ወንድሙ መኰንን፣ ሎንደን ሚያዝያ ፳፭ ቀን ፪፼ ዓ.ም (3rd May 2013)
ይኽቺ ጦማር የግሌ እንጉርጉሮ ናት። ዛሬ “እኔ” እበዛባታለሁና ተገሡኝ። በኔ ዕድሜ ያላችሁ፣ መቼም “ተንኮለኛው ከበደን” ታስታውሱታላችሁ! ይብላኝላችሁ ለወጣቶቹ እንጂ፣ እኛስ ዘንጠንባታል። ዛሬ ዛሬ ላይ አባ ተንኰሉ የሚሠሩትን ትርዒቶች ሳይ፣ የተንኰለኛው ከበደ ታሪክ ትዝ ይለናል። ሎንደንና አካባቢዋ የምንኖር ኢትዮጵያዉያአን ሁለት ከባድ ነገሮች ከብደውናል። ኤምባሲው ውስጥ ብርሀኑ ጠፍቶ ጨለማው ከበደ። ቤተክርስቲያናችን ውስጥ ግሩም ሰው ጠፍቶ ተንኰለኛው ከበደ። አይ አባ ተንኰሉ! አዋጊ አቡናት አመጡብን!
የኸን ጦማር መጦመር የጀመርኩት፣ በዕለተ ስቅለት ነው። እንደ ድሮው ቢሆንልኝማ ኑሮ፣ በዛሬይቱ ዕለት፡ ቤተክርስቲያኔ ሂጄ፣ ከጠዋቱ በጉልበቴ ውድቅ ብድግ እያልኩ፣ ጌታዬ መድኅኒቴ እየሱስ ክርስቶስ ከጌተ ሰማኒ ከአትክልቶች ቦታ ከተያዘባት ሰዓት አንስቶ፣ ጎልጎታ ራስ ቅል ተሰቅሎ ሕይወቱን ለኔ ቤዛ አድርጎ እስከሰጠበት ጊዜ ድረስ የተቀበላትን ስቃይ እያስብኩ፡ “ጊዜ ሠለስቱ ሰዓት! አሐዝዎ ለኢይሱስ” ... “ጊዜ ስድስቱ ሰዓት፣ ሰቅልዎ ለኢትየሱስ በቀራኒዮ መካን” ... “ጊዜ ተሰዓቱ ሰዓት፣ ጸርሐ በቃሉ ወይቤ ‘ኤሎሄ! እሎሄ!” በዜማ እያልኩ፣ በየማሀሉ አርባ ጊዜ ደፋ ቀና ብዬ እግዚዖ “ማሐረነ ክርስቶስ” የምልበት ጊዜ ነበር። አይ አባ ተንኰሉ! ነፍስዎ አይማርም። ዘንድሮ ቤተክርስቲያኔን ዘግተውብኝ፣ አሰናከሉኝ አይደል። እርስዎና ዲያብሎስ ዘንድሮ ተሳካላችሁ! ከመከራ ኃጢአት እንኳን እሸሸግበት አጥቼ ሜዳ ላይ አስቀሩኝ። የጌታ በግ ወደ አምላኬ እጣራለሁ!
ጽሕፏ የግሌ ታሪክ ብትሆንም፣ መቸም መስገድ አልቻልኩ፣ ባይሆን ለንባብ ላብቃትና ሰቆቃዌ ወንድሙ ብላችሁ አንብቡልኝ። እንግዲህ እጅ ያፈራው ነውና፣ በዓለም ዙሪያ ተበትናችሁ የምትኖሩ ዘመዶቼና ጓደኞቼ፣ እዚህችም ለንደን ከኔ ጋር የኤምባሴው ጨላማው ከበደና የቤተክርስቲያናችን ተንኰለኛው ከበደ ዶልተውብን ውጪ ቢያስቀሩንም፣ በዓሉ በዓል ነውና እንኳን ለብርሀነ ሥቅለቱ አደረስን ልበላችሁ! ደግሞ ለትንሳኤው ሰው ይበላችሁ እያልኩ እንደነግሩ እንድታነቡልኝ ስጋብዛችሁ እግረመንገዴን እንድትጸልዩልኝም አድራ እላለሁ። አይ አባ ተንኰሉ!
የዘንድንሮው የስቅለት በዓል ዋዜማ፣ የዕስልምና ተከታይ ወንድሞችና እህቶቻችን “ቀናቸውን አናበላሽባቸውም” በማለት ካስተላለፉት የተቃውሞ ሰልፍ ሌላ አንድም የሚያሰደስት ደግ ዜና አላጋጠመንም። ሁሉም የሚያሳዝን፣ የሚያሸበርና የሚያናድድ ነው። የእስልምና ሀይማኖት ተከታሆች የሆኑትን ወንድሞችና እህቶቻችንን፣ እናመሰግናለን። እግዚአብሔር ወይም አላህ ለቸርነታችሁ ይባርካችሁ፣ ለጥያቄአችሁም መልስ ይስጣችሁ እንላለን። በትላንትናው የስቅለት ዋዜማ የአራት ኪሎው ሰይጣን ታላላቅ በደሎችን ፈጽሞብናል። በአዲስ አበባ፣ ዓይን አውጣው የወያኔ ገዥ የታላቁን አርብኛ ሰማዕት የአቡን ፔጥሮስን ሐውልት አንስቷል። መድኃኔ ዓለም፣ እንደዚያ ሐውልት፣ ግንድስ ያርገው! ሁለተኛም ያው በካንጋሩው ፍርድ ቤት በጀግና በጋዜጠኛው እስክንድር ነጋ፣ በዕውቆች ፖሊትከኞች አንዱዓለም አራጌ፣ ናትናኤል መኰንን እና ሌሎችም የሞት (ውጪ ባሉት የግንቦት ሰባት አባላት!)፣ ከዕድሜ ልክ እና የአሥራ ስምንት ዓመት እሥራት ፍርድ ብያኔ አጽንቶባቸዋል (ፕሮፊሰር ኤፍሬም ይስሐቅ ሌላ ሥራ አገኙ በሉኛ!)። የቤኒ ሻንጉሉን እሪታ ተውት! የዋልድባውን ጩኸት ተውት! 150 000 ኦሮሞዎች ትላንትና ከኦጋዴን ተፈናቅለዋል! ዋይታ ነው! ኡኡታ ነው!
ወደ ሎንደን መለስ ስንል፣ በተክርስቲያን ጠርቃሚው “አባ ተንኰሉ” ወይም ተንኰለኛው ከበደ፣ ሁለት ነገር አደረጉ፡፤ አንደኛው በጠዋት ሂደው በዘጉት ቤተክርስቲያን ደጃፍ ላይ ድንኳን አስተከሉ። የኛም ሰዎች ሩጠው የራሳችንን ዘረጉልን! “ሁለት ለሰማይም ለምድርም የከበዱ” አዋጊ ጳጳሳት ከአዲስ አበባ ለውጊያ ኢምፖርት ማድረጋቸውን ቢዲዮ ተቀርጸው አነበነቡልን። “እነሱ በተገኙበት በድል ቤተክርስቲያናችሁን ስክፍትላችሁ፣ ኑ እና እጃችሁን ስጡ፣ ይቅርታ ጠይቁኝ” የሚል ብጤ መልዕክት ነበሩ በዩ-ቱዩብ የለቀቁብን! በገንዘባችን የገዛናትን ቤተክርስቲያን በፈልጉበት ሰዓት የሚከፍቱና የሚዘጉ የግል ሱቃቸው አደረጉት አይደል? እልል እነበልላቸው ይሆን? እዲያ! አሽቃባቾቻችው በውሸት ስማቸው “ግርማ ናና!” እያሉ ዕልል ይበሉ እንጂ እኛ ምን ቆርጦን። ለመሆኑ፣ “ቤተክርስቲያኗን የዘጋነው በHealth & Safety ምክኒያት ነው” አላሉንም እንዴ! አዋጊ አቡናት በማስመጣታቸው፣ የHealth & Safetyው ጉዳይ ብን ብሎ እንደነፋስ ጠፋ ወይስ ነገሩ እንዴት ነው? መቸም እንሞታታለን እንጂ፣ እንደአዋሳ ወንድምና እህቶቻችን “ገብርኤል ናና! ቀውስቶስ ናና!” ብለን ዘምረን እጃችንን እንደማንሰጥ ይገባችሁ ይሆን! ከመጀመሪያው ጀምራችሁ፣ ሕዝብ የምትንቁ ስለሆናችሁ መቸ ይታያችኋል? ለማንኛውም አንባቢዎቼ፣ አባ ተንኰሉ፣ ተኳኩለው፣
ተሽሞንሙነው (ሽቶም የቀራቸው አይመስለኝም - በነገራችን ላይ ሽቶአቸውን አሽተተዋቸው አታውቁም መስቀል ልትሳልሙ ስትቀርቡ!) የሎንደኑን ራስፑቲን የላኩልንን መልዕክት በሚከተለው ቅጥያ፣ ዘና ብላችሁ ቼዝ ሲጫወቱ ተመልከቱልኝማ። አባ ሽሙንሙኔ አባ ተንኰሉ!
“አይ አባ ተንኰሉ” በሉ እስቲ ሁላችሁም ይኽችን መለዕክታቸውን ሰምታችሁ ስትጨርሱ! ሲለመኑ፣ ሲለመኑ ከርመው ይኽቺ ነገር አሁን እንዴት ብልጭ አለችላቸው? በ11ኛው ሰዓት? ዓይናቸውን አስተዋለችላቸው እንዴ? እሳቸው እራሳቸው የጎነጎኗትን ውስብስብ ክር በቀላሉ ተረተሩልን አይደል? በጣጠሷት ነው የሚባለው! ቆይ እስቲ! አሁን እኚህ ሰውዬ “ይቅር እንባባል” ሲሉ “The member of the
Congregation are not the member of the Charity and, therefore they cannot
remove the Trustee.” ብለው በሕግ አማካሪአቸውን (solicitors) በኵል ያጎረሱንን ደብዳቤ ረስተው ይሆን? አይ ምናልባት እንግሊዝኛው አይገባቸው ይሆናል ብለው አስበው ከሆን፣ በጠበቃቸው በኩል የተጻፈው ደብዳቤ፣ “የሰበካ ጉባኤው አባላት የቻሪቲው (የቤተክርስቲያኗ) አባላት ስላልሆኑ ባለአደራዎቹን ማንሳት አይችሉም።” ነው ትርጉሙ! እንዲህ ዓይነቱን ክህደት ወደጎን ትተው ነው አሁን የተጣላነው በኮምፓኒው ጉዳይ ብቻ ነውና “እወዳቸዋለሁ” ብለው የሚያሾፉብን! አራዳ! ቤተክርስቲያኗ አባል የላትም ያሉትንስ እንዴት ማስተባበል ይችላሉ። 15 የቀጠራቸውን አባል (በኋላ ለካስ 21 አድርሰዋል) እዚህች እንዳትደርሱ ብለው ሲያግዱ፣ ኢትዮጵያ የሚኖሩ መሰላቸው? በጠበቃ ያስጻፉት ደብዳቤ “The Charity (St Mary
of Debretsion Church, register Charity number 1060394) does not have any
members. The Charity is constituted as a Trust, of which are there are a number
of Trustees, who hold the asset of the Trust.....” አይደል የሚለው ሌላው ክርክራቸው?? ኤድያ! ተጃጅለው
አጃጃሉን ጃል! በኵሩ ወንድማቸው ይሑዳስ ከዚህ የበለጠ ምን ክሕደት ፈጽሟል በተሰቀለው ጌታችን መድኃኒታችን እይሱስ ክርስቶስ ላይ!
ቢዲዮው ላይ፣ ሽሙንሙኔው ተንኮለኛው ከበደ፣ ከመርካቶ በገዙት አክሴማ እራሳቸውን ተጠቅልለው ልክ እንደ ራስፑቲን ከግራ ወደ ቀኝ፣ ከቀኝ ወደግራ እያማተሩ ባትሪያማ ዓይኖችቻቸውን አብለጨለጩብን አይደል? ጨርሶ ትኵር ብለው አያዩዎትም እኮ። እዚያች ዓይን ውስጥ የትዕቢት፣ የንቀት እንጂ አንዲት ጠብታ ፍቅር የለችባትም። ሁሌ እንደ ቆቅ ግራ ቀኙን እንዳማተቡ ነው። ዕውነት መሆኑን አላውቅም እንጂ፣ አንድ በቅርብ የሚያውቃቸው ወጣት እንደነገረኝ ከሆነ፣ በቤታቸው አጉሊ መነጽር አላቸው ይባላል። አንድ ሰው መምጣቴ ነው ብሎ ከደወለላቸው፣ አጉሊ መነጽራቸውን በመስኰት አጮልገው “ማን አብሮት አለ” በሚል ጥርጣሬ ሁሌ ከሩቅ መከታተል አንደሚወዱ አጫወተን። አይ አባ ተንኰሉ!
ሥራቸውን ሁሉ እንዳየነው ከሆነ፣ ሴቶችን ሁን ብለው ሲያማግጡ አልተያዙም እንጂ፣ ልክ እንደራሻዊው ዓለማዊ አስመሳይ መነኵሴ፣ እንደራስፑትን በተንኰል የተሞላ ነው። የሴቱን መናገር መረጃ ስለሌልን አንዳችም ቃል ልንተንፍስባቸው አንችልም። ስማቸውንም አናጠፋም። ምናልባት አሽኮርምመውኛል፣ “ቡና አፍልተሽ አንቺም ተጣጥበሽ ጠብቂኝ” ብለውኛል፣ ወይም ደግሞ “አውቶቡስ ላይ አግኝተውኝ ነይ ቡና ልጋብዝሽ ብለው ወጥረው ይዘውኛል”፣ አለበለዚያም “እንዲህ ለብሰሽ የመጣሽው ማንን ልታሳስቺ ነው”፣ ብለው በመስቀላቸው ጠቆም ጠቆም አድረገውኛል እና የመሳሰሉትን የሚሉ ሴቶች ካሉ፣ እንሱው ወጥተው ይናገሩት እንጂ፣ እኛ በዚህ ሕማማት ኃጢያትም ስንገባ አንገኝም! ነቅተናላ! ተንኰለኛው ከበደ ሆን ብለው ሀጢያት ሊያናግሩን ነው? ለመሆኑ ሆም ኦፊስ ዕውነተኛው ስማቸውን ያውቃል? ግሩም አስገራሚ ሰው ናቸው? አይ አባ ተንኰሉ!
አባ ተንኰሉ፣ በዕውነትም ከተንኰለኛው ከበደ ይብሳሉ። አባባሱባት አለ አንድ ሰው! አብርዋቸው ለሚንከራተቱ፣ ለወጣቶቹ ቀሳውስት፣ ለአባተና ለዳዊት መጥኔ! ከሕዝብ አጣልተዋቸው፣ የግል አሽከራቸው ሊያደርጓቸው ነውና እነዚህን ሁለት ስንወዳቸው የነበሩትን መልካም ሰዎች ከአባ ተብዬው አዚም አላቆ ከጉያቸው ማን ይፈልቅቃቸው? ተንኰለኛው ከበደ እኮ፣ ሲፈልጉ አርበኛው ከበደ ናቸው! ስለአገር ታሪክ፣ ቅርስ ሲያወሩ ከሳቸው ወዲያ አገር ወዳድ ላሳር ነው። እንዲህ የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓላማ ይዘው ሲታዮ፣ ለምንጊዜውም ከወያኔ ጋር የማይታረቁ ጀግና መስለውን ስንቶቻችን እሥራቸው የተነጠፍንላቸው? አገር ቤት ግን ቤት እንደሚሠሩ የሰማነው በቅርብ ሰሞን ነው! ልክ አዝማሪ ሰሎሞን ተካልኝ እንደሠራልን እኮ ነው 1800 ዙረው በሶልዲ የሸጡን። ፖለቲካኛው ከበደም ናቸው! ቀኝ እጃቸውን አውጥተው “ወያኔ ያሰረውን ይፍታ!” እንዳላሉ፣ ዛሬ ዋንድስ ዎርዝ በሚባለው መንገድ ላይ በሚገኘው መስከረም በተባለ ሬስቶራንት ውስጥ ከወያኔ ካድሬዎች ጋር ሲዶልቱ ይውላሉ ቢባል ማን ያምናል? ሰላማዊ ሰልፍ ላይ ብቅ ብለው አይዞአችሁ እንዳላሉን፣ ዛሬ ለወያኔ ንብረታችንን ሊያስረክቡ ሲሞክሩ እንዴት ይታመናል? በአንድ ወቅት ለቤተክህነት የሚቆረቆሩም መነኵሴው ከበደም ሁነው ታይተዋል። እስቲ ስለዋልድባ ገዳም ምን ነበር ያሉት? አዲሶቹ ወዳጆቻቸውም እንዲጠነቀቁ፣ እስቲ በሚቀጥለው ቪዲዮ ቪዲዮ ጸር-ወያኔ እንደነበሩ እንይላቸው።
ይኸንን ቪዲዮ ያየ ዛሬ ከወያኔ ወኪሎች ጋር ሲሞዳሞዱ ምን ይሰማዋል? በዚህች ሰዓት የዋልድባ መነኰሳት ቆባቸው እየወለቀ፣ እየተደበደቡ፣ ገዳሙ እየተዘረፈ፣ ለብዙ መቶ ዓመታት ከተቀበሩበት ጉድጓድ የመነኮሳት አጽም እየተማሰ እየወጣ ከመጣል ያልፈ ግፍ ምን ይምጣ! ዋልድባና አካባቢው ከነገዳሙ እንዳለ በሕወሀት ጉልበተኞች ከጎንደር ተቅምቶ ወደ ትግራይ በመከለሉ፣ “አማራ የሆናቸው መነኰሳት፣ ከገዳሙ ውጡና ወደክልላችሁ ሂዱ (በነገራችን ላይ አባ ተንኰሉም “አማራ ሳይንቴ ነኝ” ባይ ናቸው። ኦ! አማራ ሳይንት ከሰቆጣ ምን ያህል ይርቃል?) እየተባለ፣ ዋልድባን ማዳን ሳይሆን የሎንደኗን የስደተኛ ቤተክርስቲያን ለወያኔ ስሊያስረክቡ ሁለት ጳጳሳትን፣ ከዚህ በፊት እራሳቸው ካወገዙት ሲኖዶስ፤ ኢምፖርት ማድረጋቸው ትንሽም አያሳፍራቸውም? ሰውዬው ሒሊና የምትባል አልተፈጠረችባቸውም!
ከሕዝብ ወገን መሆን ያዋጣኛል ባሉበት ጊዜ ሁለቴ ነበር የአዲስ አበባውን ሲኖዶሱ የወረፉት! አንዴ በሟቹ ታጋይ ጳውሎስ ይመራ የነበረው ሲኖዶስ፣ ለአንግሊካን ቤተክርስቲያን ደብዳቤ ጽፎ፣ ቤተክርስቲያኗን አትሽጡላቸው ብሎ ሲጠይቅ ሲሆን፣ ሁለተኛው ጊዜ ደግሞ አሁን በቅርቡ፣ የአዲስ አበባው ሲኖዶስና ስደተኛው ሲኖዶስ ሲደራደሩ፣ የወያኔው ገዢ መሀል ገብቶ ድርድሩን አስቁሞ የራሱን ፓትሪይርክ ለመምረጥ ሲያውጅ፣ አውደምሕረቱ ላይ ወጥተው ድርጊቱን አውግዘውት ነበር። ከዚያም አልፈው ተርፈው በሰብካው ጉባዔ ስም (ምዕምናን አባላት በሙሉ ለቀውላቸው ወጥተው ካህናት ብቻ በቀሩበት የሰበካ ጉባኤ) ስም፣ መግለጫ አውጥተው በሚከተለው ደብዳቤ በድረ-ገጽ ለጥፈው ይገኛል (ድንገት ካነሱት እኔ ጋ ኮፒው ለዘልዓለም አኑሬዋለሁና ጠይቁኝ)።
ታዲያ አሁን
ከወያኔ ባለሥልጣናት
ጋር ሽር
ጉድ ማለት፣
ከኮነኗቸው የአዲስ
አበባው፣ ሲኖዶስ
ለንደን ደብረጽዮንን
ቀላቅዬአታለሁ ማለታቸው
ላቆመሷቸው ለአቡነ
ማቲያስ ስጦታ
መሆኑ ነው?
በተለይ የአዋሳን
ቤተክርስቲያንን በማስዘጋት
የሚወነጀሉትን፣ አቡነ
ገብርኤልን እና
የውጪውና የውስጥ
ሲኖዶሶችን አንድ
ለማድረግ የተጀመረውን
ድርድር ያጨናገፉትን
አቡነ ቀውስጦስን
ማስመጣት “ውሻ
ወደትፉቱ ... ” የሚባለው
ቀፋፊ ነገር
አይሆንባቸውም?
ጽሑፋቸው ሁሌ
የሚመስጠኝ፣ የዘመናችን
ዕውነተኛው የነገረ
መለኮት ሊቀ-ሊቃውንት
ናቸው ብዬ
የምተማመንባቸው፣ ስለአዋሳው
ጉድ “ዘመነ-መንሱት”
በተባለው ግሩም
ጽሁፋቸው፣ የድሮው
የአዲስ አበባ
ዩኒቨርሲቲ የነበረው
ተማሪዬ አቤል
ጋሼ ከጻፈው
The Wisdom Compass to Eternal Life ጽሑፍ ውስጥ
ከሰፈሩት ቁምነገሮች
ጋር እያነጻጸሩ፣
[1]ከግጽ
6 ጀምሮ እንደሚከተለው
አስፍረዋል።
በሐዋሳ ቅዱስ
ገብርኤል የተፈጠረውን
ሁካታ የሚያሳይ
ቪዲዮ ስመለከት
ባዲሱ ቤተ
ክርስቲያን ቅጽር
ውስጥ የተሰበሰበሰው
በሽህ የሚቆጠር
ህዝብ ይንጫጫል።
ምን እያለ
እንደሚንጫጫ ለመስማት
ስሞክር “ፋኑኤል
ናና ገብርኤል
ናና” የሚል
ድምጽ ሰማሁ።
ከብዛቱ የተነሳ
ህዝቡ ለክብረበአል
የተሰበሰበ መስሎኝ
ነበረ። ፎቶግራፋቸውን
ከፍ አርጎ
በማሳየት የተሰበሰበው
ህዝብ፡ በቀኝ
በግራ ተሰልፈው
ዝማሜ እንደ
ሚቀባበሉ ካህናት
የቀድሞውን የዲሲውን
አባ የአባ
መላኩን የዛሬውን
የብጹዕ ፋኑኤልን
ፎቶ ግራፍ
ተሸክሞ “ፋኑኤል
ናና” ሲል:
በግራ በኩል
ያለው ደግሞ
በተራው የቀድሞውን
አባ ኢያሱ
የዛሬውን አቡነ
ገብርኤልን ስም
እየጠቀሰ “ገብርኤል
ናና” እያለ
ይንጫጫል። ከተመለከትኩት
በኋላ የዘመኑን
መንሱትነት አጉልቶ
አሳየኝና እጅግ
በጣም ገረመኝ።
ቀሲስ አስተራየ የሚተርኩለት ቢዲዮ አሁን ተነስቷል። ዳሩ ግን የአቡነ ግብርኤል ቁስለኞች ዛሬም አሉ። የቀሲስን ጽሑፍ እንድታነቡ እጋብዛችኋለሁ። አንጀታቸው እርር ድብን ብሎ እየተምሰከሰኩ፣ ስለዚህ ምስኪን ምዕምን ስለተበተነው የክርስቶስ
መንጋ ቀሲስ ይናገራሉ። እኛ የሎንደኖቹም አንድ ላይ ካልቆምን፣ ዕጣ ፈንታችን የአዋሳው ሊሆን ነውና ምዕምናን እንደምንጊዜው በአጭር ታጥቃችሁ ቁሙ!
አንድ እንጉርጉሮ ትዝ አለኝ።
አንጀቴ ተቆርጦ፣ ከሆዴ ከወጣ
ከእንግዲህ ሐኩሙ ምን ሊቀጥል መጣ?
ያውም እኮ ተዋጊዎቹ አቡናት፣ ቆርጦ ቀጣይ ሲሆኑ ታይተውም አይታወቁም።
ቆርጦ በጣሾ እንጂ!። ሎንደን ድረስ መጡ! እግዚአብሔር የአዋሳ ወንድሞችና እህቶችን ለቅሶና ዋይታ ለንደን ላይ ሊበቀል ነው መሰለኝ!!!
መስቀሉን ተቀብሎ መትረየስ ቢያቀብላቸው፣ ወያኔ በተሻለው ነበር። የኛ የአባ ተንኮሉ ጉዳይ መቼም ቢሆን አብቅቶሎታል። ድሮ ሲለመኑ፣ አሻፈረኝ ብለው ሁላችንንም አዋርደውናል! የቤተክርስቲያን ጉዳይ በቴዎክራሲ እንጂ በዲሞክራሲ አይፈታም ብለው ተራቀውብናል! “እኛም ነቅተናል፣ ጉድጓድ ምሰናል” ነው ያለችው ያቺ ደካማ የሆነች እንስሳ? እዚህ ላይ እሷም ከአባ ተንኰሉ ትሻላለች! ለመሆኑ፣ የአዋሳው የቤተክርስቲያን ምዕምናን ብተና አርኪተክት፣ አቡነ ገብርኤልና፣ የሲኖዶሱ ዕርቅ ሰላም ድርድር ብተና አርኪቴክት፣ አቡነ ቀውስቶስ[2] በጀግንነት፣ መስቀላቸውን መዘው ዘው ብሎ ሎንደን ሲመጡ፣ የአዋሳውን ብተና ከልምድ የተነሳ እዚህ ለንደንም እንደግማለን ብለው ወይስ ምን ሊቀጥሉ ነው የሚመጡት? ይኸ ሁሉ ፉክራቸው ግን ምን ይባላል። በተለይ ዋና አዋጊው ጄኔራል፣ አቡነ ገብርኤል ከአባ ትንኰሉ ጉን ለተሰለፉት እፍኝ ለማይሞሉ ዓይን አውጣ ወጣቶች የወያኔው መሰብሰቢያ ሥላሴ
ቤተክርስቲያን እልል እንዳስባሉላቸው ሰምንተናል። ድሮውንም ወያኔ ልብ የላችሁም። አሁን ቤተመቅደስ አስገብታችሁ
ያስቀደሳችኋቸው አባ ተንኰሉ፤ ለመኖኑ፣ እያንዳንዳችሁን ልብሰተክህኖአችሁን እያስወለቁ፣ እዚህ አትቀድሱም ብለው ያባረሯችሁም አይደል? የአዋሳው አዋጊ አቡን ጀኔራል፣ አቡነ ገብርኤል፣ “ደርሰንላችኋል! አይዞአችሁ” ያሉት ብለውም ሲደነፉ ተሰምቷል! ሊያዋጉን እንደመጡም አውቀናል። እንተያያለና!
አዋጊዝው ጀኔራል፣ አቡነ ግብሪኤል! እንዚያ ትላንትና እንደዚያ ያስጨበጨቡላቸው
የአባር ተንኰሉ ደንገጡሮች ስዶች፣ ታላላቆቻቸውን የማያከበሩ፣ ለዕድሜ ባለጸጋነት ደንታ ቢሶች መሆናቸውን ሳያውቁ ነው?! ለምን
ቢሉኝ፣ እነዚህ፣ አባ ተንኰሉ፣ ልብሰ ተክህኖ አስለብሰዋቸው፣ ሽማግሌዎችን፣ “አንተ አንድ ሐሙስ የቀረህ ሽማግሌ! አንተ የእንጭት
ሽበት!” ብለው እንዲሳደቡ ያሰለጠኗቸው ቡችሎቻቸው ናቸው። ሲሳደቡ ቪደዮ የተንሱ ቢዲዮም አለልዎት። በተለይ፣ በተልይ፣ እርስዎ
እንኳን ገና ሩጠው ያልጠገቡ ጎረምሳ ነዎትና ነገሩ ባያሳስብዎትም። አብረዎት ለመጡ ለአቡን ቀውስቶስ ይዘኑላቸው። እሳቸም በዕድሜ
“አንድ ሐሙስ ቀራችሁ” ከተባሉት አዛውንት ቢያረጁ እንጂ ወጣትነት አይታይባቸውም።
አሁን እንግዲህ ወደ ትንሳኤው እየተቀረበ ሰዓታት ቀርተዋል።
አባ ተንኰሉ፣ ቤተክርስቲያኗን እከፍታለሁ ብለው እንደፎክሩት፣ ሊከፍቱ፣ሳውንድ ሲስተሙን ከውስጥ ገብተው ሊያስተካክሉ ሞክረው አቀቶዋቸው፣
ኢንጂኒየር ጠርተው ከፍተው ሲያስገቡ ልጆቻችን ተጋፍጠዋቸዋል። ቢዲዮም ሊያነሷቸው ሲሞክሩ፣ በሯን ጥርቅም አድርገው ዘግተዋል። http://www.youtube.com/watch?v=wApxfUbVpkQ. ልክ እንደ ዓይጥና ድመት
እየትጠባበቅን ነው። እናንተ አዋጊ አቡናት፣ ለለበሳችሁ ልብሰ ተክህኖ ስትሉ፣ እዚያ ቦታ ድርሽ እንዳትሉ፣በዚህች በቀርች ሰዓታት
ውስጥ ትለመናላችሁ።
ልመናውን አልፋችሁ ከመጣችሁ፣ እናንተን አያድርገኝ! የአባ ተንኰሉ ደንገጦሮች!
ጽሑፌን ለአቡነ ገብርኤልና ለአቡነ ቀውስቶስ አድርሱልኝ።
ድል ግን የእግዚአሔር ነው።
No comments:
Post a Comment