቀሲስ አስተርአየ ትምህርት ከቅዱሳት መጻህፍት ያልወጣና እምነታ ቸውም ያልተለየ እንዳልሆነ ጉባዔው ተረዳ ገጽ 32 ላይ ይመልከቱ።
አቡነ ማትያስ ጉዳዩን በቀሲስ ላይ አክብደው ለማቅረብ “ይህ እምነት በ20 አመት ውስጥ የተፈጠረ እምነት እንጅ የተዋህዶ እምነትና አይደለም። ሲኖዶስ እርስ በርስ የሚደባደብ ነው። አገር የካደ ነው። ስንኴን ዶክትሪን ሊያስጠብቅ ሀገርን ማስጠብቅ ያልቻለ ነው ብለው ባደባባይ ፊት ተሳድበዋል” የሚል በቀሲስ ላይ ሌላ ተጨማሪ ክስ ፈጠሩ ገጽ 41 ላይ መልከቱ። አቡነ ማትያስ “በ20 አመት ውስጥ የተፈጠረ እምነት እንጅ የተዋህዶ እምነትና አይደለም“ ላሉት አቡነ ማትያስ የሰጡትን “በሞት የተለዩት ሊቃውንት በሊቃውንት ተተክተዋል። በህይወት ያሉት ሊቃውንት የቀድሞዎችን ጽኁፎች የሚተኩ ሌሎች መጻህፍት ጽፈው ያበረከቱ መሆናቸውን መረዳት እጅግ አስፈላጊ ይመስለናል” የሚል መልስ ሰጡ ገጽ 42 ይመልከቱ።
ከማህበረ ካህናቱ ለቀረበላቸው ጥያቄ በመመለስ ፋንታ አቡነ ማትያስ “ማህበረ ካህናቱ የይግባኝ ሰሚነቱን ስልጣን ከየት አገኘው? በየትኛው ስርአተ ቤተክር ስቲያን መሰረት ነው” የሚል መልስ ሰጡ ገጽ 37 ላይ ይመልከቱ።
በማለታቸው ማህበረ ካህናቱም “በዚህ አባባልዎ አንድ ጳጳስ እንደፈለገው ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን የጻፏቸውን መጻህትና ለረዥም ዘመናት ቤተ ክርስቲያን አምናበት የኖረችውን እምነት መሻር መለወጥ ይችላል ማንም ሊቃወመው አይገባም ማለተዎ ነውን? የነገረ ሃይማኖት ውሳኔ ባንድ ጳጳስ ብቻ እንዲወሰን የታዘዘው በየትኛው ህገ ቤተ ክርስቲያን ነው? እነዚህን ጥያቄዎች እንዲመልሱልን ተስፋ እናደርጋለን“ የሚልስ ሰጣቸው። ገጽ 50 ይመልከቱ።
የቀሲስ አስተርአየ አቋም ኦርቶዶክሳዊ በመሆኑና የአቡነ ማትያስን እምነትና አቋም ከኦርቶዶክስ ክልል የወጣ በመሆኑ ማህበረ ካህናቱ ከአቡነ ማትያስ ቱ ጋራ ተጋጩ ከገጽ 46 እስከ ገጽ 54 ያሉት ዘገባዎች ይመልከቱ።
በመጨረሻም አቡነ ገብርኤል “እንደ እውነቱ ከሆነ ስለ ድንግል ማርያም ያለን እምነት በተመለከተ ከእስክንድርያ ስርአተ ትምህርትና እምነት ባንለይ እጅግ መልካም ነው። ካልሆነ ከኦሬንታል አብያተ ክርስቲያናት መለየትን ያስከትላል።” ከመወለዷ በፊት ቅዱስ ገብርል ወይም ራሱ መንፈ ቅዱስ አነጻት ካልን እናትና አባቷን አንጽቷቸዋል ወደ ማለት ያደርሳል” ብለው በጽሁፍ ገለጹ ገጽ 67 ላይ ይመልከቱ ።
“ቤተ ክርስቲያንና አማራውን ሰበርኩት” እያለ ለ27 አመታት የመከፋፍያ ምክንያት እየፈጠረ ሲከፋፍል እንደኖረና የገቡ ስህተቶች እንዲታረሙ የሁሉም ሀላፊነት እንደሆነ ለማሳሰብ ይረዳል።
አባ ሰረቀ ማሳተማቸው መልካም ቢሆንም፤ ከማህበረ ቅዱሳን ጋራ በሌላ ነገር በተጋጩበት ወቅት ማሳተማቸው ሌላ ጫጫታ ለመፍጠር እንጅ የገባው ስህተት ባለመታረሙ አሳስቧቸው እንዳልነበረ ታዛቢወች ይናገራሉ። አቡነ ጳውሎስ ሞተው አባ ማትያስ በቦታው መተካታቸውን ቢያውቁ ኖሮ ማሳተም ቀርቶ መዛግብቱን ያጠፏቸው ነበር” ይላሉ።
(ይኸ መጣጥፍ፣ የብሎገሩ ሀሳብ ሳይሆን፣ የደራሲዎቹ ሀሳብ ነው። በውስጡ ያሉትን ሀሳቦች፣ ለመጠየቅም ሆነ ለመሞገት ከተፈለገ፡Abunepetros1928@gmail.com ደራሲዎቹን መጠየቅ ይቻላል)
የወያኔ የጥፋት ዘመን በማለፍና በዮዲት፤ በግራኝ መሀመድና በጣሊያን ወደ ተሰበሰበው የታሪክ ቌት እየገባ ነው። “እውነትና ንጋት” በሚል ርእስ የታተመች ይህች የመዛግብት ስብስብም፤ የወያኔን ዘመነ ሙስና የሚቀጥለው ትውልድ የሚያስብባቸው ብዙ የታሪክ መዘክሮች አንዷ ወደ መሆን ትሻገራለች።
(መጣጥፉ የብሎገሩ ሳይሆን የደራሲዎቹ ነው። ደራሲዎቹን ማግኘት ለሚፈልግ፥ በኢሜል፥
Abunepetros1928@gmail.com
ማግኘት ይቻላል።)