Tuesday, 28 June 2022

ወይ ነገር መፈለግ፣ ወይ ዱቢ! ወይ ዱቢ!

ከወንድሙ መኰንን፣ ኢንግላንድ 26 June 2022

መግቢያ

ከአራት ዓመት በፊት የመጣው ለውጥ የተሻለ ነገር ይዞ ቢመጣ ብለን፣ ብዎቻችን ጓጉተን ነበር። ነገሩ ከድጡ ወደማጡ ሆነ። አሁንስ ግፉ በዛ! ማርም ሲበዛ ይመራል ይባላል። የኢትዮጵያ ጠላቶች ድሮም፣ ኢትዮጵያን የማጥፋት ጅማሮ፣ አማራን ከማጥፋት ቅዠታቸው ጋር ይያዛል። ኢትዮጵያን ለማጥፋት ሲባል ብቻ፣ የሌለ ምክንያት እየፈጠሩ፣ “አማራ” ተብሎ በተፈረጀ ምስኪን ብሔር ላይ ሲዘምቱበት ምዕት ዓመታት ነጎዱ። ያንን ለመገንዘብ፣ Abyssinia: The Powder Barrel  ተብሎ በBaron Roman Prochazka  የተጻፈውን መጽሐፍ ማንበብ ይበቃል። ጣሊያንም ያደረገው ያንኑ ነው። ደርግም ሲመጣ አቆርቋዥ በመባል ብዙ አማሮች ተፈናቅለዋል። ወያኔም ያንኑ ነበር ሥራ ላይ ያዋለው። አሁንም እያየነው ነው።

እስቲ እግዚአብሔር ያሳያቸው፣ “የኦሮሞ ደም ደሜ ነው” ብሎ ከወንድሙ ጎን ለቆመው አማራ ይኸ ይገባዋልግፍ ነው! የግፍ ዶፍ! የወያኔው ኢህአዴግም ሆነ፣ የኦህዴድ ብልጽግና ትኩረት፣ አሳምኖም ይሆን አወናብዶ፣ ያው የፈረደበትን አማራ የተባለ ብሔር ላይ መዝመት ሁኗል። አትኩሮ የ፣ ሦስት ነገሮችን ያስተውላል። ስልታቸው ተመሳሳይ ነው። ጠላቶቹ፣ አማራና ኦርቶዶክስ ሀማኖት ተከታይ ካገኙ፣ ሰኔና ሰኞ ገጠመላቸው ማለት ነው። የበደኖን፣ የአርባ ጉጉን፣ የወተርን ተውት ትንሽ ራቅ ብሏል። በቅርቡ የሆነውን እንይ! ከኬኛዎቹ አንዱ “ተከበብኩ” ብሎ ሲጣራ፣ ምክንያት ብቻ ይፈልግ የነበረው መንጋ፣ ብድግ ብሎ ስንቱን አማራ ነበር የጨፈጨው? ይኸ አንዱ ነው። ሌላው፣ አማራም ባይሆን፣ ኦሮሞም ይሁን ሌላ፣ ኦርቶዶክስ ሀይማኖት ተከታይ ከሆነ፣ እሱም አብቅቶለታል። ከአማራው ጋር ዕምነት ይጋራላ! ሰበብ ፈላጊዎቹ፣ ታዋቂ የኦሮሞ ዘፋኙን፣ ሀጫሉ ሁንዴሳን፣ ሰበብ ሲፈልጉ፣ ያልሆነ ነገር አናዘውት፣ እንሱው በግፍ ገድለውት፣ “ገደሉት” አሉና ግርር ብለው ተነስተው ስንቱን ጨፈጨፉት[1]። ያ ሰበብ ስንቱን አማራና ኦርቶዶክስ ሀይማኖት ተከታይ የሆነውን ለመጨፈጨፍ ዕድል ከፈተለተላቸው? በያለበት ማረድ አልበቃ ብሏቸው፣ ያወደሟት ሻሻማኔ እንደ ሰደሞና ገሞራ ስትታወስ ትኖራለች። ዝዋይ ከተማ ታርደው ደማቸው ደመከልብ የሆኑት ቤተሰብን ማን ይፋረድላቸው?  የሚገርመው፣ ወያኔ አሳዳቸው፣ ኢንግላንድ የደረሱ ጽንፈኞች፣ ለንደን ዘልቀው የንጉሥ ኃይለሥላሴን ሀውልት  አፍርሰዋል። ሶስተኛው፣ አንድ ሰው እስላምም ቢሆን በአማራነት ከተፈረጀ ለመጨፍጨፍ ተጋላጭ ሁኗል (ድሮ፣ ድሮ እንኳን፣ አማራ ማለት ክርስቲያን ማለት ነበር አሁን ግን ዘር አድርገውት አርፈውታል)። በዚህች ሳምንት እንኳን በድሮው ወለጋ፣ ጠቅላይ ግዛት/አስተዳደር ግምቢ ውስጥ የታረዱት 1,600 ንጹሀን ሰዎች የሚያረጋግጠው ያንኑ ነው። በሙሉ እስላሞች ነበሩ ማለት ይቻላል። ምን በድለው ነው አንደበግ አጋድመው ያረዷቸው? አይጥ በበላ ዳዋ ተመታ ይባላል። ጥላቸው ከመንግሥት ጋር ከሆነ፣ እንደጀግና ለምን ጦሩን አይፋለሙም? ሕጻናትንና ሴቶችን መጨፍጭፍ ቦቅቧቃ ፈሪነት ነው። የጥላቻ ጥግ በዛ! በዛ! በዛ!

የመንግሥት የመጀመሪያው ኃላፊነት የዜጎችን ደኅንነት መጠበቅና ማስጠበቅ ነበር። ያንን የማያስፈጽም መንግሥት ፋይዳ የለውም! መንግሥት ተቀዳሚ ተግባሩን ለማስፈጸም በየክፍለ ሀገሩ ተልዕኮውን የሚያስፈጽሙ ታማኞችን ይሾማል። ልማቱም ብልጽግናውም ዚጎቹ በሰላ ወጥተው የመግባታቸው መብት ሲረጋገጥ ነው ትርጉም የሚኖረው። ዜጎቹን እኩል የማይንከባከብ መንግሥት ከፋፋይ ገዥ እንጂ ለአቅመ መንግሥት የበቃ አይደለም። አሁን ያለን መንግሥት “አፈናውንና፣ ግድያውን ታገሱኝ፣ ነገ ብሩህ ተስፋ መጣል” እያለ ያጃጅለናል ደረቅ የቃላት ፍትፍት ያጎርሰናል። ላም አለኝ በሰማይ ወቱቷን የማላይ! ይኽቺ “ዶር ማታ ዶሮ ማታ” የምትሏት ቀልድ ምንም እስኪመሽ አላደረሰችንም። የቻይናው ባምቡ (ቀርከሀ መሆኑ ነው መሰልኝ) የዛሬ 25 ዓመት እስኪ ደርስ የስንቱ ምስኪን አንገቱ መቀላት አለበት?

የመደመር ፍልስፍና ሲገመገም

የዛሬ አራት ዐመት ጨፍጫፊው ወያኔ በህዝብ ቁጣ ስንገላገለው እፍወይ ልንል አሰፍስፈን ነበር። ዶክተር ዐብይ አህመድ አሊ “በቲም ለማ” ታጅበው ወደ ሥልጣን ሲመጡ ብዙ የተስፋ ቃል ሰንቀውልን በደስታ አስፈንጥዘውን ነበር። የሞት ፍርድ የተፈረደባቸውንና ዕድሜ ልክ የታሠሩትን ጨምሮ ብዙ እሥረኞችን ፈተውልናል። አመሰገናቸው! ወያኔ ለሁለት የከፈለችውን የኦሮቶዶክስ ቤተክርስቲያንን አስታረቁ። ስደተኛውንም ፓትርያርክ በአውሮፕላናቸው ይዘዋቸው ተመለሱ። የተከፋፈለውንም የእስልምና ዕምነትን ተከታይ አስታርቀው አስማሟቸው። እነዚህንና የመሳሰሉትን ደግ ሥራዎች ስለፈጸሙ አለማምስገን ንፉግነት ነው። ለአሥርት ዓመታት በባድሜ ምክንያት ለጦርነት ተፋጥተው የኖሩትን፣ ሌላ አገር በሆነችው ኤርትራና ኢትዮጵያን አስታርቀው ሰላም አውርደዋል። ለዚህ ስኬታቸውም የመጀመሪያው የኖቤል ሽልማት ተቀባይ ኢትዮጵያዊ በመሆናቸው አኩረተውናል። 

ዳሩ ምን ያደርጋል፣ የተከተሉት መሥመር ጋት አላኬዳቸውም። አሮጌውን ስልቻ ይዘው ነበር ወደ አዲሱ የወይን ጠጅ የተጠጉት። የ”መደመር” ፍልስፍናቸው ወደፊት የሚያራምድ ሳይሆን “ባለህበት ርገጥ” ሁኗል። አንዳንዴም ፊትህን “ሳታዞር ወደ ኋላ ሂድ” ዓይነት ትዕዛዝ ሁኖባቸዋል። “መደመር” ጅብ አላምዶ የቤት እንስሳ አያደርግም። እንዲያውም መደመር ለወያኔ በሰላም ወደ መቀሌ የመመልስና፣ የመደራጀት ዕድል ፈጥሮ፣ ደንበር ይጠብቅ የነበረውን የኢትዮጵያን መከላከያ ቅርጥፍ አንድርጎ እንዲበላ ረድቶታል። መደመር ጦርነት አላስቀረም። ጦርነት አስክፍቶ ህዝብ አልቋል፣ ንብረት ወድሟል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ አሊ ያልተረዱት ነገር ቢኖር፣ ቃል የገቡልንን ራዕይ ተግባራዊ ለመድረግ፣ የወያኔን በዘር ከፋፍለህ ግዛ ሕገ-አራዊት ቀዳደው ሳይጥሉት፣ በመደመር እሳቤ በብታቸው እንዳቀፉ፣ ቋንቋን መሠረት ባደረገ የዘር የክልልን ሊያስተዳድሩን መሞከራቸው ነው! እባብ ለመደ ተብሎ በኪ ይያዛል እንዴ? መደመር አልሠራም። ጥጃና ጅብ አይደመርም!

አንድ አባት “ቀኝህን ሲመቱህ፣ ግራህን አዙርለት” በሚል አርዕስት ሰበኩ። ከትምህርቱ በኋላ፣ አንድ ጋጠ ወጥ ጠጋ ብሎ በጥፊ አጮላቸው። በደመ ነፍስ የተመታውን ፊታቸው በእጃቸው እያሻሹ ደንግጠው ሳያስቡት ሌላውን ደገማቸው። ብድግ አድርገው ከመሬት አጣብቀው እስኪበቃው ወቁት። ደሙን እየዘራ፣ “አባ ግብዝ ነዎት። ያስተማሩትን ተግባር ላይ አላዋሉም” አላቸው። እሳቸውም፣ “ልጄ፣ ሁለቴ መተኸኝ የለ?” አሉት። “አዎን” አላቸው። ሦስተኛ ጉንጭ እኮ የለኝም አሉት። ወዳጄ ልቤ፣ በ“ጉንጭህን” አዙርለት” አገር አትተዳደርም። ባለጌ ከድክመት ይቆጠርብሀል። መደመር የነበረውን ክፉ አስተዳደርን ማስቀጠል ከሆነ ጉልቻው ተቀያየረ እንጂ ለውጡን አላጣፈጠም። እንዲያውም የህዝቡ ሕልውና ወደባሰው አዘቅት ወረደ። ሰው የራሱን ፊት ያለመስታወት ማየት አይችልም። መስታወት ደሞ፣ ነጻ ጋዜጠኞችና ተቺዎች ናቸው። ዛሬ እረኛ የለም! ድክመታቸው ሊነገራቸው ይገባል።

የጠቅላይ ሚኒስትሩ የፓርላማ ጥያቄና መልስ

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሻሻ ይወለዱ እንጂ አራዳ ናቸው። ክ15 ዓመታቸው ጀምሮ፣ ወያኔ ስላሳደጋቸው ዘዴዋን በልተዋታል። የጠቅላይ ሚኒስትሩ የፓራላማ ጥያቄና መልስ በጥሞና እየጎመዘዛም ቢሆን ማዳመጥ ጠቅማል። ፈገግ ካደረጉኝ ንግግራቸው አንዱ፣ ወደሥልጣን ሲመጡ በፍቅር ካከነፈንላቸው ከኢትዮጵያ ፍቅር ባሻገር አንዱ፣ “ከእንድግዲህ ሳናጣራ ማንንም አናስርም” ማለታቸው ነበረች። አሁን ግን ሽውድውድ ሲያደርጉን፡ ያለህግ ስለታፈኑት ሲጠየቁ፣ “እያጣራን እንፈታቸዋለን” ብለውን እርፍ! እ? ሌላው፣ አባባላቸው እስካሁን ኦሮሞ በኢትዮጵያ ውስጥ እንደሁለተኛ ዜጋ እራሱን ስለሚቆጥር፣ አሁን፣ አሁን ቀና ቀና ማለት ሲጀምር “አካም አካምን” አብዝቷል አሉን። ኧር ጉድ! እንዴ! ታሪክ አያውቁም ወይስ ሊሸውዱን እየሞከሩ ነው? ዕውን “አማራ” የግራኝ አህመድን ወረራ ተከትሎ፣ የኦሮሞ ወራሪ ጎንደርን ከያዛት በኋላ ሥልጣን ላይ ወጥቶ ኢትዮጵያን ብቻውን አስተዳድሯት ይታወቃል? የመንግሥቱ አንጋሽ አውራጅ ማን ሆነና! ነገሥታቱስ ቢሆኑ ማንኛቸው ነበሩ ንጹሀን አማሮች? የድሮውን አጼ ባካፋን ተዋቸው፣ የጉዲሳው የልጅ ልጅ ልጅ ኃይለሥላሴም ቢሆኑ፣12.5% ብቻ የአማራ ደም ቢገኝባቸው ነው። እናታቸውም፣ ወይዘሮ የሺመቤት አሊም ቢሆኑ፣ በእናታቸው በኩል ምናልባት ክንጉሥ ሳህለ ስላሴ የወረደች ከውሀ የቀጠነች ደም ብትኖርባቸው እንጂ፣ የወረኢሉው ኦሮሞ፣ የሼህ አሊ ልጅ ነበሩ። ከየት አመጣህ አትብሉኝ። የባልቤቴ አያትና ወይዘሮ የሺመቤት የእህትማማች ልጆች ነበሩ። የቤተሰቤን ታሪኬን ነው የማወራችሁ፣ ብትፈልጉ! እሱም ይቅር። ለመሆኑ፣ የትኛው አማራ ነው ከ50 ዓመታት ወዲህ ኢትዮጵያን አስተዳድሯት የሚያውቅ? የኮሎኔል መንግሥቱ ኃይለማርያም መንግሥት? አታስቁኝ? የአቶ የመለስ ዜናዊስ መንግሥት አማራ መሆኑ ነው? ኃይለማርያምን እንዝለል። ሚስቱ ያስኮረፈችው የኦሮሞ ወንድ ሁሉ፣ እንደ ሁለተኛ ዜጋ እራሱን ቆጥሮ ምስኪን አማራ መጨፈጨፍ መተከዣው ከሆነ ነገር ተበላሽቷል። መደመር ስህተቶችን አባባሳቸው እንጂ አላረማቸውም። 

ኢትዮጵያ ውስጥ ኦሮሞ ሁለተኛ ዜጋ ሁኖም አያውቅ? ይህቺ ናት ጨዋታ! ኧረ ተው ክቡር ጠቅላይ ሚንስትር! ለመሆኑ፣ ጽንፈኛ የኦሮሞ ሊህቃን የሚኮንኗቸው የዳግማዊ ምኒልክ በነማን ዕርዳታ ነበር ለንግሥና የበቁት? የወሎዋ ኦሮሞ ንግስት ወርቃይትም አልነበርች እንዴ ከአጼ ቴዎድሮ ቤተመንግሥት ጠፍተው ሲኮበልሉ፣ አቅፋ ደግፋ ወደ ሸዋ ያሻገረቻቸው? እንዲያው ምኒሊክ አባታቸው ኃይለመለኮት ይሁኑ እንጂ፣ እናታቸውስ ማን ነበሩ? እሱም ይቅር፣ የጦር አበጋዞቻቸው እነማን ሆኑና ነው ኦሮሞ ሁለተኛ ዜጋ የሆነው? ጠቅላላ ኦሮሞዎች አልነበሩም እንዴ የምኒሊክ ቤተመንግሥት አራጊ ፈጣሪዎች? እንዲያው የአድዋን ጦርነትና ድል ልተውና እነማን ነበሩ፣ እምቦቦ ላይ በተደረገው ጦርነት ለምኒልክ ተዋግተው ጎጃምን የመቱላቸው? መቶ በመቶ በራስ ጎበና ዳጬ የሚመራ የኦሮም ፈረሰኞች አልነበር እንዴ ምድሪቱን ቀውጢ ያደረጉት? ንጉሥ ተክለሀይማኖትን አሸንፈው ማርከው ለአጼ ምኒልክ አላስረከቡም[2]? ለመሆኑ ጎጃምን አስገብረው፣ ቤጌምድርን አስገብረው እስክ ትግራይ ድርስ ዘልቀው ሰጥ ለጥ አድርገው ያስገዙት የኦሮሞ ጦረኞች አልነበሩም? ኦቦ ሌንጮ ለታ እንኳን ዛሬ ላይ ሰከን ብለው ከሚኒሊክ ሚኒስትሮች አራት ኦሮሞ፣ ሁለት ከጉራጌ፣ ሶስት ከደቡብ፣ ሁለት ከአማራ መሆናቸውን ነግረውናል[3] ምኒልክ የተረፋቸው ንሥ መባሉ ብቻ ነበር ልቀጥል? ለመሆኑ ተወዳጇ፣ የምኒልክ ባለቤት፣ እቴጌ ጣይቱስ ቢሆኑ፣ ጎንደር ይወለዱ እንጂ የየጁ ኦሮሞስ ባላባት ትውልድ አልነበሩም?  እንዲ ወይ እንደ 15ው ክፍለ ዘመን ተመልሰን በገዳ ሥራዓት እናስተዳራችሁ ካላሉን በስተቀር፣ ሁለተኛ ዜጋም ሁነውም አያውቁም። ሁሌም አንደኛ ናቸው ።

እንዲያው ደፈር ልበለና፣ አማራ የተባለ ብሔር ምናልባት የአማርኛ ቋንቋ የኢትዮጵያ የሥራ ቋንቋ ከመሆኑ በስተቀር ለጎጃሜው፣ ለጎንደሬው፣ ለወሎዬው እንዲሁም ለሸዌው፣ ከድህነት ወጭ አንዳችም ነገር ጠብ ያለለት ነገር የለም። ቁንቋው ደሞ አገር አስተዳደሩ ላይ ከግዕዝ ቀጥሎ የመንግሥት ቋንቋ በመሆኑ፣ ከግዕዝ በወረሰው የግዕዝ ሥነጽሑፍ ስለዳበረ እንጂ በሌላ ጉዳይ አልነበረም። ወደሥልጣን የመጣው ሁሉ አማርኛ የሚቀለው ቋንቋ በመሆኑ፣ እስከወያኔ ዘመን ድረስ ዘለቀ። እንዳዛሬ የላቲን ፊደሎች ሾርባ ቀርጾ መጻፍ ሳይችል፣ አማርኛ እየተጠቀመ ሲገዛን የኖረው የኦሮሞ ሊህቅ ነው። በቀደማዊ ኃይለሥላሴም ዘመን ቁልፍ ቁልፍ ቦታዎችን የያዙ ኦሮሞዎች ነበሩ። የክብር ዘበኛ ጄኔራሎቹ በአባዛኛው ኦሮሞዎች ነበሩ። አየር ኃይሉን ተቆጣጥረውት የነበሩት፣ የወለጋ ኦሮሞዎች ነበሩ።

እንዲያ የሚገርመኝ፣ የኦሮሞ ጽንፈኛ አማራው ጨቆነኝ እያለ ያማያላዝነው ከምን ተነስቶ እንደሆነ አይገባኝም። ኦሮሞ መሀል ተወልጄ በማደጌ፣ አብሮ አደጎቼና እኔ መሀል የተለየ ነገር አልነበርም። ሁላችንም ከድሀ ገበሬ የወጣን ልጆች ነበርን። የለበሳትን ልብስ እንኳን ሳይቀይር አፈር ገፍቶ የሚኖረው አማራው ነው። ጃንሆይም የጎጃም አማጺ አፍነውት፣ ኢትዮጵያን አልከዳትም። የወሎም ህዝብ ቦሩ ሜዳ ላይ ተዋግቶ ተሸንፎ ምንም ያለው የለም። ረሀቡን እየተመላለሰበት የሚያጠቃው ያንን ሕዝብ ነው። ወያኔም “ደመኛ ጠላቴ ብላ” የተነሳችው አማራው ላይ ነው። ኦሮሞ በኢትዮጵያው ውስጥ በመሆኑ ምን የቀረብት ነገር አለ? በግድ አይደል እንዴ ጃንሆይ ልጁን አስገድደው አስተምረውለት ዛሬ በሊቀ ሊቃውንት መንበሽበሽ የቻለው? የታወቀ ሀቅ እኮ ነው።

ሌላው ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ካሉት ውስጥ የገረመኝ፣ አዲስ አበባ ውስጥ ኦሮሞ ጠሊታ የሆን ህዝብ አለ አሉን። አይባልም፣ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስቴር! አማካሪ አድርገው ያስቅመጧቸው ምን እየሠሩ ነው ደሞዝ የሚከፈላቸው? ወይስ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ምክር አይሰሙም? የአዲስ አበባ ብሔር የላትም። ህዝቡ አንድ ወጥ አይደለም። አዲስ አበባ ከማንኛውም የኢትዮጵያ ግዛቶች ተሰብስበው የሚኖርባት ከተማቸው ነች። አንድ ብሔር ረግጬ ልግዛችሁ የሚል ከመጣ ግን “ወጊድልኝ” ሊል ይችላል እንጂ፣ ለይቶ የሚጠላው ብሔር የለም። እርግጥ ዘቅዝቆ የሚሰቅልና፣ አጋድሞ እንደበግ የሚያርድ ይወደዳል ብዬ አልመጻደቅም። ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንድምሳሌም ሲያቀርቡ፣ “ለምን የኦሮሚኛ ብሔራዊ መዝሙር በትምህርት ቤት ተዘመረ” ብሎ የሚንጨርጨር እንዳለ ነገሩን። ሁለት ነገር ልበል። አንዱ ለመሆኑ፣ የአማራ ህዝብ ብሔራው መዝምር ነው ወይስ የጉራጌ ህዝብ ብሔራዊ መዘሙር ነው አዲስ አበባ ላይ በየትምህርት ቤቶች ሲዘመር የሰሙት? ሌላ ጥያቄ! በዚህ መዝሙር ውስጥ “የመቶ ዓመት ግፍን በደም አጠብንልሽ” የሚል ህዝብን ከሕዝብ የሚያፋጅ ስንኝ አንዳለበት እያወቁ! አዲስ አበባን ካልቀማሁ እያለ የሚውተረተረው የኦሮሞው ፓርቲያቸው ነገር ሲፈልግ ነው እንጂ፣ አሁን የኦሮሞን ብሔራዊ መዝሙር ትምህርት ቤቶች ተዘመረ ብለው ገና ለገና “ሳይጠሉን አይቀሩም” ብሎ ያዙኝ ልቀቁኝ ማለት አስፈላጊ ነበር? ወይ ነገር መፈለግ፣ ወይ ዱቢ ወይ ዱቢ! ይኸ ሰሞኑን አንድ ወጣት ጓደኛዬ ላከልኝ ፎቶ ነው የኦሮሞ ሊሒቃንን ነገር ፍለጋ አስታወሰኝ። 

ዕውነትም ነገር ፍለጋ ነው እንጂ፣ አዲስ አበባ ትምህርት ቤት ውስጥ የኦሮሞ ብሔራዊ መዝሙርን በጉልብት ማስዘመርን ምን አመጣው? ለዚያውም የኦሮሞን ህዝብ ባልነበረ ትርክት ቁጭት እንዲነሳሳ፣”የመቶ ዓመት ግፍን፣ በደም አጥበንልሽ” ይሉናል። የአኖሌው ሀውልት ዓይነት ልቦለድ መሆኑ ነው። ይኸው ግምቢ ውስጥ የኦሮሚያን መሬት በአማራ ደም አጥበውላታል። ኦሮሚያ አለፈላት? ያን መዝሙር ነው እንግዲህ የአዲስ አባባ ሕዝብ እንዲጋትላቸው የሚያስገድዱት

ኧረ “ባህሩን የሚያሻግረን ሙሴ መጣልን” ያልናቸው ጠቅላይ ሚንስትር፣ የአዲስ አበባ ህዝብ እንዲሸማቀቅ ምን ያላሉት አለ? “የአዲስ አባባ ህዝብ ቆሻሻውን እየደፋበት” ብለውናል። ወገናዊ ቁጭት እንዲህ ነው እንጂ! ቆሻሻ በተገቢዉ መልክ ማስወገድ እኮ እሳቸው የሚመሩት የመንግሥት ሥራ ነው። መንግሥት ካልቻለ፣ ግለሰቦች እንዲሰማሩብት ሁኔታዎችን ማመቻችት የማዘጋጃ ቤቱ ግዴታ ነው። መንግሥት ደሞ ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚመሩት የማዘጋጃ ቤት ተቋም አለው። ወደ አዲስ አበባ ገብሬው ቀረብ እያለ የሰፈረው፣ ምርቱን እያመረተ ለመሸጥ መሆኑን ረስተውታል መሰለኝ። አዲስ አበባ፣ ለኦሮሞ ከእግዚአብሔር የተሰጠው መሬት አልነበረም። የንጉሥ ዳዊት ከተማ ነበረች።

ወይ ፊንፊኔ!

ብልጽግና ውስጥ የተሰገሰጉት፣ እንደነ ኦቦ ሺመልስ አብዲሳ፣ ታየ ደንደአ ... ያሉት ጽንፈኛ የኦሮሞ ሊሒቃን አዲስ አበባን “ፊንፊኔ” ካላላችኋት እያሉ ልባቸው ውልቅ ብሎ የኛንም ልብ ሊያወልቁት ይሞክራሉ። በነገራንችን ላይ፣ የልቡን የሚናገረው ሽመልስ አብዲሳ፣ ህወሀት ለትግሬ ኢህአዴግን እንደፈጠረው ኦህዴድም ለኦሮሞዎች ብልጽግናን ፈጥረናል[4] ብሎ ዕቅጯን ነግሮናል። ዕውነቱን ስለተናገረ፣ ጫፉንም ንክች ያደረገ የለም። ድንገት ሲያልፉ! “አዲስ አበባ” ስትል ከሰሙህ “ናፍጣኛ” እየመሰልካቸው የጎሪጥ ያዩሀል።  ነፍጡ ግን ያለው በነሱ እጅ ነው። አሁን ጋሞዎች ምን አድርገዋቸው ነው በቡራዩ የጨፈጨፏቸው? የአንደኛ ዜግነትን ቦታ ይዘውባቸው መሆኑ ነው? ምስኪኖች!

ድንቁርና ወጥ ያስረግጣል። “ፊንፊኔ” ቃሉ እራሱ አማርኛ መሆኑን ማን በነገራቸው! የኩሸት አባት እንደ ዓይናቸው የሚንከባከቡት ሊቃቸው ኤዝቂኤል ገቢሳ፣ “የመጀመሪያው ሰው ኦሮሞ ነው[5]” ዋቃም በጎን አይቶት ኦሮማ አለው ሲል ተሰምቷል። የመጀመሪያው የሰው ቋንቋም ኦሮሚኛ ነው ብሎናል። ግን እኮ፣ በኦሮሚኛ የተቀረጸ አንድም ሀውልት ከጥንት አልደረሰንም። እሺ ኦሮሞ የመጀመሪያ ሰው ነው እንበል። ጥሩ! አዳም ኦሮሞ ይን። ከሆነ ታዲያ አማራውም ኦሮሞ ነዋ። ስለዚህ ወንድም ወንድሙን መግደል ምን አመጣው? የቃየል ዝርያ መሆናቸው ይሆን? አሁን አሁን የምናያቸው የጽንፈኞች አጨካከናቸውም ያሰኛል። ለማንኛውም ፊንፊኔ አማርኛ ቃል እንጂ ኦሮሚኛ አይደለም። ፊን ፊን እያለች የምትፈልቀዋን ፍልውሀን የምትገልጽ ቃል ነበረች፣ ለአካባቢው ስም ሁና ስትወጣለት። እስቲ አዋቂ ነኝ የሚል ከቆቻቸው አንዱ ይምጣና “ፊንፊኔ” የሚለው ቃል በምን መልኩ ኦሮሚኛ/ኦሮሚፋ እንደሆነ ይንገረን። የቃሉን ሥነ-መሠረት ዕውቀት (Epistemology) ያስጨብጠን። የትም የለም!

አዲስ አበባን “ፊንፊኔ” ብለን ተቀብለንላቸው እንጥራትና ቀናቸውን እናብራላቸው ማለት እየዳዳኝ ነበር። ምክያቱም ሁለቱም አጠራር፣ ማለት፣ አዲስ አበባም፣ ፊንፊኔም፣ ከሚያወግዟቸው ከዳግማዊ ምኒልክ ባለቤት፣ ከእቴጌ ጣይቱ አንደበት የወጡ ቃላት ነበሩና። ችግሩ፣ የአዲስ አበባ ክፍለ ከተሞች በተለምዶ የራሳቸው አጠራር ነበራቸው። ለምሳሌ፣ አራዳ፣ አዲሱ ገበያ፣ አባ ኮራን ሰፈር፣ ሰንጋ ተራ፣ ውሀ ስንቁ፣ ጌጃ ሰፈር፣ ባልደራስ፣ በቅሎ ቤት፣ አራት ኪሎ፣ ስድስት ኪሎ፣ ውቤ በረሀ፣ ነፋስ ስልክ፣ ጉለሌ፣ ሾሮ ሚዳ፣ አቧሬ፣ መሿልኪያ፣ ቀበና፣ ነፋስ ስልክ፣ ፊንፊኔ/ፍልውሀ፣ ሾላ፣ ልደታ ... እያለ ይቀጥላል። ታዲያ የአንዷን ክፍለ ከተማ መጠሪያ ወስዶ ለኦሮሞዎች እንዲመች በአዲስ አበባ መቀየር ተገቢ ነው? እሱን እንተወው አንድ ነገር እንይ! ካላወቁ፣ መርዶ ድግመን እንንገራቸው፣ ዕርማቸውን ያውጡ!! ፊንፊኔ ቃሉ እራሱ አማርኛ ነው። አለቀ ደቀቀ! የቃሉ ሥነመሠረትም ፊን-ፊን ለምትለው የፍልውሀ አካባቢ የተሰጠ ስም ነው። ዛሬም ፊን ፊን የምትለዋ ፍልወሀ አካባቢ ለስሙ መጠሪያ ማስታውሻ ይሆን ዘንድ ለብዙ ዓመታት የቆመ “ፊንፊኔ አዳራሽ” የተባለው ሆቴል/ሬስቶራንት አለ። ሆቴሉ ሌላ ቦታ ሳይሆን ለምን እዚያ ሆነ ብሎ መጠየቅም የአባት ነው? ያንን ሆቴል ስወደው!

እንዳልኩት፣ አዲስ አበባን ፊንፊኔ ብንለው ባልከፋም ነበር። ሌሎች የአዲስ አበባ ክፍለ ከተሞች ይቀየማሉ እንጂ፣ ፊንፊኔ ብለንላቸው ባሳረፍናቸው ጥሩ ነበር። በዚያ የሚቆሙ ከሆኑ ምናለበት! ዳሩ ግን ነገራቸው ሁሉ ኬኛ ሆነና ተቸገርን ። ስንዝር ብትሰጣቸው ለክንድ ይመጡልሀል። ትዝ ይለኛል፣ በወያኔ ጊዜ አንዱ የኦነግ ታክሲ ነጂ አክቲቪስት ሎንደን ላይ አበሻ ሬስቶራንት ቁጭ ብሎ ሲያወጋ፣ አንዱ ጓደኛው “ለምን በቡድን ተደራጅተን ፊንፊኔ ቦታ ተመርተን ቤት በማኅበር አንሠራም?” ሲለው ምን መለሰለት መሰላችሁ። "ነገ ፊንፊኔ ከአማራውና ከምናምኑ ጸድታ የኦሮሚያ ዋና ከተማ ስትሆን፣ ከዚያ ሁሉ ከተሠራው ቤት መርጠን እንገባበት የለ? ምን አደከመህ!” አለው ደረቱን ገልብጦ! ለማንኛውም፣ መላውን አዲስ አባባ ፊንፊኔ ካልነውማ፣ ጉለሌስ ምን ጎደለው?

ፊንፊኔ አማርኛ ለመሆኑ፣ አንድ ጋጠ ወጥ እምቡር እምቡር እያለ ሲያስቸግር፣ አሁንም “ፊን ፊን! አትበል” እየተባለ አደብ ያስገዙታል። ፊን ፊን እያላችሁ የምታስቸገሩን ጽንፈኛ የኦሮሞ ልሒቃን፣ ፊንፊኔ ተብሎላችሁ ምንም ለውጥ ላታመጡ ተውት። ፊንፊኔ ኦሮሚኛ ስላልሆነች አታፈናፍናችሁምና ለአዲስ አበባ ባይሆን ሌላ ስም ፍጠሩለት። ታሪክ የመፍጠር ችግር መቼም የላባችሁም። በዛ! አበዛችሁት!

ማጠቃለያ!

አዲስ አበባ፣ አዲስ አበባ ከመባሏ በፊት፣ ሌሎች ስሞች ነበሯት። አንዱ ሸገር ነበር። እሱም ኦርሚኛ ይሁን አይሆን አላውቅም። “ሻጋር ጉሉፋኒ” (SHAGGAR GALUUFANII) የተባለ በቦሀራ ብርሀኑ ( Bohaara Birahaanu)[6] የሚዘፈን ዘፈን አለ አይደል? ወደሸገር ግልቢያ መሰለኝ ትርጉሙ! እና ሌሎችም አሉ። ሸገር ሬዲዮስ አለ አይደል? በጥናት የተረጋገጠ፣ የጥንት ስሟም አለ። በረራ! እሱም ኦሮሚኛ አይመስለኝም። ነው እንዴ? እንጃ! አዲሳ አበባ የኦሮሞ ስም ካልነበራት፣ እንግዲህ አዲስ አበባ ኦሮሚያ ሁናም አታውቅም ማለት ነው። ምን ይሻላል?

እንግዲህ፣ ፊንፊኔ፣ ካላፈናፈነቻቸው፣ አዲስ ስም ያውጡና እንደልማዳቸው የጥንት ስሟ ነው ይበሉን። ለምን “ዳራራ ሀራ” (Haaraa) አይሏትም? “እቴጌ ጣይቱ እንደ የምኒልኳ ፈረስ ከዚያ ሰርቀው ነው” ማለት ይችላሉ። አይችሉም? ማን አባቱ ከልክሏቸው! “አባቦ ሀራ” በሉት እንዳልላችሁ፣ አባቦ የተንሻፈፈ የአማርኛው አበባ ስም ስለሆነ ነው።

“ፊንፊኔ የቀድ ስሟ ነበር እያሉ የኦሮሞ ልሒቃን ዊኪፒዲያ ላይ እየቀየሩ ይገኛሉ። ዳሩ ግን ስሟ ለመሆኗ አንዲት ምንጭ እንኳን አይጠቅሱም። ከየት አምጥተው! የለማ! ሲፈልጉ በኦሮሞ አፈታሪክ አለ ይሉሀል። ኤዲያ! ልክ የመጀመሪያው ሰው ኦሮሞ ነበር እንዳሉን መሆኑ ነው። በመጀመሪያ ደረጃ ያ ቦታ እልም ያለ ጫካና አውሬ የሚታደንበት አካባቢ ነበር። ዛሬም አዲስ አበባን ከቦ የሚኖረው ጅብ፣ ከዚያ የተረፈ የዱር አራዊት ነው። አዲስ አበባን ጣይቱ ናቸው የሰየሟት። ቦታውን ያዩዋትም፣ አጼ ምኒልክ ሐረር ሂደው፣ እቲጌይቱ ፊን ፊን ከምትለው ጸብል ሊታጠቡ ከንጦጦ ወርደው ነበር። ያቺን ፊን ፊን የምትል ፍልውሀ ጥለው መሄድ አልፈጉም። ንጉሡን አሳምነው ከተማ ቆረቆሩ። በዚህ ምክንያት የኢትዮጵያ ዋና ከተማ የመሆን ዕድል ገጥማት፣ የአፍሪካም ዋና መዲና ሆነች። ያ የሁሉ ኩራታችንና የሁላችን ውርስ ነው። አንዱ ቀማኛ ብሔር ዓይኑን የሚያሳርፍባት መሆን የለባትም። የአዲስ አበባ ሕዝብ እንዴት ጊዜው ቢከፋበት ነው፣ በወያኔ ጊዜ እንኳን የነበረውን የክልልነት ደረጃ አጥቶ በብልጽግና ጊዜ የኦሮሞ እንዲሆን ዲሞግራፊውን ለመቀየር እነ ሺመልስ አብዲሳ የሚሯሯጡት? ሀይ ሊባሉ ይገባል። ኢትዮጵያን ወክሎ የፌዴራል መንግሥቱን ሥልጣን የጨበጠው ክፍል፣ ሕዝቡን ማሸማቀቅ ትቶ መብቱን ማስመልስና ማስጠበቅ የግድ ይሏል። 

ኬኛዎች ሰላም ስጡን! ነገር አትፈልጉ! አብረን በሰላም እንደዱሯችን ተከባብረንና ተፋቅረን እንኑር! የአንድ እናት ልጆች ነን!

አበቃሁ!

Tuesday, 11 January 2022

ዶሮው ለ3ኛ ጊዜ ጮኸ!


"እውነት፡እልኻለኹ፥በዚች፡ሌሊት፡ዶሮ፡ሳይጮኽ፡ሦስት፡ጊዜ፡ትክደኛለኽ፡አለው።"

ማቴዎስ 26 ቁጥር 34

ከወንድሙ መኰንን፥ ኢንግላድ 11 January, 2022


መግቢያ

ጥቅምት 24 ቀን 2013 በውድቅት ሌሊት በትዕቢት የተወጠሩ የጦርነት ከበሮ ደላቂ የሕወሀት ባለሥልጣናት፥ ለዘመናት በገነቡት የጦር ኃይላቸው የትግራይን ሕዝብ ደሙንና አጥንቱን መስዋዕት እየከፈለ ሲጠብቃቸው የነበረውን የሰሜን ዕዝ የመከላከያ ሠራዊት አባላትን፥ የጭካኔ ጥግ በሚሆን አኳኋን፥ በተኙበት ጦራቸውን አምዘግዝገው ወጉት፥ ሳንጃቸውን ወድረው አረዱት። የሞቱትንም ሬሳቸውን ታይቶ በማይታወቅ ሆኔታ ልብሳቸውን ገፈው እርቃናቸውን ሜዳ ላይ ደርድረው የትግራይን ህዝብ አስጨፈሩት። በሕይወት የተያዙትን ፥ ጥይት ላለማባከን በማለት አስተኝተው ሲኖ ትራክ ነዱበት።


ይኸ በወገናችን ላይ የደረሰው ግፍ አንገሽግሾን፣ በመንግሥት ላይ የየራሳችንን ቁርሾ፣ ለምሳሌ አማራው ላይ በአጣዬ፣ በሸዋ ሮቢት፣ በወለጋ፣ በጋሞው ላይ በቡራዩ፣ ኦሮሞ ባልሆነው ሕብረተሰብ ላይ በሻሻማኔ፣ በዘዋይ፣ በአርሲ የተፈጸመውን ግፍ በማየት፣ ለህዛባችን የመኖር ዋስትና ላልሰጠ መንግሥት ላይ ጥርሳችንን ነክሰንበት የነበረው ሁሉ ለጊዜው ልዩነታችንን ወደጎን ገፍተን ከመንግሥት ጎን ተሰለፍን። የሕወሀት ጭካኔ ያንን አስጥሎን በአንድ ላይ አቆሞን ነበር። በየጊዜው ከመንግሥት በኩል የሚደረጉት አንዳንድ አስደንጋጭ ውሳኔዎች ግን ይኸንን አንደነታችንን እይሸረሸረ መሄዱ አልቀረም። በየጊዜው ለሚፈጠረው ቅሬታ መንግሥት ብቻ ነው ተጠያቂው!



የኢትዮጵያ ህዝብ ቁጣ

ወራሪውና ጨፍጫፊው የትግራይ አሸባሪ ቡድን ይኸን አሳፋሪ ድርጊት የፈጸሙት ለ27 ዓመታት ዓይን ባወጣ ዘረፋ፥ በታጠቁት የጦር መሣሪያ፥ በዘረኝነት ጠበል አጥምቀው፣ ከሰውነት ወደ አውሬነት በቀየሯቸው የትግራይ ተዋጊና ባካበቱት ኃብት ተማምነው ነበር "ጦር አውርድልን" እያሉ መሬቱን ሲገርፉት የነበሩት። ዓላማቸውንም ለማሳካት የያንን የመሰለ እኵይ የጦር ወንጀል ከፈጸሙ በኋል፣ ወደ አዲስ አበባ ገስግሰው ገብተው መንግሥት ገልብጠው ኢትዮጵያን በመበታተንና ታላቋን ትግራይን የመመሥረት ዓላማቸውን አንግበው ፎክረው ዘመቻቸውን ጀመሩ። ነግር ግን በመንገዳቸው ላይ ለ27 ዓመታት ረግጠው የገዙት፣ መሬቱን ቀምተው፥ መብቱን ገፈው፥ ሀብቱን ዘርፈው የጨቆኑት የአማራ ሕዝብ በጀግንነት በልዩ ኃይል ሚሊሺያውና በፋኖው ተደራጅቶ ከፊታቸው ተጋረጠባቸው። አዲስ አበባ ለመግባት ይኽን ልበ ሙሉ ጀግና ሕዝብ፥ ዳሽቆ ማለፍ ቀላል አልሆነላቸውም።


በጭካኔና ከዱር አውሬነት በባሰ ወንጀል የተደፈረው የኢትዮጵያ ህዝብም ተቆጣ። ከዳር እስከዳር ከወንድሙ የአማራው ሕዝብ ጎን ለመቆም ሆ ብሎ ወጣ።። በየቦታው ተሠማርቶ የነበረ የመከላከያ ሠራዊትም ከያለበት ተሰበሰበ። ሕይወቱን አትርፎ አምልጦ ወደ ኤርትራ ተሻግሮ የነበረውም የመከላከያ ሠራዊት ተደራጅቶ ተመለሰ። የአማራው ሕዝብ ገትሮ የያዘለትን አውሬ ለመምታት፣ ደረሰለት። የአማራው ልዩ ኃይልና ፋኖው አላሳልፍ ከማለቱም ባሻጋር ገስግሶ ከጎንደር የተቀማውን ርስቱን ተዋግቶ ወልቃይትንና ሁመራን ነጻ አወጣቸው። የወያኔ ገዳይ ቡድን መሸነፉን ሲያውቅ በማይካድራ 1,100 ንጹህ ምስኪን አማሮችን ጥቅምት 29 ቀን ላይ ጨፍጭፎ ወደ ሱዳን ፈረጠጠ። በሂደት ራያም ነጻ ወጣች። የአማራን ምድር ረግጦ ማለፍ ቀረበትና በሦስት ሳምንት ውስጥ ዕብሪተኛው የሕወሀት አመራር የጥጋብ ፊኛው ተነፈሰ። የራሱን ህዝብ እንደጅል ቆጥሮ፥ "ባጫ ደበሌን ማረኩልህ ደስ ይበልህ፥ አበባው ታደሰን ገደልኩልህ እልል በል፥ 180,000 ጦር ደመሰስክልህ" እያለው "ደቂሴ ንሬን" አንከስ እያለ አስጨፈረው። የማታ የማታ ዕውነትና ንጋት እያደር ይጠራል ሆነና፥ ዋና ከተማውን ጥሎ ወደ ተንቤን ተራራ እግሬ አውጩኝ አለ። "አቅምን አውቆ መኖር ጥሩ ነው፣ ታላቅ ቾሎታ ነው" አለ ዘፋኙ! ተዋጊዎቹም ልብሳቸውንና መለዮአቸውን አውልቀው ከሲቪሉ ከሕዝብ ተቀላቅለው ተመሳሰሉ። ኢትዮጵያም ለመጀመሪያ ጊዜ ከተሰነቀረባትን የሕወሀት እሾህን ነቅላ ከስቃይ የምትገላገልበት ቀን የደረሰላት መሰላት። ህዝቡ ደስ አለው። የአንድነት ጡሩምባ ከዳር እስከ ዳር ተነፋ። አኩርፎ የነበረው ውጪ የሚኖር ኢትዮጵያዊ ሁሉ በአንድነት ቆመ። የኢትዮጵያ ትንሳኤ የደረሱላት መሰለው። መከላከያው፣ ልዩ ኃይሉ፣ አመራሩን እያሳደደ የገባበት ግብቶ፥ ከተቻለ ከነሕይወቱ ይዞ፥ እምቢ ያለውን እስከወዲያኛው ሸኝቶ ሕወሀትን ታሪክ ለማድረግ ተጋድሎውን ተያያዘው።


ጉድና ጀራት ከወደ ኋላ

የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ፥ ልዩ ኃይሉና የአማራው ወዶ ዘማች ፋኖው፥ እንዲሁም በወያኔ ርኬት ድብደባ ተጋብዘው ወደ ውጊያው የተቀላቅሉ ኤርትራውያን ተዋጊዎች ፥ በአየር ኃይሉ ተዋጊ ጄቶችና ሰው አልባ በራሪዎች (ድሮናች) በታጀበው ውጊያ የተንቤን ተራራ ጋየች። በዚያ እልህ አስጨራሽ ውጊያ 15 ገደማ የሚሆኑ፥ ስብሀት ነጋን ጨምሮ ከዋሻ እየተጎተቱ ወጡ። ወደ ዘብጥያም ወረዱ። እነ ሥዩም መስፍንና ዐባይ ጸሀይ የተባሉት የወያኔ አመራሮች ግን እጅ አንስጥም ብለው ወደማይቀርላቸው ሲኦል ተሸኙ። የኢትዮጵያ ህዝብ በከፊልም ቢሆን አንጀቱ ራሰ። የውጭ ጠላቶቻችን ቢጮሁ፥ ቢያላዝኑ፥ ኢትዮጵያ ፍንክች አላለችም። የተቀሩትን የሕወሀት አመራሮችን ማደኑ ቀጠለ። እነደብረጽዮን፥ ጻድቃን፥ ታደሰ ወረደ፥ ... የመሳሰሉት በየጢሻው እየተሽሎከሎኩ እስከ ሰኔ ድረስ ከመያዝ አመለጡ።

የዓለም አቀፉ ጫና ቢበዛ፥ የምዕራቡ ዓለም ጋዜጦች፥ ቴሌቪዥኖች እና ማህበራዊ ሚዲያዎች የውሸት መረጃዎችን ቢለቁም ኢትዮጵያውያን በአንድነት ቁመው መከቱት። የአባቶቻችን የጀግንነት ወኔ የተመለሰ መሰለ። እኛም የመንግሥት ቃል አቀባዮች በጊዜው እየወጡ፣ ይኸን ያህል ተደመሰሰ፣ ይኸን ያህል ተማረከ እያሉ ሲያስረዱን፣ በኩራት ተዝናንተን፣ የቀሩትን አመራሮች የሚያዙበትን ወይም የሚወገዱብትን ዜና ስንጥብቅ በድንገት ወሽመጣችን ቆረጠ።

ሰኔ 21 ቀን ደረሰ። የኢትዮጵያ መንግሥት ጆሮ ጭው የሚያደርግ መርዶ ነገረን። ማንም ያልጠበቀ በጣም የከፋ ዋጋ የሚያስከፍል፥ የኢትዮጵያ ሕዝብ ዕምነቱን የጣለበት የሚሸረሽር: መንግሥት  እርምጃ ወሰደ። የያዘውን ይዞ፥ የቀረውን ታንኩን፥ መድፉን፥ ዲሽቃውን፥ ብሬሉን ጥሎላቸው፥ ከትግራይ ከወጣ በኋላ ልክ ወያኔዎች እንደሚያደርጉት፣ "አሸንፌ ተመለኩ፥ ደስ ይበላችሁ ብሎ" ሊያስጨፍረን ሞከረ። "ሕወሀት ከዚህ በኋላ ኢትዮጵያን የሚያሰጋ ደረጃ ላይ እንደሌለች አውጆ አርፋችሁ ተኙ ተባልን። ክው አልን። ባለንበት ኩምሽሽ አልን። መንግሥት "የምንፈልገውን እያሳየን ወደበረሀ ወስዶን እዚያው ጥሎን ተመለሰ" ጉድና ጅራት ድሮም ከወደ ኋላ ነው። ለመጀመሪያ ጊዜ ዶሮ ጮኸ።




የወሎው፥ የሰሜን ሸዋና የአፋሩ ሕዝብ ከነከብቶቹ እልቂትና መፈናቀል የማን ስህተት ነው?

ይኸን መጠየቅ ጊዜው አሁን አይደለም ልትሉኝ ትችላላችው። ለመሿሿምና ለመሸላለም ጊዜው ካመቸ፣ ዋጋ የሚይስከፍሉ ስህተቶችማ ሲሠሩ ዝም ማለት አድር ባይነት ነው። እንዳይደገም! እንዲህ ዓይነት ጥቆማ መንግሥትን ቢጠቅመው እንጂ አይጎዳውምና፣ ካድሬዎች አደብ ግዙ። ጃንሆይንም መግሥቱንም ገደል የከተታችሁት የእናንተ ዓይነቶቹ ናችሁ። ጠቅላይ ሚኒስትሩና መንግሥታቸው ሊነገራቸው ይገባል።


መከላከያችን መቀሌን በድንገት ጥሎላቸው ሲወጣ፣ ባይሆን ደጀኑ የሆነውን የአማራና የአፋር ድንበር ላይ እንደመቆየት ዕድላችሁ ያውጣችሁ ብሎ ሁለቱን ሕዝብ አጋፍጦ ዞር ማለት ምን ይባላል! በዚህ ላይ አማራው እንዳይታጠቅ ላለፉት 30 ዓመታት ተፈርዶበታል። ቆይ እንጂ! ልክ አሜሪካና እንግሊዝ ናዚ ጀርመኒና ኮሙዩኒስት ራሺያ ሲተላለቁ በራሳቸው እስከሚመጣ ድረስ ዝም እንዳሉት መንግሥታችን አማራውና ትግሬው እንዲተላለቅለት አውቆ የተዋቸው አስመስሎበታል። የሕወሀት አመመራሮች በወርቅ መሶብ የቀረበላቸውን ድል ሳያስቡት ተቀብለው፣ መቀሌን በከበሮ ድለቃ ቀውጡት። እግዚአብሔር ዘፈን ሲያምረው ማንን ነበር ያጠግባል የተባለው? ረሳሁት። የሕወሀት አመራሮች ከተሸሸጉበት ጎሬ ወጥተው፥ መሣሪያቸውን ከደበቀቡት ጉድጓድ ቆፍረው አውጥተው፥ መከላከያውም ትቶላቸው የወጣውን ዘመናዊ መሣሪያ "እናመሰግናለን" ብለው ተቀብለው፥ እንደ እባብ አፈር ልሰው ነፍስ ዘርተው፣ ወደ የዕዝ ማዕከላቸው ተመለሰሱ። የምዕራቡ ዓለም አደነቋቸው። የጦር ታክቲክና ስትራተጂአቸውንም ዕጹብ-ድንቅ አሉላቸው። የጻድቃን የጦር አመራር ብቃት በአፍሪካ ታይቶ የማይታውቅ ተብሎ ተጨበጨበለት። እነ ጌታቸው ረዳ የምዕራቢያውያን ሜዲያ ኮከብ ሁነው የጋዜጦቹን ገጽ ሞሉት። የቴሌቪዥኑንና የሬዲዮውን ሜዲያ ተቆጣጠሩት። በዚያ አላበቁም።


"ከአማራው ጋር የምናወራርደው ሂሳብ አለን" በማለት፥ ሕወሀቶች አማራው ላይ ዘመቱ! ጎንደርን በከፊል፥ ወሎን መሉ በሙሉ፥ ሰሜን ሸዋ ተቆጣጥረው የደም መሬት አደረጉት። ወንዶቹ ታረዱ፥ ሴቶቹ፥ ሕጻናቱና አሮጊቶች ሳይቀሩ በተፈራራቂ የሕወህት መንጋ ተደፈሩ። ከመንግሥት ተቋም እስከ የግለሰብ ንብረት ዘረፉ፥ የቀረውን አወደሙት። ከብቶቹም ተረሸኑ። የአማራው ሚሊሺያና ፋኖ አንዳንንዴ ብቻውን ሌላ ጊዜም በመከላከያው እየታገዘ ቢዋጋም እንድ በአንድ የወሎን ትላልቅ ከተሞች፥ ላሊበላ፥ ደሴና ኮምቤልቻ ሳይቀሩ በሕወህት ቁጥጥር ሥር ወደቁ። ወያኔዎች ሸዋም ዘለቁ። ተሰምቶ የማይታወቅ ግፍና ጭፍጨፋ አደረሱ። የአንድ ቀን መዘዝ በዘጠኝ ወር ይመዘዝ ይሉሀል ይኸ ነው። ይኸ ጉድ ተሸፋፍኖ መታለፍ የሌለበት ግፍ ነው። ተመዝግቦ ይቀመጥ። የስህተቱ ምንጭ ከመቀሌ መውጣቱ ብቻ ሳይሆን ደጀኑንም ለቆ ማፈግፈግ፣ አማራና አፋርን ዋጋ አስከፍሏል።


ሚሌ የምትባለዋን መተላለፊያ ዘግተው የኢትዮጵያን ጉሮሮ እንዘጋለን ብለው ዝተው ማንንም አስቀይሞ በማያውቀው አፋር ህዝብ ላይ ዘመቱበት። አፋሮች ተጨፈጨፉ። ሕዝባቸው አለቀ፥ ንብረታቸው ወደመ። ጭፍራ የምትባለው ከተማቸው ወደመች። አፋሮች ግን ታይቶ በማይታወቅ ጀግንነት ሚሌን ላለማስነካት በታላቅ ጀብዱ ታሪክ ሠሩ። ሕወሀቶች ሚሌን ለመያዝ እንደቋመጡ ዓላማቸው በአፋር አናብስት ከሸፈባቸው። ኪሳራ! 


በወሎ ግንባር ግን ታሪኩ ሌላ ነበር። ደሴንና ኮምቦልቻን በብዙ መስዋትነት ከጨበጡ በኋላ፥ ሕወህቶች ደብረሲና ደረሱ። አዲስ አበባን ለመያዝ ቀናት ሲቀራቸው፥ የኢትዮጵያ መንግሥት የምር ሰይፉን መዘዘ። በራሱ ደረሰአ! ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሳይቀሩ ከተኙበት ባነኑ። ልክ ናዚ ጀርመኒ ፖላንድን መውረራቸው ሳያንስ ፓሪስን ተቆጣጥረው የእንግሊዝ ወደቦችና ከተሞችን መደብደብ ሲጀምሩ እንግሊዝ እንደባነነችው ማለት ነው። ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ እራሳቸው  ታጥቀው ጦሩን ሊመሩ እንደቀድሞዎቹ መሪዎች ግንባር ገቡ። በራሳቸው መምጣቱ በጀ ልበል?! ቢዘገይም የሚደነቅ እርምጃ ነበር። የሰው ወኔው ተመለሰ። ሕዝቡ እንደገና ሆ ብሎ ወጣ። መከላከያው፥ ልዩ ኃይሉ፥ ፋኖውና አፋሩ ልዩ ኃይልና ሕዝብ በተቀናጀ መልኩ በጀግንነት፥ በቆራጥነትና በወሳኝነት፥ ወራሪ፥ ጨፍጫፊ እና ዘራፊ የወያኔ፥ ሪፍራፍ ተዋጊን መክቶ፥ ለአራት ወራት ሙሉ  እየገደሉም እየሞቱም፣ ተንፏቅቀው ተንፏቅቀው ደብረሲና የደረሱትን ጉዶች፥ በሁለት ሳምንት ከሰሜን ሸዋና ወሎ ጠራርገው፥ እንዲፈረጥጡና ሬሳቸውን እንኳን ሳያነሱ ኮረም እንዲገቡ አደረጓቸው። አፋርም ሙሉ በሙሉ ተለቀቀ። ይኸ ምንድነው የሚያሳየው? ቀድሞውኑ መንግሥት ችላ በማለት የውሎ፥ የሰሜን ሸዋና የአፋር ምድርን እንዲይዙ ዕድል ሰጥቷቸው ነው እንጂ፣ የነዚህን መሬቶች የመርገጥ አቅም ወያኔዎች ባልነበራቸው ነበር ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ግባቸውን በከፊል ፈጽመው በኋላ ወደ አዲስ አዲስ አበባው ቢሮዋቸው ተመለሱ።


ጦሩ በሽሽት ላይ ያሉትን የወያኔ "እውር ድንብር" ተዋጊዎችን አባርሮ ኮሩም ደረሰ። የመቀሌ ባለሥልጣኖች ተደናብረው፣ ጓዝና ጉዝጓዛቸውን ቀርቅበው፣ ተስፋ በመቁረጥ፣ የዓለም አቀፉን ሕብረተሰብ "አድኑን" እያሉ እየተማጸኑ፣ ወደተምቤን ተራሮች መጓጓዝ ሲጀምሩ እንደገና "ደጉ" መንግሥታቸው ነፍስ ዘራላቸው። የኢትዮጵያ ጦር አሳዶ የወያኔን አመራር ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ አከርካሪ ይሰብራል ብለን ስንጠብቅ፣ ዋጃን እንደተቆጣጠሩ፣ አላማጣን ሙሉ በሙሉ ለመቆጣጠር አንድ ቀን ሲቀራቸው፣ "ባለህበት እርጋ" የሚል ትዕዛዝ መንግሥት አስተላለፈ። እንደገና ወሽመጣችን ተቆረጠ። ወያኔ እንዳትጠፋ አልተፈለገም ማለት ነው? አውላላ ሜዳ ላይ እንደገና ተጣልን! ዶሮው ለሁለተኛ ጊዜ ጮኸ! 


ሦስኛው ዶሮ!

ለሁለተኛ ጊዜ የመኖር ዕድል የተሰጣቸው የወያኔ ተዋጊዎች፥ መፈርጠጣቸውን አቁሙው አፈሙዛቸውን ወደኋላ አዞሩ። በወልቃይት ጠገዴ በኩልም ያለ የሌለውን ጦራቸው ሰብቀው ውጊያ ጀምሩ። እስካሁን አዲ አርቃይን ሙሉ በሙሉ በሚባል መልኩ ተቆጣጥረው፣ ጎንደሬ አማራውን እያፈናቀሉት ነው። በአፋር በኩል የአባላ ከተማን በመድፍ አያወደሙት ነው። በአላማጣ በኩል ውጊያቸውን አጧጡፈው  ዋጃና፥ ጥሙጋ የተባሉትን ከተሞች ተቆጣጥረው ወደቆቦ የምድር ክላስተር ቦምብ እይተኮሱ እየገሰገሱ ነው። ቆቦን በመድፍ ከርቀት ማጋየታቸውን ቀጥልዋል። ምስኪኑ ህዝብ፣ ከዋጃ ወደ ቆቦ ተፈናቀለ። ቆቦም መደብደብ ሲጀምር፥ ከቆቦ ወደወልዲያ እየተመሙ ነው። ከወልቃይት ጠገዴም አማራው እንደገና ተክዷል እየተባለ ሽብር እየተነዛ ነው፥ መካላከያም፥ ልዩ ኃይሉም፥ ፋኖውም ይውጣ የሚባል መመሪያ እንደተሰጠ ሹክሹታው ቀጥላል። ጭስ ካለ እሳት አለ። ከዚህ በፊት የተንሾከሾከው በሙሉ ዕውን ሁኖ የእለ? የኮሎኔል ደመቀ ዘውዴ የቁጣ ንግግርም ይኸንኑ አመላካች ይመስላል። አማራው እንደገና በጎንደር ቅስሙ እስኪሰበር ከተተወ ሥራ ለሠሪው እሾህ ላጣሪው እንደሚባለው ለመንግሥትም ጦስ ይዞ ይመጣል። አለባበሰው ቢያርሱ በአረም ይመለሱ ይባል የለ? የሱዳን ኮሪዶር ሕወሀቶች ማስከፈት ከቻሉና እንደገና መታጠቅ ከቻሉ፣ መንግሥትንም የመግልበጥ ሕልማቸው ሊሳካ ይችላል። ጦር መሣሪያቸው አልቆ ያልጨረስናቸው፣ ሌላ አውዳሚ መሣሪያማ ከታጠቁ  ሕዝባችንን ይጭርሱና ኢትዮጵያን ወደመበታተናቸው ሁለተኛ ደረጃ እቅዳቸው ይራምደሉ። ለኃጢአን የመጣ ለጻድቃን ይተርፋል ይባላል። 


ጦርነቱ ገና አላላቀም። የምን አሸሻ ገዳሜ ነው? መንግሥት ሆይ! የጦር አማራሮቹን ጠርተህ ከምትሾምና ከምትሸልም ይልቅ፣ መጀመሪያ ጦርነቱን በድል ፈጽም! ለመሆኑ፣ መቼና ለማን ነው የማርሻልነት ማዕረግ የሚሰጠው? ጦርነቱ እስኪጠናቀቅ ፌሽታው መቆየት አይችልም ነበር? የልጅ ነገር አደረጋችሁት። የምታቦኩት ሁሉ ለራት አልበቃም! 


ውጪ ኗሪው ኢትዮጵያዊ (ዲያስፖራው) ተጋብዞ በገፍ ወደ አገር ገብቷል። ለምን ጋበዛችሁት? በስሜት የተዘጋጀለትን ሁሉ እየጎበኘ በደስታና በጉጉት አገሩን እንዴት እንደሚረዳ፥ የወደሙትን መልሶ እንዴት አድርጎ እንደምያቋቋምለት በታላቅ ተነሳሽነት እየተመካከረበት ባለበት በዚህ ጊዜ ሌላ ዱብ ዕዳ ለምን አወረዳችሁበት? ብዙዎቻችሁን ሕወሀት ለዚህ ደረጃ አሰልጥና አሳድጋ እንዳደረሰቻችሁ እናውቃለን። ለምን ከዚያ አስተሳስብ ሰብራችሁ አትወጡም? ለምን አገራችንን ዋጋ ታስከፍሏታላችሁ? ለኢትዮጵያ እንደምታወሩት ከቆማችሁ ብሰሉ እንጂ! ከጎናችሁ የምንቆመው ስንተማመንባችሁ ነው። ስንት ጊዜ በእናንተ ላይ ያለንን እምነት ትሸረሽራላችሁ? የምነፍልገውን እያሳያችሁን ወስዳችሁ በረሀ የምትጥሉን ደነዞች አድርጋችሁ አትቁጠሩን።


እኛ የቀሩትንም የሕዋህት ባለሥልጣናት የተከፈለው መስዋዕትነት ተክፈሎ ተይዘው ለፍርድ ይቅርባሉ ብላን ስንጠብቅ ጠቅላይ ሚኒስትሩ፥ በዕለተ ዓርብ፣ ያውም በጌታችን የመድኃኒታችን የእየሱስን ክርስቶስ በአለ ልደት በሚከበርበት ቀን፥ ተስፋችንን አጨለሟት። በስንት መስዋዕትነት የተያዙት የወያኔ ቁንጮ መሪዎችን፣ አቶ ስብሀት ነጋን፥ ወይዘሮ ቅዱሳን ነጋን፥ አቶ አባይ ወልዱን፥ እቶ አባዲ ዘሙን፥ ወይዘሮ ሙሉ ገብረእግዚአብሔርን እና አቶ ኪሮስ ሀጎስን በይቅርታ ፈትቼአቸዋልሁ፥ ብለውን እርፍ! ምን? ይኸን ሲያውጁ፣ ለ3ኛ ጊዜ ዶሮው ጮኸ! በደም የተበከለችው፣ በጣዕር በስቃይ ላይ ያለችው  ምስኪኗ እናት ኢትዮጵያም ዕንባ ባቀረሩ ዓይኖቿ ጠቅላይ ሚኒስትሯን አየች።



 






4




Monday, 3 January 2022

THREE THOUSAND FIVE HUNDRED VACOUS INTELLECTUALS OF THE TPLF!

I hate when people confuse education with intelligence, you can have a Batchelor’s degree and still be an idiot”

Elon Musk

 By Wondimu Mekonnen, 02 January 2022

Introduction

Intellectuals are supposed to be men of great knowledge. An intellectual possesses the ability to think in a logical manner. An intellectual is guided by his own consciousness and knowledge, by means of independent research output and not by emotions. An intellectual is an independent thinker, who is capable of thinking outside the box. takes pleasure in serious study and thought and is constantly critical of the information he /she receives….with the sole intention of defending a concrete proposition or to denounce an injustice. To be called a scholar and a professional one needs to be governed and guided by the code of ethics of that profession or defending a system of values.

One wonders how on earth the Tigray Liberation Front (TPLF) managed to create a bunch of zombie “scholars and professionals” thinking and acting in the same way as their creators, devoid of a gram of common sense. They do not seem to have an iota of elements that takes to become “intellectuals”. They are like brainless drones, distance operated by remote control by the TPLF. They are programmed like robots behaving in the way that the TPLF wanted them to behave. Just like the North Koreans are conditioned to blindly follow the Kim Il-sung dynasty, so do the predominant the so-called Tigrayan intellectuals obtain their directions from the TPLF. They are the TPLF worshippers devoid of their own thoughts and moral compass.

The Role of Tigray Intellectuals in the TPLF war on Ethiopia

When the TPLF was beating the war drum in 2020, mothers in tears[i]   from all over Ethiopia travelled to Tigray, going on their knees, begged Debretsion, the president of the Tigray region, to avoid war and resolve the issues Tigray had with the central government in a peaceful manner. The president ignored them. A team of elders, including the Olympic legend Haile Gebrselassie and religious leaders, also travelled to Tigray to convince the authorities of Tigray, to avert war, but the TPLF ignored them too. Overconfidence/deceit is as dangerous as losing confidence. Many mistakenly hoped that the Tigray intellectuals would talk the TPLF out of their nightmarish madness. Instead, they became their beasts of burden, soon beating the war drums in the chorus.

Journalist Abebech Kahsay raised her observation of the role of Tigray “scholars and professionals” to avoid the war with amazement[ii]. The TPLF invited so so-called Tigray intellectuals and professionals from all over the world to lecture down to them what they were going to do with the Abiy Government in their bravado quest to dismantle Ethiopia and build the “Great Republic of Tigray”. The team of Tigray intellectuals included within them Ph.D., master’s degree holders, doctors, engineers you name it. Among them, one brave intellectual questioned the possible negative consequence of starting the war with the Federal Government on Tigray and proposed to settle the differences through peaceful means. His fear was that, if the TPLF started the war, Abiy’s Government might cut off electricity, telephone, transport, and other utilities putting Tigray in the dark. Then one of the veterans “Tegadalay” known by her nom de guerre Monjorino (Fetlework Gebreigziabher) barked back at the inquisitor with such authority: “If Mekelle would be in the dark, just for one night, do you think Addis Ababa would be in the light? If that happens, then we should be considered dead! That would never ever happen!” The Tigrayan intellectual coiled back with shame for undermining the TPLF and resorted to dancing to their tune. That is why we say overconfidence is as dangerous as losing confidence.

While the TPLF was massacring civilians, raping, looting, destroying infrastructure in Afar, and in Amhara from Northern Wello to Northern Shewa, the Global Society of Tigray Scholars and Professionals (GSTS) came up with a 7-point position[iii]. In those 7 points, they were lamenting that a genocide has been committed against the people of Tigray, which the United Nation did not find a shred of evidence such a crime was committed against the civilians on purpose. The genociders were crying “genocide on Tigray” to obscure their own crime on Amharas (Mai Kadra, Chena, Haiq, Kombolcha, Dessie, Lalibela, Northern Shewa…, on Afar, at Galicoma and Chifra. In fact, the term “genocide” has become a national hymn of the TPLF, which they have been dancing to that tune since 2005 when they stole electoral ballots and gunned down 100s of protestors on the streets of Addis Ababa. They introduced for the first time the term “Interhamwe” in Ethiopia, which forced Ethiopian intellectuals to run to google to find out what that term was exactly meant. Anyway, the so-called Tigrayan Scholars and professionals almost demanded the Amhara and the Afars to surrender at their 6th position point. They demanded to lay their arms while they were fighting, looting and, raping.

Expect more surprises from “Tigray Intellectuals”. The purpose of this article is to expose the extent of ignorance of the so-called Tigray intellectuals thinking in line with the TPLF leadership.

The cart before the horse

To the amazement of millions of people across the world, The Global Society of Tigray Scholars and Professionals (GSTS)”, which claims to have more than 3500 members, recently surprised us on Twitter with “Position Statement on the Vital interest of Tigray[iv], which includes three statements. Position 3e is the most bizarre statement. It reads:

“Equally essential and related to the territorial integrity of Tigray is access to international borders, and the right of access to and from the sea and freedom of transit as provided in article 125 of the Law of the Sea. These constitutional and international rights are non-negotiable vital interest of Tigray”

Doesn’t that sound like putting the cart before the horse? There is an adage in the Ethiopian proverb: “Let the common duiker be meat first” (እስቲ መጀመሪያ ሚዳቋ ሥጋ ትሁን). These guys have no clue that Tigray has been an integral part of Ethiopia for thousands of years and remains a territory of Ethiopia up until this article is written. The border of Tigray is determined by the Ethiopia Government and not by the United Nations or anybody else outside Ethiopia as a matter of fact. This is common sense. These guys act as if Tigray is an independent country. It is not. The TPLF is not in charge of the Government of Ethiopia anymore, if they have forgotten, to determine the future of Ethiopia!

Even if they manage to defeat the Government forces and control Tigray, the road to independence is bumpy and complicated as long as they wouldn't overthrow the Federal Government and reseize power. For example, look at Abkhazia, Somaliland, and the Turkish Republic of North Cyprus. They have been de facto states for several decades now, but they are not recognized by the United Nations, because they couldn’t obtain recognition from the Governments of the countries they were trying to break away from. The state of Eritrea was so lucky to have a traitor Government in the image of the TPLF to oversee the Ethiopian Government by force, coming to power through the barrel of guns in 1991. To the bewilderment of the international community, they had to run on the corridors of the United Nations and African Union with dossier to beg for the recognition of Eritrea, a breakaway province of Ethiopia, making Ethiopia landlocked losing its the only two ports built with the sweat and blood of Ethiopians. Ironically, the good news is, now the independent state of Eritrea is fighting the treacherous TPLF to save Ethiopia from further dismemberment. Therefore, the Tigrayan intellectuals must wake up and smell the coffee before talking about the international border or an outlet to the sea. They have no legal or moral authority to demand that. Only the Ethiopian Government decides what to do with them, as Tigray is in Ethiopia and Tigrayans are Ethiopians throughout the existence of Ethiopia for thousands of years. They need to swallow the bitter pill.

There must be more than 3,500 Tigrayan season intellectuals, perhaps in the tens of thousands. However, their silence makes them just as guilty as the 3,500 clueless scholars and professionals as they are representing them.



The red area within the map of Ethiopia is the historical map of Tigray excluding the lands of Amhara forcefully annexed 30 years ago. The land annexed after 1991 is now back to their ancestral routes after the greedy and expansionist TPLF imposed war on the Ethiopian Government. On 03 November the TPLF made a terrible mistake of starting the war they had been preparing for two years. An Amharic saying comes to mind: “one who doesn’t know when full, spends the night getting sick” (አልጠግብ ባይ ሲተፋ ያድራል).

The Genocide on Amhara and Afar

Six days after they started the war, realising they were losing, on 9 November 2020, the TPLF soldiers fighter started going from house to house and began massacring Wolqaite Amharas. Within a matter of hours, they hacked down 1,100 Amharas at Mai Kadra (Muchena, 2020) with the intention of cleaning hundreds of thousands of civilian indigenous Amhara from Welqit, Tegede, and Humera. Luckily the arrival of the Amhara militia and Fanno just in time stopped the massacre forcing the murderers to flee. The genociders crossed the border into Sudan, from where they are now attempting incursion to come back. Incidentally, they have now burned down the UN refugee camp[v] in Sudan and fully moved to training military camps, sponsored by the Egyptian and Sudanese Governments. Therefore, the struggle of Tigrayan elites to get back Welqait, Tegede, and Humera is a moot case to get access to Sudan. What access to the international border are they talking about? They should learn the history of Lesotho and Kingdom Swaziland, which are surrounded by South Africa and landlocked.

This group of the so-called Tigrayan intellectuals had completely forgotten how their leadership persecuted Ethiopian intellectuals such as Hailemariam (Hailemariam, 2018), Kahsay (Kahsay, 2007) who were demanding the right of Ethiopia to the sea outlet based on the very article 125 of United Nations, that she lost in 1991 when the TPLF came to power. The Tigrayan Scholars and Professionals were vilifying them then. Now, the same intellectuals are demanding for the tiny renegade province of Ethiopia, Tigray, to have an international border and sea outlet which they denied to the bigger Ethiopia for 27 years. Do they know what shame means?

Is that reason why they invaded Afar, to incorporate into Tigray? Still, had they succeeded in defeating the Afars, they need either to defeat Eritrea to grab Port of Assab, or invade and defeat Djibouti, to annex the port and incorporate it into Greater Tigray. Tigrayan “intellectual” daydreamers are devoid of intellectual common sense, blinded by TPLF propaganda, and make themselves a laughingstock.

Conclusion

Let the so-called Tigray Scholars and Professionals understand this! There is no international law that would take land from an independent country to let a province of a country have a sea outlet. Eritrea is an independent country since 28 May 1993, thanks to the TPLF. They lost the chance in 1993. No one has the right to award Assab to Tigray or no legal means to allow them to annex Djibouti. As for the international borders, if Tigray remains an integral part of Ethiopia, they will never ever have the legal power to claim any of those demands because the border within internal territory is defined by the authorities of Ethiopia and not an international body. There is an international law that prohibits interference in the internal affairs of any country. Ethiopia is not an exception. If they succeed to become independent, then Eritrea and Ethiopia will be their international borders! There they would have their international borders! What is the fuss about?!

In 1991, when the TPLF became the Government of Ethiopia, they took by force the historical territories of Gondar Province, Welqait Tegede, and Humera incorporating them into Tigray, so that Tigray would stretch to the border with Sudan. However, for 27 years, the people of Welqait and Humera were fighting for their rights demanding to be back with their natural blood relatives, the Amhara. The residents have gone through ethnic cleansing and suffered linguistic and cultural genocide. It is a different time now. The dream of Welqaites became the reality when the TPLF deliberately started the war and got kicked out of Welqait Tegede, Humara, and Raya. Without violating international law, no power under the sun has the right to reverse that. They have lost! They need to face the reality. Just to serve the interest of the TPLF, the people of Tigray should not be subjected to more suffering. The criminals need to be apprehended. The Tigray intellectuals need to save their place in history by trying talking sense to the TPLF rather than being considered ordinary cadres of the war criminals.

 Case closed!

References

Hailemariam, Y., 2018. Borkena. [Online]
Available at: https://borkena.com/2018/05/09/dr-yacob-haile-mariam-peaceful-settlement-of-the-ethio-eritrean-conflict-is-an-idea-whose-time-has-come/
[Accessed 2 January 2022].

Kahsay, A. T., 2007. Ethiopia's Sovereign Right of Access to the Sea under International Law. University of Georgia Law.

Muchena, D., 2020. Amnesty International. [Online]
Available at: https://www.amnesty.org/en/latest/news/2020/11/ethiopia-investigation-reveals-evidence-that-scores-of-civilians-were-killed-in-massacre-in-tigray-state/
[Accessed 2 January 2022].

 

 



[i] https://www.youtube.com/watch?v=Ni4bGOU6I6M

[ii] https://www.youtube.com/watch?v=y62IopI-pU8

[iii] https://twitter.com/GlobalGsts/status/1477017800501829642

[iv] https://mobile.twitter.com/globalgsts/status/1474404089719099398

[v] https://www.dabangasudan.org/en/all-news/article/fire-breaks-out-in-refugee-camp