Thursday 8 December 2011

የብሶት ምጥ!


የጐንቻው!

ሃያ ዘመን ሕዝብ ያረገዘው፤ውል እድሩ፤ የብሶት-ምጥ፤

የተጣባ ከውስጣችን፤ሕመማችን ሥር የሰደደ አለቅጥ፤

ሲያስጨንቅ ሲያስጠብበን፤የኖረ፤ሲያንቆራጥጥ፤

ስንድህ በእንብርክክሽል’ በውስጣችን  ሲገላበጥ፤

የሁለንተናችን ግልግል ውስጠ-ደማሚት እበጥ፤

አልፈነዳ፤ አልወለድ፤ ብሎ፤ወገን በሕቡ፤ሲናጥ፤

በቁርኝት አሳስሮን፤እጅ መዳፉችን፤ሲላጥ፤

ግፍ፤ቆሰቆሰው፤ሊያቀጣጥሉን፤‘የቀኑ ሰዎች’ በፈሊጥ፤

ስም እያዋሱን ‘ሞግሸነት’ መዘባበቻ፤ሽብር ስላጥ፤             

ባጐረስን እየተነከስን፤ሲገፉን፤ኖረው፤ከድጥ ወደ ማጥ፤

‘ብሶት ወለደን’ ብለው፤ያነገሱት፤የእንግዴ-ልጅ ምጥማጥ፤

የትውልድ ተስፋ የምያመክኑ፤ለእሳት ዳረገውን ለረመጥ፤

በስለን አረናል፤በየጐጇችን፤እየተቃጠለን፤ሳንገላበጥ።
እነሆ፤የነፍስ፤የስጋችን አረሞን፤ሰውነታችን እንዲገለጥ፤

በየሜዳው፤በየጓዳው፤እንደ እንጉዳይ፤ እንደ ፈርጥ፤

ምድራችን ታብቅል፤አገር በቀል፤ሥር ነቀል ለውጥ፤           

እሙን ይሁን፤የበኩር ልጅ ለአበሻ፤ዘር፤ትንሣኤ፤አመጥ

ይቀጣጠል በውስጣችን፤የብሶት፤የምሬታችን፤ገሞራ፤ቀውጥ፤

እንዲተፋ፤አሮ-ተክኖ ዓሞታችን፤ሕዝባዊ-አፎት ታንክ፤መትረየስ፤የሚያቀልጥ፤

ወያኔ፤እበጡ እንዲፈርጥ፤መርዙ፤እንዲመክን ከነሰንኰፉ፤ ይገልበጥ፤

ኢትዮጵያዊ ነፃነት፤ክብሩን፤እንዲጨብጥ፤ሕልዊናውን፤እንዲያረጋገጥ።


የሰማዕታት፤ትንሣዔ፤አስርተ ዓመታቱ፤ደርሶ፤አልተረሱም ጨርሶ፤

ሁለት መቶ ለጋ ወጣቶች፤ደረት፤ግንባራቸው በአጋዚ ጥይት ፈርሶ፤

በአገራችን መዲና በአውራ ጎዳናዎች አፍላ ደማቸው በግፍ ፈሶ፤

ገዳይ አጋዚ፤እንደ ጉንዳን በአደባባይ ተኩነስንሶ፤

የአፍሪካን መዲና፤የምንሊክን በተመንግሥት በእብሪት ወርሶ፤

ምርጫ ቢረታ የባንዳው ልጅ ጠብ ደግሶ ቂም አርግዞ፤

የወጣ የወረደውን፤ያለፈ-ያገደመውን በካሚወን አግዞ፤

በየጫካው፤በየዱሩ፤መቶ ሺህ፤ዜጐችን፤አሳር ፈጥዞ፤

ዳግማዊ ሞሶሎኒ የቁጣ ‘ማዕቱን’ ሰደደብን፤ድቃላ ዛሩን አዝዞ።

እስከ መቼ እንኖራለን፤እየተፈጀን ቤታችን በእሳት፤ተያይዞ።



መንታላ እናት፤ ኢትዮጵያ በደሳሳ ጎጆዋ እሳት ተለቆ መከራ፤

ልጆቿን አቃጥሎ እየበላ፤የዜጎቿን ደም፤በየቦዩ እያዘራ፤

ክፉ መንግሥት፤ሕዝብ አስለቃሽ የጥፋት በረዱ፤የማያባራ፤

ሚስኪን እናት ኩርማን ቀና ያሳደገችው ልጇን፤ተጠሟራ፤

ስታገኘው፤አስከሬኑን፤ቀን በጠራራ ደም ተለውሶ በአቧራ፤፤

ማን ደረሰ?፤ጧሪ ቀብሪዋን፤ ሙት-ልጅ ታቅፍ ’አሎሄ’ ስትጣራ፤

እስካሁን፤እስከዛሬ፤ልጇን፤ካፈር፤ብሶት-ሃዘኗን፤በውስጧ፤ቀብራ፤

የመኖር ተስፋዋ፤ ጨልሞ የወላድ ማጧ፤ከዓመት-ዓመት ሳያባራ፤

ጎስቋላ እናት ቤቷን ዘግታ፤’ታለቅሳለች’፤እያማጠች፤ ቅስሟን ሰብራ፤

ትባላለች፤አጨብጭቢ፤አቀንቅኝ እንዲደራ፤የጐጠኞች፤ ‘ጭፈራ’፤

የአገራችን መዲና በአስከሬን ተቦ፤አድባራችን፤በሃዘን ማቅ ተወጥራ፤

አስደገሱ፤ለልእልታቸው፤ ‘ወይዝራ’ ‘አቦይ ንጉስ፤ በሸራተን፤ዳንኪራ፤

እንድረስላት ለእምያችን፤ተስፋ ሳትቆርጥ በወያኔ ከበሮ፤ ደንቁራ።
አዎ እናክብራለን፤እንዘክራለን፤ሰማዕታት፤
የትግራይ ጀግኖች፤በኢትዮጵያ ሰም ለተሰውት፤
አደራ አለብን ምርት ከእንግርዳድ የመለየት፤
ከመለስ ባንዶች ስም ግብራቸውን ካጠለሙት፤
ለእልቂት አሻጥር ‘ሃውዜን’ በጅምላ ካስጨረሱት፤
የዘመናችን ‘ረቂቅ ባንዳ’ መንበረ-ሰይጣን ጥልመ-ጣዖት፤
የ‘ከበሩ፤የደለቡት፤በንጹሃን ደም፤ በሕዝብ እልቂት፤
በዚያ ክፍ ቀን፤እናት አጽሟን ለልጇ አንተርሳ ስትሞት፤
ድረሱልን፤ በዓለም ዙሪያ ስንዋትት፤ለምጽዋት፤
ሕይዎት፤ሊታደጉን፤ከባር ማዶ፤እርዳታ ከቸሩት፤
‘የአኬልዳማው’፤ደራሲ፤የመለስ ሰይጣኑ፤ቅጥፈት፤
ብልጣ ብልጡ ንጉስ፤ ‘በለበጣ የወርቅ ዘር’ ለሚሉት፤
ሺህ ‘ወገናቸው’ ዝምብ-አፈር ሲቅም፤ግድ ያላሉት፤
ዝርፊያ ተጠምደው፤ስርቆት፤የሚሊዮን ዶላር፤በጀት፤
በቁጭ በሉ፤ገበያ፤ተውኔት፤ስንዴ በአሸዋ ያቀኑለት፤
ተከፋፍለው፤ቀማኛ-ጆቢራዎች ገንዙቡን፤ቅርምት፤
አደርጉት፤ሃራጅ መግዣ አገር ሕዝብ መነገጃ፤ወረት፤
እነሆ! ይወለዳል፤የዚህ ሁሉ ግፍ አበሳ ምጥ ብሶት።

እናማ፤ ጐበዝ፤ ወያኔ ጠላትነቱን ከዚህ ወዲያ እንዴት ያሳይ፤
ንቆ ሕዝብ አገር፤ዜጎችን፤በግፍ፤አሳዶ፤ከመግደል በላይ፤
ትውል ከማፍለስ፤አገር ከማፍረስ፤ባንዳው ደላላይ፤
የመረጥናቸው እንደራሶችን፤አስሮና ገርፎ በቁም ሲያሰቃይ፤
የአገር አንጡራ ሃብት፤ሲያባክን፤ተቀራምቶ፤ለካድሬ ሲሳይ፤
ቅርጣን ላይተርፍ፤ከረሰ ምድር፤እሚያመክን መንጋ ተባይ፤
ለሰላም፤ለአንድነታችን፤የሞገቱትን፤መቀጣጫ፤ በ‘አኬልዳማይ’፤
ሲዘባበቱ፤ሲሳለቁብን፤እኛስ አንፈጥርም፤ አንጠብም ወይ፤   
ቅዥት ይዧቸው፤’የሙት-ትንብይ’ ጐጥ ሲያስታትጥቁ፤በተለይ፤
መሃል አገሩ፤አበሻው፤ችግኝ፤ጫካው፤ጠላልፎ እንዲያደበይ፤
አንዴ እንነሳ፤ሳንገባበዝ፤በዘር-በማንዝር፤ሳንለያይ፤
የብሶት፤ምጣችንን ተገላግለን፤ድላችንን፤ በአይናችን እንድናይ።


የጎንቻው!       yegonchaw@yahoo.co.uk

ከሰማኒያ ሚሊዮን በላይ ኢትዮጵያዊያን፤በጣት በሚቆጠሩ፤ የወያኔ ተኩላዎችና ፍርፋሪ በሚጣልላቸው ሆዳም ቀበሮዎች፤ተከበን ወደ ጥፋት ገደል ስንነዳ፤ስንናዳ ሳር፤አፈር እየጋጠ በደመነፍስ ከሚንጋጋ የበግ መንጋ የተሻለ የፈጸምነው ጠላትን የሚመክት፤በአንድ ላይ እንኳ፤የሚያስደነግጥ ድምጽ አላሰማንም። ከፊታችን የተደቀነውን አደጋ ለማየት ቀና ብለው የሞገቱትን፤የመከሩትን አስተዋይ፤ መሪዎቻችንን፤ታጋዮቻችንን እያናጠለ፤ፊታችን ላይ ሲያዋርዳቸው፤ ሲያርዳቸው፤በእሥር ሲቀጣቸው፤ከሽሙጥ፤ከቡና ወሬ፤ከአሉባልታ ያለፈ በሰሜን አፍሪቃ እንደታየው ፤እንደ ጀግና ሕዝብ፤ አልወገንም፤አልታገልንም፤ይህ፤ትልቅ፤ ጥፋት፤ክህደትም፤ ነው።
እነሆ፤ አሁን ገደሉ፤ አፋፍ ላይ ደርሰናል፤ከእንግዲህ ወዲያ

“ጨው ለራስህ ብትል ጣፍጥ፤……….               !”

1 comment:

  1. This is yet another powerful poem from Yegonchaw. It is the last call. We need to respond!

    ReplyDelete