Friday 20 June 2014

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን የተግሳጽ ድምጽ

ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያ የተግሳጽ ድምጽ
ከሐመረ ኖኅ ኪዳነ ምህረት ምእመናን
75 South Bragg Street, Alexandria, Virginia 22312

ፍካሬ ዘጻድቃን በላዕለ ኃጣአንመዝ፣1)
በእርመኞች ላይ የሚሰነዘር ተግሳጽ፤
ሰኔ ፲፪ ቀን ፳፻፮ ዓ. ም.


 አባትና እናቶቻችን እርም (የታወቀ ኃጢአትታቅፈው ለጸሎት ወደ ቤተ ክርስቲያን ሊሄዱ ቀርቶ በቤታቸው ፍካሬ ዘጻድቃን ወዘኃጥአንየሚለውን ይደግሙ ዘንድ፤ ዳዊት ለመግለጥ አይደፍሩም ነበር። በመካከላቸው የተከሰተውን እርም ሳያወጡ እህል ውሀ አይቀምሱም ነበር። በዚህም ጥንቃቄያቸው ለሚያቀርቡት ጸሎት እግዚአብሄር ፈጥኖ ይመልስላቸው ነበር።

በንስሀ ፈጥነው ከእርም እንዲላቀቁ እያተጉ የሚመሯቸው ካህናት ነበሯቸው። ዛሬ ብዙ ካህናቶቻችን ከገባንበት እርም እንድንወጣ ሊመሩንና ሊያስተምሩን ቀርቶ፤ እንዲያውም ራሳቸው እርም አድራጊና አደራራጊ ሆነው ቤተ መቅደሳችንን የእርም መፍለቂያ፤ ክህነታቸውን የእርም ማስፈጸሚያ መሳሪያ፤ ህዝበ ክርስቲያኑንም የእርማቸው መከማቻ ደለል አድርገውናል።

የገባቸው አባቶች ካህናት፤ በኩዳዴ ጾም መርሀ ግብር ማጠቃልያ የስቅለት እለት ማታየይሁዳ ልጅና የልጅልጅ ይደምሰስእያሉ በመቋሚያቸው የጧፏን ጢስ ለማጥፋት የሚያከናውኗት የረቀቀች መንፈሳዊት ኪነት ለልማድ የሚያደርጔት አልነበረችም። ይህች ኪነት የምታሳየው በይሁዳ የገባው ክፉ መንፈስ በመካከላችን የገባበት ካለ ይደምሰስ ለማለት ነው። ከነ እርማችን ለበዓል ተሰሰብሰበን እልል ብንል፤ ሰባኪ ላቡ እስኪንጠበጠብ እንደ ግስላ ቢደነፋ፤ ከበሮ ተሸክመን ብናሸበሸብ ከስሜት ማስገንፈል አልፎ፤ የቤተ ክርስቲያን ድምጽ በመሆን ጸሎታችን ቅድመ እግዚአብሄር አይደርስም። ስለዚህ እኛ ዛሬ በመካከላችን ያሉ እርመኞች ንስሀ ገብተው የገባባቸው ክፉ መንፈስ ከነሱ እስኪወጣ ድረስ ከቤተ መቅደስ ይገለሉ በማለት እንደ ጧፏ ጢስ ይጥፋ በማለት ይህችን መንፈሳዊት ኪነት እናከናውናለን። ከሁሉ በፊት መቅደም ያለበት ይህ ነውና፤ እርሰዎም የቅድስት ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ተከታይና ተቆርቋሪ ከሆኑ፤ ከዚህ በታች እስከ የተዘረዘሩትን የቤተ ክርስቲያነዎን ድምጽ እየሰሙ እርመኞችን እየገሰጹ ላልሰማው ያሰሙእንደ ገለልተኛ ቆመው በመመልከትና እኔ ምን አገባኝ በማለት የእርም ተካፋይ አይሁኑ

የቤተ ክርስቲያን የተተግሳጽ

ኛ:-   “ለኩሉ ዘዐለወ፤ ወተቃረነ ንባበ መንፈሳዌ፡ ወተግህሰ እምነ ጽድቅ፡ውስተ ኩሉ ሃበ ሀለወ፡ ወለኩሎሙ ከሀድያን፡ ወሰብእ እኩያን፡ወሕጉላን፡ እለ አልቦሙ ሃይማኖት፡ ወዘዐለው ሃይማኖተነ፡ ወእለ ሤሙ ላዕሌሆሙ መገብተ ከሐድያነ ንኴንኖሙ በግዘት በኩሉ መዋዕል (ሃይ ምዕ ፻፩፡፳፫)

የሚዋሹ፤የሚሸፍጡ፤ራሳቸው ጠፍተው ለሰው ጥፋት ምክንያት የሚሆኑ፤እምነት የሌላቸው፤ቤተክርስቲያናችን ከምታስተምረው ጋራ የሚጋጩ ክፉ ሰዎች ከቤተ ክርስቲያን ይገለሉ። ይህ አይነት ባህርይ ያላቸውን እንደ ታደሰ ያሉትን ሰዎች ለንስሀ ከመገፋፋት ይልቅ በድፍረት ወደ አገልግሎት የሚልኩትና የሚተባበሩትም አብረው ከነሱ ጋራ ከቤተ ክርስቲያናችን ይገለሉ።ትላለች ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን።

ኛ፦   “የሀበነ ኪያሆሙ ለነዋህ መዋእል  በልቡና ያርትኡ ቃለ ሃይማኖት በንጹህ ዘእንበለ ነውር እስመ እሙንቱ ቀዋምያኒሃ ለቤተ ክርስቲያን” (፵፩፡፸፬)::

ከነቀፋና ከነውር ራሳቸውን ጠብቀው፤ እምነታችንን አቃንተው የሚያስተምሩ የቤተ ክርስቲያናችን ጠበቆች ናቸውና ረዥም እድሜ ሰጥቶ ያቆይልንከምንላቸው አባቶች ጋራ አባ ፋኑዔል (አባ መላኩ) ቁጥር የሚገቡ አይደሉም። ስለዚህ አባ ፋኑኤል ተልእኳቸውን ሊወጡ ቀርቶ እምነቱን ስለማያውቁት፤ በቅዳሴ ጊዜ ስማቸው ሊጠራ ይቅርና፤ ከቅድስት ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያናችን ቤተ መቅደስ መውጣት ያለባቸው ናቸው።ትላለች ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን።

ኛ፦   “እስመ ቤተ ክርስቲያን ወለደቶሙ  ለኩሎሙ በጥምቀተ ክርስትና። ወፈድፋደሰ ለዓቃብያነ ህግ እስመ ጳውሎስ ሐዋርያ ስምዐ ኮነ እንዘ ይብል ከመ እለ ተጠምቁ በክርስቶስ ፩ዱ እሙንቱ” አን፱፡ ቁ ፪፻፹)።

ለምእመናን እንቅፋት የሆነውን ግለ ሰብ፤ ከቤተ ክርስቲያን ለይተው የማስወጣት መብት የተፈቀደው ለሊቃውንት ብቻ አይደለም። በቤተ ክርስቲያናችን ተጠምቀው፤ ከሊቃውንቱ እየተማሩ መመሪያዋን የተረዱ ከሆኑ፤ በቅርብ ያሉ ምእመናንንም በከሀኑ ላይ የተረጋገጠ ስህተት ካዩ፤ ሊያስወጡት ይችላሉ። በዚህም መሰረት፤ ታደሰ መጀመሪያ ባካባቢው ባሉት ምእመናን ተወግዞ በሶስቱ ካህናት የጸደቀበት ውጉዝ ነው። ትላለች ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን።

ኛ፦   “እመሰ ኮነ እኩየ በሑረቱ ወተከስተ አበሳሁ ወጸንአ በዝ፤ድልው ለሊቃውንት ከመ ይፍትሁ ላዕሌሁ”( ፍ አ ፱፡ ቁ ፫፷፱)

ካህን በምእመናን ተመክሮ የምእመናንን ምክር አልቀበልም ብሎ በትቢት መንገድ በመቀጠሉ ምእመናን አንፈልግህም ካሉ፤ስህተቱን የቤተ ክርስቲያናችን መጻሕፍት መርምረውና ተርጉመው በመመዘን የቤተ ክርስቲያናችን ሊቃውንት የምእመናኑን ውሳኔ እንዲያጸድቁበት ቤተ ክርስቲያናችን ትፈቅዳለች። ተወጋዡ በስህተት ተወገዝኩ ካለ፤በይግባኝ እንዲታይለት በቅዱሳት መጻሕፍት ወደ ሚመራው ሲኖዶስ ጉዳዩን ማቅረብ አለበት። የተላለፈበት ውግዘት በስህተት ከሆነ፤ አውጋዦች ተወግዘው ይወጣሉ። በስህተት የከሰሱት ምእመናንም ንስሀ ይገባሉ። የተወገዘው ወደ ክህነቱ ይመለሳል። በዚህ መንገድ ካልሆነ በቀር፤ ታደሰ ምንጊዜም የተወገዘ ነው። ትላለች ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን።

ኛ፦   “ህቱ እምውስት ህዝብክሙ በአበይኖ፡ ኢይቁም፡ ወኢይህበር፡ ምስሌክሙ በጸልዮ፡ ኢዘማዊ፡ ኢሰራቂ፡ ኢሀሳዊ  ዘውእቶሙ ፭ቱ አክላባት እለ በአፍአ ይትኴነኑ አትናቴዎስ” (ቅ ቁ ፰ )

“ውሻ ወደ ትፋቱ ይመለሳል። የታጠበች እሪያም ተመልሳ በጭቃ ትንከባለላች” (፪ኛ ጴ ፪፡፳፪” ሲል ቅዱስ ጴጥሮስ የተናገረውን፤ቅዱስ አትናቴዎስም መሰረት በማድረግ፤ “በሚዛናዊ ፍርድ ውስጣችሁን ፈትሹ። ዘማዊ፤ ሌባ፤ አታላይ፤ ሸፍጠኛ የመሳሰሉት ባህርያት በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ሊከሰቱ ቀርቶ፤ ከክርስትና ውጭ ባሉ ሰዎች መካከል እንኴ መከሰት የሌለባቸው የውሻ ጠባያት ናቸው። ስለዚህ እነዚህ ባህርያት ያሉባቸው ሰዎች በጸሎት እንዳይተባበሩ ከመካከለችሁ ለዩዋቸው” ብሏል። ታደሰ የራሱን ትዳር አፍርሶ፤ ለሌላ ትዳር መፍረስ ምክንያት በመሆኑ ንስሀ ሳይገባ ቀድሶ ማቁረብ ቀርቶ፡ መቁረብ አይችልም። ወደ ቤተ መቅደስ እንዲገባ አይፈቀድለትም። በነዚህ ባህርያት የሚከሰሱና የሚወቀሱ ታደሰን የመሳሰሉ ሰወች ተወግዘው መውጣት አለባቸውትላለች ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን።

ኛ፦   “ርኩሳንሰ  እለ ያረኩሱ ይከውኑ ስዱዳነ እም አንቀጸ ዴዴ ዘምሥጢራት” (አረጋዊ መንፈሳዊ ምዕ ፴፭)

ራሱ በኃጢአት ወድቆ፤ በውድቅ ምሳሌነቱ ለህዝብ እንቅፋት የሆነ ካህን ንስሀ ይገባል እንጅ ቀድሶ ማቁረብ ቀርቶ፤ ሊቆርብ አይፈቀድለትም። እንዲያውም የክህነት አገልግሎት ከሚከናወንባት መቅደስ መድረስ የለበትም። ታደሰ የምእመናንን መንፈስ አቆሽሿል፤ ቤተ መቅደሳችንንም አርክሷልና ከክህነት አገልግሎት መገለል አለበት። ትላለች ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን።

ኛ፦   “አንተሰ ሕዝባዊ አልብከ ሥልጣን ከመ ትኮንኖ ለካህን በእንተ መስዋዕት” (ሰለ ፳፪፡፲፪

የቤተ ክርስቲያናችን መመሪያ ካህንን መቃወም ለምእመናን የማይፈቅድላቸው፤ ካህኑ ፩ዱ አብ ብሎ ስርአተ አምልኮ ከጀመረባት፤ በሰላም ወደ የቤታችሁ ግቡ እስኪሚባልበት ሰአት ድረስ ብቻ ነው። ለምእመናኑ እንቅፋት የሚሆን የታወቀ ስህተት የተገኘበት ካህንም፤ እንደማነኛውም ክርስቲያን በማነኛውም ሰአትና ቦታ በህዝበ ክርስቲያን መወቀስ፤ መከሰስ፤ መወገዝ አለበት። በቅዳሴዋ ሰአት ብቻ የተከለከለውም፤ ከቅዱስ አምልኮታዊ ተግባር ጋራ በመተሳሰሩ እንጅ፤ ለግለ ሰቡ ክብር አይደለም። ስለዚህካህን የፈለገውን በደል ቢፈጽም፤ አምላክ ይቅጣው እንጅ ህዝብ ካህንን መቃወም የለበትምየሚለው መታረም ያለበት በልማድ ሲነገር የኖረ ትልቅ ስህተት ነው።  

ከ፩ እስከ ፯ የተዘረዘሩትን የቤተ ክርስቲያናችን ተግሳጾች ሲጠቃለሉ፦

አባቶቻችን “ፍካሬ ዘጻድቃን ወዘኃጥአን” የሚለውን ህሊና ወቃሽ የሆነውን መዝሙረ ዳዊት በጸሎት መንገድ ለመድገም ከመዘጋጀታቸው በፊት፤ በውስጣቸው የገባውን እርም በገለልተኝነት ዝም ብለው በመቆም አይመለከቱም ነበር። የገባውን እርም ሳያወጡ ዳዊቱን በጣቶቻቸው ለመንካት አይደፍሩም ነበር። በመካከላቸው የተከሰተውን እርም ሳያወጡ እህል ውሀ አይቀምሱም ነበር። በዚህም ጥንቃቄያቸው ለሚያቀርቡት ጸሎት እግዚአብሄር ፈጥኖ ይመልስላቸው ነበር። እኛም በመካከላቸው የገባውን እርም እያስወጡ ዳዊት ደጋሚዎች እንደ ነበሩት እንደ አባቶቻችንና እናቶቻችን እንጅ፤ እርም ታቅፈን ዳዊት የምንደግም አነብናቢዎችና አሸብሻቢዎች ብቻ አንሁን።


እግዚአብሄር ጸሎታችንን ይሰማ ዘንድ፤ መጀመሪያ ታደሰን በመሳሰሉ አስመሳይ ሰዎች የገባውን እርም እናስወጣ። ደጋግ ካህናት አባቶቻችን በስቅለት ኃጢአት በደል የሚፈጽሙ በጻድቃን ማህበር በክርስቲያኖች መካከል አይቆሙም። እግዚአብሄር የጻድቃንን መንገድ ያውቃል የክፉወች መንገድ ግን ትጠፋለች።መዝ 14_6እያሉ የጧፋን ጢሲ እንደሚያጠፉ፤ እኛም እንዳባቶቻችን ባንደበታችን በመናገር፤ በቃላችን በመመስከር እንዲህ በማድረግ በታደሰና ታደሰን በመሰሉ ሰዎች በኩል የገባብንን እርማችንን ከመካከላችንና ከቤተ መቅደሳችን እናውጣ። ይህን በማድረግ ክርስቲያናዊ ድርሻችንን ሳንወጣ፤ በእርም የተጠቀለሉ ካህናት ፩ዱ ብለው እየቀደሱ ከነእርማችን ሆነን የእኛም ማስቀደስ፤ ለበዓል ተሰሰብሰበን እልል ብንል፤ ሰባኪ ላቡ እስኪንጠበጠብ እንደ ግስላ ቢደነፋ፤ ከበሮ ተሸክመን ብናሸበሸብ ስሜታችንን ከማስገንፈል አልፎ፤ በንስሀና በጸጸት እንደቀረበ ጸሎት ቅድመ እግዚአብሄር አይደርስም። እንዲያውም ክርስቶስዕውርን ዕውር ቢመራው ሁለቱም ወደ ገደል ይወድቃሉ (ማቴ፲፭፡፲፬)” እንዳለው፤ በእርም በታወሩ መስለው በገቡ ታደሰንና አባ መላኩን በመሳሰሉ ካህናት እየተመራን ገደል መግባት ነው። ገደል ከመግባታችሁ በፊት እርማችሁን አውጡ የሚለውም የቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን የተግሳጽ ድምጽ ነው።

No comments:

Post a Comment