Wednesday, 7 September 2016

"አልጠግብ ባይ ሲተፋ ያድራል"

"አልጠግብ ባይ ሲተፋ ያድራል"

ከወንድሙ መኰንን፣ ብሪታኒያ (ነሐሴ 28 ቀን 2008 ዓ.ም - 3 September 2016)

መግቢያ


አይ ወያኔመጨረሻቸውን በዓይናችን ልናይ ይሆን? አቦ አታስጎምጁን! ዓለማቸዉን ሲቀጩ ማቆሚያ ያጠራት ዓለማቸው ጨርሳ ልትቀጭባቸው ነው መሰል! እየዘረፉ እየገፈፉ፣ ሕዝቡን አደኸዩት፣ አስራቡት፣ አሳረዙት። እነሱ ግን ለዕርድ እንደተዘጋጀ ሰንጋ ሲደልቡ፣ ሲሰቡ ሩብ ምዕት ዓመታት አለፉ! አልጠግብ ብለው ግን መትፋት ጀምረዋል! ሕዝባችንን፣ አንገሽግሸውት አንገቱ ድረሰውታል። የከፋው የከረፋው ሕዝብ ከዳር እስከ ዳር ተነቃንቋል! ኦሮሞው ተነስቷል። አማራው ተነስቷል። ኮንሶው ተንስቷል። ኦጋዴን ተነሷል። ... እስከወዲያኛው ከፋፍለነዋል ያሉት ኦሮሞ እና አማራ ተስማምቷል! ዕቅዳቸው ከሽፏል።  


የወያኔ የግድያ ቡድን አባላት፣ ያልታጠቁ ዜጎቻችንን ደም በጭካኔ አፍስሰው፣ እኵይ ተግባራቸውን ከጀግንነት ቆጥረው ይፎክሩበታል፣ ያቅራሩበታል። አሁን ሴት ገድሎ ምን ያስፎክራል? ሕጻን ገድሎ ምን ያስሸልላል? እኵይ! እኵይ! እኵይ! የእንግሊዝኛው ቋንቋ የበለጠ ይገልጻቸዋል! COWARDS! ያ አልበቃ ብሎአቸው በግፍ ገድለው በነሱው ብሶ ሕዝቡን ሲኮንኑት ማየት አያንገሸግሽም? ንጹህ ዜጎችን እያሰሩ “ሽብርተኞች ናቸው” እያሉ ሲወነጅሉ ማየት አያበሽቅም? የታሠሩትን እያሰቃዩ፣ ያሾፉበታል። አዎን፣ ሰላም ያሸብራቸዋል። አንድነት ያሸብራቸዋል። አገር ወዳድነት ያሸብራቸዋል። አፋቸውን ሞልተው “ልማታችንን ለማደናቀፍ የተነሱ ጸረ-ልማት ኃይሎች በቁጥጥር ሥር አዋልን” እያሉ ይበሻቀጣሉ። ዕውነት ነው፣ እነሱ ከድኃው አፍ እየነጠቁ፣ እየሰቡ፣ እየዳበሩ ለምተዋል። አብዛኛው ከአፉ እየተነጠቀ ያጎርሳቸዋል። እየተራበ፣ እየከሳ እየሰለለ መንምኖ እንሱን ያለማል። ይኸ  ሁሉ መብት መጋፋት፣ የዘረፋ ተግባር ዕድሜአቸውን የሚያራዘምላችሁ እየመሰላቸው ጭካኔአቸውን በላይ በላዩ ይጨምራሉ። የወያኔ አጨካከን ከሰው የተፈጠሩ አያስመስላቸውም። የመረረው የመጨረሻውን ዕርምጃ የመውሰዱን ሐቅ፣ ያ በኮለስትሮል የደነደነው አዕምሮቻቸው መረዳት ተስኖታል። ወያኔዎችች የበሉት ያገሳቸዋል! በላይ በላዩ!


ልጆቻቸውን የሚስተምሯቸው መርዝ አሳሳቢ ነው። ብልግናና አስጸያፊ ስድብን ያስተምሯቸዋል። ብልግናን ባህላቸው አድርገወታል። ለመሆኑ የዚህችን ምስኪን ሴት አዕምሮ እንዴት ቢመረዝ ነው፣ ምድረ ወያኔ ሲገናኙ የሚያወሩትን አስጸያፊ የስድብ ናዳዋን በአማራውና በኦሮሞው ላይ በአደባባይ፣ እራሷን በመቅረጸ-ሥዕል (ቪዲዮ) እየቀዳች፣ የተፋቸው? ጤናማ ናት? https://www.facebook.com/lydia.zewdu/videos/10153635730341268/ ? ከዚህ በኋላ ዕድሏ ምን ሊሆን ይችላል? እዚህ ከደረሱ፣ ቆምንለት የሚሉትን ብሔር፣ ብሔረሰብ እና ሕዝብ፣ በአደባባይ ካዋረዱት፣ መጨረሻቸው መቃረቡን አብሳሪ መሆን አለበት። በቃ፣ የከፋፍለህ ግዛ መርዛቸው ተበረሰባቸው። ይኽቺ ምስኪን እናትና አባቷ ሲያወሩ እየሰማች ያደገቸውን ነበር የዘከዘከችላቸው። ለመሆኑ በምን ዘዴ ነው፣ ከትግራይ የተሰደደችው? ኤርትራዊት ስደተኛ ነኝ ብላ? ይኸንንም ዜዴአቸውን ደርሰንበታል። እያንዳንዳቸው ወያኔዎች እርስበርሳቸው የሚነጋገሩት እሷ እንዳቀረበችው፣ በወረደ ቋንቋ ነው። በነሱ ቤት ከነሱ በላይ ሰው የለም። ብሔር፣ ብሔርሰቦችና ሕዝቦች፣ በአማሮች ተጨቁነዋል። እኛ ግን ‘ናጽነት’ አመጣንለት” እያሉ፣  ሕዝብ ለሕዝብ እያፋጁ፣ ከፋፍለው ገዙት። ለራሳቸው በክፍለ ሀገራቸው፣ ሆስፒታል፣ ትምህርት ቤት፣ መንግድ ሲያሰሩ፣ ኦሮሞውና አማራው እንደተቃቃረ እንዲኖር፣ የተቆረጠ ጡት ሀውልት ሠሩለት! ነገረ ሥራቸው የጆርጅ ኦርዊአልን የእንስሣት ግብርናን (Animal Farm) ያስታውሰናል። “ሁሉም ብሔር፣ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች፣ እኵል ናቸው። የትግሬ ብሔር ግን ወርቅ ነው” ይሉናል ወያኔዎች። ምስኪን ልጅ!  ከተወለደች ጊዜ ጀምሮ፣ እሷ ወርቅ ስትሆን አማሮችና ኦሮሞዎች አህዮች ናቸው ተብላ ሲነገራት አድጋ ምን ታድርግ? ወደፊት የዘረፋቸውን ዕድሜ የሚያራዝም ተተኪ ዘረኛ ትውልድ ማፍራታቸው መሆኑ ነው። “ገና ዕድሜ ልካችሁን፣ ልጆቻችሁን፣ የልጅ ልጆቻችሁን ትግሬ ለዘልዓለም ይገዛችኋል” አለችን። ድንቄም! ስንሰማ መጀመሪያችን እኮ አይደለም። በለንደን፣ የፈረንጅ ቤት እየጠረገች የምትኖር አንዲት የትግራይ እህት፣ ሰላማዊ ሰልፍ ላይ እያለን አይታን፣ አንገቷን ሰግጋ፣ አንዴ እንዲሁ ብላናለች። አዲስ አበባ በልመና የሚኖሩትም እንዲሁ ያስቡ ይሆን? እነሱ በተራበ አንጀታቸው እንዲ ሲሉን፣ የጠገቡትማ እንዴታ! ግን አልጠግብ ባይ ሲተፋ ማድሩን ማን በነገራቸው! በወገሩን ቁጥር እንደሚስማር እንጠብቃለን። ሊከፋፍሉን በተነሱ ቁጥር፣ አንድነታችን ሥር የሰዳል! ዘረኝነት ከወያኔ ጋር ይቀበራል።

አማራና ኦሮሞ መሰደቡን፣ አትጥሉት። ይኸ የወረደ ተራ ስድብ፣ ከዚህ በኋላ፣ እርስ በርስ እንደጠላት የመቆጣጠር የወያኔን መርዝ ያበርስበታል። ኦሮሞና አማራ የኢትዮጵያ ዋና ግንዶች ናቸው። ቀንደኛና መርዘኛ ጠላቱ ማን እንደሆነ ስድባቸው በበለጠ አጣርቶ ለማየት ይረዱታል። አሁን የተጀመረው መተባበር፣ እስከወዲያኛው ዘልቆ፣ ከድል በኋላም፣ አማራና ኦሮሞ የአንድ እናት ልጆች መሆናቸው እንደገና ይረጋገጣል። የማንም ዘረኛ መርዝ በማያነቃንቀው የማዕዘን ድንጋይ ላይ ይታነጻል። ይብላኝ ለወያኔ። ወያኔና አሽቃባጮቻቸው ውርጭ ላይ ይቀሯታል። እነሆ ተንኮላቸው ተንኮታኩቶ ሲሰበርባችው፣ ሆዳቸው ወደ አባው፣ ወደ ተራ ስድብ ወረዱ።

ልጅቷ ብቻ እኮ አይደለችም ሰሞኑን የምትሳደበው። ደብረጽዮን የሚሉት ዶክተራቸው፣ ጌታቸው ረዳ የሚሉት አፈ ቀላጤአቸው ያንን ሲዘረግፉ በቪዲዮ ተቀድተው አየናቸው አይደል! ሰማናቸው! ድሮውንም እኮ ትንሽ ነው የሚበቃቸው። በቀላሉ ግንፍል-ግንፍል! ሆደ ባሻ! ገፋ ሲደረጉ፣ የሆዳቸው ዝርግፍ! ድሮም ሆዳም አልጠግብ ባይ ባፉ ሲተፋ አይደል የሚያድረው!
ከዚህ በኋላ የሚሞኝላቸው ያለ አይመስለኝም። ምን ነበረ፣ ሰሞኑን የሰማናት? የመቀሌን ሕዝብ ሰላማዊ ሰልፍ አስወጥቶ “የኦሮሞ ጥያቄ፣ በኪራይ ሰብሳቢነት ስህተት የተነሳ ትክክለኛ ጥያቄ ነውና ተገቢ መልስ ይሰጠው” ለማለት? ዋ! የ“ከፋፍለህ ግዛ” የዘር ፖሊቲካ እቁባቸው ተበልቷል፣ ሌላ ቁማር ካላቸው ይልቅ ይጫወቱ!  “ኦሮሞና አማራ አንድ ሆነ” ማለት ለወያኔ ትልቅ መርዶ ነው። የጠገበ ጭንቅላት፣ ማሰብ ይሳነዋል። ወያኔዎች፣ ያለልክ ስለጠገቡ፣ የተደነቀረባቸውን አደጋ ማየት አልቻሉም። ኦሮሞን “ሞኝ ነው” ብለው ስለሚገምቱት፣ ቁማር ጨዋታ ሊጀምሩ ነውና፣ ኢጆሌ ኦሮሞ! ቃቢካ! ከሁሉ ከሁሉ የሚገርመው ንቀታቸው ነው። ጥግብ ብለው ከትግራይ ክልል ውጪ ያለው የሰው ዘር በሙሉ ሰው አልመስል ብሎአቸዋል። ከነሱ ወዲያ ጀግና መኖሩን ማሰብ ተስኗቸዋል። ከነሱ ወዲያ ብልጥ ያለ አይመስላቸውም። ሲቻል አታለው፣ ካልተቻለ በጉልበት የኢትዮጵያን ሕዝብ ማንበርከክና ለመግዛት እንደሚችሉ በአጉል ዕምነት ተጀብነዋል። ዘረኝነት ዋናው መሣሪያቸው ነው። ያ ደግሞ መልሶ እንድሚባርቅባቸው ጨርሶ መገንዘብ አይችሉም። ኢትዮጵያ ከወያኔ ወዲያ ጠላት የላትም! አከተመ።

የአገር ክህደት ወንጀል።

የወያኔ የሀገር ክህደት ወንጀል ተዝቆ አያልቅም ኢትዮጵያን ያለ ባሕር በር ማን ነበር ያስቀራት? ሰሞኑን Tigray Online[i] በሚባለው ድረ-ገጻቸው የተጻፈውን አስተውላችኋል? እኛ አሰብን አላስወሰድንምአንቺው ታመጪው አንቺው ታሮጪው! ከሀዲውን መለስ “አባይን የደፈረ መሪ” እንዳሉት፣ ኃይለማርያ ደሳለኝን፣ “አሰብን ለማስመለስ የደፈረ መሪ”፡ ብለው እንደገና ሊያዘናጉን ነውና ጎብዝ አን በሉ። “አሰብን እናስመልስ” በሚልስ ሰበብ፣ ጦርነት ውስጥ ዱለውን፣ አሁን የተጀመረውን የሕዝባዊ አመጹን አቅጣጫ እንዳያስቱ ከወዲሁ መጠንቀቅ ያሻል። ዓባይ ጸሐይና ስብሀት ነጋ የማይሽረቡት ተንኰል አያልቅም። ስለ አሰብ ገና ታሪክ ይፋረዳቸዋል። የሰውን ልጅ የሚያሳፍር ቆሻሻ ተግባር ፈጽመው ሲደንፉበት ሰምተናቸው የለ? “ገንጣይ አስገንጣይ”ታሪካቸው ተጽፎ ተቀምጦ ለፍርድ ይጠብቃቸዋል።  ኢትዮጵያን ለመቆራረጥ ያፈሰሱት የንጹኃን ደም ይጮሃል ከሚያስገርመው ነገር ሁሉትላንትና የሻዕቢያን እግር እንዳልላሱ፣ ዛሬ አገር አፍቃሪ ኢትዮጵያን ከነዚህ ጉደኛ ነቀርሶች ለመገላገል የሚያደርገውን ትግል (ከሻዕቢያም ተባበረ - በራሱ ቆመ) “ሻዕቢያ ላከብንእያሉ ያላዝናሉ አገር አፍቅሪ ሁሉ፣ ማንኛውንም ያዋጣኛል ያለውን ታክቲክና እስትራተጂ ቢጠቅምና ኢትዮጵያን ከነዚህ መዥገሮች ነጻ ካወጣት፣ አንዳችም የሚያሳፍር ነገር አይኖርበትም። ብልጥ መሆናቸው እኮ ነው። እዴያ! ለመሆኑ የሻዕቢያ አንድ ቁጥር ተላላኪ ማን ነበርና ነው! እስቲ ቆይ! ይኸ ፎቶግራፍ የሚያሳየው፣ ምንድን ነው? የጌታና የአሽከር ፍቅር!




ኧረ ሌላም እንጭምርላቸው! በኤርትራ “ናጽነት” ቀን መለስ “የጠላቶቻችሁን አከርካሪ ዳግም እንዳይነሱ አብረን ሰብረናል” እያለ የተናገረው ይኸ ንግግር የፍቅር ነው ወይስ የጥል? http://www.fettan.com/MeleseZenawi/MeleseEritreaTIG.ram. ስብሀት ነጋስ ስንት ጊዜ ወጥቶ ነው፣ “የኤርትራ ነጻነት ከተነካ እንደገና በረሀ እንወርዳለን” ሲል የሰማነው?

የትግራይ ነጻ አውጪ ድርጅት ወይም ወያኔ ለፈጸመው ክህደት፣ የተባበሩት መንግስታትና የአሪካ ሕብረት ኮሪዶ እኮ ቋሚ ምስክሮች ናቸው። "ተገንጣይዋን ኤርትራን ዕወቁልን” ለው ዶሴ ተሸክመው እነማን ነበሩ የተሯሯጡት? አድራጎታቸውን ኢትዮጵያውያን ብቻ ሳይሆኑ ዓለም በአግራሞት ያስታውሰዋል።  እነርሱ ቢረሱ እኛ አንረሳውም። ነርሱ ያንን የሀገር ክህደት ወንጀል ፈጽሙ ኑሮ፥ ኤርትራ እስከዛሬ እንደ ሶማሌላንድ ተተብትባ ቁጭ ባለች ነበር። ለእነርሱም የራስ ምታት ባልሆነችባቸው! "ሥራ ለሠሪ እሾህ ላጣሪው" የሚባለውን ይኸው አይደል? በዚህ ጉዳይ፣ አንድ ጊዜ የኤርትራው ኢሳይያስ አፈወርቂ "አፋሮች ታግለው ንጠል ቢችሉ ምን እርምጃ ልትወስዱ ትችላላችሁ?" ተብሎ በጋዜጠኛ ለቀረበለት ጥያቄ ሲመልስ፣ "እዚያ አይደርሱም እንጂ ከደረሱ የተባበ መንግስታትም ሆነ አፍሪ ሕብረት ላይ ዕውቅና አንሰጥም" ብሎ መለሰ። እናንተስ ለነጻነትችሁ ታግላችሁ ነጻ ስትወጡ ነጻነትችሁ ታውቆላችሁ የለ?" ሲባል፥ "ያማ የኢትዮጵያ መንግሥት እራሱ መጀመሪያ ዕውቅና ሰጥቶን ቱም ድርጅቶች ላይ ዕውቅና እንድናገኝ ስለተባበረን ነው የተሳክልን። እኛ ግን ማንኛውም የኤርትራ አካል ልገንጠል ቢል እንፈቅድንልትም" በማለት በጠራራ ጸሐይ ሰከረባቸው  ከሀዲዎች! አፋቸውን ሞልተው “ከእርትራ ጋር ቆሙ” እያሉ ሌላውን ይከሳሉ! ዓይን አውጣዎች! ማፈር የምትባል እሴት መቼም አልተፈጠረችባቸውም!


በዘር ከከፋፈሉን በኋላ ሥራቸው መልሶ ሲባርቅባቸው፣ እኛን ዘረኞች ማለት ጀምረዋል? እነርሱ ሕገ-መንግሥት ቀርጸውለት ያጸደቁትን ዘረኝነት ረስተውታል እንበል? ከወርቁ ዘር ውጪ፣ የመለመሏቸው ጉዳዮቻቸውን የሚያስፈጽሙላቸው “ኦሕዴድና” “ብአዴን” መሆናቸውን በአደባባይ ይነግሩናል። ለቀባሪ አረዱ። ብአዴንን ሲያዋርዷቸው፣ “የትግራይ ሕዝብ፣ ለአማራ ወንድሙ ጠፍጥፎ ሠርቶ የሰጠው ስጦታ ነው” ብለው አፋቸውን ሞልተው ሲናገሩ ሰማናቸው። በሁኑ ሰዓት አንዳንድ ኦሕዴድ ሆኑ ብአዴን “ሕዝባችንን አንጨፈጭፍም” ሲሉ አቅለ ቢሶቹ ወይኔዎች፣ ወደ ተራ ስድብ ወርደዋል። http://aigaforum.com/article2016/andm-hijacked-commentary-080716.htm

ከዚህ ጽሑፍ፣ ሁለት ነገሮችን ተማርን። ድሮውንም የዚያ የበላይ አመራሮች፣ ቁጩ አማሮች እንጂ ዕወነተኛ አማሮች ለነሱ ሲያገለግሉም አይገኙም። ማነው አማራ? በረከት ስምዖን (መብራቱ ገብረሕይወት) ነው? በመብራትም በፈልግ የአማራ ድም አይገኝበትም። ዴኤነኤውናማ ተውት! ትግሬው ሕላዊ (ፍቅሬ) ዮሴፍ ነው? እርትራዊው/ትግሬው ታደስ ጥንቅሹ (ካሳ) ነው?  ታምራት ላይኔ (ጌታቸው ማሞ ወቅኬኔ) ነው? ጊሚራው ተፈራ ዋልዋ ነው ወይስ ኤርትራዊው ተስፋዬ ገብረ-አብ (የዓይን ምስክር ስለነበረ “ጥቁር አማሮች” ብሎአቸው ነበር በመጽሐፉ) ነው? ዛሬ ሲገነፍልባቸው በአደባባይ አወጁ እንጂ  እኛ እኮ ድሮዎንም ብለን ጨርሰናል[1]። እርግጥ ተራው (rank and file) የቸገራቸው አንዳንድ አማሮች የተጠጓቸው አይጠፉም። “የቸገረው እርጉዝ ያገባል” ይባል የለ? ስድቡ፣ ብዝበዛው፣ ክህደቱ፣ እንዲህ ዓይን አውጥቶ ሲመጣ፣ ቁጩ አማሮቹ ዝም ይበሉ እንጂ ዕውነተኛው አማራ ጠጥቶ ዝም አይላቸውም። ያገለግለናል ብለው በጥቅም ደልለው እስካፉ ያስታጠቁት የአማራ ሚሊሺያ መልሶ እንደሚደፋቸው ለማወቅ እንኳን የመረዳት አቅም የላቸውም። ደብረጽዮናቸው “ትጥቅ እናስፈታዋለን” ብሎ ሲዝት ሰምተናል። እስቲ ከትግራይ ተነስቶ ብቻውን የጎንደርን ሕዝብ ትጥቅ ሲያስፈታ እናያለን። ትልቁ ውድቀታቸው፣ ከኛ በላይ ብልጥ በዚህ ምድር ላይ የለም ብለው ማሰባቸው ነው። ወይ ጥጋብ!

አማራንና ኦሮሞን አጋጭተው 25 ዓመት ሙሉ ኢትዮጵያ ላይ ተንሰራፍተው፣ ዝርፊያቸው ማቆሚያ አጥቶ ሞሉቶ ተርፎ ያስተፋቸው ገብቷል። አሁን ግን በሁለቱ መንቃት ተደናብረዋል። ጥጋብ አሳውሮአቸዋላ! አፈቀላጤአቸው ጌታቸው ረዳ ይኸን ሳያፍር በአደባባይ ተናገረ፡ http://www.zehabesha.com/amharic/archive ዝs/64195። “እንዴት የአንድነት ኃይልና ተገንጣይ ተባበረ! እኛ ጋ የቤት ሥራችንን በድንብ አልሠራንም ማለት ነው”፡ እያለ “እዬዬውን!” አቅለጠ። “ዋይ-ዋይ!” ማለቱን ረስቶታል! ወይ ጥጋብ!

የአገር ክህደት እኮ ዳር ድንበር አለው። የወኔ ክህደት ግን በታሪክ ታይቶም ተሰምቶም የማይታወቅ ነው። ለመሆኑ ቀደ አያቶቻሁ የተዋደቁልትን መሬት፣ አጼ ዮሐንስ የተሰውላትን መሬት ምን ዓይነት የተረገ ቢሆኑ ነው ለሱዳን ገምሰው ሊሸልሟት የተነሱት?  ለመሆኑ፣ “አባቶችህ የሠሩትን የቀሞውን ንበር ክት አታፋልስ።” የሚለውን ምሳሌ 22/28 ካህናቶቻቸው አላስተማሯቸውም? ይኸ ትውልድ ብቻ ሳይሆን የልጅ ልጆቻችን እና ያልተረገሙ የትግራይ የልጅ ልጆች ሳይቀሩ በዚህ ጉዳይ ይፋረዷቸዋል ቀኒቱ ተቃርባለችና የአምላክን ሥራ ጠብቁ።

ስግብግብነት ቀንድ ያስነክሳል!

እንደዚያ “ከአንድ መሶብ ካልበላን፣ በአንድ አልጋ ካልተኛን፣ በአንድ ጉድጓድ ካልሸናንን” ብለው ከአስገነጠሏት ኢርትራ ጋር በፍቅር እፍ-ብትን ሲሉ፣ ምን አጣላቸው? መልሱ ቀላል ነው! ስግብግብነት። ሲከፋፈሉ በድርሻ መጠን ተጣልተው አደሩ! “ሌባ ሲዘርፍ ሳይሆን ሲካፈል ነው የሚጣላው” ያለቸው ማን ነበር? ቁም-ነገሩ፣ በመጀመሪያ ደረጃ፣ ኤርትራ እንድገነጠል የገፋፏት ራርተውላት ሳይሆን፣ ዋናው ምክንያት የኢትዮጵያን ኃብት ብቻቸውን ለማግበሰበስ፣ ለብቻቸውን ኢትዮጵያን ሊግጧት ቋምጠው ነበር። ኤርትራ ሂዳም አሄደችላቸውም ነበር። ኤርትራ የራሷን ገንዘብ እንድታትም ሲያበረታቷት ከርመው፣ ናቅፋ ሲታተም፣  ቶሎ ብለው ብርን ቀየሩትብልጠት መሆኑ ነው። ኤርትራ ብዙ ብር ስለነበራት በብር በርካሽ ከኢትዮጵያ ገዝታ ወደ ኤርትራ እንዳታሻግር የሸረቧት ወያኔያዊ ተንኰል ነበረች! በመስግብገ ለዘረፋ የከሸኗት ብልሀት ኤርትራ ጋር ለጦርነት ዳግም ዳረገችን። ኤርትራ መሬታችንን ልትወስድ ወጋችን ብለው ወደ ሕዝቡ ጮኹ ሕዝቡ ክህደታውን ወደጎን ትቶ ከጉድ አወጣቸው
የኤርትራ መሸነፍ ደግሞ ሌላ ጣጣ ነበረው። የኤርትራ ነጻነት አደጋ ላይ እንዳይወድቅ፣ ድሉን ውሀ ቸለሱበት። የክህደት ክህደት! የሕዝቡን ውለታ የከፈሉት ሮብዓም የተባለው ትዕቢተኛ ንጉሥ እሥራኤላውያን ላይ የፈጸመውን ግፍ ያስንቃል። ሮብዓም፣ ከነገሠ በኋላ፣ የእስራኤል ሽማግሌዎች፣ በአባቱ ዘንድ የነበረውን የግፍ አጋዛዝ አስታውሰውት፣ “አባትህ ያከበደብንን ቀንበር አቅልልን፣ ሲሉት፣ ከማይረቡት ጓደኞቹ ምክር ወስዶ፡ “ትንሿ ጣቴ ከአባቴ ወገብ ትወፍርላለች። አባቴ ቀንበር አክብዶባችሁ ነበር፤ እኔም በቀንበራችሁ ላይ እጨምራለሁ፣ አባቴ በአለንጋ ገረፋችሁ፣ እኔም በጊንጥ እገርፋችኋለሁ።” (መጽሐፈ ነገሥት ቀዳማዊ፣ ም12 ቁ10) እንዳለው፣ ሕዝቡን ከማመስገን ወደ መጨፍጨፉ ገቡ። በመጀመሪያ ደረጃ፣ ትንሽ ኢትዮጵያዊ ስሜት የነበራቸውን እንስዬን ከመሀላችሁ በሙስና በማሳበብ፣ መነጠሯቸው። የነበረውን ሕግ በአንዲት ጀምበር በመቀየር እስር ቤት አጎሯቸው። የተቀሩትንም ከመሀላቸው አባረሯቸው። ሕዝቡ ላይ ግን የግፍ ቀንበራቸውን ጭነው የብቻ ዘረፋቸውን ተያያዙትየዚህ ሁሉ ጣጣ መነሻ የወያኔ ስግብግነት ነው!

ስብሀት ነጋ፣ እንዴት አድርጎ ብዝበዛውን፣ ገፈፋውን እንዴት አድርጎ እንደሚያስተባብለው ስሙልኝማ!

https://www.youtube.com/watch?v=S34AAFS1g6M

የወያኔ 33 ጀኔራሎች በአንድ ቀን ሲሾሙ፣ “ልብ አላልኩትም” ብሎ ሸመጠጠ። “ለማወቅ አልፈለግኩም። ማወቅ አስፈላጊ አይደለም፣” ይለናል፣ አፉን ሞልቶ፣ የወያኔ ቱባው ተጋደልቲ።

እስቲ ከኦሮሞው ጋር ምን እንዳጋጫቸው ትንሽ እንይ! የኦሮሞ ሕዝብ ቸር ስለሆነ፣ በማግባባት፣ በዘዴ፣ በብልሀት፣ “ከአማራ ጭቆና ነጻ አውጣንህ” እያሉ፣ ቀስ በቀስ ሀብቱን እየተካፈሉ መበልጸግ ይችሉ ነበር። ግን ያ አዝጋሚ ሆነባቸው። አንድ ታሪክ አለ። ወያኔ መሰል አንድ ስግብግብ ገበሬ ነበር። በየጊዜው የወርቅ ዕንቋላል የምትጥለለት አንዲት ለየት ያለች ዶሮ ነበረችው። ታዲያ አንድ ቀን ዶሮዋን የወርቅ እንቋላል እስክትጥል ከመጠበቅ ይልቅ፣ አርዶ በውስጧ ያለውን ዕንቋላሉ በሙሉ በአንዴ አውጥቶ መክበር ተመኘና አረዳት። ሲከፍታት እንኳን የወርቅ ዕንቋላልን ምልክቱንም አልተገኘባትም። ወያኔዎች እንደዚያ ነው የሆኑት! አልጠግብ ብለው ኦሮሞውን ገፍተው ከዳር ባያደርሱት ይኸ ሁሉ አደጋ ከ9 ወር በፊት ባልተጫረባቸው ነበር።  ወያኔም በአዲስ አበባ አካባቢ ያሉትን ከተሞች ወደ አዲስ አበባ ጠቅልሎ ተጫማሪ የከተማ መሬት ቀምቶ የጦር መኰንኖቹንና ሌሎች የወያኔ ባለሥልጣናትን ለማበልጸ በወሰደው እርምጃ፣  ባርቆበት ቋያውን አነደደበት። እንቁላል ጣይዋ ዶሮ፣ “ኦሮሚያ” ሆነች። ገብጋባው ገብሬ ወያኔ ሆነ። ትፋ ያለው ጥጋበኛ ሲተፋ ያድራል! የወያኔ ጉልበት እዚያ ላይ ተፈትሾ ነው ውስጦ ባዶ መሆኑ የተጋለጠው።

ወያኔዎች ከጎንደርና ከወሎ የቀሙት መሬት እንዲጸናላቸው፣ አንዳንድ ከአካባቢው ወጣቶችን አስተባበረው የቻሉትን በገንዘብና በጥቅማ ጥቅም ደልለው፣ ያልቻሉትን ጭፍጭፈው ቀሙ። በተለይ የወልቃይት ጠገዴ ሕዝብ “ትግሬ ነህ” ከተባለ በኋል፣ አንዳንድ ለወያኔ የተዋጉልትን ልጆቻቸውን “ለባርነት ዳረጋችሁን” እያሉ ሲኮንኗቸው መስማት የሰለቻቸው የወልቃይቴ ተወላጅ ተዋጊዎች፣ በሰላም መንገድ ወልቃይት ወደ ጎንደር እንዲመለስ መንቀሳቀስ መጀመራቸው ይታወሳል። እስቲ ወይዘሮ ርስቴ መብራቴን ስሙ። https://www.youtube.com/watch?v=CF7SpxAHVekያንን በስልት፣ በዘዴ ማለሳለስ ማርገብ ያቃተው ትዕግስት የለሹ ገብጋባ ወያኔ፣ ከትግራይ አፋኝ ቡድን ጎንደር ድረስ ልኮ የወልቃይት ጥገዴን ማንነት ኮሚቴ አባላትን ለማፈን ለ8 ቀናት አደፈጠ። ያንን ዕቅድ፣ ለጉዳይ አስፈጻሚአቸው፣ ለየብአዴን ባለሥልጣንትን እንኳን አላሳውቋቸውም። ነቀት ነው! ሕዝቡ ግን ያውቅ ነበር። ትዕግስት አልባው ወያኔ፣ ወልቃይቴዎችን፣ በጉልበት ሊሰብራቸው የወሰደው ጀብደኝነት፣ ቀንድ አስነክሶት እርፍ! ሐምሌ 6 ቀን 2008 ዓ.. ድቅት ሌሊት፣ የትግራዩ አፋኝ ቡድኑ አራቱን ካፈነ በኋላ፣ ሌላውን ወልቃይቴ አማራ፥ ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱን ለማፈን ቤታቸውን በመክበብ እጃቸውን እንዲሰጡ ጠየቁ። “ሲነጋ ኑ” አሏቸው። ተኵስ ከፍቱባቸው። ኮሌኔል መልስ ትኵስ ሰጡ። ሁልቱን የትግራይ የደፈጣ አፋኞችን ደፏቸው። በተኵሱ የነቃ ጎንደሬ ግልብጥ ብሎ ሂዶ እነዚያን አፋኞች በቁጥጥር ሥር አዋለ። የወያኔ ጥጋብ ሌላው ኢትዮጵያዊን በንቀት እንዲያዩት የዓይን ግርዶሽ አለባቸው። አልጠግብ ባይ ሲተፋ ያድራል ማለት ይኸው አይደል? ከወር በላይ ጎንደሬው የበሉትን እያስተፋቸው ነው። ይኸው ማጠፊያ አጠራቸው፣ ያለ የሌለ ጦራቸውን ባህር ዳር አከማችተውል!


ነባሯ ትግራይ


የዛሬዋ የተስፋፋችው ትግራይ


መነሻው ያው ዘረፋ ነበር። ዘርፈው ቢበቃቸውስ! ኢትዮጵያን፣ በዘርና በቋንቃ ከከፋፈሏት በኋላ፣ ዓይን በአወጣ ድፍረት፣ ብዙ ለም መሬት ከጎንደርና ከወሎ ቀሙ። በየመገንጥል ማኒፌስቶአቸው የዘገብዋት የግዛ ማስፋፋትን ዕቅድ ሥራ ላይ ማዋል መሆኑ ነው። እስቲ እንዚህን ሁለቱን ካርታዎች ጎን ለጎን አስቀምጠን እናስተያያቸው።

እስቲ በየትኛው ታሪካቸው ነው የትግራይ ድንበር ተከዜን ተሻግሮ እንደዚህ ሰፍቶ የሚያውቀው? በማን ዘመን? በአጼ ቴዎድሮስ ወይስ በአጼ ዮሐንስ ዘመን? በአጼ ምኒልክ ወይስ በአጼ ኃይለ ሥላሴ ዘመን? ይኸንን የፈጠራ ወሬአቸው፣ ቢተውት ሰላም ይፈለግ ነበር። ዕውን ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ፣ እንዚህ መሬቶች ወደትግራይ ከለሉ? ልዑል ራስ መንገሻ ስዩም የት ሂደው? ያሉትን እንስማ! http://av.voanews.com/clips/VAM/2016/02/27/98973055-696e-4bee-a4fe-f939e9c569c7.mp3. ራስ ዳሸን ተራራም የትግራይ ተራራ ነው እያሉ የልጆቻችሁን በየትምህርት ቤቱ እያስተማሩ ጭንቅላታቸውን እያዞሩ ነው። ኧረ ጉድ ነው። ሰሞኑን አንድ የቱሪስት ቪዲዮ በእንግሊዝኛ ለቀዋል። ውደ ስሙትማ። https://www.youtube.com/watch?v=BubzW-4f3hk:: ላሊበላ በትግራይ ውስጥ ነው የሚገኘው እያሉን እኮ ነው! ምን ዓይነት ስግብግግነት ነው?
ወያኔዎች የጎሳ ክልል ሳያበጁ፣ እንኳን አዋሳኝዋን ጎንደርና፣ ትግሬዎች ኢትዮጵያ ውስጥ ጋሞ ጎፋ ነሽ - ባሌ ጎባ፣ ኢሉባቦር ነሽ - ወለጋ፣ የትም ሂደው ሠርተው ከብረው ይኖሩ አልነበር? ለመሆኑ፣ “ትግሬና ላንድሮበር ያልገባበት” የኢትዮጵያ ክፍለ ሀገር ነበረ ወይ? 99% ሾፌር ማን ነበርና! ይቅርታ! ስለሚባል ነው። ለምሳሌ ባህር ዳር ከተማን ብትወስዱ፣ ምንም ሳላጋንን ትግሬዎች ወልደው ተዋልደው፣ ከብረው በልጽገው፣ ከማንም መጤ ብሔረ-ሰብ የበለጠ ቁጥር ነበራቸው። አዲስ አበባማ አታንሷት። ጎፋ ሰፈርና ተክለሀይማኖት የትግሬዎች ሠፈር (የዛሬዋ ቦሌ ሳትነሳ) አልነበር ሌላ ስማቸው? ማን ዞር ብሎ አይቶአቸው! አንድ ሕዝብ እኮ ነበርን። አምባሻቸውን መብላት ለምደን ስንከሰክስ፣ ዘፈኖቻችሁን ወድደን እይዞርን “እስክስ” ከሎጆቻቸው ጋር አብረን አላደግንም። አብረን አልኖርንም። ወያኔዎች ያመጡብን ጣጣ ነው እንጂ፣ ለትግሬው እኮ ኢትዮጵያ አገሩ ናት። እንዲህ የሚጠሏቸው አማሮችም ሆኑ ትግሬዎች እንደ ወንድማምች ነበር እኮ ነበር የሚተያዩት። ዶርዋን ለምን ማረደ አስፈለገ? እንዲያው ያ የኢትዮጵያ ምክትል ጠቅላይ ስቃይ አድረገውት የሾሙብን ዘረ ደብረጽዮን[i] ዶክተራቸው እንደሚናገረው ሳይሆን፣ የኮንሶም ቤት ቢሆን ለትግሬዎች ቤታቸው ነበር። ኮንሶው ውስጥ የሚፈጸመው በደል ትግራይን ያገባዋል፣ ትግራይ ውስጥ የሚፈጸመው በደል ኮንሶውን ያገባዋል፣ ጎንደርንማ ተውት! ጎንዴሬውንና ትግሬውን፣ ደቡብ አካባቢ የተወለድን፣ የት ለይተናቸው! ትግሬ ነው ስንል፣ አማርኛ ያቀላጥፋል። ጎንደሬ ነው ስንል፣ ትግርኛውን እንደናቱ ቋንቋ ያስነካዋል። እንዲህ ዓይነት ጎንደሬዎች ወልቃይቴ ጎንደሬ መሆናቸውን በኋላ ነበር የተረዳነው። ትግርኛውን እንደእናቱ ቋንቋ ሲነዳው ከትግሬ በምን ሊለይ? አማርኛ ዘፈን ሲዘፍን ወይም የቅርብ ዘመዱ ሙቶበት በአማርኛ ሲያለቅስ ነው ጎንደሬ መሆኑን የምንረዳው። የኢትዮጵያው ጠቅላይ ስቃይ ባለቤት፣ ወልቃይቴዋ አዜብ ጎላስ፣ ባሏ ሲሞትባት፣ በአማርኛ አልነበር እዬዬዋን ያቀለጠችው? “አልጋው ባዶ ሆነ”[ii] ስትል እኮ ከልቧ ነበር። ትግርኛውን እኮ ከማንም ትግሬ እኩል ነበር የምትፈጨው። የልቧን ኃዘን የሚገልጽላት ግን የእንቷ ቋንቋ አማርኛ ሆኖ ተገኘ! ወልቃይቴ ጎንደሬ ናታ! አዜብ! ባልሽ ቢኖር ኑሮ፣ እንደ አስቴር የመጠራት ዕድል ነበረሽ! ዛሬማ ምን ሰምቶሽ!
እሺ፣ ትግራይ ደርቃችና ለም መሬት ያስፈልጋታል እንበል። እሱስ ይሆን፣ በማኒፌስቶአቸው መሠረት እስካልተገነጠሉ ድረስ፣ ያው ኢትዮጵያውያን ናችሁ። ገበሬውን ከዘር እስከ መንዘራዘሩ ከኖረበት ቁዬው መንግለው መሬቱን ለውጭ ቱጃሮች ብስሙኔ መሸጥ ምን ይባላል? ትንሽ እንኳን የዓለም ሕዝብ ይታዘበናል ይሉም? “አማራው በደለህ” የሚሉት፣ ጋምበላዊው አኟክ ምን አደረጋቸው? የደቡብ ኦሞውን ሕዝብ ለምን ከተወለደበት ቂዬ ነቀሉት?
የአዲስ አበባ ኗሪውን፣ ቤቱን በላዩ ላይ አፍርሰው ሜዳ ላይ ሲጥሉት፣ ምን እንደሚከተል እንዴት አልተገነዘቡም? (http://www.ethiotube.net/video/36104/breaking-news-residents-of-hana-mariam-furi-in-addis-ababa-protest-housing-demolition-gun-fire-heard-june-29-2016)። “ሽበርተኞች ናቸው” ብለው ዓይናችንን እንዳያስቁት!  እነዚያ ቤቶች እኮ በአብዛኛው የተሠሩት ገና አካባቢዎቹን ማዘጋጃ ቤት ሳያካትታቸው፣ ከገበሬው በተገዙት መሬቶች ላይ የተሠሩ ቤቶች ነበሩ። መሬቱን ቀምተው ቪላ ሊቸከችኩበትና አከራይተው ሊከብሩበት ሲሉ፣ 10 ሺህ ሕዝብ ጎዳና ተዳዳሪ አደረጉት! እንዴት ቤት አፍርሰው እናትና ሕጻን ለመግደል በቁ? ሕዝባችን ተገፍቶ ተገፍቶ ከማይገፋ ግድግዳ ተላጥፏል። የተጣበቀበትን ግድግዳ እንደ መስፈንጥሪያ ተጠቅሞ መልሶ እንደሚገፋቸእው አላስተዋሉም ለዚህ ነው የተናደደ ሕዝብ፣ ምስኪኑን ፖሊስ ያለርኅራሔ ቀጥቅጦ ለመግደል የበቃው። “በቃ! አበቃ በቅቷችሁናል” እያላቸው ነው “100 በመቶ መረጠን” የሚሉት ሕዝብ! ገብጋቦች።
ሥልጣን ከተቆናጠቱ ጊዜ ጀምሮ አንዴም ዘረፋውን አላቆሙትም። የስሚንቶ ፋብረካ ሳይቀር ነቅለው ሲውስዱ ሕዝቡ ዝም አላቸው! እንደዚያ ሲበዘብዙ ዛሬ ላይ ደረሱ! ያን ሰሞን ዳባት (ጎንደር ውስጥ) የኃይል መማንጫ መዘውር (ጄኔሬተር) በጠራራ ጸሐይ ነቅለው ለመጫን ሲሞክሩ፣ የአገሬው ሕዝብ ሆ ብሎ ወጥቶ ጭነቱን አስወረዳቸው። በተመሳሳይ ሁኔታ፣ ያለምንም ይሉኝታ፣ ማንኛውንም ተንቀሳቃሽ ንብረት እየዘረፉ፣ እየቅሙ ሲያግዙ በትዕግስት ሲታዘባቸው የኖረ ሕዝብ እንዲህ ብሎ ገጠመላችሁ።
ይጫንም እንጂ፥ ወሀ በመኪና
አይነሳም እንጂ፣ ሀይቅ በመኪና
መቀሌ ነበሩ፥ ዐባይና ጣና።

አቶ ኤርሚያስ ለገሠ፣ የድሮው ቃል አቀባያቸው፣የመለስ ትሩፋቶችበሚል መጽሐፋቸው፣ ወያኔዎች፣ አዲስ አበባን እንዴት እንድተቀራመቷት የዓይን ምስክርነት ሰጥተዋል። የአዲስ አበባ መሬት ለጄኔራሎቻቸው ሁልተኛ፣ ሶንስተኛ ዙር ተከፋፍሎ አልበቃ ስላለ፣ ገበሬውን ከቦታው አፈናቅለው፣ መሬቱን ለመቀማት፣ በአካባቢው ያሉትን ከተሞች ሊውጡ ሲሉ ሕዝቡ በነቂስ ወጥቶ ተጋፈጣቸው። http://www.ayyaantuu.net/u-s-policy-ethiopia-a-failing-state-case-of-the-oromo/ከዘጠኝ ወር ሙሉ፣ አስነጠሳቸው።

በኦሮሞ የጫረው እሳት፣ ይኸውና አሁን ወደ ሌሎችም ቋያው ተዛምቶ ይዞአቸው ሊሄድ ነው። ቆም ብለው ከነርሱ በፊት በነበሩት አምባገነን ገዢዎች ዕጣ ፈንታ ማየት አልቻሉም! ጥጋብ አሳውሮአቸዋላ! ሞት መቼ እንደሚመጣ አይታወቅም። ተንኰለኛው የሰይጣን ቁራጭ መሪአቸው እኮ የተቀጸፈው አንድ ጋዜጠኛ፣ አበበ ገላው፣ ሲጮኽበት ጊዜ ደንግጦ ነው ክንችር ያለው። የዋልድባ መነኰሳት ለቅሶ እኮ ነው ፓትሪያርካቸውን፣ ይዞባቸው የሄደው። የቀሩትንም ስግብግብነት ይዞአቸው ይሄዳል!
የዋልድባ ገዳምን ካነሳን አይቀር፣ ምንኛ እርጉሞች ቢሆኑ ነው የሙታን መነኮሳት መቃብር ቆፍረው ሬሳቸውን አውጥተው ሜዳ ላይ ጥለው ቦታውን ለመቀማት የተነሱት? የመቃብር ቦታ! አበስኩ ገብርኩ! አሁን እንደምንሰማው ከሆነ፣ ለብዙ ሺህ ዓመታት የኖሩትን ዛፎች እየቆረጡ፣ እያከሰሉ ወደ መቀሌ መጫናቸውን ተያይዘውታል። መቃብር ቆፋሪነታቸው በዓለም ታውቆላቸዋል። እዚህ የምኖርበት እንግሊዝ አገር ብዙ የመቃብር ቦታዎች ለሺህ ዓመታት ሳይነኩ፣ ሙታን ተከብረው መሀል ከተማዎች እንዳሉ አናያለን። ለምሳሌ የዚህ ጸሕፊ፣ ውዷ ባለቤቱ ስታርፍ፣ አገር ቤት መውሰድ እያማረው፣ መቃብር ቆፋሪዎቹ አውጥተው እንዳይጥሏት በመስጋት፣ ለ999 ዓመት መሬት ሊዝ ገዝቶ፣ እዚህቺው ለንደን መሀል ከተማ፣ ኬንሳል ግሪን ቀብሯት፣ በየጊዜው እየተመላለሰ መቃብሯን ይጎበኛል። በባዕድ አገር ኢትዮጵያውይን ሙታን ከአገራቸው በበለጠ፣ ተከብረው ተገኙ። ሙታንን እንኳን በሰላም የማይተው ገብጋባ ጉዶች! መሬቱን ስለፈለጉ ብቻ፣ በታሪካችን ተደርጎ የማያውቀውን ጉድ ፈጸሙ። አዲስ አበባ ቅዱስ ዮሴፍ ቤተክርስቲያን መቃብሮች ፈንግለው አስከሬኖችን አወጡ። የታወቁ ኢትዮጵያውያንን፣ የእነ አበበ ቢቂላን፣ የእነ አሳምነው ገብረወልድን፣ የእነ ብዙነሽ በቅለ ሬሳ ሳይቀር ሜዳ ላይ ተጣለ። ምን የተረገሙ ናቸው! እምነተ ቢሶቹ የወያኔ ተጋደልቲዎች በየገዳሙና በየቤተክርስቲያኑ መነኰሳት መስለው ሲገቡ፣ እግዚአብሔርን እራሱን “በስልት” የያዙት መሰላቸው? እግዚአብሔር እያንዳንዳቸውን እንደነዚያ ሁለቱ ደፋሮች ይቀስፋቸዋል። ስግብግቦች! አይጠግቡማ! አልጠግባይ ባይ ደግኒ ሲተፋ ያድራታል።  
ገዳይነታቸው፣ መዝባሪነታቸው፣ ገፋፊነቸው፣ በዓለም ሕዝብ ፊት ራቁቱን ቀርቷል። እስቲ የሚከተለውን መቅረጸ-ሥዕል ፋታ ወስዳችሁ ተመልከቱት/አዳምጡት።


እንዲያው ለነገሩ፣ አሁን ከኦሮሞው፣ ከአማራው፣ ከወላይታው፣ ከጉራጌው የበቃ መነኵሴ ጠፍቶ ነው፣ የኢትዮጵያን ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ፓትርያርክ መንበር በትግሬ ብቻ በሞኖፖሊ የተሰጠው? መጀሊሱንስ በወያኔ መበጥበጥ ነበረበት? የመምሕራን ማህበሩን አፍርሰው በራሳችሁ አሻንጉሊት ተኩት። የኢትዮጵያን ሰብዓዊ መብት ጉባዔን አሽመደምደው፣ በራሳችሁ ሹማምንት የሚመራ የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ተት። የምርጫ ኮሚሽን የሉትን ጉድ በራሳቸው ሹሞች ት። የኢትዮጵያ ጦር ኃይሎች አመራር በፊተኞች አገዛዝ ሥርዓቶች ተመጣጣኝ ስብጥር እንጂ እንደዛሬው፣ ወያኔዎች እንደሚይደርጉት 95% (95 በመቶ) የአመራር ቦታው በአንድ ብሔር ይዞት አያውቅም። http://www.ethiomedia.com/adroit/2373.html:: ያ ከመውደም ግን አያድናቸውም። የሙባረክን መንግሥት አዳነው? አላዳነውም። የጋዳፊን መንግሥት አዳነው? አላዳነውም። አማራው ነቅቶባዋል። ኦሮሞው ነቅቶባቸዋል።

መፍትሔ ሀሳብ

ከራሳቸው የበፊተኞች ጄኔራሎች፣ ጻድቃንና አበበ የተለየ መፍትሔ ልናገኝላቸው የሚቻል አይመስለኝ። አልሰሟቸውማ። የባሰውኑ ስድብ አከናነቧቸው። የትግራይ ምሑራን፣ በዚያን ሰሞን መፍትሄ ሀሳብ ሰጥተው ነበር። ማን ሰምቷቸው! ወያኔን መምከር፣ በድንጋይ ላይ ውሀ እንደማፍሰስ ነው። ቢሆንም መፍትሔው ይኸው።

፩ኛ - ወያኔዎች ከጎንደር የቀሙትን መሬት አንድም ሳያስቀሩ ሙሉ በሙሉ ይመልሱ። ወልቃይቴዎችን ይቅርታ ይጠይቁ።
፪ኛ - ከኦሮሞ ገበሬዎች የተነጠቀውን መሬት ይመልሱ፣ ኦሮሞዎችን ይቅርታ ይጠይቁ።
፫ኛ - ከሸዋ እስከ ትግራይ፣ በመንግሥት ይፈለጋሉ ብለው ላፈረሷቸው የከተማ ቤቶች ባለቤቶች በሙሉ ካሳ ይክፈሏቸው
፬ኛ - ከጋምቤላ የፈናቀሏቸውን አኟኮች፣ ወደቄዬአቸው ይመልሷቸው፣ የቀሙትን መሬት ይመልሱ
፭ኛ - እስካሁን ስለአጭበረበርቱ ምርጫ፣ የኢትዮጵያን ሕዝብ ይቅርታ ይጠይቁ
፮ኛ - የወያኔ ሰለባ ለሆኑ በሙሉ የካሳ ክፍያ ይፈጽሙ - ኤፈርት ብዙ የበዘበዘው ገንዘብ ሞልቶአቸዋል።
፯ኛ - የምርጫ ኮሚሽን ተብለው የተቀመጡት አሻንጉሊቶች ይነሱና በትክክል በተመረጡ አባላት ይተኩ።
፰ኛ - የተሰደዱት ወግኖችና የፖሊቲካ ድርጅቶች ወደአገር እንዲመለሱ፣ ሁኔታዎች ይመቻቹላቸው።
፱ኝ - ከሁሉም ብሔር፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች፣ ከሀማኖት አባቶች የተውጣጣ፣ ዕርቀ-ሰላም ኮሚቴ ይቋቋም
፲ኛ - ትክክለኛ ምርጫ ይካሄድና ጊዜያዊ ሕዝባዊ መንግሥት ሕዝቡ ይወክሉኛል በሚል አባላት ይቋቋም።

እነዚህን ነገሮች፣ ወያኔ መቀበል ከቻለ፣ ተአምር ነው። ደም በከንቱ አይፍሰስ። በትግራይ ሕዝብና፣ በሌሎቹ መሀል፣ የማይሽር ቁስል አይተው። ሕዝቡ ደግሞ የበኩሉን ይወጣ። እነዚህ ከተሟሉለት፣ ሕዝቡ ለወያኔዎችና ጀሌዎቻቸው እስካሁን ላጠፉት ጥፋት ይቅርታ ያድርግላቸው። ደኅንነታቸው ይጠበቅ! ሰው በግፍ ከገደሉትና ካስገደሉት በስተቀር፣ የበቀል እርምጃ እንዳይወሰድ። ንብረታቸው እንዳይነካ። ሕግ ይከበር። ሰላም ይውረድ!

እነዚህ ነገሮች፣ እንዲሁ የወንድ በር ልንሰጣቸው ነው እንጂ፣ አንዷንም እንደማይቀብሏት እናውቃለን። ከኛ ግን እንዳይቀር። “ዕድል እኮ ሰጥተናቸው ነበር” ለማለት ያመቸናል። እነዚህን ቀላል ጥያቄዎች ካልተቀብሉና፣ ሰሞኑን “አማራውን በጦር እንጨፍልቀው” ብለው፣ ዘጠና አምስት በመቶ ድምጽ ሰጥተው ካበቁ በኋላ፣ ኃይለማርያም ደሳለኝን ፍላጎታቸውን እንዲያስተጋባ ትዕዛዝ ሰጥተውን በአናዘዙት መሠርት ከቀጠሉበት፣ ምንም ማለት አንችልም። ወደሽ ከተደፋሽ ቢረግጡሽም አይክፋሽ ነውና ነገሩ፣ የጋዳፊና የሙባረክ ዕድል እስኪገጥማቸው ትግላችን ይቀጥላል። አምባ ገነኖች እንደውሻ ሬሳቸው ካልተጎተተ አይወጡም። ውጪ ያለነው፣ ባገኘነው ቀዳዳ አጋራችን ገብተን ከሕዝባችን ጎን ቁመን፣ የሚፈለገውን መስዋዕትነት እንክፈል። መዋጋት የማንችለው ጊዜአችንና ጉልበታችንን ለሕዝባችን ድጋፍ እናውል። ሌላው በነፍሱ እየገበረ፣ እኛ ጊዜና ጉልበታችን ለመቼ ነው?

መደምደሚያ

የወያኔ ስግብግብነት፣ እዚህ ደረጃ ላይ አድርሶአቸዋል። እንደትዕቢተኛው ፈርዖን ልባቸው ድንድኗል። የበሉት አቅሮአቸዋል። እነሱ ግን እየበላን ይብላን ብለው ቆርጠው በላይ በላዩ ይወጥቃሉ። አንድ ቀን ይዞአቸው እንደሚሂድ አንጠራጠርም! ያርገው!

“እላይ ቤት፣ እታች ቤት፣ ስትይ አገኝ-አገኝ
ጅብ አህያ ለምዷል እኔ አንቺን አያርገኝ  

አለች አንዲት እህት!


በዚህች ቅጽበት፣ በአሁኑ ሰዓት፣ ወያኔ በሺህ የሚቆጠሩትን ወታደሮችን በኢትዮጵያ አየር መንገድ እየጫነ ባሕር ዳር እየዘረገፈ ነው። ሁሉ አቀፍ ጦርነት ጎንደርና ጎጃም ላይ አውጇል። የሕዝቡ ጥያቄ አንድ ናት። ትዕዛዝ ቢሰጣቸውም፣ ትግሬ ያልሆኑት ወታደሮች ወገናቸውን ተኵሰው መግደል ሳይሆን፣ ያንን በአዘዘውን አዛዥ ላይ ያለምንም ርኅራሔና ማመንታት ያዙረ ነው። ወገናቸውን እንዳይገድሉ አደራ በሰማይ አደራ በምድር አለባቸው። ያንን የተላለፈ ወታደር ይረገም! ጥቁር ውሻ ይውለድ!


እንግዲህ በአሁኑ ሰዓት አብዛኛው ጦር ባሕር ዳር ተከማችቷል ብለናል። ይኸኔ ነው ኢሉባቦር፣ ወልጋ፣ ከፋ፣ ገሙ ጎፋ፣ ባሌ፣ ሸዋ፣ ወሎ፣ ሀረር፣ አርሲ፣ አፋር፣ ኮንሶ፣ ሸካቾ፣  ጋምቤላ፣ ሲዳማ፣ ወላይታ፣ ሀዲያ፣ ኦጋዴን... ጠቅላላ ኢትዮጵያው ሕዝብ ወፍራም የነጻነት ዕድል ጮራ የፈነጠቀላቸው። በወያኔ ተረግጦ፣ ተግፍቶ፣ ከፍቶት የሚኖር ሕዝብ በሙሉ መነሳት ያለበት አሁን ነው። የጊዜ መስኰቷ ጠባብ ናት! ተነስቶም መብቱን ማስከበር የሚችለው አሁን ነው። ወያኔ ጦሩን ከባሕር ዳር ለማነቃነቅ ጊዜና የአቅርቦት አቅም የለውም። “ዕንቁላሉን በሙሉ በአንድ ቅርጫት ወጅሯል!”። ጎንደርና ጎጃም፣ እስከመጨረሻዋ ይዋደቃታል። 10 ጎጃሜ ወይም ጎንደሬ ከሞተ፣ አንድ ወያኔ መግደል አያቅተውም። ሌሎቹ ግን ጎንደርና ጎጃም እስኪፈታ፣  መጠበቅ እንደሌለባቸው ከማንም ምክር አይሹም። “ለብልህ አይመክሩ፣ ለአንበሳ አይመትሩ”፡ ዕድሉ አሁን ነው። አለበለዚያ፣ አማራውን ጨርሶት ካበቃ በኋላ፣ ወለም ዘለም የለችም። በቀጥታ ወደ ኦሮሞው ነው የሚዞረው። ልብ ከተባለ ኦሮሞ ወንድሞችና እህቶች አሁን ነው የጠየቁትን ጥያቄ በጉልበታቸው የሚያስመልሱት! “ዋቅጅራ ዋቅጅራ! ዋቅኬኔ ኬሰን ኤጋ’”።
 ከሚከተለው አጣብቂኝ እግዚአብሔር ያድነን!

መጀመሪያ ኮሙኒስቶቹ ላይ ዘመቱ
ኮሙኒስት ስላልነበርክ ዝም አልኳቸው
ከዚያም ሶቻሊስቶቹ ላይ ዘመቱ
ሶሻሊስት ስላልነበርኩ ዝም አልኳቸው
ከዚያም የሠራተኛው ማኅበር ላይ መጡበት
የሠርተኛ ማኅበር አባል ስላልነበርኩ ዝም አልኳቸው
ከዚያም በአይሑዳዊያን ላይ ዘመቱ
አይሑዳዊ ስላልነበርኩ ምንም አላልኳቸውም
ከዚያ እኔን ለመያዝ መጡ
ሁሉም በየተራ ተወስደአልና አልቀው ነበርና ስለኔ ስለኔ ማን ይጩኽ?

ፓስተር ማርቲን ኒሞለር

እግዚአብሔርና ዕውነት ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጋር ነው! አትፍሩ! የዘመናችን አፓርታይድ ይገረሰሳል! ኢትዮጵያችን ትድናለች!

No comments:

Post a Comment