ወንድሙ መኰንን፣ ኢንግላንድ፣ 27 April 2020
በአማርኛ ጣዎስ (peafowl) እንደምትባል፣ ወንድማችን አቶ ምስጢረ ኃይለሥላሴ ነበር ከሳቴብርሀን መዝገብ ቃላትን አገላብጦ ያስተማርኝ ። እስካሁን ምንነቷንም ገዶኝ ሳላውቅ፣ ላውቃትም ጉጉት
አድሮብኝ ባለመፈልግ ብዙም አልተጨነቅኩበትም ነበር። እንዳልምል፣ ሰር ዴቪድ አተንቦሮን (Sir David Frederick Attenborough) ስለምከታተል የበርማዋንም፣ የደቡብ
ምሥራቅ ኤሲያዋንም፣ የኮንጎ ስምጥ ሸለቆዋንም አኗኗርና አረባብ በቢቢሲ ናሽናል ጂኦግራፊ ለጠቅላላ ዕውቅት ተከታትዬለሁ። ከአገሬ
ጋር የሚያገናኛት ስለሌለ በአማርኛ ስም ይኖራት አይኑራትም ለማወቅ ጓጉቼ አላውቅም ነበር።
ወንድማችን ከነገረኝ በኋላ፣ የግዕዝ መዝገበ ቃላትን ሳገላብጥ፣
ጣዎስ ጉብ ብላ አገኘኋት። በማስሊያ (computer) መስመር መዝገበ ቃላትም ላይ (online) ስፈልጋት እዚያም ጣዎስ ሁና ተገኘች ። እስካሁን አላውቃትም ነበር። ከአሁኑ ጀምሮ ግን አውቃታለሁ። መማር ዕድሜ አይገድበውም ይባል ይለ? ገዚዎቼ ሰንደቄ
ላይ እንዳለችው አሽታሮታቸው፣የብሔራዊ አርማዬ አድርገው ሊግቱኝ ሲያሟሙቅኝ ጠርጥሬአለኋ!
ሰሞኑን ስለዚህች የበርማ አሞራ ማሞካሸት በዝቶብኝ ግራ ገብቶኝ
ነበር። በተለይ አውራ ጥዎሷን (peacock) ከእንስቷ ጣዎስ (peahen) ጋር ተምታቶባቸው፣ እንደቆንጆ ሴት ሲያስውቧት፣ ግማሽ አካል እህቴ በዚያን ሰሞን፣ የአንዲት ሕጻንን ከሽንት ቤት መቅመጫ ውሀ እያመላለሰች ሌሎቹን ሕጻናት ስታጠጣ የሚያሳይ ተንቀሳቃሽ ሥዕል አጋርታን፣ “አለማወቅ እንዴትጥሩ ነው?” ያለችውን ኢያሰላሰልኩ አለፍኩት። ወንዱን ፒኮክ ሲቲቱ መስላው አዳሜ ሲያሞግስ ማለቴ ነው። የወንድሜ ግጥም ግን እንከን አይወጣውም ነበር።
እንስቷ ጣዎስ (peahen) በሥዕሉ ላይ እንደሚታየው ወንዱ ይሁንታዋን ለማግኘት መከራውን ሲያይ ሴቶ ጸጥ ብላ የምትለቅምው ናት ።
የቤት ዶሮም እኮ የአውራው ላባ ነው የሚያምረው። የሴቷም እስከዚህም
ነው። አውራው (peacock) ያንን የሚያብረቀርቀውን ላባ የሚነሰንሰው፣
የሴቲቱን ልብ በፍቅር ለማማለል ነው። አውራ ጣዎሶች ሴት ጣዎስን ለማግኘት በዳንስና በላባቸው ውብት ተወዳድረው ማሸነፍ እንዳለባቸው፣
ከቢቢሲ ባየሁት ተገንዝቤአለሁ። እዚህ ላይ ማንንም ባለማወቅ ለመንቀፍ ሳይሆን (እኔም አላውቅም ነበርና) "ፒኮክ" ሲሉ ወንዱን ማለት
እንደሆነ ግንዛቤ እንዲኖረን ነው።
እንግዲህ ወደ ሰሞኑ የሶሻል ሜዲያ (ፌስ ቡክ፣ ቫይበር፣ ዋትስአፕ)
የእጅ ስልኬ ላይ “አንብሳውን በ*ፒኮክ” ለውጡት የሚሉ ድምጾች ሲንጫጩብኝ፣ ነገሩ እንዴት ነው ብዬ ማተኮር ጀመርኩ። የየቱን ስል፣
የአዲሱን ብሔራዊ ፓርክ ነው ተባልኩ። አዲሱ ብሔራዊ ፓርክ የት ነው ስል፣ የድሮው የምኒልክ ቤተመንግስት ነው ተባልኩ። ክልጅነቴ ጀምሮ፣ ሳያቸው ያደኩት ሁለት የአናብስት ቅርጽ ወለል ብልው ታዩኝ። ብዙም ስላገናዘብ
አካኪ ዘራፌን ቀጥልኩ። በፊስቡክ የሴቷን peahen እና የአውራውን peacock ልዩነት አስረድቼ ይህቺን የአገራችን ወፍ ያልሆነችውን አርማችን እንዳታደርጓት የሚል አጭር መልዕክት አስተላለፍኩ። የአሁኑ ብልጽግና ፓርቲ፣ የድሮው ኢሕአዴግ ደጋፊዎች ዘመቻችውን አጦፉታ! “አንበሳ ጨካኝ፣ ነው፣ አንብሳ የፊውዳሉ ዓርማ ነው፣ አንበሳ ይኸ ነው፣ አንብሳ ያ ነው፣ ... “ፒኮክ” የፍቅር ተምሳሌት ናት፣ “ፒኮክ” የብዝሀነት ተምሳሌት ናት . .. ወዘት (ኧረ ጉድ ነው!) የሚል ጩኸትን አጦፉት ። የሆነውን እንሱም የተረዱ አይመስልም ግን፣ ብልጽጋና ምንም ይሁን ምን የሚሠራው ትክክል
ነው ብለው መከራከር ግዴታቸው አድረገው ውስደውታል። “ምናባታችሁን ተሆናላችሁ፣ ዐቢይ ሲፈልግ
ለጅግራ ሐውልት ይሥራ" አንዱ ያለውን አንድ እምወደውና የማከብረው ወንድሚ አሰራጭትሎት አሳቀኝ። ጅግራ እኮ
ያገሬ የቆቅ ዘር ናት ። ሥጋዋንም በልቼአለሁ። መልኳም እንደ ፒኮኮአቸው አይሁን ኢንጂ ያምራል። ምን ገዶኝ ያስጮኸኝ ነበር እሷም ብትሆን! የነሱ ኝኝኝኝ ወያኔያዊ ካድሬነት ይሉሃል ይኸ ነው። በጥሞና ማስረዳት ሲገባ ይኸ ሁሉ ጡዘት
የበለጠ ያነሳሳን እንደሆነ እንጂ ምንም የሚያረግብ አልሆነበረም።
የሆነ መልዕክት ደሞ፣ የጠቃልይ ሚኒስትሩን ፎቶ ይዞ፣ “ፒኮኳን
ከመተችት፣ አንበሳውን ምንነት ማወቅ "የሚል ተበተነልን። ጠቅላይ ምኒስትሩ ሥራ ፈትተው መልስ የሰጡን መሰለኝና አዳመጥኩት ። ላንድ
አፍታ የተባለው ያዘግጀውን ስለ አንበሳ ታሪክ አውቃለሁ የሚለውን ነው። የሚገርመው፣ አንበሳ ከመጽሐፍ ቅዱስ፣ ከእስራኤሎች መሀል
የይሑዳ አርማ መሆንኑና ነገስታቶቻችንም የዚያ ዘሮች ነን ስለሚሉ፣ እነሱ በግድ እንደጫኑብን ተነተነልን። ኧረ ተው! እሺ ኢትዮጵያስ
ከይሁዳ አንበሳ ትውሳ ጫንችብን እንበል፣ ቤልጀምስ? ኢራንስ? ማቃዶኒይስ? ነዘርላንድስ? ኖርዌይስ?፣ ዩናይትድ ኪንድምስ (ኢንግላንድ፣
ስኮትላንድ እና ዌልስ) ... ? እነዚህስ ክይሑዳ አንበሳ ውስደው ነው? ኧረ እየተስተዋለ! እነሱን ተውአቸው፣ ኬኒያስ ምን ሁና ነው፣
ሁለት አንበሶችን ብሔራዊ አርማዋ ያደረገችው? እንሱም መሀል የአሁይድ ዘሮች ኑረው ነው?
መለስተኛ ጥሩ ነው የምለው መልስ የምጣው ከሲሳይ አጌና ነበር።
ሲሳይ እንደሚለን ከሆነ፣ ሌሎቹ እንዳናፈሱት፣ ከምኒልክ ቤተመንግሥትም
ሆነ፣ ከኢዩቤሊዩ ቤተመንግሥት ላይ የነበሩት አንበሶች ተነስተው ሳይሆን፣ ደርግ ለአሥረኛው በዓሉ ያሠራው አዳራሽ መግቢያ ላይ ለ“ፒኮኮቹ”
ሐውልት እንደተሠራ አስረዳን። በጣም ጥሩ። እኛ አንበሳው ከታሪካችን ጋር የተያያዘ ነው ብለን መከራከር ስንጀምር፣ የአንበሳው ጠላቶች
ደሞ “ምን አገባችሁ፣ ዐቢይ ጥሩ ነገር ሠራ። ለፒኮክ ብቻ ሳይሆን ለምን ለጅግራም ሐውልት አይሠራም ብለው ለመከራክር አኮብኩበው
ሲነሱ፣ ሁለታችንም ስህተት ላይ ወደቅን። እኛ ለምን አንበሳችን በዚህች ባዕድ አሞራ ይለወጣል ብለን ስንከራከር፣ እነሱም ደሞ የተለወጥላቸው
መስሏቸው ጭፈራ ጀምረው ነበር። ሁላታችንም ተሳስተናል። ሕዝቡን ይቅርታ እንለምን።
ሲሳይ በዚሁ ቢያቆም ጥሩ ነበር። አለፍ አለና፣ እሱም ስህተት
ሠራ። ፒኮኮ ለአገራችን አዲስ አይደለችም አለ። ምሳሌም ሲያመጣ፣ ፒኮክ ካፌና ፒኮክ መናፈሻ የታወቁ መጠሪያ ስሞች ናቸው ብሎን እርፍ።
ወዳጄ ሲሳይ፣ በአዲስ አበባ፣ ፒኮክ ካፌም ገቢቼ ተሰትናግጄአለሁ፣ ቢኮክ መናፈሻም ሄጄ ተዝናንቼአለሁ። አይገርምህም፣ ያኔ ጣዎሷ እየተሽኮረመመች
ባጠገቤ ብታልፍ፣ ፒኮክ መሆኗን ባላወቅኳት ነበር። የአዲስ አበባ የአገልግሎት የነግድ ቤቶች፣ ምን የማይጠሩበት የውጭ ስም አለና!
ሎባርዲያ ገብቼ ብልቼአለሁ፣ ሎምባርዲያ ምን እንደሆነ እስከዛሬ አላውቅም። ኤንሪኮ ገብቼ አሮስቶ አዝዤ አንክቼአለሁ። እኒሪኮ የሰው ይሆን
የ’እንስሳ ስም መሆኑን አላውቅም። የቦታ ስምም ሳይቀር ተለውጦብናል። ለመሆኑ፣ ካዛንቺስ በጣሊያንኛ የሰራተኛ ሰፈር መሆኑን፣ ፒያሳስ
መሀል ከተማ (city
centre) መሆንኑ ስንቶቻችን ነው የምናውቀው? ቨኑስ፣ እላፎንቴ እና የመሳሰሉት
የምሽት ዳንስ ክበቦች እንዳሉ አውቅ ነበር። እነዚያ ስሞች አማርኛ ነበሩ? ፒኮክ እማ የታወቀ ቢሆን ኑሮ በአማርኛ ጣዎስ ካፌ ይሉት
ነበር። ለመዘነጥ ሲባል የውጭ ስም ተሰጣችው እንጂ “ባለውለታዋን” ጣዎስ ለማስታውስ አይደለም። ምሳሌው ውሀ አይቋጥርም።
ለማጠቃለል፣ ብልጽና ቢፈልግ፣ ፒኮኳን አርማው ሊያደርጋት ይችላል።
ማንም የሚከለክለው የለም። ጓደኛዬ እንዳለው፣ ሞአ ጣዎስ ዘእምነገደ … እያሉ ቢቅጥሉ ምን ገዶኝ!
ግን ልክ አሽታሮቷንን በሰንደቅ ዓላማችን ላይ ትላንት እንደለጠፋችሁኋት፣ ዛሬም፣ ፒኮክን የብሔራዊ ዓርማ ለማድረግ እንዳትሞክሩ ከመማጸን ጋር እጠቅያቸዋለሁ።
“የዘፈን ዳርዳሩ እስክስታ ነው” ማን ነበር ያለው?
እግዚአብሔር ከተደቀንብን ወረርሺኝ ህላችንንም ያትርፈን።
This comment has been removed by the author.
ReplyDelete