Friday, 20 June 2014

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን የተግሳጽ ድምጽ

ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያ የተግሳጽ ድምጽ
ከሐመረ ኖኅ ኪዳነ ምህረት ምእመናን
75 South Bragg Street, Alexandria, Virginia 22312

ፍካሬ ዘጻድቃን በላዕለ ኃጣአንመዝ፣1)
በእርመኞች ላይ የሚሰነዘር ተግሳጽ፤
ሰኔ ፲፪ ቀን ፳፻፮ ዓ. ም.


 አባትና እናቶቻችን እርም (የታወቀ ኃጢአትታቅፈው ለጸሎት ወደ ቤተ ክርስቲያን ሊሄዱ ቀርቶ በቤታቸው ፍካሬ ዘጻድቃን ወዘኃጥአንየሚለውን ይደግሙ ዘንድ፤ ዳዊት ለመግለጥ አይደፍሩም ነበር። በመካከላቸው የተከሰተውን እርም ሳያወጡ እህል ውሀ አይቀምሱም ነበር። በዚህም ጥንቃቄያቸው ለሚያቀርቡት ጸሎት እግዚአብሄር ፈጥኖ ይመልስላቸው ነበር።

በንስሀ ፈጥነው ከእርም እንዲላቀቁ እያተጉ የሚመሯቸው ካህናት ነበሯቸው። ዛሬ ብዙ ካህናቶቻችን ከገባንበት እርም እንድንወጣ ሊመሩንና ሊያስተምሩን ቀርቶ፤ እንዲያውም ራሳቸው እርም አድራጊና አደራራጊ ሆነው ቤተ መቅደሳችንን የእርም መፍለቂያ፤ ክህነታቸውን የእርም ማስፈጸሚያ መሳሪያ፤ ህዝበ ክርስቲያኑንም የእርማቸው መከማቻ ደለል አድርገውናል።

የገባቸው አባቶች ካህናት፤ በኩዳዴ ጾም መርሀ ግብር ማጠቃልያ የስቅለት እለት ማታየይሁዳ ልጅና የልጅልጅ ይደምሰስእያሉ በመቋሚያቸው የጧፏን ጢስ ለማጥፋት የሚያከናውኗት የረቀቀች መንፈሳዊት ኪነት ለልማድ የሚያደርጔት አልነበረችም። ይህች ኪነት የምታሳየው በይሁዳ የገባው ክፉ መንፈስ በመካከላችን የገባበት ካለ ይደምሰስ ለማለት ነው። ከነ እርማችን ለበዓል ተሰሰብሰበን እልል ብንል፤ ሰባኪ ላቡ እስኪንጠበጠብ እንደ ግስላ ቢደነፋ፤ ከበሮ ተሸክመን ብናሸበሸብ ከስሜት ማስገንፈል አልፎ፤ የቤተ ክርስቲያን ድምጽ በመሆን ጸሎታችን ቅድመ እግዚአብሄር አይደርስም። ስለዚህ እኛ ዛሬ በመካከላችን ያሉ እርመኞች ንስሀ ገብተው የገባባቸው ክፉ መንፈስ ከነሱ እስኪወጣ ድረስ ከቤተ መቅደስ ይገለሉ በማለት እንደ ጧፏ ጢስ ይጥፋ በማለት ይህችን መንፈሳዊት ኪነት እናከናውናለን። ከሁሉ በፊት መቅደም ያለበት ይህ ነውና፤ እርሰዎም የቅድስት ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ተከታይና ተቆርቋሪ ከሆኑ፤ ከዚህ በታች እስከ የተዘረዘሩትን የቤተ ክርስቲያነዎን ድምጽ እየሰሙ እርመኞችን እየገሰጹ ላልሰማው ያሰሙእንደ ገለልተኛ ቆመው በመመልከትና እኔ ምን አገባኝ በማለት የእርም ተካፋይ አይሁኑ

የቤተ ክርስቲያን የተተግሳጽ

ኛ:-   “ለኩሉ ዘዐለወ፤ ወተቃረነ ንባበ መንፈሳዌ፡ ወተግህሰ እምነ ጽድቅ፡ውስተ ኩሉ ሃበ ሀለወ፡ ወለኩሎሙ ከሀድያን፡ ወሰብእ እኩያን፡ወሕጉላን፡ እለ አልቦሙ ሃይማኖት፡ ወዘዐለው ሃይማኖተነ፡ ወእለ ሤሙ ላዕሌሆሙ መገብተ ከሐድያነ ንኴንኖሙ በግዘት በኩሉ መዋዕል (ሃይ ምዕ ፻፩፡፳፫)

የሚዋሹ፤የሚሸፍጡ፤ራሳቸው ጠፍተው ለሰው ጥፋት ምክንያት የሚሆኑ፤እምነት የሌላቸው፤ቤተክርስቲያናችን ከምታስተምረው ጋራ የሚጋጩ ክፉ ሰዎች ከቤተ ክርስቲያን ይገለሉ። ይህ አይነት ባህርይ ያላቸውን እንደ ታደሰ ያሉትን ሰዎች ለንስሀ ከመገፋፋት ይልቅ በድፍረት ወደ አገልግሎት የሚልኩትና የሚተባበሩትም አብረው ከነሱ ጋራ ከቤተ ክርስቲያናችን ይገለሉ።ትላለች ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን።

ኛ፦   “የሀበነ ኪያሆሙ ለነዋህ መዋእል  በልቡና ያርትኡ ቃለ ሃይማኖት በንጹህ ዘእንበለ ነውር እስመ እሙንቱ ቀዋምያኒሃ ለቤተ ክርስቲያን” (፵፩፡፸፬)::

ከነቀፋና ከነውር ራሳቸውን ጠብቀው፤ እምነታችንን አቃንተው የሚያስተምሩ የቤተ ክርስቲያናችን ጠበቆች ናቸውና ረዥም እድሜ ሰጥቶ ያቆይልንከምንላቸው አባቶች ጋራ አባ ፋኑዔል (አባ መላኩ) ቁጥር የሚገቡ አይደሉም። ስለዚህ አባ ፋኑኤል ተልእኳቸውን ሊወጡ ቀርቶ እምነቱን ስለማያውቁት፤ በቅዳሴ ጊዜ ስማቸው ሊጠራ ይቅርና፤ ከቅድስት ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያናችን ቤተ መቅደስ መውጣት ያለባቸው ናቸው።ትላለች ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን።

ኛ፦   “እስመ ቤተ ክርስቲያን ወለደቶሙ  ለኩሎሙ በጥምቀተ ክርስትና። ወፈድፋደሰ ለዓቃብያነ ህግ እስመ ጳውሎስ ሐዋርያ ስምዐ ኮነ እንዘ ይብል ከመ እለ ተጠምቁ በክርስቶስ ፩ዱ እሙንቱ” አን፱፡ ቁ ፪፻፹)።

ለምእመናን እንቅፋት የሆነውን ግለ ሰብ፤ ከቤተ ክርስቲያን ለይተው የማስወጣት መብት የተፈቀደው ለሊቃውንት ብቻ አይደለም። በቤተ ክርስቲያናችን ተጠምቀው፤ ከሊቃውንቱ እየተማሩ መመሪያዋን የተረዱ ከሆኑ፤ በቅርብ ያሉ ምእመናንንም በከሀኑ ላይ የተረጋገጠ ስህተት ካዩ፤ ሊያስወጡት ይችላሉ። በዚህም መሰረት፤ ታደሰ መጀመሪያ ባካባቢው ባሉት ምእመናን ተወግዞ በሶስቱ ካህናት የጸደቀበት ውጉዝ ነው። ትላለች ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን።

ኛ፦   “እመሰ ኮነ እኩየ በሑረቱ ወተከስተ አበሳሁ ወጸንአ በዝ፤ድልው ለሊቃውንት ከመ ይፍትሁ ላዕሌሁ”( ፍ አ ፱፡ ቁ ፫፷፱)

ካህን በምእመናን ተመክሮ የምእመናንን ምክር አልቀበልም ብሎ በትቢት መንገድ በመቀጠሉ ምእመናን አንፈልግህም ካሉ፤ስህተቱን የቤተ ክርስቲያናችን መጻሕፍት መርምረውና ተርጉመው በመመዘን የቤተ ክርስቲያናችን ሊቃውንት የምእመናኑን ውሳኔ እንዲያጸድቁበት ቤተ ክርስቲያናችን ትፈቅዳለች። ተወጋዡ በስህተት ተወገዝኩ ካለ፤በይግባኝ እንዲታይለት በቅዱሳት መጻሕፍት ወደ ሚመራው ሲኖዶስ ጉዳዩን ማቅረብ አለበት። የተላለፈበት ውግዘት በስህተት ከሆነ፤ አውጋዦች ተወግዘው ይወጣሉ። በስህተት የከሰሱት ምእመናንም ንስሀ ይገባሉ። የተወገዘው ወደ ክህነቱ ይመለሳል። በዚህ መንገድ ካልሆነ በቀር፤ ታደሰ ምንጊዜም የተወገዘ ነው። ትላለች ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን።

ኛ፦   “ህቱ እምውስት ህዝብክሙ በአበይኖ፡ ኢይቁም፡ ወኢይህበር፡ ምስሌክሙ በጸልዮ፡ ኢዘማዊ፡ ኢሰራቂ፡ ኢሀሳዊ  ዘውእቶሙ ፭ቱ አክላባት እለ በአፍአ ይትኴነኑ አትናቴዎስ” (ቅ ቁ ፰ )

“ውሻ ወደ ትፋቱ ይመለሳል። የታጠበች እሪያም ተመልሳ በጭቃ ትንከባለላች” (፪ኛ ጴ ፪፡፳፪” ሲል ቅዱስ ጴጥሮስ የተናገረውን፤ቅዱስ አትናቴዎስም መሰረት በማድረግ፤ “በሚዛናዊ ፍርድ ውስጣችሁን ፈትሹ። ዘማዊ፤ ሌባ፤ አታላይ፤ ሸፍጠኛ የመሳሰሉት ባህርያት በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ሊከሰቱ ቀርቶ፤ ከክርስትና ውጭ ባሉ ሰዎች መካከል እንኴ መከሰት የሌለባቸው የውሻ ጠባያት ናቸው። ስለዚህ እነዚህ ባህርያት ያሉባቸው ሰዎች በጸሎት እንዳይተባበሩ ከመካከለችሁ ለዩዋቸው” ብሏል። ታደሰ የራሱን ትዳር አፍርሶ፤ ለሌላ ትዳር መፍረስ ምክንያት በመሆኑ ንስሀ ሳይገባ ቀድሶ ማቁረብ ቀርቶ፡ መቁረብ አይችልም። ወደ ቤተ መቅደስ እንዲገባ አይፈቀድለትም። በነዚህ ባህርያት የሚከሰሱና የሚወቀሱ ታደሰን የመሳሰሉ ሰወች ተወግዘው መውጣት አለባቸውትላለች ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን።

ኛ፦   “ርኩሳንሰ  እለ ያረኩሱ ይከውኑ ስዱዳነ እም አንቀጸ ዴዴ ዘምሥጢራት” (አረጋዊ መንፈሳዊ ምዕ ፴፭)

ራሱ በኃጢአት ወድቆ፤ በውድቅ ምሳሌነቱ ለህዝብ እንቅፋት የሆነ ካህን ንስሀ ይገባል እንጅ ቀድሶ ማቁረብ ቀርቶ፤ ሊቆርብ አይፈቀድለትም። እንዲያውም የክህነት አገልግሎት ከሚከናወንባት መቅደስ መድረስ የለበትም። ታደሰ የምእመናንን መንፈስ አቆሽሿል፤ ቤተ መቅደሳችንንም አርክሷልና ከክህነት አገልግሎት መገለል አለበት። ትላለች ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን።

ኛ፦   “አንተሰ ሕዝባዊ አልብከ ሥልጣን ከመ ትኮንኖ ለካህን በእንተ መስዋዕት” (ሰለ ፳፪፡፲፪

የቤተ ክርስቲያናችን መመሪያ ካህንን መቃወም ለምእመናን የማይፈቅድላቸው፤ ካህኑ ፩ዱ አብ ብሎ ስርአተ አምልኮ ከጀመረባት፤ በሰላም ወደ የቤታችሁ ግቡ እስኪሚባልበት ሰአት ድረስ ብቻ ነው። ለምእመናኑ እንቅፋት የሚሆን የታወቀ ስህተት የተገኘበት ካህንም፤ እንደማነኛውም ክርስቲያን በማነኛውም ሰአትና ቦታ በህዝበ ክርስቲያን መወቀስ፤ መከሰስ፤ መወገዝ አለበት። በቅዳሴዋ ሰአት ብቻ የተከለከለውም፤ ከቅዱስ አምልኮታዊ ተግባር ጋራ በመተሳሰሩ እንጅ፤ ለግለ ሰቡ ክብር አይደለም። ስለዚህካህን የፈለገውን በደል ቢፈጽም፤ አምላክ ይቅጣው እንጅ ህዝብ ካህንን መቃወም የለበትምየሚለው መታረም ያለበት በልማድ ሲነገር የኖረ ትልቅ ስህተት ነው።  

ከ፩ እስከ ፯ የተዘረዘሩትን የቤተ ክርስቲያናችን ተግሳጾች ሲጠቃለሉ፦

አባቶቻችን “ፍካሬ ዘጻድቃን ወዘኃጥአን” የሚለውን ህሊና ወቃሽ የሆነውን መዝሙረ ዳዊት በጸሎት መንገድ ለመድገም ከመዘጋጀታቸው በፊት፤ በውስጣቸው የገባውን እርም በገለልተኝነት ዝም ብለው በመቆም አይመለከቱም ነበር። የገባውን እርም ሳያወጡ ዳዊቱን በጣቶቻቸው ለመንካት አይደፍሩም ነበር። በመካከላቸው የተከሰተውን እርም ሳያወጡ እህል ውሀ አይቀምሱም ነበር። በዚህም ጥንቃቄያቸው ለሚያቀርቡት ጸሎት እግዚአብሄር ፈጥኖ ይመልስላቸው ነበር። እኛም በመካከላቸው የገባውን እርም እያስወጡ ዳዊት ደጋሚዎች እንደ ነበሩት እንደ አባቶቻችንና እናቶቻችን እንጅ፤ እርም ታቅፈን ዳዊት የምንደግም አነብናቢዎችና አሸብሻቢዎች ብቻ አንሁን።


እግዚአብሄር ጸሎታችንን ይሰማ ዘንድ፤ መጀመሪያ ታደሰን በመሳሰሉ አስመሳይ ሰዎች የገባውን እርም እናስወጣ። ደጋግ ካህናት አባቶቻችን በስቅለት ኃጢአት በደል የሚፈጽሙ በጻድቃን ማህበር በክርስቲያኖች መካከል አይቆሙም። እግዚአብሄር የጻድቃንን መንገድ ያውቃል የክፉወች መንገድ ግን ትጠፋለች።መዝ 14_6እያሉ የጧፋን ጢሲ እንደሚያጠፉ፤ እኛም እንዳባቶቻችን ባንደበታችን በመናገር፤ በቃላችን በመመስከር እንዲህ በማድረግ በታደሰና ታደሰን በመሰሉ ሰዎች በኩል የገባብንን እርማችንን ከመካከላችንና ከቤተ መቅደሳችን እናውጣ። ይህን በማድረግ ክርስቲያናዊ ድርሻችንን ሳንወጣ፤ በእርም የተጠቀለሉ ካህናት ፩ዱ ብለው እየቀደሱ ከነእርማችን ሆነን የእኛም ማስቀደስ፤ ለበዓል ተሰሰብሰበን እልል ብንል፤ ሰባኪ ላቡ እስኪንጠበጠብ እንደ ግስላ ቢደነፋ፤ ከበሮ ተሸክመን ብናሸበሸብ ስሜታችንን ከማስገንፈል አልፎ፤ በንስሀና በጸጸት እንደቀረበ ጸሎት ቅድመ እግዚአብሄር አይደርስም። እንዲያውም ክርስቶስዕውርን ዕውር ቢመራው ሁለቱም ወደ ገደል ይወድቃሉ (ማቴ፲፭፡፲፬)” እንዳለው፤ በእርም በታወሩ መስለው በገቡ ታደሰንና አባ መላኩን በመሳሰሉ ካህናት እየተመራን ገደል መግባት ነው። ገደል ከመግባታችሁ በፊት እርማችሁን አውጡ የሚለውም የቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን የተግሳጽ ድምጽ ነው።

ፓትርያርኩ ከመንግሥት ጥገኝነት ነፃ ለመኾን እንደማይችሉ ያምናሉ


ፓትርያርኩ ከመንግሥት ጥገኝነት ነፃ ለመኾን እንደማይችሉ ያምናሉ


በአብዮቱ መባቻ ዓመታት ከደርጉ ‹‹የለውጥ ሐዋርያት ›› ጋራም በቁርኝት ሠርተዋል ከደርግ ጋራ አብሮ በመሥራትና ደርግን በማውገዝ መካከል የሚታዩት የፓትርያርኩ የአቋም ጽንፎች ፀረ አማሳኝ መስሎ የአማሳኞች ከለላ ኾኖ የመገኘት ፍፃሜ ነው !!
(ፋክት መጽሔት፤ ቅጽ ፪ ቁጥር ፵፱፤ ግንቦት ፳፻፮ ዓ.ም.)

ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቤተ ክርስቲያኒቱና መሪዎቿ ከመንግሥት ጥገኝነት ነፃ ሊኾኑ እንደማይችሉና
መንግሥት በቤተ ክርስቲያኒቷ የአስተዳደር ጉዳይ ጣልቃ ቢገባ ሕገ መንግሥቱን እንደማይፃረር አቋም ይዘው መከራከራቸው
ተገለጸ፡፡

የፓትርያርኩ አቋም የተንጸባረቀው፣ ከአንድ ሳምንት በፊት በተጠናቀቀው የቅዱስ ሲኖዶሱ የርክበ ካህናት ምልዓተ ጉባኤ
ስብሰባ በሕገ ቤተ ክርስቲያን ማሻሻያ ረቂቅ ላይ ለቀናት ውይይት ባደረገበት ወቅት እንደነበር የስብሰባው የፋክት ምንጮች
ተናግረዋል፡፡

የሕገ ቤተ ክርስቲያኑ ማሻሻያ ለካህናት ስለተከለከሉ ተግባራት አስመልክቶ፣ ጳጳሳትና በቤተ ክርስቲያኒቱ በሓላፊነት ደረጃ ላይ
የሚገኙ ካህናት ከማንኛውም የፖለቲካ እንቅስቃሴ አባልነት ወይም አራማጅነት ነፃ መኾን እንደሚገባቸው ይደነግጋል፡፡
ስለ አንቀጹ አግባብነትና አስፈላጊነት በተሰጠ ማብራሪያ፣ ‹‹እስከመቼ ድረስ አንድ ላይ ተጣብቀን እንኖራለን፤ ሕገ መንግሥቱ
እንደሚለው ነፃ መኾን አለብን፤ ነፃ መኾናችንን ለማረጋገጥ ጳጳሳትና በሓላፊነት ደረጃ ያሉ ካህናት ከፖሊቲካ እንቅስቃሴ
አባልነትና አራማጅነት ነፃ እንዲኾኑ መከልከል አለብን፤›› መባሉ ተዘግቧል፡፡

ፓትርያርኩ አንቀጹን በመቃወም ‹‹ከመሐንዲስ፣ ከዶክተር ነፃ ልንኾን እንደማንችለው ከመንግሥት ጥገኝነትም ነፃ ልንኾን
አንችልም፤›› የሚል አስተያየት መስጠታቸው ተዘግቧል፡፡ አያይዘውም በሕገ መንግሥቱ የተደነገገው መንግሥት በሃይማኖት
ጣልቃ እንደማይገባ እንጂ በቤተ ክርስቲያኒቱ አስተዳደር ጣልቃ ቢገባ ድንጋጌውን እንደማይፃረር የሚያሰማ አቋም አራምደዋል
ተብሏል፡፡

አቡነ ማትያስ የቤተ ክርስቲያኒቱ ጉዳይ የመጨረሻ ወሳኝና ላዕላይ የሥልጣን መዋቅር ከኾነው ከቅ/ሲኖዶሱና አባላቱ ይልቅ
ከመንግሥት ጋራ አላቸው የሚባለው ያልተገራና ያልተገደበ ግንኙነት የሊቃነ ጳጳሳቱን ቁጣ ቀስቅሷል በተባለበት ኹኔታ ይህን
አቋም ማራመዳቸው እያነጋገረ እንደሚገኝ ምንጮቹ ጨምረው ገልጸዋል፡፡´´Patriarch Abune Mathias formerly known as Aba Teklemariam with Dergue’s Renewal committee members ሌሎች የፋክት ምንጮች በበኩላቸው፣

ፓትርያርኩ ከመንግሥት ጋራ አላቸው በሚል በተቺዎቻቸው የሚጠቀሰው ልክ ያልኾነና ያልተገራ ግንኙነት ጵጵስና ከመሾማቸው አስቀድሞ የሦስተኛው ፓትርያርክ አቡነ ቀሲስና ምክትል ልዩ ጸሐፊ በነበሩባቸው የአብዮቱ መባቻ ዓመታትም፣ የወቅቱን የሥርዓት ለውጥ በቤተ ክህነቱ ለማሥረጽና ተቃዋሚዎች (በተለይ ኢዲዩ) የሕዝብ ተቀባይነት እንዳያገኙ ወደ ስሜን ኢትዮጵያ ተጉዘው የፈጸሙትን ተግባር በአስረጅነት ይጠቅሳሉ፡፡´´

´´YeTahisas Girgir ena Mezezu በግርማዊ ቀዳማዊ ንጉሠ ነገሥት ዐፄ ኃይለ ሥላሴ መንግሥት ከ፲፱፻፵፰ – ፶፫ ዓ.ም.
በአገር ግዛት ሚኒስቴር የሕዝብ ፀጥታ ጥበቃ መምሪያ ሓላፊ ሌተና ኮሎኔል ወርቅነህ ገበየሁ ልዩ ረዳት የነበሩት አቶ ብርሃኑ
አስረስ ‹‹ማን ይናገር የነበረ… የታኅሣሥ ግርግርና መዘዙ›› በሚል ርእስ በቅርቡ ለኅትመት ባበቁት መጽሐፍ፣ የብፁዕ ወቅዱስ
አቡነ ማትያስ የፊት ስማቸው አባ ኃይለ ማርያም እንደነበር የጠቀሱት በስሕተት ይመስላል፡፡´´

በ፲፱፻፷፰ ዓ.ም. በወልቃይት፣ በፀገዴና በአርማጭሆ ቆላ ደርግን በመቃወም የተንቀሳቀሰውን የኢዲዩ ኃይል ለማቆምና ደገኛው
ከቆለኛው ጋራ እንዳይተባበር ለመምከር በደርግ ተመልምለው ወደ በጌምድርና ስሜን ጠቅላይ ግዛት ካቀኑት መካከል በወቅቱ
አባ ተክለ ማርያም ዓሥራት አኹን ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ አንዱ የቡድኑ አባል እንደነበሩ የመጽሐፉ አዘጋጅ ገልጸዋል፡፡
አባ ተክለ ማርያም በወቅቱ ‹‹የአቡነ ተክለ ሃይማኖት ፓትርያርክ ዘኢትዮጵያ አቡነ ቀሲስ፣ በኋላ አቡነ ማትያስ ናቸው››
የሚሉን ጸሐፊው፣ ከአባ ተክለ ማርያም ጋራ አለቃ ቀለመ ወርቅ(የቤተ ክህነት ደብተራ ይሏቸዋል) በቡድኑ ውስጥ የተካተቱት
‹‹ለሃይማኖት ነክ ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት እንደነበር›› አስፍረዋል፡፡

የሕዝብ ተሰሚነት አላቸው በሚል ከጠቅላይ ግዛቱ ሰባት አውራጃዎችና የጎንደርን ከተማ በመወከል ከተመረጡት መካከል
በወቅቱ የደብረ ታቦር አውራጃ ተወካይ አቶ(በኋላ ሊቀ ማእምራንና ደርግ የቤተ ክርስቲያኒቱን አስተዳደር በኅብተረሰብ ተሳትፎ
ላይ መመሥረት በሚል ሐዋርያዊ አገልግሎቷን በሶሻሊስታዊ መንፈስ ለመቃኘት ያቋቋመው ጊዜያዊ ጉባኤ ጸሐፊ) አበባው
ይግዛው አንዱ እንደነበሩ ተመልክቷል፡፡

´´Patriarch Abune Mathias with renewal committees ከዘመቻው ጉዳይ ጋራ በተያያዘ ስብሰባ የተደረገው
በጎንደርና ደብረ ታቦር ላይ ብቻ እንደነበር የሚገልጹት አቶ ብርሃኑ፣ ‹‹ኢዲዩ እየበረታ መጥቷል፤ እኛም በሰላም ተነጋግረን
ደገኛውንና ቆለኛውን እንዳይተባበር ማድረግ አልቻልንም፤›› በማለት ዘመቻው ስኬታማ እንዳልነበር ጠቅሰዋል፤ አያይዘውም
‹‹ኹለቱ የሃይማኖት ሰዎች የተመለሱት አንድም አስተያየት ወይም ማብራሪያ ሳይሰጡ ነበር፤›› ብለዋል፡፡ (ገጽ 400 – 421) ´´
በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የታሪክ ምሁር ዶ/ር ውዱ ጣፈጠ ካሱ ለዶክትሬት ዲግሪ ማሟያ በሠሩት ጥናት፣ የሦስተኛው
ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ተክለ ሃይማኖት አቡነ ቀሲስ የነበሩት አባ ተክለ ማርያም ዓሥራት (በኋላ ብፁዕ አቡነ ማትያስ)
ደርግ ‹‹የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን የለውጥ ጊዜያዊ ጉባኤ›› (the EOC provisional council or Renewal
Council) በሚል ያቋቋመው ጊዜያዊ ጉባኤ አባል የነበሩ ባይኾኑም የምክር ቤቱ ሊቀ መንበር ከነበሩት ዶ/ር ክነፈ ርግብ ዘለቀ
ጋራ በጥብቅ ቁርኝት መሥራታቸውን ገልጸዋል፡፡

ጊዜያዊ ጉባኤው በነሐሴ ወር ፲፱፻፷፰ ዓ.ም. በጊዜያዊ ወታደራዊ አስተዳደር ደርግ ምክትል ሊቀ መንበር ኮሎኔል አጥናፉ አባተ
ቀጥተኛ መመሪያና ቁጥጥር የተቋቋመ ነበር፡፡ ከኹለተኛው ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ቴዎፍሎስ ጋራ ቀጥተኛ ግጭት
ውስጥ የገባው ጊዜያዊ ጉባኤው፣ ቅዱስነታቸው በአራት መዋቅሮች(የፓትርያርክ ልዩ ጽ/ቤት፣ የስብከተ ወንጌልና ማስታወቂያ፣
የሰበካ ጉባኤ ማደራጃ፣ የውጭ ጉዳይና ልማት ኮሚሽን) የቤተ ክህነቱን አስተዳደር ለማጠናከር ያቋቋሙትን ኮሚቴ በመጋፋት
ለውጥና መሻሻል ያመጣል ያለውን የራሱን ባለአምስት ኮሚቴዎች (የሕግና አስተዳደር፣ የስብከተ ወንጌልና ትምህርት፣
የኢኮኖሚ ጉዳዮች፣ የታሪክና ባህል ጉዳዮች እና የአቤቱታ ሰሚ) መዋቅር ዘርግቷል፡፡

ከጊዜያዊ ጉባኤው ጋራ ያልተግባቡትና የማሻሻያ መዋቅሩን ያልተቀበሉት ቅዱስነታቸው በወርኃ የካቲት ፲፱፻፷፰ ዓ.ም. ጊዜያዊ
ጉባኤው ለደርጉ ባቀረበው የክሥ ሪፖርት ‹‹ሲጠበቅ የቆየ ፍርድ›› በሚል ዐዋጅ ከመንበረ ፕትርክናው ተገፉ፡፡ በቅዱስ
ሲኖዶሱና በጊዜያዊ ጉባኤው መካከል ሽኩቻ የተካሔደበት ቀጣዩ የፕትርክና ምርጫ በጊዜያዊ ጉባኤው በኩል ታጭተው
የቀረቡትን ሐዋርያዊውን ባሕታዊ አባ መላኩ ወልደ ሚካኤል – ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ተክለ ሃይማኖት በመንበሩ ሠየመ፡፡ጊዜያዊ ጉባኤው በኤጲስ ቆጶሳት ምርጫና ሹመት፣ በአህጉረ ስብከት ዝውውር እንዲሁም የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ
አስኪያጅ ሹመት በቀጥታ ይቆጣጠር የነበረ ከመኾኑም በላይ ከደርጉ ጋራ እጅና ጓንት ኾነው በአባልነት የሠሩ አባላቱ በዋና
ሥራ አስኪያጅነትም ተቀምጠው ነበር፡፡ ጵጵስና እስኪሾሙ ድረስ የቅዱስነታቸው አቡነ ቀሲስና ምክትል ልዩ ጸሐፊ የነበሩት
አባ ተክለ ማርያም ዓሥራት ከጊዜያዊ የሃይማኖት ጉባኤው ጋራ በጥብቅ ቁርኝት መሥራት ብቻ ሳይኾን ወደ ስሜን ኢትዮጵያ
ተነቃንቀው ስለ አብዮቱ ካስተማሩና የሥርዓት ለውጡን የሚቃወሙ እንደ ኢዲዩ ያሉ ኃይሎች የሕዝብ ተቀባይነት እንዳያገኙ
ከቀሰቀሱ የደርጉ ‹‹የለውጥ ሐዋርያት› አንዱ ነበሩ፡፡

By Mmesay belay getachew

Obtained from: https://ia902504.us.archive.org/5/items/PatriarcInAddis/Patriarc%20in%20Addis.pdf

Tuesday, 17 June 2014

ማስተካከያ

ማስተካከያ 
ስህተት የተዘዋወረውን ለማስተካከል 
ለንደን  (ገጽ 9 የሚገኝ ዉን )  

በቅርቡ “በሳጥናኤል መንገድ ነጎዱ” በሚል ርእስ ባቀረብኩት ጽሑፍ ለንደን ላይ ባተትኩት አንቀጽ
ላይ፤ የአቡነ እንጦንስ እና ዲዮስቆሮስ ስም በመጣለፍ ከህጻን ጋራ የተነሱት ፎቶ የሚለው አረፍተ ነገር፤ ከዚህ
በታች በግልጽ እንደተቀመጠው፤ የአቡነ እንጦስ ሳይሆን የሳቸው ቡድን ተካፋይ የአቡነ ዲየስቆሮስ ነው። ከዚህ
በታች ይመልከቱ።

ጉዳዩ በሕዝበ ክርስቲያኑ ዘንድ ትኩረት አግኝቶ ለቤተክርስቲያኑ አንዳች መፍትሔ ያመጣ ይሆናል በሚል ሐሳብ ገበናቸውን መግለጽ አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል። ምናልባት ልብ ገዝተው ንስሃ ይገቡ ይሆናል።




የአፋልጉኝ ማስተወቂያ  ይህ  ልጅ  አያሳዝንም?  …….  አያሳሳም?  ……  እርሱ ጠፍቶ  እንዳይመስለዎ።  አባቱን  ማግኘት  ባይችልም
አባቱን  ይፈልጋል፤  እንደሌላው  በህግ  እንደተወለደ  ልጅ
ከእናቱ ጋር አባቱን ማግኘትና አብሮ ለመኖር አልታደለም።
ያለው  አማራጭ  አባቴ  ማነው?  እያለ  በመጠየቅ  ማደግ
ነው። ማን ያውቃል? የማንነት ጥያቄው አንድ ቀን ምላሽ
ያገኝ ይሆናል።

ያንዱ ላንዱ ተዘዋውሮ በመቅረቡ እርማት ለመስጠት እንጅ፤ አቡነ እንጦስ ከዚህ ውጭ ናቸው ማለት አይደለም።

ወንድሙ መኮንን ያቀረቡትን ከዚህ በታች ተመልከቱ።

“በኮልፌ ቀራንዮ የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ላይ እማሆይ ምግቤ ታከለ የተባሉ ከብጹዕ አቡነ እንጦንስ ጋርእንደባልና ሚስት ኖረዋል በማለት በጠበቆቻቸው አማካኝነት የንብረት ጥያቄ ክስ አቅርበው ...”

“አባ”እንጦንስን ለማጋለጥ ስል ከፍርድ ቤት ያገኘሁትን ጉድ እንዳለ ብዘከዝክ የቤተክርስቲያኔን ገጽታ በድንገት እንዳልጎዳ ሳስቼ፣ ለጊዜው አቆይቼዋለሁ።” ይላሉ። ስለዚህ እኒህ ሰው  አባ እንጦንስ ቀሪ ዘመናቸውን ከህዝብ ገለል ብለው በንስሀ መጨረስ

ሲገባቸው፤ ህጸጽ ያልተገኘበትን ህዝባዊ ክህነት ማውገዝ ቀርቶ ከዚህ በታች መመሪያችን እንደሚያዝዘው ወደ ቁርባኑ መቅረብ አይገባቸውም።




ቅዱስ ጳውሎስ “ስለምናገለግለው ስጦታ ማንም እንዳይነቅፈን እንጠነቀቃለን (፪ኛ ቆሮ ፰፡፳) እንዳለው፤ ከነዚህ እንቅፋቶች ባንዷ ተሰናክለው ለህዝብ እንቅፋት እንዳይሆኑ  የጰራቅሊጦስን ስጦታ የተቀበሉ መንፈሳውያን መሪዎች፤  እጅግ ለጠነቀቁ ይገባቸዋል።

ለምሳሌነት ብቁ ጳጳስ ነኝ የሚል ሰው ቀርቶ፤ ያልተፈቀደውን ይቅርና “የተፈቀደው ሁሉ ግን አይጠቅመኝም”፩ኛ ቆር ፭፡፲፪) ብሎ ራሱን የመግታት መንፈሳዊ ሃይል ሊኖረው ይገባል። የጵጵስና ዋና ተልእኮ መመሪያችን “ወኩኖሙ አምሳለ ለምእመናን በቃል፡ወገድል፡ወበፍቅር ወበሃይማኖት ወንጽህ”( ፭፡፻፲፬) ብሎ በሚያዝዘው መሰረት፤ መንፈስ ቅዱስ ከሚጠላው ለመሸሽ፤ የሚወደውን በመከተል ቅዱስ አትናቴዎስ “ኢይቁም ወኢይህበር ምስሌክሙ በጸልዮ ኢዘማዊ ወኢቀታሊ ኢሰራቂ ወኢሀሳዊ ዘውእቶሙ ፭ቱ አክላባት እለ በአፍ ይትኬነኑ (አት ፰) የሚለውን ለማስተማር ነው።

ዝሙት የውሻ ጠባዮች ናቸው ከተባሉ አንዱ ነው። እሳቸው በዚህ ነገር ፍርድ ቤት የደረሰ ነገር ተሸክመው ሳለ፤ የሰሩት በደል ሳያንስ  ከዚያ አልፈው ተርፈው፤በሚያስወግዝ በነገረ መለኮት ጥሰት፤ እንቅፋት ሆነውብናልና ይወገዱልን የሚል ክስ የሚገለግሉት ህዝብ  ሳያቀርብባቸውና  ሳይረጋገጥባቸው፤ አባ እንጦንስ ካህኑን ማውገዝ ቀርቶ ማዘዝ አይችሉም። ይህም ራሱ ከዝሙት ከስርቆትና ከነፍስ መግደል ያለነሰ በደል ነው።

 “ወለዘኢአከሎ ክህደቱ ባህቲቱ እስከ ያወጽኦ ለካልዑ እምሃይማኖቱ ወኮነ ምክንያተ ለክህደቱ ይኩን
ንስሓሁ ፈድፋደ”( አ ፳፡፯፻፷) ራሱ የሰራው በደል አልበቃው ብሎ በሚሰራው ስህተት ለሌላው እንቅፋት
ለሚሆብ ሰው፤ ንስሀው ከባድ ይሁን።”ይላል።በስም መጣለፍ በተደረገው ስህተት አንባቢን ይቅርታ
እጠይቃለሁ።

ቀሲስ አስተርአየ