ዲያስፖራ
ላሜ ቦራ
ወንድሙ መኰንን፣ ከታላቋ ብሪታኒያ
ይኸ መጣጥፍ መጀመሪያ የተጻፈውና በኢትዮመዲያ፣ በኢካዲኤፍ፣ በአዲስ ቮይስ፣ በኢኤምኤፍ እና በጎልጎልጕል ድረ-ገጾች የተበተነው በእንግሊዝኛ ተደርሶ ነበር። በጣም ብዙ አስተያየት ሰጪዎች፣ በዩኒቨርሲቲዬም ኢ-ሜይል ሳይቀር የተሰማቸውን አካፍለውኛል። ሁሉም ወደ አማርኛ እንደመልሰውና ብዙ ኢትዮጵያውያን ለማንበብ ዕድል እንዲያገኙ አጥብቀው ስለአሳሰቡኝ ጥይቄአቸውን ተቀብዬ ወደ አማርኛ መለስኩት።
ከኢትዮጵያ የሚደርሱን ቀልዶች ለዛቸው ጨምሯል። ሰሞኑን፣ አንድ ከአገር ቤት የመጣ እንግዳ፣ የወያኔ ባለሥልጣናት፣ ዲያስፖራን “ላሜ ቦራ” እያሉ እንደሚያሾፉብን አጫውቶን አዝናንቶናል። እውን እኛ በተለያዩ ምክንያቶች ከኢትዮጵያ የተሰደድን ኢትዮጵያውያን ያለማቋረጥ የምንታለብ የካሽ ጥገቶች ነን?
መቼም በኔ ዕድሜ ትምህርት ቤት የሄዳችሁ ሁሉ፣ስለላሜ ቦራ የተተረከ የልጆች ጣፋጭም አሳዛኝም ታሪክ ሳታነቡ ወይም ሳይነበብላችሁ አልቀረም። የላሜ ቦራ ታሪክ እጅግ አንጀት የሚበላ ተረት ነው። ነገሩ እንዲህ ነው። አንዲት ሁለት ሕጻናት የነበሯት እናት በጣም አሟት በአልጋዋ ላይ ሁና ትጣጣራለች። እሷ ስትሞት ባሏ ሌላ ሚስት ካገባ፣ የእንጀራ እናት በልጆቿ ላይ ልታደርስ የምትችለውን ጭካኔ ስትገምተው ከራሷ መሞት በላይ አስጨነቃት። ከዚህም የተነሳ፣ ሰው አላምን ብላ (ሰው ምን ይታመናል? ዛሬ እዚህ ብታስቀምጠው ነገ ሌላ ቦታ ተንሸራትቶ ታገኘዋለህ) የምትወዳትን ላሜ ቦራ የተባለችውን ላሟን አልጋዋ ድረስ አስመጣቻት። “ላሜ ቦራ! ላሜ ቦራ! የልጆቼን ነገር አደራ” ብላ አዜማ እንደ ጨረሰች ሞተች። ሟቿ እናት እንደገመተችውም፣ የልጆቹ አባት፣ ብዙም ሳይቆይ ሌላ ሚስት አገባ። እንጀራ እናቲቱ ሕጻናቱ የሷ ልጆች ባለመሆናቸው በጣም ጨከነችባቸው። በረሀብ መንምነው እንዲሞቱ፣ ምግብም ትከለክላቸው ገባች። ልጆቹ ሲርባቸው፣ በቀጥታ ወደላሚቱ እየሄዱ፣ “ላሜ ቦራ! ላሜ ቦራ! የእማምዬን አደራ” ብለው ሲያዜሙላት፣ ላሜ ቦራ እግሮቿን ፍረክረክ አድርጋ ከጦቶቿ በቀጥታ ወተት እንዲጠቡ ታደርግ ነበር። ቀሪው ታሪክ ገብስ ነው። የሚገርመው ነገር፣ ላሜ ቦራ ያለመንጥፏ ነው። ክረመቱንም በጋውንም ዓመቱን ሙሉ ብትታለብ፣ ብትታለብ የማትነጥፍ የወትት ጅረት ናት ተብሎ ነው የሚገመተው!
ወያኔዎች፣ በሚያስገርም አኩኋን ታርኩን ዲያፖራው ላይ ደገሙልን። ታዲያ ታሪኩ በዲያስፖራው (ውጭ አገር ኗሪውን ኢትዮጵያዊ) ላይ መሆኑ አያንገበግብም? ያርገበግባል ኢንጂ። “ዲያስፖራ - ላሜ ቦራ” አሉን? ዕውነት አላቸው። ምን ያድርጉ! “አረሱት! አረሱት! የመተማን መሬት! የአርማጨውን መሬት፣ ያውም የኛ ዕጣ፣ እነሱ ምን ያርጉ ከኝ ሰው ሲታጣ!” ብሎ ደምድሞት የለ ዘፋኙ! ወያኔዎች፣ የወጭ ምንዛሬ በደረቀባቸው ቁጥር ጨርቄን ማቄን ሳይሉ፣ ባዶ ሻንጣቸውን አንጠልጥለው ወደ ዲያስፖራ - “ካሽ ጥገት”፣ ከተፍ ነዋ! ከዚህ ቢታለብ-ቢታለብ ከማይነጥፈውን ጥገት ዲያስፖራ በተለያየ ምክኒያት ተሰዶ በብዛት ከሚኖርበት የአሜሪካና የአውሮፓ ከተሞች፣ እንደለነድንና ዋሽንግተን ካሉት ከቸች ነዋ! ለዚህ እንዲመቻች ደግሞ፣ ከዚህ በፊት እንዴት ተደርጎ ዲያስፖራው ሊጠመድ እንደሚችል፣ 52 ገጾች[1] በፈጀ ምርምር ጥናትና ዕቅድ ተነድፎ የወያኔ ኤምባሲዎች ሥልጠና አግኝተዋል። ላሜ ቦራን እያጠመዱ ይዞ ድርቅ እስክትል ድረስ እልብ ነዋ! ቅርብ ጊዜ ከተፈጥሩት ወጥመዶች መሀል፣ “የሕዳሴ ደደብ” (ይቅርታ፣ “ግድብ” ማለት ፈልጌ አዳልጦኝ ነው) ቦምብ፣ ውይ በሞቴ -ቦንድ ሽያጭ ነው። “አባይን ለደፈረ መንግስታችን ገንዘብ?” እንዴታ! ሌላው፣ የተለያዩ ለጥቅም የተደለሉ ላሜ ቦራዎችን እየሰበሰቡ፣ በየዘር ሀረጋቸው የሌማት - ይቅርታ ኦሆሆ ምን ነካኝ ዛሬ! – “ልማት” ማኅበር ማደራጀት ነው። ሌላው “ኢንበስተሮች” የሚል ሹመት ብጤ ስጥቶ፣ ላሜ ቦራዎቹ አድረገዋቸው አገር ቤት ንዋይ እንዲያፈሱ አግባብቶ ጠልፎ ማለብ ነው። ሰሞኑን ደግሞ ሌላ ያማረች አሽክላ ፈጥረው መጥተውልናል። 40/60 የሚሉት በአቋራጭ የቤት ማግኛ ፎርሙላ ወይም ቀመር ነው። አንድ ሎንደን ውስጥ ቤተክርስቲያናችንን ካዘጉት ካህናት መሀል፣ ሰሞኑን በዚያ ፎርሙላ ተጠቃሚ ለመሆን ሌሎቹን ጓደኞቹን አስከትሎ ሲሂድ፣ ጥግብ ያሉት የወያኔ እልፍኝ አስከልካዮች፣ “አንተ የላሜ ቦራን መስፈርት አታሟላም” ብለው ሲከለክሉት ሰድቦአቸው እንደሂደ ሰምተን ስንስቅ ነበር። አይ መሪጌታ! ቅኔውናንና ዜማውን እንደ ጅረት ስታወርድለት ወዶህ የነበረ አምላክ አዝኖልህ፣ እስክትደርቅ ከመታለብ አተረፈህ! ይልቁንስ ነዴቱን ትተህ “ሐሌ ሉያ” በል!
ወያኔዎችን የሚያዋጣቸው ፍቱን ዘዴ ሁኖ የተገኘው አንዳንድ ጅላጆሎችን በብሔር ብሔረሰባቸው አደራጅቶ የልማት ማኅበር ማቋቋም ነው፡፡ ዘረኝነት ደግሞ አንዴ ከተጠናወተ የማይለቅ ውርዴ ነው። በዚህ መንገድ፣ “የአማራ የልማት ማህበር፣”፣ “የኦሮሞ የልማት ማህበር፣” “የሲዳማ የልማት ማህበር” ወዘተ እያሉ መድበዋቸው ወይ ያልቧቸዋል፣ ወይ አሰልጥነው ሌሎቹን ላሜ ቦራዎችን ያሳልቧቸዋል። ከየብሔረሰቡ የተገኙ ጥቂት ሆድ አደሮች ካልሆኑ በስተቀር፣ ተደጋግመው ማህበራቱን የሞሉት እነዚያው የፈረደባቸው ጥቂት የማይባሉ ከትግራይ የተገኙ “የወርቅ” ዝርያ አባሎች ናቸው። የአማራ በዓል ላይ እነሱ ናቸው “እስክስ” የሚሉት! የኦሮሞው በዓል ላይም እነዚህው ናቸው “ሆ!” የሚሉት! የትግሬም በዓል ላይ እነሱው
ናቸው “አጅዋ!” የሚሉት።
በዚህ ወር ላሜ ቦራን የማለቡ ተራ፣ ወያኔ ኤምባሲ ግቢ ተወልዶ ፍርፋሪ እየበላ ያደገው “የአማራ የልማት ማህበር” ነው። “በአማራው ማኅበር” ሥር የተደራጁት ዕውነተኛ አማሮች ሳይሆኑ በሙሉ ቁጭ አማሮች ናቸው። የዘር ሐረጋቸውን እንደውያኔዎች ከቆጠርን፣ አማራ ሳይሆኑ የአማሩ ማለት ነው። እርግጥ አንዳንድ እንደያለው ከበደ ያሉ ወዶ ገቡች አይጠፉም። እነዚህ ማህበራት “የልማት” (የ”ጥፋት” ማህበራት ማላቱ ይቀላል፟)፣ ለማወናበድ እንዲመች ስማቸው ተቀየረ እንጂ፣ ወያኔ ለየአንዳንዱ ብሔር ብሔረሰብ በአገር ቤት ለለጠፋላቸው ዋና ዋናዎቹ የወያኔ አገልጋይ ተለጣፊ የፖሊቲካ ድርጅቶች “የድጋፍ ኮሚቴዎች” ናቸው። እንደ ኦሕዴድ፣ ብአዴን ... ምናምኖች ማለቴ ነው።
እስቲ ከነዚህ በዘር ከተደራጁት አንዱን የአማራን ብሔረሰብ እንዲቀብርላቸው የፈጥሩትን ተለጣፊ የአማራ ድርግጅት ቀርብ ብለን እንይ! ይኸምውም “የብሄረ አማራ ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ” (ብአዴን) ነው። አማራውን ሕዝብ ለመቀጥቀጥ የተጠፈጠፈለት መዶሻ ነው። (አንጽሮዕተ ስሙ ሲደብር!) ይኸን ድርጅት ወያኔዎች ጠፍጠፈው የሠሩት፣ በትቅምት ወር ፲፱፻፸፪ ዓ› ም› (Nov. 1980) ኢሕአፓን በድንገት ደርሰውበት አባላቱን ከጨፈጨፏቸው በኋላ፣ ከሞት ካተረፏቸው ምርኮች ሰብስበው “ተክራርዉሀ” በተባለ ስፍራ ነበር። ድርጅቱም የኢትዮጵያ ሕዝብ ዲሞክራቲክ ንቅናቄ (ኢሕድን) ነበር። ዕውነትም፣ በጊዜው ኢሕአፓ አባላቱ ዘር ቆጥረው የተደራጁ ሳይሆኑ ከሁሉም ብሔረሶቦች የተወጣጡ ነበርና ምርኮኞች ቢሆኑም ስሙ ትክክለኛ ነበር። ወያኔ ግን “ኢትዮጵያ” የሚለውን ስም መስማት ስለማይፈልግ፣ በዘዴ “ብሔር አማራ ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ” (ብአዴን) ብሎ እንደገና አጠመቀው። አርማም ቀርጾ ሰጠው። ታዲያ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ እስከዛሬ አመራሩን የያዙት ቁጩ አማሮች እንጂ አማራ በመብራትም ቢፈልግ አመራሩ ውስጥ አይገኝም። በመጀመሪያ ረድፍ የሚገኘው ቁጩ አማራ፣ አማራን በጣም የሚጠላ፣ አማርኛን መናገር የሚጠይፍ፣ ሻቦ ባንዳ፣ እናቱም አባቱም ከኤርትራ የፈለቁ፣ ጎንደር የተወለደ “በረከት ስምዖን”፣ ሕወነተኛ ስሙ ግን መብራቱ ገብረሕይወት የተባለው ነፍሰ ገዳይ ነው። ሒላዊ (ዕውነተኝ ስሙ “ፍቅሬ”) ዮሴፍ ወይ የእርትራ፣ አለበለዚያም የትግራይ ትግሬ እንጂ፣ አንዲት ጠብታ ደም በደም-ሥሩ ውስጥ የማትዘዋወር ቁጩ አማራ ነው። ታደሰ ጥንቅሹ (ዕውነተኛ ስሙ ታደስ ካሳ) ስሙን ቢያምር እንጂ፣ የትግራይ ትግሬ በመሆኑ፣ አማራነቱ በዲ ኤን ኤ ኤክስፐርትም ቢመረመር አይገኝበትም። ተፈራ ዋልዋ፣ ጊሚራ ነው። አማራና ጊሚራ ድምጹ ለጆሮ ቢመሳሰል እንጂ፣ አምሮም አያውቅም። ካሱ ኢላላ አማራ ነው የሚለኝ ሰው ካለ እራሱን የስነ አዕምሮ ሐኪም ጋ ሂዶ ይመርምር። ያስ ደግሞ፣ በአማራነት ሲያጭበረብረን የኖረ ጠቅላይ ሚኒስቴር ታምራት ላይኔ? ስማቸውን እየቀየሩ እኮ ነው የሚያምታቱን። ለመሆኑ ጌታቸው ማሞ ዋቅኬኔ መሆኑን ስንታችሁ ናችሁ የምታውቁት? ስለዋኬኔ አማራነት እናንተው መርምራችሁ
ድረሱበት። አዲሱ ለገሰ፣ ሰሙ ነው እንጂ አማራ፣ የሐረር ቆቱ ነው። አያሌው ጎበዜስ ቢሆን አማራ ነው? በአማራና በአገው መሀል ብዙም ልዩነት ባይታይም፣ ለሥልጣን የበቃው በአማራነቱ ሳይሆን ነገሩ ሌላ ነው። ቁጩ አማሮች በመሆናቸው አይደል፣ የአማራው መሬት ከጎንደር ተነጥቆ ለትግራይ፣ ከወሎ ተቆርጦ ለትግራይ ሲሰጥ፣ ጭጭ ብለው የተቀበሉት! እሱስ ይሁን ትግራይ የኛ ናት! የአማራው መሬት ተቦድሶ ለሱዳን ሲሰጥ የማያማቸው ቁጩ አማሮች በመሆናቸው አይደል! ቁጩ አማሮች ቢሆኑም አይደል፣ የዋልድባ መነኩሳት ሲደበደቡ ጆሮ ዳባ ልበስ ብለው የተቀመጡት። ቁጩ አማሮች ቢሆኑ አይደል፣ አማሮች ከየክልሉ ቁምጥና እንደያዘው ከቄዬአቸው ተፈንቅለው ሲባረሩ፣ ከየክፍለ ዞኖች ከቤታቸው ተመንግለው ሲሰደዱ የማያማቸው? ቁጩ አምሮች በመሆናቸው እኮ ነው፣ የወያኔ መሠሪዎች አማሮች እንዳይወልዱ በኪኒን ስያመክኗቸው በዓይናቸው ብሌን እያዩ ትንፍሽ የማይሉት። ውጪ አገር በአማራ ልማት መልክ የተደራጁትም እንግዲህ የዚያው መልክ የተጠፈጠፉ ተቀጥሎች ናቸው! ሌሎችም ብሔረሰቦችን እነወክላለን የሚሉት፣ ቁጩ ኦሮሞዎች፣ ቁጩ ጉራጌዎች ... በዚህ አኳኋን ነው የተፈጠሩት።
ወደ ላሜ ቦራችን ስንመለስ፣ ላሜ ቦራዎችን ለማለብ የተደራጁት፣ “የአማራ ልማት ማህበር - ዩኬ” (“Amhara’ Development Association – UK”) የተባለው ነው። እነማን እንደሆኑ ለማወቅ፣ ከፈለጋችሁ፣ እንደ አውሮፓ አቆጣጠር 2011 የገነዘብ ማሰባሰቢያ በዓላቸውን ሲያከብሩ የተቀዱትን ፊልም አብረን እንይ። http://www.youtube.com/watch?v=8fmeHCLPgpU።
መቼም ለንደን የምትኖሩ ኢትዮጵያውያን እዚያ ፊልሙ ላይ ከሚታዩት ማን ምን እንደሆነ ታውቃላችሁ። ከተሳሳትኩ አርሙኝ። እንደ አለማየሁ (አሌክስ) ብርሀኑ ያሉ የለየላቸው ትግሬዎች ናቸው። አለበለዚያ ጃማይካኖች ናቸው (ጀማይካኖቹ ቁጩ አማሮች ሲሆኑ ለመጀመሪያ ጊዜ ማየቴ ነው)፣ እንግዲህ በጣት የሚቆጠሩ የሌሎች ብሔርሰቦች (ሞቅዲሾ ሶማሌዎች ሳይቀሩ) አባላትና ሆዳደር አማሮች ሊታዩ ይችላሉ። የለየለት ሆድ አደር አማራ፣ ያለው ከበደ በር ጠባቂ በመሆኑ አታዩትም። ታዲያ ያ ሆዱ የተቀፈደደው፣ እንግዶቹ በልተው፣ ጠጥተው ጠግበው ሲሄዱ ቀሪውን ፍርፋሪ እየበላ መሆን አለበት።
በዚህ ዓመት ሎንደን ውስጥ፣ ዲያስፖራ ላሜ ቦራን ለማለብ የታቀደው 28 September 2013 ነው። መግቢያው በነጻ ነው። ሁላችንም ተጋብዘናል። ምግብ መጠጥም በሽበሽ ነው። ለምን ሁላችንም ግልብጥ ብለን ሂደን አንጋበዝላቸውም? ታዲያ ኪሳችሁንና ሆዳችሁን ባዶ አድርጋችሁ ነው መሄድ! በመተት እንዳትታለቡ! ሌላ የረሳሁት! የቁጩ አማሮችን የገንዘብ ማሰባሰቢያ በዓል ማን እንዳስተዋውቅላቸው ታውቃላችሁ? http://www.tigraionline.com/’Amhara’-ada-event-uk.html! ሌሎችማ ድረ-ገጾች ምን ቁርጥ ቢያደርጋቸው ነው የቁጩ አማሮችን ዝግጅት የሚያስተዋውቁላቸው!
ቁጩ አማሮች መቼም ሕሊና የምትባል አልተፈጠረችባቸውም። ወያኔዎች የውጭ ምንዛሬ ምንጭ ሲደርቅባቸው ነው የሚፍልጓቸው። ቢሞቱ ይሻላቸዋል። የላሜ ቦራ አላቢዎች ናቸው። ቁጩ አማሮች ካልረዷቸው በስተቀር፣ የወያኔ አምባሳደሮችማ ሥራቸውን መሥራት አቅቶአቸው፣ ሰሞኑን ከየኤምባሲው እየተባረሩ ነው። ኢትዮጵያዊው በየከተማው ውርደት እያከናነባቸው፣ ባዶ ኮሮጆአቸውን እያሸከማቸው ወደመጡበት ስለመለሳቸው፣ ያላቸው ምርጫ፣ ቁጩ አማሮችን የሙጥኝ ይዘው ወራዳ ሥራቸውን እንዲሠሩላቸው ማሠማራት ነው። ውሻ በር በድንብ እንዲጠብቅ ከተፈለገ፣ በየጊዜው ልፋጭ ይወረወርለታል።
አሁን በጥሩ ሁኔታ ወያኔዎች ላሜ ቦራን ለማለብ የፈበረኩት ዘዴ፣ ይኸ 40/60 የተባለው ቀመር ነው። ፎርሙላው የሚሠራው፣ እንዲህ ነው። ታላቢው ላሜ ቦራ ዲያስፖራ 40 ከመቶውን በውጭ ምንዛሪ ይከፍላል። 60 በመቶውን ወያኔ በብድር መልክ ይሸፍል። 100% በዶላር፣ በዩሮ፣ በፓወንድ
(ሀርድ ከረንሲ) ለሚከፍል ቅድሚያ ይሰጣል። ለዚህ ተብሎ የተሠሩ ቤቶች አሉና፣ ዲያስፖራ ሆዬ በቀጥታ አዲስ አበባ ሂዶ መረከብ ነው ተብሎ ተሰብኳል። ለዚያ የሚጣደፉ ብዙ ኢትዮጵያውያን ሞልተዋል። ምነው ቢባሉ፣ “እንዴ ለወያኔ ብቻ ማን አገሪቱን ሰጣቸው፣ እኛም እመሀላቸው ገብተን ቦርቡረን ከውስጥ ገዝግዘን እንጣላቸው” የሚሉ ወንድሞች አጋጥመውኛል። ወያኔ ከግምታችን በላይ ተንኰለኛ ነው። አባላቱ ሲፈጠሩ እኮ ተንኰልን ከሆድ ተምረው ነው የሚወጡት። እነሱ ዕቅዳቸው ላሜ ቦራን አስጠግተው፣ ሙልጭ አድርገው በደርቁ ሊያልቡ እንጂ ሊታለቡ እንዳልሆነ ማወቅ ይኖርብናል። ሌባን ደህና ሰው ሊሰርቀው፣ ታይቶም ተሰምቶም አይታወቅም። ቤት አዲስ አበባ ይኖረኛል ብሎ ወያኔን መጠጋት፣ አንደኛ፣ አድራሻ ለመስጠት፣ ከዚያም ወያኔን ለመቃወም ሰላማዊ ሰልፍ ላለመውጣት፣ ከዚያም አሻራ ሰጥቶ የወያኔ ንብረት ለመሆን ነው። ወያኔ አልቦህ ሲጨርስ፣ እንደማስቲካ መጥቶ፣ “ኪራይ ሰብሳቢ” ብሎ ይተፋሀል። የኢትዮጵያ መሬት እንዳለ የወያኔ ንብረት መሆኑን ለአንዳችም ደቂቃ አንዳንስት። ወያኔ ሲፈልግ፣ “መሬቱ ለልማት ይፈለጋል፣ ሞርታርህንና ጡብህን ይዘህ ብትፍልግ አንጨቆረር ውረድ” ብሎ ያሾፋል። ነገሩ ከዚህ በፊት ስለደረሰ ነው እንዲህ የምላችሁ፣ ያጣ ወሬ ሁኖብኝ አይደለም። ሰዎች ሲሸወዱ አይቼ ነው። ወደሽ ከተደፋሽ
ቢረግጡሽም አይክፋሽ ከመባል አምላክ ያድናችሁ።
ከወያኔ ጋራ ሕሊና ሳይሸጡ ቢዝነስ መሥራት አይቻልም። ሥርዓቱ የነቀዘ ሥርዓት ነው። በጥቅም ተስባችሁ ወደወያኔ ስትቀርቡ የሞቱትን እንኳን ባታስቡ፣ እስቲ እስር ቤት በግፍ የሚማቅቁትን እነ ርዕዮት ዓለሙን፣ አንዱዓለም አራጌን፣ እስክንድር ነጋን፣ ናትናኤል መኰንንን፣ ክንፈሚካኤል ደበበን፣ ዮሐንስ ተረፈን፣ ሻምበል የሺዋስ ይሁናለምን፣ አንዱዓለም አያሌውን፣ በአሥርት ሺህ የሚቆጠሩትን የኦሮሞ ብሔርሰብ አባል እስረኞችንና፣ የእስልምና ሀማኖት መሪዎችን ስቃይና እንግልት አስቡ። ወንድሞቻችን እና እህቶቻችን በመሆናቸው ጥቃታቸው ይሰማን።
ዲያስፖራ ስደተኛ ወንድሞቼና እህቶቼ! አታስፎግሩን (በአራዳ አማርኛ)! እሺ ለታሠሩት፣ ለሚንገላቱ የሚራራ አንጀት ባይኖራችሁ፣ ላማንም ደንታ እንኳን ባያኖራችሁ ለራሳችሁ አስቡ። ገንዘባችሁን እየወሰዳችሁ አታስረክቡ። ወያኔ አምጣ-አምጣ እንጂ ሕንካ-ሕንካ የሚል አማርኛ መዝገበ ቃላቱ (ድክሺነሪው) ውስጥ የለም። ሰዶ ማሳደድ ካላማራችሁ፣ ገንዘባችሁን ሌላ ቦታ ብታስቀምጡ ደህና ገቢ ይኖራችኋል። አለበለዚያም፣ እናንተው በገንዘባችሁ እንደፈለጋችሁ የፈለጋችሁን ግዙበት፣ ብሉበት፣ ጠጡብት፣ ልበሱበት። ላሜ ቦራ መባል ይቅርባችሁ። ዛሬ አንዳንድ ላሜ ቦራዎች እንኳን ነቅተው የራሳቸውን ወተት ለራሳቸው መጠጣት ለምደዋል። እምቧ ከምትለዋ ላም ታንሳላችሁ? እስቲ የላሜ ቦራን ብልጠት በዝህች ፊልም ተመለክቱ!
አበጀሽ ላሜ ቦራ! ጎበዝ ላሜ ቦራ! አንቺ እንኳን ከአንዳንድ ኢትዮጵያውያን ተሽለሽ ተገኘሽ!
Yet one more evidence that the sow was ran by Woyyane thugs follow the below link
ReplyDeletehttp://www.tigraionline.com/articles/ada-uk-urges-members.html