† በአክራሪ ሙስሊሞችና ጽንፈኛ ብሔርተኞች በኦርቶዶክሳውያን ላይ የደረሰው ዝርዝር መረጃ።†
መምህር ታሪኩ አበራ
ሎንዶን
ሰኔ 22 ላይ ከምሽቱ 3፡30 ጀምሮ እስከ ሰኔ 23/2012 ዓ.ም ድረስ በሁለት ቀን ብቻ በአክራሪ ብሔርተኞች እና በአክራሪ እስላሞች የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አማኞችን ዒላማ ያደረገ ጥቃት ሪፖርት
️✍️✍️✍️✍️✍️✍️✍️✍️✍️✍️️
1. ጥቃት የተፈጸመባቸው አከባቢዎች
10 ዞኖች (ምሥራቅና ምዕራብ አርሲ፤ ምስራቅና ምዕራብ ሐራርጌ፤ ምሥራቅ ሸዋ፤ ደቡብ ምዕራብ ሸዋ፤ ጅማ፤ ባሌ፤ሐራሪ ክልልና መቱ ሲሆን በጣም አነስተኛ የሆነ ሁከት በቡሌ ሆራ ነበር)
2 የከተማ አስተዳደር(አዲስ አበባ እና ድሬደዋ)
45 ወረዳዎች እና ከተሞች (ቦታዎች)
2. የቤተ ክርስቲያን ቀጠሎ
በባሌ ዞን ኮኮሳ ሆጊሶ መድኃኔ ዓለም ሙሉ ለሙሉ ተቃጥሏል
3. የተገደሉ ምዕመናን በተመለከተ
በጥቃቱ የተገደሉ ሰዎች ብዛት 67 ሲሆን ሁሉም የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አማኞች ናቸው፤ ሌሎች የሞቱ ሰዎች ተብለው የተገለጹት ከፖሊስ እና ከመከላከያ ሀይል ጋር በተደረገው የአጸፋ ተኩስ ልውውጥ የሞቱ አጥቂዎች እንደሆነ መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡
ከሟቾች ውስጡ አንዱ ካህን መሆናቸው የተረጋገጠ ሲሆን ብዙ ካህናት ላይ የአካል ጥቃት ደርሷል፡፡
የተጠቁና የሟቾች ብሔርን በተመለከተ፦ አብዛኞች ከኦሮሞ እና አማራ ብሔር ሲሆኑ ጉራጌ፤ ዳዉሮ፤ ወላይታ፤ ትግሬ እና የም ከሟቾች ውስጥ ይገኙበታል፡፡
በዕለቱ ከፍተኛ ጥቃት የደረሰባቸውና በሞትና በሕይወት መካከል ያሉ ብዙ ሰዎች የነበሩ ሲሆን በአሁኑ ጊዜ ያሉበት ሁኔታ አልታወቀም፡፡
በኦሮሚያ ክልል ዝዋይ አዳሚ ቱሉ በሚባል ቦታ በእነዚህ አጥቂዎች አንድ ቤተሰብ በሙሉ 5 ሰዎች (አባት፤ እናትና ልጆች) የተገደሉ ሲሆን ብሔራቸው የሽዋ ኦሮሞ ነው፡፡
4. የሟቾች የአገዳደል ሁኔታ እና የአጥቂዎች የጥቃት መሣሪያ
ጥቃት አድራሾቹ ለግዲያ የተጠቀሙባቸው መሳሪያዎች፡- ጋዝ ፤ሜንጫ ፤ቆንጨራ፥ ዱላ እና ሽጉጥ ነው፡፡
አንገታቸውን ታርደው የተገደሉ ቢያንስ 12 ሰዎች ናቸው
ከውጭ በር በመቆለፍ በቃጠሎ የተገደለ 1 ሰው
ተደብድቦ በእንጨት ላይ ተሰቅሎ የተገደለ 1 ሲሆን
ሌሎች በድንጋይና በዱላ በመደብደብ፤ በጥይት እና አስፋልት ላይ በገመድ በመጎተት የተገደሉ ናቸው፡፡
5. የንብረት ውድመትን በተመለከተ
በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች የንብረት ጥቃት የደረሰባቸው ሲሆን ለዘመናት ለፍተው፣ ጥረው ግረው ያፈሩትን ሀብትና ሙሉ ንብረታቸውን በማጣት በአንድ ጀንበር አጥተው ተመጽዋች ሆነዋል፡፡
ሙሉ በሙሉ በእሳት ተቃጥሎ የወደመ፤ ከፊል ጥቃት የደረሰበት እና ከፍተኛ ዘረፋ የተፈጸመ ሲሆን
በጥቃቱ፡-
6. ከመኖሪያ ቤታቸው የተፈናቀሉትን በተመለከት
በአሁኑ ወቅት ከ7000 የማያንሱ ሰዎች የጥቃቱ ሰለባዎች በመሆናቸው በቤተ ክርስቲያንና በአንዳንድ መጠለያዎች ተጠልለው የመንግሥትን ድጋፍ እየጠበቁ ይገኛል
7. ተጨማሪ መረጃዎች
1. ከኦርቶዶክሳውያን ውጭ ንብረታቸው የወደመባቸው ስለመኖራቸው
99 በመቶ ጥቃት የደረሰበትና የወደመው ንብረት የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች ንብረት ሲሆን በአንዳንድ ቦታዎች በመረጃ ስህተት ይመስላል 2 ቦታዎች ላይ የፕሮቴስታንት እና የሙስሊም ንብረት ላይ ጥቃት ደርሷል፡፡
በግድግዳ ከሚለዩ ቤቶች ውስጥ የአርቶዶክሱ ሲጠቃ የሙስሊሙ ምንም ዓይነት ጥቃት አልደረሰም፡፡
በብዙ ሙስሊም ቤቶች መካከል የሚገኝ የኦርቶዶክስ ቤት ሲጠቃ የሙስሊሞች ቤት አልተነካም /ለምሳሌ፦ ቡኖ በደሌ ጮራ ወረዳ/
በብዙ ቦታዎች ጥቃት አድራሾች “አላሀ ወአኩበር” በማለት ይጨፍሩ እንደነበር በአይን እማኞች ተረጋግጧል /በተለይም በምዕራብና ምሥራቅ ሐራርጌ አካባቢ/
2. በዘር አሮሞ ሆኖ የተገደለ ሰው ሰለመኖሩ
በብዙ ኦሮሞዎች ላይ (በተለይም የሸዋ ኦሮሞ ላይ) የሞትም የንብረት ውድመትም ጥቃት ደርሷል፡፡
በአንዳንድ ቦታዎች ቤት ለቤት በመሄድ የክርስቲያኑን የአንገት ማዕተብ እያዩ ጥቃት ያደረሱ ሲሆን እኔ ኦሮሞ ነኝ በማለት ምዕመናን ሊያመልጡ ቢሞክሩም ማዕተብ ያሰረ ኦሮሞ አናውቅም በማለት የጥቃቱ ሰለባ ሆነዋል፡፡
3. ሌሎች
ከሟቾች ውስጥ አራስ ሴት እና አቅመ ደካማ አዛውንት /ከ65-72 ዕድሜ ያላቸው/ ይገኙበታል፡፡
ረብሻውን የበለጠ ለማቀጣጠል በማሰብ መጽሐፍ ቅዱስ እና ሌሎች ንዋያተ ቅድሳት ተቃጥለዋል
ብጹዕ አቡነ ሔኖክ የጥቃቱ ዒላማ ተደርገው የነበረ ሲሆን በእግዚአብሔር ቸርነት በሰዎች ጥረትና በጸጥታ ኃይሉ ድጋፍ ከሞት ተርፈዋል (ሻሸመኔ ላይ)
የኦሮምያ ፖሊስ በአንዳንድ ቦታዎችላይ /ጅማ፤ ሻሸመኔ፤ ዶዶላ/ ንጹሐን ዜጎች ላይ ተኩሷል
መከላከያ ሠራዊት እና የፌደራል ፖሊስ እስከ ሰኔ 23/2012 ምሽት ድረስ ትዕዛዝ አልደረሰኝም በሚል በጥቃቱ ወቅት ቆመው ይመለከቱ ነበር
ሥጋት ተሰምቷቸው በአዲስ አበባ አንዳንድ ቦታዎች ላይ የቤተ ክርስቲያን ደወል በመደወላቸው ከ10 በላይ የሆኑ የኦርቶዶክስ ወጣቶች ሁከት ፈጠራችሁ፣ ረብሽ ቀሰቀሳችሁ በሚል በእስር ላይ ይገኛሉ፡፡
8. ማጠቃለያ አስተያየት
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የአክራሪ እስልምና እና የአክራሪ ብሔርተኞች የጥቃት ዒላማ ከሆነች 30 ዓመት የሞላት ሲሆን በነዚህ አመታት በጅማ፤ በአርሲ፤ በሐራርጌ ፤በባሌ እና በሌሎችም አንዳንድ አካባቢዎች ታላላቅ አደጋዎች ደርሶባታል፡፡
የሰኔ 2012 ዓ.ም ጥቃትም በአዲስ አበባ ከተማ ከተፈጸመው የጅምላ ውድመት በስተቀር በሌሎች አካባቢዎች ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ የኦርቶዶክስ ምዕመናንን ዒላማ ያደረገ ለመሆኑ የሚከተሉትን ማሳያዎች እንመልከት፡
ንብረታቸው የወደመባቸው እና በስጋት ምክንያት ሸሽተው በቤተ ክርስቲያን ተጠልለው ከሚገኙ ከ7000 በላይ ተጎጂዎች ውስጥ አብዛኞች ኦርቶዶክስ ክርስቲያኖች መሆናቸውን
ጥቃቱ በደረሰባቸው አካባቢዎች በሚኖሩና ከጥቃቱ ከተረፉ ክርስቲያኖች ባገኘነው መረጃ መሠረት ከሰኔ 22 እስከ ሰኔ 23/2012 ዓ.ም ድረስ በእነዚህ ጥቃት አድራሾች ሕይወታቸውን ያጡ ወገኖች ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ የተለያየ ቋንቋ ተናጋሪዎች የሆኑ የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች መሆናቸው
ከተገደሉ ክርስቲያኖች ውስጥ አብዛኞች ብሔራቸው ኦሮሞ ሲሆኑ አንዳንዶቹ ለገዳዩቹ ከጥቃቱ ለመትረፍ እኛ ኦሮሞ ነን ሲሉ “እኛ መስቀል ያሰረ ኦሮሞ አናውቅም” በማለት መገደላቸውን በቦታው የነበሩ እና ከጥቃቱ የተረፉ የዐይን እማኞች ገልጸዋል
በአጠቃላይ ባለፉት 30 ዓመታት በተለይም ደግሞ በለፉት 3 ዓመታት በከፋ መልኩ እየተተገበረ የሚገኘው ከኦርቶዶክስ ክርስቲያኖች ነጻ የሆነች ኦሮምያን መፍጠር የሚለው የአክራሪ እስላሞችና የአክራሪ ብሔርተኞች ጥምር ዕቅድ መሆኑ በአሁኑ ጥቃት በግልጽ የወጣበት፡፡
ለዚህ ግልጽ ማሳያ ውስጥ
አንደኛው የጥቃት ኢላማ ሆኑ ተብሎ ከሚነገርላቸው የአማራ ብሔር አባላት ሆነው እምነታቸው የእስልምና የሆኑትን ጥቃቱ ያላካተተ መሆኑ ሲሆን
ሁለተኛው ኦሮሞዎች ሆነው ኦርቶዶክሶች ከሆኑ ኦሮሞ ሆኖ ባለመስቀል አናውቅም በማለት የጥቃቱ ሰለባዎች መሆናቸውን ማየት በቂ ማሳያ ነው፡፡
ከዚህም በተጨማሪ ከአክራሪ ብሔርተኞች ጋር የሚሠሩት የኦሮሚያ ቤተ ክህነት አደራጆች ኦርቶዶክሱ ክርስቲያን ላይ የተፈጸመውን ጥቃት በማስተባበሩ ረገድ ድርሻ እንደነበራቸው በፖሊስ ምርመራ አንዳንድ ማሣያዎች እንዳሉ የተጠቆመ ሲሆን በቀጣይ ሲጣራና ሙሉ መረጃ ሲደርሰን ይፋ የምናወጣው ይሆናል፡፡
በቀጣይም እነዚህ አክራሪ እስላሞች እና አክራሪ ብሔርተኞች ኦርቶዶክስ ክርስቲያኑን እና ቤተ ክርስቲያንን የጥቃት ዒላማ አድርገው እየሠሩ መሆኑን መረጃዎች ይጠቁማሉ። መንግሥት ሕግ ለማስከበር በአሁኑ ወቅት እያደረገ የሚገኘው ጥረት በጣም የሚደነቅ ሲሆን የእነዚህን የአክራሪ እስላሞች እና አክራሪ ብሔርተኞች ድብቅ አጀንዳ (ኦርቶዶክስን ከኦሮሚያ ማጽዳት) የሚለውን ተረድቶት ይሆን? የሚለው ጉዳይ ግን አጠያያቂ ነው፡፡
ውድ አንባቢዎቻችን ይህ ሪፖርት የተጠናቀረው እስከ ሐምሌ 1 2012 ድረስ በተሰበሰበ መረጃ መሰረት ሲሆን በቀጣይም እየተከታተልን ተጨማሪ ሪፖርቶች ወደናንተ የምናደርስ መሆኑን እናሳውቃለን።
በጥቃቱ ሕይወታቸው ያለፈውን እግዚአብሔር አምላክ ነፍሳቸውን በአጸደ ገነት ያኑርልን፤ አንገታቸው ላይ ስላሠሩት መስቀል፣ ስለ ኦርቶዶክሳዊት ሃይማኖት የተሰዉትን የሰማዕታትን አክሊል ያቀዳጅልን፤ ለቤተሰቦቻቸው መጽናናትን ያድልልን፤ በመከራ በስደት በጭንቀት ያሉትን ፈጣሪ በቸርነቱ ይጎብኝልን።
ሐምሌ 01/2012 ዓ.ም
|
No comments:
Post a Comment