Wednesday, 22 February 2012

የትግራይ ሱሪ፣ ከአሉላ ጋር አበሮ ተቀበረ


Tigray Suri K Alula -

Thursday, 2 February 2012

BASHA ASRES TESSEMA
MELES ZENAWI'S BANDA GRAND DAD!

Who is Basha Asres Tessema? He is the one who massacred Ethiopian patriots in the servicie of Italians. His grand son is the Prime Misery of Ethiopia, today. The following pictures are historical facts in that they show him in action.

Basha Asres Tessema on the day he was appointed an official of Italian invaders.


Basha Asres Tessema with his Italian masters (6th from left) at the stale buil in memory of fallen Italian solidiers at the Battle of Adwa in 1896.


More news can be obtained from:


Or Isat news:


God save Ethiopia from the grand children of the Bandas!


Tuesday, 31 January 2012

“ይድረስ ‘ለዳኞች፦ዳኛ’ ”

የጐንቻው!

ሳር ቅጠሉ፤ ገመድ ተፍተለተለና፤

ሽምቀቅ ማተብ ሆነ፤እምነቱ፤ቀረና፤

በላይን ሰቀሉት፤የላቀውን ጀግና፤

ማነቆ አደባባይ፤የትውልድ ገመና፤

ከጠላት ባዳናት፤በአገሩ፤መዲና፤

ስቅላት ውለታው፤እርግምት ነውና፤

ብርክ መዳህ ጀመርን ነፃነት፤ልመና፤

ያውም ከባዕድ አገር ተሰፍሮ፤በቁና፤

በላይ እምቢ ብሎ አኛ እጅ ሰጠንና፤

እንጠፋፋለን ‘አሳር’፤ እንደገና፤

ይድረስ፤ለአገር ዳኛው፤‘ሕዝቡ በደፈና’፤

ዛሬም ‘ክህደታችን’፤አልተፋቀምና፤

ስንት ‘በላይ’ ሰቅለን እንሰይም ጐዳና።



በዘመነ ንጉሥ፤‘በግርማሜ’፤ሞት፤

አገር ሳይቆጣ፤ሳይተጋ፤ወጣት፤

በዘመነ ‘ደርግም’፤በ‘ሺህዎቹ፤እልቂት’፤

ጥቂቶች፤ሲተጉ፤’መንጋው’ ሲራኮት፤

የባሰ፤ደንቀራ፤ተጋረጠበት፤

‘እናት’ በጓዳዋ፤የልጅ ቁርኝት፤

ዘመነ፤ወያኔ፤መከራ፤ግዞት፤

አገር-ሕዝብ፤የሚያሥር፤በዘር ሰንሰለት።



ሕዝብ የሚያስጨርስ ነፍሰ-በላ፤ዳኛ፤

ለምን አይጠየቅ፤በአገር አደባባይ፤ችሎት ‘መስቀልኛ’፤

ሁነኛ ሰው ጠፍቶ፤ጠበቃ፤የሚሆን፤ አዋቂ ቁርጠኛ፤

‘እድሜ፤ልክ’ እሥራት፤ ተፈረደ ‘በእኛ’፤

ይድረስ ለአገር ሸንጐ፤ይድረስ ለአገር ዳኛ፤

ለምን ፍትህ አትሰጥ፤ይግባኝ የማይሸረው፤በአሳሪና እስረኛ፤

ብይን አስቆጭተህ፤እጥር ምጥን ያለ፤‘ሰውኛ-አገርኛ’፤

አትደግስም ወይ፤በቀናት፤በወራት፤ወያኔን መሸኛ።


በፍርሃት ማዕበል፤አገር ሲጥለቀለቅ፤

በክህደት፤ጐርፍ ምጣት፤ሰው ከቀየው ሲለቅ፤

እንባ ባዘነበው፤ደም በቋጠረው፤ ሃይቅ፤

በወያኔ አዞዎች፤በቁም ሰው፤ሲቦጨቅ፤

ገመና እሚሸፍን፤ሱሪ፤የሚያስታጥቅ፤

በአገር ጀግና ሲነጥፍ፤ወንዙ፤ምንጩ፤ሲደርቅ፤

ጓዳ እሚያወላዳ፤ቀሚስም እሚያጠልቅ፤

በአዘቦት፤በጥምቀት፤አድባር ሲሸማቀቅ፤

ቅርጣን የተረፉ፤ቃል፤የጠበቁ፤ሃቅ፤

እውነት ትንፍሽ ያሉ፤ዓለማችን እንዲያውቅ፤

የ’ግርማሜን’ መንፈስ፤የበላይን ሰንደቅ፤

እንቁ የአበሻ፤ልጆች፤የትውልድ ፈርጥ ወርቅ፤

ስማቸው፤አርማቸው፤በአለም የሚደነቅ፤

ማተብ ይሁን አልቦ ካቴናቸው፤ይውለቅ፤

ይድረስ ለአገር ዳኛው፤አፎት፤እንዲታጠቅ፤

አሳሪው ይታሰር፤ክህደቱ፤ይሽምቀቅ።



በአኬልዳም ሽብር፤የተፈረጁት፤

‘ጥፋት’ ባጋለጡ፤እስር ስቅላት፤

አንዷለም፤እሥክንድር፤ጀግናዋ ርዕዮት፤

ዘመኑ፤በቀለ፤ናትናዔል፤አሳምን፤ደግሞም፤ውብሸት፤

ከሺህ ተቆራኝተው፤ስለ ሕዝብ፤ስለ አገር የተሳሰሩት፤

ለዓለም መቀጣጫ፤ንብረት-ነፍስ፤አራጣ፤የሚገብሩት፤

መጋጥ በለመደው፤ ያረጀ ያፈጀ ነቅዝ፤ስርዓት፤

ይድረስ የአገር ዳኛ፤ዋስም ጠበቃ ሁን፤ውጣና ‘ታገት’፤

አበሳችን ይሻር፤ሰይም አደባባይ፤የእምነት የምህረት፤

ሕዝብ ሸንጐ፤ጠርቶ፤የብይን ችሎት፤

ይፍረድ፤ የአገር ዳኛ፤በቀን በወራት፤

ታሳሪ፤አሳሪውን፤እንዲጠይቁት፤

በአገር ‘መስቀልኛ’፤እንዲያፋጥጡት።

በእስራትና በቅጣት፤ለሚንገላቱ፤ብርቅ ድንቅ ኢትዮጵያዊያን ድጋፍ፡-
·        በውስብስብ ታሪካችን፤ውድ ሕይዎታቸውን መስዋዕትነት ከፍለው፤እንደ ሰው፤እንደ ዜጋ፤ ሰብዓዊ ክብር፤ጸጋ፤ኩራት፤ማንነት አጐናጽፈውን ያለፍ፤ኢትዮጵያዊያን ቁጥር በጣም ግዙፍ ነው፤ ይኸንን ጀግንነታችውን፤ መስዋዕትነታቸውን በአብዛኛው ስንዘክር ኖረናል።
·        ይሁንና በተለይ፤በዚህ በቅርቡ ‘በኛ ዘመን’ ለጊዜውም ቢሆን ‘ደመ-ከልብ’ያደረግናቸው፤እስኪሚያሰኝ፤ የረሳናቸውና፤የተሰውለትን ዓላማ ችላ ያልነው፤ወይም፤ የሕዝቡ፤ቁጭት፤ የደበዘዘ፤ይመስላል። ኃያው ጀብዱ፤ ሰርተው ያለፉ፤ እህት ወንድሞቻችን፤ ወላጆቻቸው እንባ ሳይታበስ፤ ሃዘናቸውን በውስጣቸው ቀብረው፤ በተስፋ የሚኖሩ ወገኖቻችን በጣም ብዙ ናቸው።
·        አሁንም የወያኔ መንግሥት፤ ስለገመተን፤ስለናቀን፤ በሽብር አሳቦ፤ቁጥር ስፍር የሌላቸውን፤ ወገኖቻችንን፤ ብርቅዬ መሪዎቻችን፤ የላቁ፤ ባለሞያዎቻችንን፤ ጋዜጠኞቻችንን፤በእስራት፤ስቅላት፤ ሲያንገላታ፤ሲያሰቃያቸው፤ከንፈር እየመጠጥን፤በየጓዳው፤ቡና የምናቃርር፤ወሬ፤የምናመንዝክ፤ ሞልተናል።
·        እንደዚህ በቀላሉ፤ ለእውነት፤የቆሙ፤እህት ወንድሞቻችንን አሳልፈን የምንሰጥ ከሆነ፤ፍጹም ነፃነት የማይገባን ሕዝቦች ነን፤ከዚህ በኋላ፤በትውልድም፤በታሪክም፤ተጠያቂዎች፤የለየለት የጠላት፤ድቃላ፤ወያኔ ብቻ ሳይሆን፤ ዝምተኛው፤ ‘ሰማኒያ ሚሊዮን’ ሕዝብ ጭምር ነው።
·        በዚይ የሚገርም የታሪክ አጋጣሚ፤ዘመነኞች፤ ደባ-ድራማ፤ በአደባባይ፤እያቀነባበሩ፤ሲያቀርቡልን፤በቁጣ እንኳ፤ ‘ጠጠር’ የወረወረ፤ወይም አመጹን፤ተቃውሞውን፤ በሥራ ማቆም አድማ የገለፀ’ የለም። ከዚህ በላይ ምን ሊመጣ ነው? መቼ ነው ሕዝብ የሚቆጣው?
·        ከአብራኩ የወጡ፤እህት ወንድሞቹን፤ልጆቹን፤ወላጆቹትን፤ እድሜ ልክ ሲያስሩበት፤ሞት፤ስቅላት፤ሲፈርዱባቸው፤ሳይዋደቅ፤ዝም ብሎ ካዬ፤ የዚህ ዓይነት ሕዝብና አገር፤ወገንም፤ዜጋም መሆን፤የሚያስፍር ነው።                    yegonchaw@yahoo.co.uk

Friday, 9 December 2011


የጐንቻው !

ወዮላቹህ፤የቀን ጅቦች ሳታስቡት፤መሸባቹህ፤             

ሕዝብ መሽጓል በዋሻቹህ፤መሸሸጊያም የላቹህ፤

አጥንት ነካሽ ‘የቄራ ውሾች’፤ተራብታቹህ፤

ስትጮሁ ለከርሳቹህ፤የሕዝብ እሮሮ ነቅፋቹህ፤

ምንደኞቹ፤ሕዝብ-አገር በቅርጫ ያረዳቹህ፤                       

ምረነኛ፤ጉጅሌዎች ‘ስጋ-በስጋ’ የደለባቹህ፤

እርም እምነት የበላቹህ፤በዘር በደም ተሳክራቹህ፤

የወየናቹህ፤በእብሪት በጥጋብ ተወጥራቹህ፤

ጎኁ ቀዷል፤ሊያባራ ነው ምጣችን፤ምጣታቹህ፤

በዓለም መስትዋት የበቀል ቁና ፍዳቹህ፤

ተቆልሏል፤አበሳቹህ፤ልክ ያለፈ ስንክሳራቹህ       ፤     

እንዳይነቱ ግብራቹሁ፤የአደባባይ ፍጻሜያቹህ፤

እንደ ቱኒዙ፤ግብጽ፤ሊብያ፤ ነው እጣ ፋንታቹህ።



በቁስላችን እሾህ የምትሰዱ፤የወያኔ፤ቁንጮዎች፤

እሾሁ ሲነጣጠር ወደ አይናቹህ በሚሊዎኖች፤

በሞተ ሰዓት የሟርት ሽብር ከበሮ ደላቂዎች፤

ስንቱን ክቡር ዜጋ ጭቃ ቀቢ፤የአገር ጉድፎች፤

የምታስሩ፤የምትገርፉ፤ወንድም፤ እህት፤ወላጆች፤

‘ቴሬሪስት፤ድራጊስት፤አልካኢዳ፤አልሸባብ ’ ክሶች፤

የወንበዴ ታርጋ ለጣፊዎች፤ምህረት የማትሹ፤ቂሎች፤

‘ዝና-ስሙ’ ለናንተ እንጂ እድራችሁ አጥፍቶ-አጥፊዎች፤

በፓርላማ፤በ‘አረንጓዴው አደባባይ’፤ባዶ አኬልዳማዎች፤

አይሰሩምና የ‘ጋዳፊ’ መፈክሮች፤የቅጥፈት ስልቶች፤

ወዮላቹህ! ፍጻሜያቹህ፤ለምህረትም-ለተረትም አይመች።



በግንባራችን የደቀናቹህ የወያኔ ‘ጠብ-አንጋቾች’፤

ቃታ ከሳበ ጣታቹህ ዛሬም ልትገድሉ የሕዝብ ልጆች፤

ቅጽፈት ናቹህ፤የሰማይ የምድር ዘላለም ሙቶች፤ 

በህግና በፍትህ ስም የምትቀልዱ ዳኛ ጠበቆች፤

የምታንገላቷቸው፤የትውልድ የሰላም አንኳሮች፤

የአገር-ሕዝብ አውራ፤ንግሥት ናቸውና እስረኞች፤

ዛሬ አስተውሉ፤እንዳይነድፏቹህ ኋላ ‘ሆ!ብለው ንቦች።                  

የኔሰው ገብሬ፤ የዳውሮ ዋርካው፤ ምሁሩ ሻማ፤በራሱ ለቆ፤

የጋረደንን የፍርሃት ድባብ በኃይዎቱ፤ውጋገን ለኛ፤ፈንጥቆ፤

አይሆንምና ደመ-ከልብ ቃል በምድር፤ቃል በሰማይ፤ተሰንቆ፤

እንዲጧጧፍ ትግላችን በየጉልቻው፤አናዳጆችን ማግዶ፤አስጨንቆ።



ወዮላቹህ! ወያኔዎች፤‘ሙባረክን’፤‘ጋዳፌን’ ያዬ፤

እዝነ-ልቦናቹህ፤ካልፈራ፤ዓይነ-ህሊናቹህ፤ካላዬ፤

እንደ ደመራ ልትሞቁን ከዳዳቹህ፤ሕዝብ ሲቃጠል እየታዬ፤

ኢትዪጵያዊ በግፋቹሁ እየጋዬ፤ንስሃቹህ፤ከዘገዬ፤

ወዮላቹህ፤ወገን ጥዶ ያብስላቹህ መስቀል ከቦ እያጋዬ።





እነሆ፤የተዳፈነው እሳት፤ተቀጣጥሏል፤ሰደዱ፤

የተቆጡት፤የቆረጡት፤በየማዕዘኑ፤ሊነጉዱ፤

‘የፎጡን’፤ግንብ፤ሊንዱ፤ቅልቦችን ሊያስርዱ፤

ወዩላቹህ!፤ሕዝብ ሃያል ነውና የቁጣ ክንዱ፤

መውረጃቹህ ይኸኔ ነው፤ብትሰሙ፤ብትረዱ፤

በግብጽ ‘ሙባረክ’፤ሕዝብ የናቁት፤ ‘አንበሳ’፤

እንደ ጨርቅ አልቀው ሲጓጓዙ በሳንሳ፤

አልጋ ወራሾች፤ተሳስረው ከንጉሱ፤የቁም እሬሳ፤

የሊቢያው ‘ጋዳፊ’፤ሕዝብን በስድብ አርክሰው፤

ተያዙ፤አይጥ ጉድጉድ ተወትፈው፤በቆሻሻ ማኩሰው፤

የሞት-ሞት፤ ሞቱ፤ያልማሩትን ሕዝብ ምህረት ለምነው፤

ወዮላቹህ! ወያኔዎች፤በደመ ነፍስ፤ያላቹህ፤

ቅንጣት እምነት ካላቹህ፤በደል ጥፋታቹሁን፤አምናቹህ፤ 

ግቡ ንስሃ ፤ባለቀ ሰዓት ሽብር አሳሩን ትታቹሁ።


 





ለኢትዮጵያ ሕዝብ ነፃነት መስዋዕቱ፤ ሰማዕታቱ የኔሰው ገብሬ!  ዳውሮ-ዋርካ
በወያኔ በደልና ግፍ ተንገብግቦ ሕይዎቱን በአደባባይ ለወገኑና ለሐገሩ መስዋዕትነት በቁሙ እሳት አጋይቶ የመጨርሻውን የሕይዎት ዋጋ ለከፈለው ጀግናው ወጣት ምሁር የኔሰው ገብሬ መታሰቢያ ትሁንልኝ።

እነሆ አምላካችን ነፍሱን ይማርልን፤ ለወላጅ ቤተሰቦችም ጽናትን ለመላው ኢትዮጵያ ሕዝብ በሙሉ ቆራጥነትን፤ እሻለሁ፡ ወንድማችን ደመ-ከልብ ሆኖ እንዳይቀር መልዕክቱን፤ተቀብለን መስዋዕትነቱን ግብ እናድርስ፡ የትግሉን ሰደድ አቀጣጥለን፤ለድል እንብቃ፤የሰማዕታቶቻችንን ነፍስ ይማር።

የወጣቱ ምሁር የኔሰው ገብሬ እንደ ቱኒዚያው መሐመድ ቡዋዚዚ ለዓረብ ሕዝብ ተምሳሌ ሆኖ በርካታ ህሕዝቦንችንና አገራትን ከዘመናት ከባርነት ያልተለየ አገዛዝ ነፃነት እንዳቀዳጀና እያቀዳጀም እንዳለው ሁሉ፤ የቆራጡ ወንድማችን ገድልም ለኛ ለኢትዮጵያዊያን ብቻ ሳይሆን እንደኛ በጨካኝ፤ገዥዎቻቸው ስር ለሚማቅቁ፤ ጥቁር አፍሪቃዊያን ወገኖቻችን ሁሉ፤የነጻነት ቀንዲል ይሆናል።

የጐንቻው!      yegonchaw@yahoo.co.uk