Tuesday 13 September 2011

ሊበሏት ያስቡአትን አሞራ …

ሊበሏት ያስቡአትን አሞራ …

ወንድሙ መኰንን፣ መሰክረም 1 ቀን 2004 ዓ.ም.

አፓረታይዱ የወያኔ ዘርኛ ሥርዓት ቅጣምባሩ እየጠፋበት መጥቷል። የወሮባላ ሥርዓት መሆኑ እየተነቃበት በሄደ ቁጥር ዓይን-አውጣነቱ ብሶበታል። ዓይኑን በጨው ሙለጭ አደርጎ አጥቦ፣ በደረቁ ሊላጨን ይሞክራል። ኤዲያ! ለሚፈጽመው ወንጀል ሁሉ፣ ወንጀለኛነቱ በግልጽ እየተነበበበት ምን ምክኒያት ያስደረድረዋል? ብልጥ ነኝ ማልቱ ይሆን? ድንቄም! “ውሸት ሲደጋገም ዕውነት ይሆናል” የሚባለውን አባባል ከነጠሬ ቃሉ ወስዶት ይመስል፣ ውሸቱን በየዕለቱ ይተረትረዋል። አሁን አሁንማ፣ ወያኔ ተሳሰቶ ዕውነት ቢናገር፣ ዜጎቻችን “መንገስታችን ታሟል ማለት ነው” እሚሉበት ደረጃ ደርሰዋል። ለምሳሌ አሥራ አምስት ሺ ሕዘብ በረሀብ እየረገፈ መሆኑን የተባበሩት መንግሥታት ነግረውን የሰው አጥንት በቴሌቪዢን እያስቆጠሩን ለወገን ድረሱ እየተባለ፣ በረሀብ የተጠቁት የቦረና ከብት አርቢዎች ቀርበው “እኛም ከብቶቻቸንም እያለቅን ነው የወገን ያለህ ደረስልን!” እያሉ ሲማጠኑን፣ “ገንዘቡን ሁሉ የት አደረሱት” እንዳይባል ነው መሰል መቀባዠሩ! የኛ ዘመናዊ ጠቅላይ ሥቃይ መለሰ ዜናዊ አንደለመደው፣ “የለም! ነገሩ አልገባችሁም! አኛ አገር፣ ዕድሜ ለኢህአዴግ፣ ድርቅ እንጂ፣ ወይ እንደ ንጉሡ ዘመን፣ ወይ እንደ ደርጉ ዘመን ረሀብ የለም” በማለት አቀርሸብን። ቅርሻቱን ተቀባብለው ሕዘባችንን ማደንቆር ሥራቸው የሆነው ካደሬዎቹም ያንኑ አስጠሊታ ማደንቆራቸዉን ያራገቡብን ገቡ። ይባስ ብለውም፣ የወያኔ ሬዲዮና ቴሌቪዢን አልበቃ ብሎአቸው፣ ያንኑ የገማና የገለማ የመለስን ቅረሻት ያለወትሮአቸው ቪ ኦ ኤ የአማርኛው አገለግሎት ላይ በእርሻ ሚኒስቴር ዲኤታው  በኩል ብቅ ብለው እንዳለ ዘረገፉብን። ቪ ኦ ኤ ዎች! እግዚአብሔር ይይላችሁ። ሕዘባችንማ ለእንቁጣጣሸ፤
“አበባ አየሸ ወይ? ለምለም!
ዶሮ ወጥ አለሽ ወይ? የለም!
በግ ወጥ አለሽ ወይ? የለም!
ትንሽ ጥበስ አለሸ ወይ? የለም!
ገነዘብ እስኪመጣ፣ ለምለም!
ቀኑ እሰኪወጣ፣ ለምለም!
ልምከርሽ ወይ? ለምለም!
አዴይ - የብር ሙዳይ ኮለል በይ!
አዴይ - ሀሸን ጠጥተሽ ጋደም በይ!”

እያለ እየቀለደ ርሀቡን ለመረሳሳት የሞከራል። በዚያን ሰሞን “ፈረቃ” የምትል ድራማ ሠረተው እንዳዝናኑን ማልት ነው።

ሰሞኑን ደግሞ ወያኔ የሕዳሴ ግድብ እያለ ሕዝባችንን መዋጮ በመዋጮ ኪሱን እያራቆተው ነው። ያለው አንጡራውን አርከፈክፎ፣ የሌለው ተበደሮ እያዋጣ ነው። የቸገረው ወገናችን በራሱ ስቃይ እያፌዘ ለመዝናናት የሞክራል። “አይ አባይ፣ ለበዙ መቶ ሺሕ ዓመታት አፈራችንን እየሸረሸርክ ያጋዝከው አንሶህ፣ አሁን ደገሞ ኪሳችንን እየበረበርክ ማራቆት ገባህ?” እየተባባለ ይሳሳቃል። ምን ይደርግ?

የወያኔ ሥርዓት የሚተነፍሰው በጠቅላይ ሥቃዩ መለስ ሳምባ ነው። ያ በሲጋራና በጫት የተበከለ ሳምባ ነው እስከአሁን በመጨረሻዋ ደቂቃ ላይ እየደረሰላቸው ነብስ የሚዘራላቸው። እነ ሰዬና ገበሩ ከወንበሩ ሲያነቃነቁት አንዲት ሌሊት ሲያምጥ አድሮ፣ “ቦናፓርቲዝም” የሚል ቅርሻት ተፋባቸው። የ”ቦናፓርቲዝምን” ምንነት ለማወቅ ሲደናበሩ፣ ውሾቹ ተቀርማመቱአቸውና ግሟሹን አሥር ቤት ሲከቱት (በሙስና! ጉድ ነው!)፣ ሌሎቹን አስቦክተው የበላይነትን ተቀዳጁ። እንደዚሁ ወያኔ ተዘናገቶ ሲቀላምድ፣ ቅንጅት ደርሶ ከሥሩ ሲነቀንቀው፣ ጀሌዎቹ ተደናብረው የሚይዙትንና የሚጨብጡትን አጥተው ሲደናብሩ፣ አሁንም መለስ ሆዬ ሲቃዥ አድሮ፣ አንድ ጠዋት “ኢንተርሐምዌ” የምትለውን ቃል አግኝቶ ከብብቱ ሥር አውጠቶ አቀረሸብን። ካድሬዎቹም ያቺን ተቀባብለው ተንጫጩብን። ብዙዎቻችን ግራ ተጋብትን “የድክሺነሪ ያለህ! የኢንሳይክሎፒዲያ ያለህ” እያልን መሯሯጥ ገባን።ነገርዮውን ለማወቅ ስንሯሯጥ ምረጫው ደረሰና በአፍ ጢሙ ደፋው። ኢነተርሐመዌ እንደቦናፓርቲዝሟ ሳትሠራ ቀረች። አሁን መለስ ያፈጠጠ ወንጀል መሥራት ነበረበት። እሱ ወንጀለኛ ሁኖ ሳለ፣ እሱ ከሀዲ ሁኖ ሳለ፣ ነጹሐንን በወንጀልና በሀገር ከሕደት ከሰሰ። ዓለም “ጉድ” እያለም “ዕድሜ ይፍታህ” አሰፈረደባቸው። ከዚያ በሁዋላማ የሚገድለውን ገደሎ፣ የሚያሥረውን አሥሮ፣ ሥልጣኑን ካረጋጋ በሁዋላ “ምሬአቸዋለሁ” በማለት ዓይኑን በጨው አጠቦ ለቀቃቸው። የተወናበዱት የቅንጅት መሪዎችም አዚም እንደዞረባቸው ዋናውን የሀገር ጠላት መለስንና ግብረአበሮቹን ተትው እርስበርስ ሲናቆሩ ብትንትናቸው ወጣ። ያ ዓይን ያወጣ አሠራር በተመጻዋች አገሮች ዘንድ በዙም ጉዳት ሳያስከትል ማለፉ ስለተሳካለት፣ አሁን ዐይን ያወጣ ማጭበርብሩን በጠራራው ፀሐይ በሰፊው ተክኖት ያላንዳች ማወላወልና ማመንታት የማይመስሉ ሰንካላ ምክኒያቶች እየደረደረ ተቀናቃኞቹን አየገደላቸውና፣በዓለም ሕብረተሰብ ዘንድ የሚታወቁትንም እንደ ደበበ እሸቱ ያሉትን በእሥራት እያስወገዳቸው ነው።

ወያኔ የዘመኑን ቴክኖሎጂም ያላገባብ እየተጠቀመ፣ ቅረሻቱን ዩ-ቲዩብ በሚባልው ዜዴ ውጭ ኗሪ ኢተዮጵያውንን ሊበክል ድራማ እየሠራ እየረጨብን ነው። ከነዚህ ድራማዎች መሀል፣ ግንቦት 7 ሊገለብጠኝ ሲሞክር ተከታትዬ እንት እንደደረስኩበት እዩልኝ ብሎ የበተነብን የገማ፣ የገለማ የውሸት ዝግንትል የቅርብ ትዝታ ነው። በወቅቱ መልስ ተሰጥቶታል። በጊዜው ያላያችሁ፣ የሚከተለውነ ደረ-ገጽ ይጫኑ። http://wondimumekonnen.blogspot.com/2011/09/blog-post.html። ብሎጌ ነው።

ይኸ ብልግናው በዓለም አቀፍ ሕብረተሰብ ዘንድ ተበልቶበታል። ለምሳሌም ሰሞኑን የወጣው ዊኪ ሊክ እንደሚያስረዳን ከሆነ፣ የአሜሪካን ኤመባሲ ለመንግሥቱ ባስተላለቸው የምሰጢር የቴሌግራም መልዕክቶች አዲስ አበባ ውሰጥ በየጊዜው ይፈነዱ የነብሩት ፈንጂዎች፣ ሆን ተበለው የተፈጸሙ “የመንግሥት ሥራዎች” ናቸው ብሎ ደምድሞታል። እንዲያውም አንዱ ጋ ሲያትት ምን አለ መሰላችሁ! “ሁለት ሰዎቸ ከሁለት ቀን በፊት ይያዛሉ። ከሁለት ቀናት በሀዋላ፣  ቦምብ በተጠመደበት፣ ቤት ወሰጥ ከሁዋላ ይቆለፍባቸዋል። የጸጥታ አባሎች፣ ቦምቡን በርቀት ያፈነዱትና (remote control detonation) ያጋዩአቸዋል።” ይታያችሁ። ምስኪኖቹ የወያኔ ጥቃት ሰለባዎች እዚአችው ቤት ወሰጥ ገላቸው በግፍ ተበጣጠቆ ሕይወታቸው አለፈች። ልብ በሉ፣ ይኸንን ጉድ የሚዘከዘኩት፣ የአሜሪካን ዲፕሎማቶች ናቸው። ከዚያ በሁዋላማ የተሠራው ድራማ አሰገራሚ ነበር። “ሸዕቢያ አዲስ አበባን ባግዳድ ለማደረግ የላከቻቸው የኦነግ አባላት ቦምብ ለማፈንዳት ሲገጣጠሙ በድንገት ፈንድቶባቸው ፈጃቸው” ተበሎ ቲያትር ተሠራበት። ወያኔ ውሸት ሀጢአት መሆኑ ጨርሶ አያውአወም። “ሰው ምን ይለኛል”ማ ደሮም በአባሎቹ ህዋስ (DNA) ውሰጥ አልተፈጠረባቸውም። በነሱ ዕይታ ሁሉ ነገር፣ የተገላቢጦሽ ነው። ዕውነትና ውሸት ቦታ ተቀያይረዋል። ወንጀልና ንጽህና ቦታ ተደበላለቆባቸዋል። ከፋትና ደግነት ተምታቶባቸዋል። እነሱ ግን ገራ ግራውን ያዙ።
ይህቺ የተበላባት ዕቁብ ለመሆኑ ከየት መጣች? የመጣቺውማ ከ1997 ነበር። አንደኛውን እንደ ወትሮው ፊትለፊት ተኩሶ መግደል በዓለምአቀፍ ርዳታ ለጋሾች ዘንድ አስወቃሽ  እየሆነ ስለመጣ፣ መለሰ ከብብቱ ስር የመዘዛት “ትሪክ” ናት። ዘዴይቱም “ማስብ” ትባላለች። ከእንገሊዝኛ የተገኘች ቃል  Minimize Accusations and save bullets – MASB ብሎ ነው ለክ እንደቦናፓርቲዝሙ የፈበረካት። በዚህች ዘዴ ሕዝባችንን ቁም ስቅሉን እያሳየውና አበሳውን እያበላው ነው። ሀሳቧን አመጦ የወለዳት መለስ ነበር። በፈረንጆቹ አቆጣጠር ሜይ 8 ቀን 1997 ዓ. ም. አቶ አሰፋ ማሩን በጠራራ ጸሐይ በአውላላ ሜዳ ላይ ተኩሶ ከገደላቸው በሀዋላ ዓለም ከዳር እስከዳር “ዓይንህን ላፈር” አለው። መለ  አምጦ አምጦ "ማስብን" ወለደ።“ማስብ” ብሎም ሰየማት። “ማስብ” የምትባለዋ ኮድ ሥራ ላይ ከዋለች ወዲህ ሕጉንም እነዳሰፈላጊነቱ በመጠመዘዝ ማሰር፣ እንደማጅራት መቺ አደፍጦ መግደል፣ ከተጋለጡም ሽምጥጥ አድረጎ መካድና ፊሸካ ነፊዎቸ ካሉም ማሰፍራራት፣ ሆድ-አደሮችን በጥቅም እየደለሉ ወራዳ ሥራ ማሠራትና ወንጀል ማስፈጸም፣ የመሳስሉን በሰፊው ተያያዙት። ለምሳሌም የመርካቶ  ኪስ አውላቂ የነበሩ ሌቦች አሁን የወያኔ ግብረ አበሮች ናቸው። ሥራ አግኘተው አለፎላቸዋል። ወያኔ ማጅራት ለማሰምታት ይልካቸዋል። የተቃዊሚ አባላትን ቢሮ ሆነ በሎ ሠብሮ ለማዘረፍ፣ ያሠማራቸዋል። የኸንን ጉድ የከዱአቸው የድሮ አባሎቻቸው በመጽሐፍ ሳይቀር አወጥተው እያጋልጡት ይገኛሉ። ተስፋዬ ገበረ አብን ለዋቢነት መጥራት ይቻላል። በዚህም መሠረት በመቶ ሺ ሚቆጠሩተን ዜጎቻቸንን ያለ ጥፋት ጥፋት  እየተፈበረከላቸው ወይ ወህኒ ታጉረል፣ አለበለዚያም ሕየወታቸው ጠፍቶ ደማቸው ደመ-ከልብ ሁኗል። ሰሞኑን ወንድማችንን ተወዳጁንና ታዋቂውን ተዋናይ ደበበ አሸቱን ያጋጠመው የሰበዓዊ መብት ጥሰት የዚሁ የወያኔ ድር ዝግንትል ውጤት ነው።
http://www.ethiotube.net/video/15485/Breaking-News-ETV-News--Artist-Debebe-Eshetu-arrested-for-allegedly-conspiring-with-Ginbot-7

ሁለት ነገሮችን እናስረግጥ። በመጀሪያ ደረጃ፣ ወያኔ የሰበሰባቸው ሙትቻ አሻንጉሊቶች በቀላቢ ጌታቸው በመለስ ትዕዛዝ ግንቦት ሰባትን “አሸባሪ” ብለው ስለፈረጁት ግንቦት ሰባት አሸባሪ ሊሆን አይችልም። እንደዚያማ ቢሆን ሞት የተፈረደበት፣ ዶር ብርሀኑ ነጋ በሰላም አሜሪካን ዩኒቨርሲቲ ወስጥ ባላስተማረም ነበር። ቀጣሪውም በርከሌይ ዩኒቨርሲቲሰ ለምን አይከስም? ሌላው ወያኔ ሞት የፈረደበት፣ አንዳረጋቸውም በሰላም እንገሊዝ አገር እንዴት መኖር ቻለ? ይልቅስ የለየለት አሸባሪ፣ ሕወሀት ነው። ጫካ እያለ የውጭ ዜጎችን በማፈን በአሜሪካን መንግሥት የወንጀል ተመራማሪ መሑራን ከአሸባሪዎች መፈረጁን ዛሬም በሚከተለው ደረ-ገጽ ይነበባል። ወያኔ ሥልጣን ላይ ፈጥ ካለ 20 ዓመት አስቆጠሯል። የዩኤስኤም አቲ ቴረሪዝም ጓድንት ደረጃም በቀቷል። ምነው እስከዛሬ የህቺ መረጃ አልተሠረዘችለትም?

http://www.start.umd.edu/start/data_collections/tops/terrorist_organization_profile.asp?id=4287

ወያኔ አሸባሪነቱን፣ ዛሬም “መንግሥት” ተበሎም አልተወም። ጎረቤት አገር ደረስ ነብሰ ገዳዮችን ልኮ መቶ አለቃ ጃታኔ አሊን ኬኒያ ውስጥ አሰገደሏል። ሰዎቸን ከጂቡቲ አሳፍኖ ኢትዮጵያ ድረስ አሰውሰዷል። አገር ውሰጥ ከሕግ ውጪ በመቶ ሺሕ የሚቆጠሩትን በሰበብ በአሰባቡ ፈጀቷል፣ አሰፈጀቷል። ያለበቂ ምክኒያት በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎችን አሰሮ አንገላቷል። ለመሆኑ እነጸጋዬ ገብረመድህንን፣ እነስጦታው ሁሴንን፣ እነአበራሽ በርታን እምን መቃብር ወሸቃቸው?

ሀቁ፣ በብርሀኑም እጅ፤ ሆነ በአነዳረጋቸው እጅ ግን እስካሁን አንዲትም ሕይወት አልጠፋችም። ስለዚህ የለየለት ቴረሪስት የወያኔ መንጋ እንጂ የግነቦት 7 አባላት አይደሉም። ወያኔ የማይመስል ደራማ እየሠራ ባያደነቁረን ምናለበት! ሳታመካኝ፣ ብላኝ ነበር ያለቺው ያቺ ምስኪን እንስሳ? “ዘረፋዬን ሊያሰቆሙበኝ፣ ዘረኝነቴን ሊየስጥሉኝ የሚሞክሩትን ሁሉ አሳድዳቸዋለሁ” ቢል ያምርበታል። ደርግ አንድ የሚያስመሰግነው ነገር ቢኖር፣ የሚፈጽመውን ወንጀል ለመቀባባት አለመሞከሩ ነው። አገር ከሀዲም አልነበረም። ወያኔ ግን፣ ከገዳይነቱም ባሻገር የ’አገር ከሕደት ወንጀሉን፣ ተጠምቆበታል።
ወያኔን ሻዕቢያ እዳንልፈጠርው፣ እንዳልኮተኮተው፣ እንዳላሳደገው፣ ዛሬ ከሻዕቢያ ጋር የተነጋገረውን ሁሉ ከአሸባሪነት እየፈረጀው ያደነቁረናል። የሚገርመው እሱ ትላንት ከሻዕቢያ ጋር “በአንድ አለጋ ካልተኛን፣ በአንድ ጉደጓድ ካለሸናን” እያለ ሲያሰቃየን እነዳልነበረ፣ የሞራሉን ብቃት ከየት አባቱ አምጠቶ ነው ዛሬ ከሻዕቢያ ጋር አትነጋግሩ ሊለን የደፈረው? ለመሆኑ አንቀጽ 37 ሕገ መንግሥቴ የሚለው ውስጥ የተጠነቀረው የማንን ጎፈሬ ለማበጠር ኑሯል? ሻዕቢያ ሁለት የባሕር በሮቻችንን እንደያዘች ኤርትራን እንድትገነጠል ማን ነበር የረዳት? ተገነጣይዋን ጠቅላይ ገዛቴን ዕወቁልኝ እያለ በተባበሩት መንግሥታትና በአፈሪካ አንድነት ኮሪዶሮች ላይ ማን ነበር ኩስኩሰ እያለ ሲለማመጥ የነበረው? ዛሬስ ቢሆን ያ ሰብህት ነጋ የሚሉት ጉደኛ ኤርትራ ከተጠቃች "አለንላት" እያለ ሲፎክርብን ምን ተብሎ ሊተረጎም ይሆን? “ኢትዮጵያ ትበታተናለች እነጂ የ’ኤርትራ ናፅነት አደጋ ላይ እንዲወድቅ አንፈቅድም” አልነበር ያለን?

ብዙ ብዙ ነገር ማለት ይቻላል። ጋዜጠኛ ርዕዮት ዓለሙ፣ የት ቦታ ነው ከግንቦት ሰባት አባላት ጋር ተገናኝታ የተሰባጠረችው? ጋዜጠኛ እንደመሆኗ፣ የመሰላትን ብትጽፍ “ሕገ መንግሥት” በተባለው የወያኔ ሰንክሳረስ የተፈቀደም አይደል? ዘርይሁን ገበረ እግዚአብሔርና ውብሸት ታዬስ ከሙያቸው ባሻገር ምን ወንጀል ፈጸሙ? የሚገርመው የኤሊያስ ክፈሌ ነገር ነው። አሱን ሊደርሱበትም፣ ሊያንበረክኩትም ስለማይችሉ ቢተውት ይሻላቸው ነበር። መካሪም የላቸው ልበል እነዚህ ጋጠ-ወጦች? ኤልያስን ባያባብሱበት ይበጃቸው ነበር።
አሁን ደበበ እሸቱን ማሰራቸው ወያኔዎች የፈሩትን ሕዝባዊ አመጽ ሊያስቀርላቸው መስሏቸው ይሆን? በግፍ ላይ ግፍ በጨመሩ ቁጥር የኢትዮጵያውያን ንዴትና ቁጭት እየበዛ ነው የሚሄደው።

እንዲህ ዳመኖ ዳምኖ የዘነበ እንደሆን
የጎረፉ መውርጃ፣ በየት በኵል ይሆን?
እንዲህ ጢሶ ጢሶ፣ የነደደ እንደሆን?
አመዱ ማፍሰሻ በየት በኵል ይሆን?

የተዳፈነ እሳት፤ ጢሶ ጢሶ መንደዱ አየቀርም። ዳመኖ ዳመኖ መዝነቡ አይቀርም። ሰሜን አፍሪካ የዘነመው የሕዝብ አመጽ ዶፍ ኢትዮጵያም የወርዳል። የወያኔ መፈጨረጨር ከጎረፉ አያድነውም። ጠራርጎ ከነዝግንትሉ ይዞት መሄዱ አየቀሬ ነው። ይለቅ ሊበላት የከጀላትን አሞራ ሁሉ ጅግራ ባይላት ከትዝበቱ በተረፈ!!!
በ2004፣ ይደመሰስ የወያኔ ሥርዓት!

No comments:

Post a Comment