ማስተካከያ
በስህተት የተዘዋወረውን ለማስተካከል
ለንደን (ገጽ 9 የሚገኝ ዉን )
በቅርቡ “በሳጥናኤል መንገድ ነጎዱ” በሚል ርእስ ባቀረብኩት ጽሑፍ ለንደን ላይ ባተትኩት አንቀጽ
ላይ፤ የአቡነ እንጦንስ እና ዲዮስቆሮስ ስም በመጣለፍ ከህጻን ጋራ የተነሱት ፎቶ የሚለው አረፍተ ነገር፤ ከዚህ
በታች በግልጽ እንደተቀመጠው፤ የአቡነ እንጦስ ሳይሆን የሳቸው ቡድን ተካፋይ የአቡነ ዲየስቆሮስ ነው። ከዚህ
በታች ይመልከቱ።
ጉዳዩ በሕዝበ ክርስቲያኑ ዘንድ ትኩረት አግኝቶ ለቤተክርስቲያኑ አንዳች መፍትሔ ያመጣ ይሆናል በሚል ሐሳብ ገበናቸውን መግለጽ አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል። ምናልባት ልብ ገዝተው ንስሃ ይገቡ ይሆናል።
የአፋልጉኝ ማስተወቂያ ይህ ልጅ አያሳዝንም? ……. አያሳሳም? …… እርሱ ጠፍቶ እንዳይመስለዎ። አባቱን ማግኘት ባይችልም
አባቱን ይፈልጋል፤ እንደሌላው በህግ እንደተወለደ ልጅ
ከእናቱ ጋር አባቱን ማግኘትና አብሮ ለመኖር አልታደለም።
ያለው አማራጭ አባቴ ማነው? እያለ በመጠየቅ ማደግ
ነው። ማን ያውቃል? የማንነት ጥያቄው አንድ ቀን ምላሽ
ያገኝ ይሆናል።
ያንዱ ላንዱ ተዘዋውሮ በመቅረቡ እርማት ለመስጠት እንጅ፤ አቡነ እንጦስ ከዚህ ውጭ ናቸው ማለት አይደለም።
ወንድሙ መኮንን ያቀረቡትን ከዚህ በታች ተመልከቱ።
“በኮልፌ ቀራንዮ የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ላይ እማሆይ ምግቤ ታከለ የተባሉ ከብጹዕ አቡነ እንጦንስ ጋርእንደባልና ሚስት ኖረዋል በማለት በጠበቆቻቸው አማካኝነት የንብረት ጥያቄ ክስ አቅርበው ...”
“አባ”እንጦንስን ለማጋለጥ ስል ከፍርድ ቤት ያገኘሁትን ጉድ እንዳለ ብዘከዝክ የቤተክርስቲያኔን ገጽታ በድንገት እንዳልጎዳ ሳስቼ፣ ለጊዜው አቆይቼዋለሁ።” ይላሉ። ስለዚህ እኒህ ሰው አባ እንጦንስ ቀሪ ዘመናቸውን ከህዝብ ገለል ብለው በንስሀ መጨረስ
ሲገባቸው፤ ህጸጽ ያልተገኘበትን ህዝባዊ ክህነት ማውገዝ ቀርቶ ከዚህ በታች መመሪያችን እንደሚያዝዘው ወደ ቁርባኑ መቅረብ አይገባቸውም።
ቅዱስ ጳውሎስ “ስለምናገለግለው ስጦታ ማንም እንዳይነቅፈን እንጠነቀቃለን (፪ኛ ቆሮ ፰፡፳) እንዳለው፤ ከነዚህ እንቅፋቶች ባንዷ ተሰናክለው ለህዝብ እንቅፋት እንዳይሆኑ የጰራቅሊጦስን ስጦታ የተቀበሉ መንፈሳውያን መሪዎች፤ እጅግ ለጠነቀቁ ይገባቸዋል።
ለምሳሌነት ብቁ ጳጳስ ነኝ የሚል ሰው ቀርቶ፤ ያልተፈቀደውን ይቅርና “የተፈቀደው ሁሉ ግን አይጠቅመኝም”፩ኛ ቆር ፭፡፲፪) ብሎ ራሱን የመግታት መንፈሳዊ ሃይል ሊኖረው ይገባል። የጵጵስና ዋና ተልእኮ መመሪያችን “ወኩኖሙ አምሳለ ለምእመናን በቃል፡ወገድል፡ወበፍቅር ወበሃይማኖት ወንጽህ”( ፭፡፻፲፬) ብሎ በሚያዝዘው መሰረት፤ መንፈስ ቅዱስ ከሚጠላው ለመሸሽ፤ የሚወደውን በመከተል ቅዱስ አትናቴዎስ “ኢይቁም ወኢይህበር ምስሌክሙ በጸልዮ ኢዘማዊ ወኢቀታሊ ኢሰራቂ ወኢሀሳዊ ዘውእቶሙ ፭ቱ አክላባት እለ በአፍ ይትኬነኑ (አት ፰) የሚለውን ለማስተማር ነው።
ዝሙት የውሻ ጠባዮች ናቸው ከተባሉ አንዱ ነው። እሳቸው በዚህ ነገር ፍርድ ቤት የደረሰ ነገር ተሸክመው ሳለ፤ የሰሩት በደል ሳያንስ ከዚያ አልፈው ተርፈው፤በሚያስወግዝ በነገረ መለኮት ጥሰት፤ እንቅፋት ሆነውብናልና ይወገዱልን የሚል ክስ የሚገለግሉት ህዝብ ሳያቀርብባቸውና ሳይረጋገጥባቸው፤ አባ እንጦንስ ካህኑን ማውገዝ ቀርቶ ማዘዝ አይችሉም። ይህም ራሱ ከዝሙት ከስርቆትና ከነፍስ መግደል ያለነሰ በደል ነው።
“ወለዘኢአከሎ ክህደቱ ባህቲቱ እስከ ያወጽኦ ለካልዑ እምሃይማኖቱ ወኮነ ምክንያተ ለክህደቱ ይኩን
ንስሓሁ ፈድፋደ”( አ ፳፡፯፻፷) ራሱ የሰራው በደል አልበቃው ብሎ በሚሰራው ስህተት ለሌላው እንቅፋት
ለሚሆብ ሰው፤ ንስሀው ከባድ ይሁን።”ይላል።በስም መጣለፍ በተደረገው ስህተት አንባቢን ይቅርታ
እጠይቃለሁ።
ቀሲስ አስተርአየ
No comments:
Post a Comment